የሕወሃት ኃይሎች ስልታዊቷን የደሴ ከተማን መቆጣጠራቸውን ትናንት ቅዳሜ ካስታወቁ በኋላ የመንግስት ኃይሎች በከተማዋ ዛሬ እሁድ አዲስ ውግያ መክፈታቸው ተሰማ

የጥቅምት 21 ቀን 2014 ዓ/ም የዓለም ዜና በድምጽ
ርዕሶቹ
• የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት መቀሌ ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ የህወሃት ኃይሎች ማሰልጠኛ ጣብያ ላይ ያነጣጠረ የአየር ጥቃት ማድረሱን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ዐስታወቀ።
• በሱዳን የዴሞክራሲ ተሟጋች ቡድኖች ትናንት ጠርተውት በነበረው የህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ፖሊስ በከፈተው ተኩስ በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች ሳይገደሉ እንዳልቀሩ የህክምና ምንጮች ገለጹ። ፖሊስ በከፈተው ተኩስ ከሞቱት በተጨማሪ ከ100 በላይ ሰዎች ቆስለው ወደ ሕክምና ተወስደዋል።
• በምጣኔ ሃብት የበለጸጉት የቡድን 20 አባል ሀገራት መሪዎች በውጭ ሀገራት በድንጋይ ከሰል ኃይል ለማመንጨት የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ እንዲያበቃ ከስምምነት ደረሱ። አባል ሃገራቱ ጣልያን ሮም ውስጥ ለሁለት ቀናት ሲያካሄዱ የነበረውን ስብሰባቸውን ዛሬ ሲያጠናቅቁ ባወጡት መግለጫ በጎርጎርሳውያኑ የክፍለ ዘመኑ እኩሌታ አልያም በተቀራረበ ጊዜ የካርቦን ልቀትን በምድር ላይ የተጣጣመ እንዲሆን የተያዘውን መርኃ ግብር ለማሳካት እንደሚጥሩ አስታውቀዋል።
DW

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.