“አብረን ወደ ፊት እንሄዳለን፤ አብረን የጀግንነት ሥራ እንሠራለን” ኮሎኔል አለበል አማረ

230885137 1605320519642936 7620135922838000905 nባሕር ዳር: ነሐሴ 02/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ወደ ግንባር ያመራው የፋኖ ሠራዊት በንፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪዎች አቀባበል እና ሽኝት ተደርጎለታል፡፡ ሠራዊቱም በታላቅ ወኔ ወደ ግንባር አምርቷል፡፡
በሽኝት መርኃግብሩ ላይ ኮሎኔል አለበል አማረ ባደረጉት ንግግር “አብረን ወደ ፊት እንሄዳለን፤ አብረን የጀግንነት ሥራ እንሠራለን” ሲሉ ለፋኖ ሠራዊት ተናግረዋል፡፡
አማራን በማዳከም ኢትዮጵያን ለማፍረስ የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ግብ አድርገው እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ኮሎኔሉ ይሄንን በጀግንነት ቀልብሰን የአማራን ታሪክ እናድሳለን፤ የኢትዮጵያን ሉዓላዊት እናስከብራለን ብለዋል፡፡

229659649 1605320626309592 5975731700981338627 n

ፋኖ ቤዛዊት አያሌው በህልውና ዘመቻው ከተቀላቀሉ ወጣቶች መካከል አንዷ ናት፡፡ “ፋኖዎች ትግሉን አስበንበት እና ቆርጠን ወጥተናል፤ ጠላት የገባበት ገብተን እንደመስሰዋለን፡፡ ትግሉ ሴት ወንድ ብሎ አይለይም፤ የሁሉም ጉዳይ ነው” ብላለች፡፡
229847946 1605320572976264 8172080414263719219 n
ፋኖ ደረጀ በላይ በበኩሉ ከመከላከያ ሠራዊት፣ ከልዩ ኀይልና ከሚሊሻ ጋር በቅንጅት ጠላትን ድል ለመምታት መዘጋጀቱን ገልጿል፡፡
Alebal Amare
Col. Alebal Amare
ዘጋቢ:- ቢኒያም መስፍን
AMC
ተጨማሪ ያንብቡ:  ጠበቃ ዶ/ር ሼክስፒር ፈይሳ የሃይለመድህን አበራን ጉዳይ ለመከታተል ጄኔቫ አመራ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share