” ፀረ _ሙሥና አብዮት አሁኑኑ ! ” ( አባ መላ ዘ አብደናጎ )

bribery
bribery

” ወደሽ ከገባሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ ። ” ይላሉ አበው ። ጥፋትን አውቆ ወዶና ፈቅዶ ወደጥፋት የገባ ወይም የዘንዶ ጉድጎድን በእጄ ካለካው ብሎ ዘው ብሎ የገባን ፤ ” ተው ዘንዶ አለ … ” ብትለው ” ምን አገባህ ? ” ስለሚልህ በሐዘኔታ ከንፈርህን ከመምጠጥ በሥተቀር ከቶም ልትታደገው አትችልም ።
የዚህ እውነት ማጠናከሪያ ተረት ልንገርህ ።

ርዕስ ፤ ” ምከረው ፤ ምከረው ፤ ደጋግመህ ምከረው ፤ ኢንቢ ካለ መከራ ይምከረው ። ” ይሰኛል ። “ አንድ ሰው የሚኖርበትን ቀዬ ከእጅ ወደአፍ ኑሮ በመጥላት ፣ ሀብት ወደተፍረፈረበት አገር ቅልና ጨርቁን ጥሎ ፣ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ጉዞ ጀመረ ። ቀን እና ሌት ተጉዞም ወደሁለት አገር የሚከፋፍል ድንበር ላይ ደረሰ ። በቀኝ አቅጣጫ ፍትህ ፣ ረዕትህ እና የሰው እኩልነት ያለበት ፣ ደኞች ያለአድሎ ለሁሉም ትክክሐኛ ፍትህ የሚሰጥበት ። ሁሉም በችሎታው ሰርቶ የመኖር መብት ያለው ፣ የተሻለ ኑሮ ለመኖርም እጅግ ልፋት የሚጠይቅ አገር ሲሆን ፣ በስተግራው አቅጣጫ ያለ አገር ግን በፍርደ ገምድልነት የታወቁ ዳኞች የበዙበት ፣ ህግና ሥርዓት የማይከበርበት ሆኖ ፣ ምግብና መጠጥ የተትረፈረፈበት ፤ ሰው ማጭበርበርን ስራዬ አድርጎ በሌላ ሰው ድካም የሚበለፅግበት አገረ ነው ። ይህንንም እውነት በየድንበሩ ካሉ ኗሪዎች ጠይቆ ተረዳ ። እናም የጥጋብ እና የምንግዴ አገር ውሥጥ ከእነ ሞላ ቤተሰቡ መኖር መረጠ ።

በጥጋብ አገር እንዳሻው እየበላና እና እየጠጣ አራት ልጆች ወልዶ በደስታና በተድላ ሲኖር ሳለ ፣ ከአጠገቡ ጎጆ ቀልሶ የሚኖር ሰው ልጅ ሥለሌለው ቀናበትና ” ሚሥትህን ሥጠኝ ። ” ብሎ ቢጠይቀው እንቢ ሥላለው በአገሬው ፍርደ ገምድል ዳኛ ላይ ከሰሰው ና ዳኛው ፊት ቀረበ ።
ክሱም “ ይኼ ጎረቤቴ ብዙ ልጆች አሉት ። እኔ ግን የለኝም ። እናም ሚስቱን ሰጥቶኝ ለእኔ ልጅ ትውልድልኝ ዘንድ ብጠይቀው እንቢ አለኝ ።ክቡር ዳኛ ያለልጅ መቅረት የለብኝምና ወላድ ሚስቱን ይሰጠኝ ዘንድ ለክቡር ፍርድ ቤቱ አመለክታለሁ ። “ የሚል ነው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰርገኛ ወጎች ‘ግብፅ ጠላታችን ምን አመጣዉ?’ - ዶ/ር መኮንን ብሩ

ዳኛውም ” አንተ በለ ብዙ ልጅ ሆነህ እርሱ ልጅ ሳይኖረው ይቅር ማለት ነው ። ሚስቴን አልሰጥም ማለትኽ ? … ከዚህ ደቂቃ ጀምሮ ምሽትህ የእርሱ ሆና እንድትወልድለት ወስኛለሁ ። …” በማለት አሥደንጋጭ ፍርድ ፈረዱ ። በዚህ ፍርደ ገምድል በሆነ ፍርድ ሚስቱን የተነጠቀው ክፉኛ ታመመ ።
ጎረቤቶቹ ተሰብስበው ሲያዩት ሲያቃሥት እና አይኑንን ሲያሥለመልም አዩና “ይኽ ሰው ነገ ከሞተ ሥራ ያሥፈታናልና ዛሬውኑ ከእነ ህይወቱ እንቅበረው ። ” አሉ ። ልጆቹም ” እንዴት ሳይሞት አባታችን ከእነ ህይወቱ ይቀበራል ? ” በማለት ተቃወሙ ። ይህም ጭቅጭቅ ተባብሶ አካባቢውን በማወኩ በፖሊሥ ተይዘው ሁለቱም ወገኖች የአገሬው ዳኛ ፊት ቀረቡ ።
“ የጠባችው መንስኤ ምንድነው ? “ ሲል ጠየቀ ዳኛው ።
“ የታማሚው ልጆችም አባታችን ታሞ እቤት ተኝቷል ። እነዚህ ጎረቤቶቻችን ነገ ሥራ ሥላለብን ነገ ከሞተ ሥራ ያሥፈታናልና ዛሬ እሥከነ ነፍሱ እንቅበረው ። “ነው ፤ የሚሉት በማለት ለዳኛው አሥረዱ ። ዳኛውም ፍርደ ገምድል ነበርና ” ነገ ሞቶ ሥራ ከሚያሥፈታችሁ ዛሬውኑ ወሥዳችሁ ቅበሩት ። “ በማለት ትዕዛዝ ሰጠ ። በፖሊሶች ትዕዛዝ አሥፈፃሚነትም “ ኧረ አልሞትኩም ። በህይወት እያለሁ እንዴት ትቀብሩኛላችሁ ? ! እባካችሁ ማሩኝ ። አትቅበሩኝ ። ነገም አልሞትባችሁም ። ኡ !ኡ ! …” እያለ ልጆቹ በፖሊስ ተይዘው አይናቸው እያየ እሥከነ ህይወቱ ተቀበረ ።

እንደዚሁ ተረት አይነት እውነት በገሃዱ ዓለም ቢሰራ ብዙሃኑ በዜና ካልሰማ እውነት አይመሥለውም ። ይሁን እንጂ በፍርደ ገምድልነት ያለጥፋታቸው የታሰሩ ፣ የሰው ይቅርና የዶሮ ነፍስ ያላጠፉ የተገደሉ ሰዎችን ለመቁጠር እንደሚያዳግት የዛሬው የዓለም እውነት ፍንትው አድርጎ ያሳየናል ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ቃላትን ማባከን! (ከበልጅግ ዓሊ)

በዛሬው የዓለም እውነት መነፅር ፍርደ ገምድልነት በፖለታካ ተቃርኖ ሰበብ የተለያየ ሥም እየተሰጠ የሚከናወን ኢሰብአዊ ተግበር መሆኑንም አንባቢ ተረዳ ።
ይኸውልህ በዚህ በ21 ኛው የዘመነ ክ/ዘ እንኳን ኢትዮጵያችንን ፣ አይናችን እያየ እስከነ ህይወቷ ሊቀብሯት የተነሱ ግለሰቦች ከ1983 ዓ/ም ጀምሮ ተከስተው ዛሬ እየበዙ መጥተውልኻል ።ትላንት የአሜሪካ መንግሥት ለሥልጣን ያበቀው የህውሃት የፖለቲካ ኢሌት ና ካድሬ … ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት ለ 50 ዓመት ከመድከሙምም በላይ ዛሬ በይፋ በኢትዮጵያ ላይ ቢላ ሥሎ ሊያርደን ተነሥቷል ።በተለይም ባለፉት 30 ዓመት ከሆድ የዘለለ የማያስብ የየተቋም እና የየክልል አሥተዳዳሪና ካድሬ ለመፍጠር ያለእረፍት በመሥራቱ ዛሬም በእርሱ እየተጠቀመ ነው ።

አብይ መራሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ይኽንን ረቂቅ ሴራ በሦሥት ዓመት ከመንፈቅ ሙሉ ለሙሉ መቀልበስ አዳጋች መሆኑ ቢታወቅም ፣ መንግሥት የሚቆጣጠራቸውን ተቋማት ቢያንሥ ህሊና ባላቸው ፣ ለኃላፊነቱ በሚመጡን ግለሰቦች እሥካልተካ ና አገር እንዲያከስሩ የተቋቋሙትን የመንግሥት ተቋማት ደግሞ እሥካላፈረሳቸው አዲስ ጠያቂ ያለው ተቋም እሥካልገነባ ጊዜ ድረስ ፤ የፍርደ ገምድልነት እኩይ ተግባራትን ደጋግመን እየተመለከትን ማዘናችን እንደማያባራ እናውቃለን ።
ይህንን ፅሑፍ ያፃፈኝ ዋነኛ ምክንያትም ይኸው ኘው ።የህላና ቢሶቹ ና ለገንዘብ ሲሉ አገርን ከመሸጥ ወደኋላ የማይሉ ሙሥኞች መብዛት ።

ይኸው ዛሬ አገርን ካዋረዱ አንዳንድ የአትሌቲክሱ መሪዎች እውነታውን እየተረዳን ነው ። በህሊና ቢሶቹ ፣ የአትሌቲክ ፌዴሬሽን ባለሥልጣናት አሻጥር የተነሳ ፣ አትሌቶቻችን የኔዘርላንድ ፣የቤለሩስ ፣ የበሐማስ ፣ የባህሪን ወዘተ ። ዜጋ ለመሆን መገደዳቸውና ለባዕድ አገር መኩሪያ ለእኛ ማፈሪያ እንደሆነ በጃፓን ኦሎፒክ ተመለከትን ።
የ 2020 ው ፣የጃፓን የኦሎፒክ ውድቀታችን መንስኤ በመፈተሽ ና እጅግ የተሰራፋውን እና ሥር የሰደደውን ሙሥናዊ አሰራር በማሥተዋል ፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በመላው አገሪቱ እየተከናወነ ካለው ፍርደ ገምድልነት አንፃር ፤ ጠንካራ እርምጃ በመውሰድ ሙሥናንን ማቆሚያ አብዮት በአፋጣኝ ማካሄድ እንዳለበት ይኽ ፀሐፊ ያምናል ።
በሥፖርቱ ፣ በጉምሩኩ ፣ በውጭ ግንኙነቱ ፣ በወደቡ ፣ በቁም ከብቱና በወርቅና በማዕድን ንግዱ ፣ በባህልና ቱሪዙሙ ፣ በአየር መንገዱ ፣ በህዝብ ማመላለሻው ፣ በከተማ ውሥጥ የደላላ ንግዱ ፣ በመንግሥት ሥር ባሉ ተቋማት ሁሉ ፤ የሀብት አሰባሰባችን እንከን ጨምሮ ( ለመከላከያው የሚደረገው የሎጀስቲክ አቅርቦት አሰባሰብ ከቀበሌ ጀምሮ ከሙሥና የፀዳ መሆኑ መረጋገጥ አለበት ።) የህግ አሥፈፃሚው ምድር ላይ ያለ ተግባሩ በአሥቸኳይ ተገምግሞ ታላቅ አብዮት ተካሂዶ ይኽቺ አገር ከደም መጣጮቿ ተላቃ እፎይ በማለት ወደ እውነተኛ ብልፅግና ማምራት አለባት የሚል ሃሳብ ይኽ ፀሐፊ አለው ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምነዋ ! ማንዴላችን ? !

መንግሥት የዚኽን አብዮት አሥፈላጊነት ከዛሬው የህልውና ፈተና አንፃር ና ከመላው ህዝብ አገርን የመውደድ ልባዊ ሥሜት አኳያ በውል እንደሚገነዘብ ይኽ ፀሐፊ ያምናል ። አብዮቱንም በቅርቡ ተግባራዊ በማድረግ ፣ በግለሰቦች እየተፈፀመ ያለውን ፍርደ ገምድልነትና ብዝበዛ ያሥቆመል የሚል ተሥፋ አለኝ ። ለማንኛውም ዕድሜ ይስጠን እና ይኽንን ቀን ለማየት ያብቃን ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share