ከሰሞኑ ከፍተኛ ወታደራዊና ፓለቲካዊ ኪሳራ የደረሰበት አሸባሪው ህወሓት ለተባባሪዎቹ የቅማንት እና ጉሙዝ ታጣቂዎች የመጨረሻ ድረሱልኝ ጥሪውን ልኳል

xsbgalwfexqliv5x60ed45805a655

የህወሓት አሸባሪ ቡድን መንግስት የወሰደውን የተናጠል የተኩስ አቁም ውሳኔ ወደጎን በመተው ትንኮሳ በከፈተባቸው የአማራ እና አፋር ግንባሮች ከፍተኛ ሽንፈት ገጥሞታል።

ህልውናቸውን ለማስጠበቅ በተከላከሉ ሃይሎች የአሸባሪው ቡድን ታጣቂዎቹ ሙሉ በሙሉና በከፊል ተደምሥሠዋል። ይህ ሽንፈቱ ያሳሰበው የአሸባሪው ሃይል ከፍተኛ አመራሮች ለቅማንት እና ጉሙዝ ታጣቂዎች የመጨረሻ ድረሱልኝ ጥሪውን መላኩ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ታማኝ ምንጮች ባደረሱን መረጃ የሽብር ቡድኑ ሽንፈት በተከናነበባቸው ግንባሮች ላይ ሲያዋጉ የንበሩ አመራሮቹን መግደልና አንገት መቅላት የጀመረው አሸባሪው ህወሓት፤ የመጨረሻ ግብአተ መሬቱን ለመፈጸም ኢትዮጵያዊያን ከዳር ዳር በመነሳታቸውና በየግንባሩ እየደረሰበት ባለው መራር ሽንፈት ተስፋ በመቁረጡ ለሌሎች ጸረ ሰላም ሃይሎች ድረሱልኝ ብሏል።

የመኖርና ያለመኖር ህልውናውን ብቻውን ማሳካት ሲያቅተው፤ ሀይል ለመበታተንና ትኩረት ለማስቀየር፤ የሽብር እንቅስቃሴውን የሚደግፉና የቡድኑዓላማ ተጋሪ የሆኑትን የቅማንትና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ታጣቂ ሀይሎችየውክልና ጦርነት እንዲያደርጉና ይህን ፍላጎቱን እንዲያሳኩለት እየተማፃናቸው ይገኛል ሲሉ ነው ምንጮቻችን የገለጹት።

የአሸባሪው የህወሃት ቡድን በሱዳን በኩል በዳንሻና በሁመራ መውጫና መግቢያ ኮሪደር እንዲኖረው ለማድረግ በተደጋጋሚ እየፈፀመ ያለው እልህ አስጨራሽ ትግልና ትንቅንቅ የመከላከያ ሀይል፤ የአማራ ክልል ልዩ ሀይልና ታጣቂ በጥምረት እየወሰዱበት ባለው ከባድ እርምጃ ፍላጎቱን እውን ማድረግ ተስኖታል፡፡

በእነዚህ ተላላኪ ሀይሎች በኩልም ሚናቸውን ለመወጣት ፈቃደኛነተቸውን በማረጋገጥ በተለይም ደግሞ የቅማንት ታጣቂዎች በሰሜን

ጎንደር በኩል ትንኮሳ ለመፈፀም ጥረት እያደረጉ ቢሆንም፤ይህ እንቅስቃሲያቸው ከሀገር ወዳዱ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም ከመንግስት እይታ የተሰወረ ባለመሆኑ ተገቢው ቅጣትና እርምጃ በአሸባሪው ሃይል ላይ እየተወሰደበት መሆኑን ምንጮቻችን ገልጸዋል፡፡

(ኢ ፕ ድ)

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.