በኢትዮጵያ የጦር አበጋዝ መንግሥቶች አንድ ሽህ አንድ የድንበርና ወሰን ግጭቶች ሃገሪቱን ወደ ማያባራ ጦርነቶች ከቷል!!

(ክፍል አንድ) / ፂዮን ዘማርያም (ኢትኢኮኖሚ)

nmap
nmap

በኢትዮጵያ የሚገኙ ክልሎች ድንበርና ወሰን የሃሳብ መስመር እንጂ ምድር ላይ የሌሉ ልዩነቶች ናቸው!!! መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ምድሪ ህልውና ግን ይቀጥላል!!!

የ‹አዲሱ ዘመን› የሙዚቃ ዘውግ መንፈሳዊ ንቅናቄ ታዋቂውና ዝነኛው ፒያኒስትና ኮምፖስር ያኒ ክሪሶማሊስ (Yiannis Chryssomallis) በዓለም ካርታ ላይ ስላሉ መሥመሮች ካለው ‹‹እነዚህ መሥመሮች በእርግጥ የሉም፡፡ ሆኖም መሥመሮቹ ተስተካክለው ሙሉ በሙሉ ተሠርተዋል፣ እንደምንም ሁላችንም አንዳችን ከአንዳችን የተለያየን ተደርገናል፣ በማያበቃ፣ በማያቆርጥ ለዘላለም በተሳሳተ ሃሳብና እምነት የህልመኛ ምህታታዊ ቀለበት ውስጥ እስረኛ ሆነናል፡፡ እኔ እንደማስበው ዓለማችን በጣም የተሻለች ሥፍራ ትሆን ነበር፣ አንድ ቀን የሃሳብ መሥመሩ እንደሌለ ማስመሰል ያቆምን ጊዜና ፣ እኛ በህሊናችን ከሚያለያዩን ነገሮች ይልቅ፣ የሚያመሳስሉን ነገሮች ላይ አትኩሮታችንን እንደ መልህቅ ከጣልን፡፡››

Music genres distinguished from the “New Age” spiritual movement Lines on maps …..“These lines really don’t exist. They are made up-completely- and they perpetuate this illusion that somehow we’re all different from each other. I think the world would be a much better place if some day, we stopped pretending that these lines exist and we concentrated on our similarities rather than our differences.”…………….(1)

map of amhara
Ethiopia

በኢትዮጵያ፣ በኤርትራ፣ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ ፣ ወዘተ የሚገኙ ክልሎች ካርታ ድንበርና ወሰን የሃሳብ መስመር እንጂ ምድር ላይ ያልተሰመሩ ምናባዊ መሥመሮች ናቸው!!! መንግሥት ይሄዳል ይመጣል፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ምድሪቷ ህልውና ግን ይቀጥላል!!! በዚህ የልብ ወለድ ታሪክ ካቻምና ሻብያና ወያኔ በህብረት ኢትዮጵያን በጦርነት ወግተው ድል አደረጉ፡፡ አምና ወያኔና ኢትዮጵያ በህብረት ሻብያን ወጉ፡፡ ዘንድሮ ደግሞ ሻብያና ኢትዮጵያ በህብረት ወያኔን ወጉ፡፡ የኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ በካርታው ላይ የተሳለውን የሃሳብ መስመር ጥሰው ከሃያ አመታት መለያየት በኃላ በፍቅርና በነፃነት ድንበርና ወሰኑን ጥሰው አንድ ሆነዋል፡፡ የትግራይ ህዝብም ከዚህ ጦርነት በኃላ ከኢትዮጵያና የኤርትራ ህዝብ ጋር በካርታው ላይ የተሳለውን የሃሳብ መስመር ጥሰው በፍቅርና በነፃነት ድንበርና ወሰኑን ጥሰው ዳግም አንድ ቀን አንድ ይሆናሉ፡፡ የሻብያ የወያኔ የብልፅግና የጦር አበጋዞች መንግስት ልብ ወለድ ታሪክ፣ ልብ ወለድ የካርታ የድንበርና ወሰን የሃሳብ መስመር ድርሰት፣ ምክንያት ብዙ ዜጎች ሞተዋል፣ ቆስለዋል፣ ተሰደዋል፡፡ በኢትዮጵያ የጦር አበጋዞች መንግሥት የድንበርና ወሰን ግጭት ወደ ማያባራ ጦርነት ውስጥ አገሪቱን ስለሚከታት ከወዲሁ ህገመንግሥቱን ማሻሻል፣ የዘር ፌዴራሊዝምን ድንበርና ወሰን በማጥፋት እውነተኛ ፌዴራሊዝም በመገንባት ራስን በእራስ የማስተዳደር መብቶች የሚከበርባት ኢዮጵያን በሠላም መገንባትና ሳይንሳዊ የሠለጠነ መንገድ ችግራችን እንዲፈታ ማድረግ ዘለቄታዊ መፍትሄ ያመጣል እንላለን፡፡ የኢትዮጵያ በሰሜን በደቡብ፣ በምስራቅና በምዕራብ የሚያዋስኖት አገሮች ብቻ ካርታ ሲኖር፣ ውስጣዊ በዘር ላይ የተመሰረተ ድንበርና ወሰን አይኖርም፡፡ በኢትዮጵያ ክልላዊ የጦር አበጋዞች መንግሥታት ምን እንማራለን፡፡ ትላንት በህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት የአገዛዝ በትግራይ ካርታ ሥር ይገኙ የነበሩት ባድሜ፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ራያ፣ አላማጣ፣ የአፋር መሬት ነበሩ፡፡

  • የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት በኃይል ይዞት የነበረውን መሬት የኤርትራን ባድሜ መሬት ዛሬ ለኤርትራ አስረክቦል ጦርነቱ ቀጣይ መሆኑና ለመጭው ትውልድ እንደሚሸጋገር ጥርጥር የለንም፡፡
  • የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት የአማራን ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ሁመራ፣ ራያ፣ አላማጣ፣ መሬት አስረክቦል ጦርነቱ ቀጣይ መሆኑና ለመጭው ትውልድ እንደሚሸጋገር ጥርጥር የለንም፡፡
  • የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት የአፋርን መሬት አስረክቦል ጦርነቱ ቀጣይ መሆኑና ለመጭው ትውልድ እንደሚሸጋገር ጥርጥር የለንም፡፡

በኢትዮጵያ አንድ ሽህ አንድ የድንበርና ወሰን ግጭት ሃገሪቱን ወደ ማያባራ ጦርነቶች ይከታታል!!!የኦሮሞ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የአማራ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የአፋር የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የሱማሌ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የቤኒሻንጉልጉሙዝ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የጋምቤላ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የሲዳማ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የሃረሪ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ የየደቡብ የጦር አበጋዞች መንግሥት፣ አንድ ሽህ አንድ የድንበርና ወሰን ግጭቶችን ማስቆም እንዴት እንችላለን!!!

  • በትግራይ ክልላዊ መንግሥት 1,578,463 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሰባ ስምንት ሽህ አራት መቶ ስልሳ ሦስት) የሥራ አጥ ይገኛሉ፣527 ሚሊዮን ብር ተመድቦ ነበር
  • በትግራይ ክልላዊ መንግሥት 1,800,000 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ሽህ) በሴፍቲ ቴት ለአለፉት ሃያ ሰባት አመታት በምግብ እርዳታ የታቀፉ ሰዎችና ምግብ የሚሰፈርላቸው ናቸው
  • የግብርናው ዘርፍ፣ የኢንዱስትሪው ዘርፍ፣ የአገልግሎት ዘርፍ (ቴሌኮሙኒኬሽን፣ስልክ ፣ኢንተርኔት፣ መብራት፣ ውኃ ወዘተ)፣ የጤና አገልግሎት፣ የትምህርት ቤት፣ ባንክ ቤቶች ተዘግተዋል፣ የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በረራ ቆሞል፣
  • የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት አመራሮች ስዩም መስፍን፣ አባይ ፀሓዬ፣ አስመለሽ ወልደሥላሴ፣ ወዘተ ተገድለዋል::ስብሃት ነጋ፣ አብርሃም ተከስተ፣ አባይ ወልዱ ወዘተ ታስረዋል
ተጨማሪ ያንብቡ:  የኛ ነገር፡ የአባይ ችግር፡ የአያልሰው ምክር፡ ከልጅ ተክሌ፤ ተረንቶ

በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰ የስብዓዊ መብቶች ጥሰት፡-

  • ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ የህወሓት ኃይሎች የፈጸሙትን ጥቃት ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት ሳቢያ 52 ሽህ ወጣቶችን ህይወት እንደቀጠፈ መረጃ ወጥቶል፡፡
  • ከዚህ በተጨማሪም ግጭቱን በመሸሽ ከ60 ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች ድንበር ተሻግረው ወደ ሱዳን የገቡ ሲሆን በመቶ ሺህ የሚቆጠሩት ደግሞ እዚያው በክልሉ ውስጥ ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡
  • በትግራይ ከነበሩት 226 (ሁለት መቶ ሃያ ስድስት) የጤና ተቌማት ውስጥ በሥራ ላይ ያሉ 20 ብቻ ናቸው፡፡
  • በትግራይ ከነበሩት 40 (አርባ ) ሆስቲታሎች ውስጥ በሥራ ላይ የሚገኙ አሥር ብቻ ናቸው፡፡
  • በትግራይ ከነበሩት 250 የጤና ተቋማት አምቡላንሶች ተዘርፈው የቀሩት 54 አምቡላንሶች ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ጠቅሶ በቀጣይ ጊዜያትም ተጨማሪ 52 አምቡላንሶች ተጠግነው አገልግሎት መስጠት ይጀምራሉ ብሏል።
  • በትግራይ ከነበሩት 271 (ሁለት መቶ ሰባ አንድ) ትምህርት ቤቶች ተዘርፈዋል ወድመዋል፡፡ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተለይተዋል፡፡
  • በፌደራል መንግሥቱና በትግራይ ኃይሎች መካከል በተነሳው ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሞተዋል እንዲሁም በመቶ ሺዎች ደግሞ ከመኖያቸው መፈናቀላቸውን የረድኤት ድርጅቶች ገልጸዋል። 700 000 (ሰባት መቶ ሽህ) የተፈናቀሉ ዜጎች በትምህርት ቤቶች ውስጥ ተጠልለው ይገኛሉ፡፡
  • ህወሓት ከሥልጣን ሲወገድ በፌደራል መንግሥቱ የተሾመው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር እንደሚለው ከትግራይ ክልል ነዋሪ ውስጥ ከግማሽ በላይ ወይም አራት ሚሊዮን ያህል ሰዎች የእርዳታ ድጋፍ ይፈልጋሉ።
  • ከአንድሚሊዮንየሚበልጡሰዎችደግሞተፈናቅለዋል።
  • በትግራይ 524 (አምስት መቶ ሃያ አራት) ሴቶች ተደፍረዋል፡፡
  • ህወሓት በበኩሉ 33 000 (ሠላሳ ሦስት ሽህ) የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ወታደሮችን እንደገደለና ስድስት ሽህ እንደማረከ ብዙ መሣሪያ እንደማረከና ጦርነቱን እንዳሸነፈ ገልፆል፡፡ በቀጣይነትም የአማራ ክልልንና ኤርትራን እንደሚወር መግለጫ ሰጥቶል፡፡
  • የኢትዮጵያ መንግስት በጦርነት ኢኮኖሚ ውስጥ ተዘፍቆል፣ ሃገሪቱ በትግራይ ክልል 52 ሽህ ወጣቶችን ህይወት የቀጠፈ በልማት ሊሰማራ የሚችል ትኩስ ኃይሎን አጥታለች፣ በሌላ በኩልም ሱዳን ኢትጵያን ወራለች፡፡ በዚህ የጦርነት ኢኮኖሚ በአንድ በኩል በመላ ሃገሪቱ በትግራይ ጦርነት ምክንያት 3.5 ሚሊዩን ህዝብ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል፣ በትግራይ ከ50 ሽህ ሰዎች በላይ ወደ ሱዳን ተሰደዋል፣ በትግራይ መቐለ የውኃ ችግር ተባብሶል፣ በአማራ ክልል የአንድ ቢሊዮን ብር የሚገመት የእርሻ የሰብል ምርት በሱዳን ወታደሮች ተዘርፈዋል፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በወለጋ በአማራ ዜጎች ላይ የዘር ማፅዳት የተነሳ ብዙ ሰዎች ታርደዋል ከመቶ ሽህ ህዝብ በላይ ተፈናቅለዋል፣ በደቡብ ክልል በአማሮና ቡርጅ ግጭት ሃያ ሰባት 27 ሽህ ሰው ተፈናቅሎል፣ ኮንሶ ሃምሳ ስድስት ሰዎች ተገደሉ፣ ከሃምሳ ስድስት ሽህ ሰዎች ይፈናቀላል ይሰደዳል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የሆኑት ሚሼል ባሽሌት በትግራይ ግጭት የተሳተፉ አካላት “የጦር እና በሰብአዊነት ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ፈጽመው ሊሆን እንደሚችል” ገልጸው ነበር። ሚሸል ባሽሌት “የሚረብሹ” ያሏቸው የመደፈር፣ የዘፈቀደ ግድያ፣ መጠነ ሰፊ የንብረት ውድመትና ዘረፋ መፈጸማቸውን የሚያመለክቱ ሪፖርቶች እየወጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ግልጽና ነፃ ምርመራ ካልተካሄደና ጥሰቱን የፈፀሙትን አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ ካልተቻለ እነዚህ ጥቃቶች ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ስጋታቸውን ገልጸው ነበር።

በዘሐበሻ ድረገፅ በተለያዩ ጊዜት ስለጦርነት አስከፊነት የተፃፉትን ደግም አስታውሱ!!!

‹‹የሰው አንገትን ከመሠየፍህ በፊት አስብ፣ ምክንያቱም መልሰህ አተክለውምና!!!››

በኢትዩጵያ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የአካል ጉዳተኞች ይኖራሉ፡፡

በ1994 ዓ/ም በኢትዩጵያ በተካሄደ የህዝብ ቆጠራ 988,853 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ በዛን ግዜ 53,073,322 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት ውስጥ 1.9 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ የአካል ጉዳተኞች፣በደረሰባቸው የአካልና የስነ-ልቦና ጭንቀት ምክንያት ጤነኛ ሰዎች ሊሰሩት የሚችሉትን ሥራ መሥራት ይሳናቸዋል፡፡ በዚህም የተነሳ ገቢ የሚያስገኝ ሥራና የማህበራዊ ኑሮ ህይወት መምራት አይቻላቸውም፡፡ ከሠንጠረጅ ላይ በኢትዩጵያ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ውስጥ የሚገኙ የአካል ጉዳተኞች ብዛት እንቃኝ፡፡

Table 2-B: – prevalence of disability by regional states of Ethiopia (1994 census)

  • ኦሮሚያ ክልል የህዝብ ብዛት 18,465,449 ውስጥ 333,653 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • አማራ ክልል የህዝብ ብዛት 13,828,909 ውስጥ 281,291 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ደቡብ ክልል የህዝብ ብዛት 10,368,449 ውስጥ 174,941 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ትግራይ ክልል የህዝብ ብዛት 3,134,470 ውስጥ 90,742 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ብዛት 2,100,031 ውስጥ 45,936 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ሶማሌ ክልል የህዝብ ብዛት 3,382,702 ውስጥ 34,156 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • አፋር ክልል የህዝብ ብዛት 1,097,067 ውስጥ 14,140 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የህዝብ ብዛት 460,325 ውስጥ 7,341 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የህዝብ ብዛት 248,549 ውስጥ 4,226 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ሃራሪ ክልል የህዝብ ብዛት 130,691 ውስጥ 2,909 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • ጋምቤላ ክልል የህዝብ ብዛት 162,271 ውስጥ 2,581 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
  • በኢትዮጵያ የህዝብ ብዛት 53,379,035 ውስጥ 991,916 የአካል ጉዳተኞች ናቸው
ተጨማሪ ያንብቡ:  አቶ ቡልቻ ከአንድነት ፓርቲና አባላት አናት ላይ መቼ ይወርዱ ይሆን ?

PWD (People With Disabilities)

Baseline Study on the Status of Persons with Disabilities and the Influence of the African Decade Pronouncement in Ethiopia may, 2010……………(2)

የጦርነት አዙሪት፣ኢትዩጵያ ከጦርነት አዙሪት ውስጥ ወጥታ አታውቅም ለአርባና ሃምሳ ዓመታት በተደረገ ውጊያ ብዙ ዜጎቻችን የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ የጦርነት ሰለባ የሆኑ፣ አካል ጉዳተኞች በሃገሪቱ ትክክለኛ ማስረጃ ለማግኘት ባይቻልም፣በአንደኛ ደረጃ በኦሮሚያ ክልል 333,653፣በሁለተኛ ደረጃ በአማራ ክልል 281,291፣ በሦስተኛ ደረጃ በደቡብ ክልል 174,941፣በአራተኛ ደረጃ በትግራይ ክልል ከ90,742 ሽህ አካል ጉዳተኞች እንዳሉ የኢትዩጵያ ስታትስቲክስ ፅ/ቤት መረጃ ይገልፃል፡፡ ጦርነት የሚያካሂድ አገር በኢኮኖሚ ሊበለፅግ አይችልም፡፡ ደርግና ህወሓት አንባገነኖች በጦርነትና በኃይል የሚያምኑ በመሆናቸው ሃገር በኢኮኖሚ ሊበለፅግና ህዝብ ከድህነት አረንቆ ሊወጣ አልቻለም፡፡ የፖለቲካ ልዩነታችንን፣በጠረጴዛ ዙሪያና በሰለጠነ መንገድ በውይይት ችግሮቻችንን መፍታት እስካልቻልን ድረሰ ዓለም ከደረሰበት ስልጣኔ መድረስ ቀርቶ ዜጎቻችን ከርሃብ፣ ከድንቁርና፣ ከስደት፣ ከአካል ጉዳተኞች፣ከሥነ-ልቦና ጠባሳ ለመውጣት አይቻልም፡፡ በጦርነት የሚዳክሩ ሃገራት ምርታቸው የግብርና ምርት፣ የኢንዱስትሪ ሸቀጣ ሸቀጦች ሳይሆን የሃገር ገንቢ ዜጎቻቸው ሞትና የአካል ጉዳተኛ ምርት ሲያጭዱ ነው የሚኖሩት፡፡ ኢትዩጵያ በጦርነት አዙሪት ውስጥ ተዘፍቃለች፡፡ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ በጦርነት ኢኮኖሚ መቅኒው ድረስ ተበልቶል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ በተደጋጋሚ የአስቸኮይ ግዜ አዋጅ ስበብ ብዙ ወጣቶች ገሎል፣አካለ ስንኩል አድርጎል፡፡ በየእስር ቤቱ በኢሰበአዊ ግርፋት ብዙ ዜጎች እግርና እጃቸው ሽባ ሆኖል፣ ሥነ- ልቦናቸው ተናግቶል፡፡ ሃገሪቱን በጦርነት ኢኮኖሚ ዘፍቆል፣‹‹ሁሉ ነገር ወደ ጦር ግንባር!›› እንደ ደርግ ካለ ሠነበተ፡፡ በሰው ሠራሽ፣ ፀረ-ሰው ፈንጅ፣ ፀረ ታንክ ፈንጅ፣ የእጅ ቦንቦች የጦር መሣሪያዎች የሚሞተውና የሚቆስለው ወገኖቻችን ቤቱ ይቁጠራቸው!!! ለዚህ ነው ‹‹የሰው አንገት ከመሠየፍህ በፊት አስብ፣ ምክንያቱም መልሰህ አተክለውምና!!!››የሚሉት የቻይና አበወች ምክር ማስታወስ የሚገባው፡፡ በ2010 እኤአ የህዝብ ቆጠራ በኢትዩጵያ 805,492 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ ከኢትዩጵያ 73,750,932 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት 1.1 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ በኢትዩጵያ የአካል ጉዳተኞች ቁጥር ከ1994 እኤአ እስከ 2010 እኤአ መቀነስ ዋና ምክንያት የህዝብና የቤቶች ቆጠራ ወቅት፣ አባወራዎችና እማወራዎች በጎጂ የባህል ተፅዕኖ ምክንያት በቤተስቡ ውስጥ የሚገኝ አካል ጉዳተኛን ባለማስመዝገባቸው ነበር፡፡ በኢትዩጵያ ጠቅላላ የአካል ጉዳተኞች በክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች፣ የህዝብ ብዛት፣የአካል ጉዳተኞች ቁጥርና፣ በፆታ ያለው ንፅፅርን ከሠንጠረጅ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡……………..(3)

የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ኦግስት 2010፣ አዲስ አበባ ገፅ 134-138

በኢትዩጵያ የአካል ጉዳተኞች ትልቁ ችግር ሰው ሠራሽ የአካል ክፍል (Prosthetics)፣ ተሸከርካሪ ወንበሮች፣ምርኩዝ (Crutch)፣ወዘተ የመሳሰሉት መገልገያዎች እጦት የተነሳ አስታዋሽ አጥተው ይሰቃያሉ፡፡……………….(4)

የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግስት የትግራይ ክልል ህዝብን በጦርነት አዙሪት ውስጥ አስገብተውታል፡፡የትግራይን ህዝብ ከኤርትራ ህዝብ፣ ከጎንደር ህዝብ፣ ከአፋር ህዝብ፣ ከወሎ ህዝብ መሬት በመዝረፍ፣ ታላቆን ትግራይ በመሬት ቅርምትና ዘረፋ ለማሳደግ በሚያደርጉት ጥረት ሃገሪቱንና የትግራይ ህዝብን ወደ ማያባራ ጦርነት ውስጥ ከተዋል፡፡ በዚህም የተነሳ በትግራይ ክልል ከ90 ሽህ አካል ጉዳተኞች እንዳሉና ወደፊትም በዚህ የጦርነት አዙሪትና የማያባራ ጦርነት፣ ይህ አሃዝ እንደሚጨምር ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ህወሓት በትግራይ ክልል መሽጎ ወንጀለኞችን አሳልፎ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም፡፡ ህወሓት በትግራይ ክልል ልዩ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ህዝባዊ ሚሊሽያ 1.2 ሚሊዮን ታጣቂ በማደራጀት፣ በዘረፉትን የጦር መሣሪያ ታንኮችና የጦር አውሮፕላኖች በመመካት አጎራባች የአማራ ክልሎች አካባቢ ሠፈራ በማድረግ እንደሚገኙ ይታወቃል፡፡ የአማራም ክልል በተመሳሳይ ልዩ ፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና ህዝባዊ ሚሊሽያ በማደራጀት ህዝብ በማስታጠቅ ላይ ይገኛል፡፡ በመላ ሃገሪቱ የመሳሪያ ዝውውርና የገንዘብ ዝውውር በአስደንጋጭ መልኩ ሲሽለከለክ ሠንብቶል፡፡ ያለፈው አልበቃ ብሎ ወንድም ወንድሙን ለመግደል በዘር ተከፋፍሎ ዶልቶል፣ ማንም አሸነፈ ማንም የሁላችንም ምርት የወጣቶች እልቂትና የአካል ጉዳተኞች ምርት ከመጨመር ሌላ የወልቃይት፣ ራያና አፋር ወዘተ የመሬት ጥያቄ በሽማግሌዎች ያለምንም ደም መፋሰስ መፍትሄ ማግኘት ይችላል፡፡ ወደ ህሊናችን እንመለስ ለሚቀጥለው ትውልድ ፍቅር እናውርሰው፣ ጥላቻን አናውርሰው፡፡ የአዲስ አበባ፣ ድሬዳዋ፣ ሐረር፣ ሃዋሳ ወዘተ የከተማው ህዝብ፣ በህዝብ የተመረጠ ከንቲባ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት በፌዴራል መንግሥት የከተማ አስተዳደር ፖሊሲ በህዝብ ውይይት በማድረግ ተግባራዊ መሆን አለበት እንላለን፡፡ በውይይት ሁሉም ነገር ይፈታል፡፡ ካለፈው ታሪካችን እንማር፡-

  • በኢትዮጵያና በኤርትራ ጦርነት ከሰባ እስከ መቶ ሽህ ዜጎች ከሁለቱም አገራት እንደሞቱ፣ ምን ያህል ሠራዊት እንደቆሰለና የአካል ጉዳተኞች እንደሆኑ መረጃ አልተገኘም፡፡
  • በ1997ዓ/ም ምርጫ ወቅት ከ200 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፣ ከ5000 ሽህ ሰዎች በላይ በጥይት ቁስለኛ ሆነው የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ በ2007/8 ዓ/ም በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኛነትና የአማራ ተጋድሎ የመከላከያ ሠራዊት፣ የፖሊስ ሠራዊት፣ የአጋዚ ጦር ከ1500 ሠላማዊ ሠልፍ የወጡ ዜጎቻችንን ገድለዋል፣ ብዙ ሽህ ሰዎች በጥይት ቆስለው የአካል ጉዳተኞች ሆነዋል፡፡ በጋምቤላ ከ400 ሰዎች ተገድለዋል፣በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል፡፡ በሲዳማ ሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ዜጎች በግፍ ተረሽነዋልና ቆስለዋል፡፡ በአረካ ብዙ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል፡፡ ከለውጡ በኃላ ለእነዚህ ሠማዕታት መታሰቢያ እንኮን አልቆመላቸውም፣ የመለስ መታሰቢያ ለነዚህ ሠማዕታት መታሰቢያ መሆን ይገባዋል እንላለን፡፡
  • በ1994 የህዝብ ቆጠራ በኢትዩጵያ 988,853 የአካል ጉዳተኞች መኖራቸው ታውቆል፡፡ ከኢትዩጵያ 53,073,322 ሚሊዩን ህዝብ ብዛት 1.9 በመቶ ዜጎች የአካል ጉዳተኞች ነበሩ፡፡ በ2008 /ም ምን ያህል የአካል ጉዳተኞች ይኖራሉ;
  • በኢትዩጵያ ውስጥ 4.6 ሚሊዩን ህፃናቶች ከወላጆቻቸው አንዱን በሞት የተነጠቁ ናቸው፡፡ በዚህም የተነሳ ሃገሪቱ ከዓለማችን የሙት ልጆች መኖሪያ ለመሆን በቅታለች፡፡
  • በኢትዩጵያ ውስጥ 1.2 ሚሊዩን ህዝብ በኤችአይ ቪ/ኤድስ በሽታ ጋር አብሮ ይኖራል፡፡ 800 ሽህ ህጻናት ከዚህ በሽታ ጋር በተያያዘ ወላጃቸውን አጥተዋል፡፡
  • በኢትዩጵያ በዓመት ከአንድ ሽህ ዜጎች መካከል ዘጠኙ ወደ ሌሎች አገራት ይሰደዳሉ፡፡ በ2015 እኤአ በኢትዩጵያ የሥነህዝብ ቁጥር 99,465,819 ሚሊዩን ውስጥ 795,726 ሽህ ህዝብ በዓመት እንደሚሰደዱ ተገልፆል፡፡
  • 2011 /8.3 ሚሊዮን ህዝብ አስቸኮይ የምግብ እርዳታ ያስፈልገዋል እንደተባበሩት መንግሥት መረጃ መሠረት፡፡ በመላ ሃገሪቱ እስከ 3 ሚሊዮን ህዝብ ከቀየው ተፈናቅሎ በርሃብ አለንጋ እየተገረፈ ይገኛል፡፡ የዲያስፖራው ዜጋችን በታማኝ በየነ ስብዓዊ የድጋፍ ጥሪ 30 ሚሊዮን ብር በማሰባሰብ ለወገን ያለቸውን ፈጣን እርዳታ ዲያስፖራው ዛሬም ሲሶ መንግሥትነታቸውን አስመስክረዋል እንላለን፡፡
  • በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኛ በተለይም የጦርነት የአካል ጉዳተኞች በመቐለ በተስፋሁነኝ ኃይለማርያም ደገፉ የተፃፈውን ጥናታዊ ፁሁፍ በማንበብ የጦርነት አስከፊነትን መገንዘብ ለአዲሱ ትውልድ ይጠቅማል እንላለን፡፡……(5)
ተጨማሪ ያንብቡ:  ከዱቄት እስከ ሰብዓዊ አንበጣነት!! (የኢትዮጵያ ‹‹ሰብዓዊ ድሮኖች›› መነሳት) መነሻ! - ቴዎድሮስ ጌታቸው

ችግራችንን በጠረጴዛ ዙሪያ በውይይት እንፍታ!!!

በጦር መሣሪያና በኃይል የህዝብ ችግር አይፈታም!!!

ህወሓት ኢህአዴግና ኦዴፓ ብልፅግና ዘረኛና ተረኛ የጦር አበጋዞች መንግሥት ናቸው!!!

ህወሓት/ ብአዴን/ ኦህዴድና ደኢህዴን/ ኢህገዴግ የጦር አበጋዞች መንግሥት ምላጭ በመሳብ አረጁ፣ ዘመኑ የሚሻው ህሊናን መሳል ነው!!!

የወንድማማቾች ጦርነት መቼም የትም አይደገም!!!

ከጦርነት ኢኮኖሚ በአስቸኳይ እንውጣ!!!

ምንጭ፡-Source:

  1. Concert’s closing comments, Yanni Live at the Acropolis September 1993
  2. Baseline Study on the Status of Persons with Disabilities and the Influence of the African Decade Pronouncement in Ethiopia may, 2010
  3. የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የ1994ዓ/ም፣ የህዝብና የቤቶች ቆጠራ በኢትዩጵያ፣ ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ጁን 1999፣ አዲስ አበባ ገፅ 60-62
  4. የኢትዩጵያ ፊዴራል ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን ማዕከላዊ ስታስቲክስ ፅህፈት ቤት፣ ኦግስት 2010፣ አዲስ አበባ ገፅ 134-138
  5. Mekelle University College of Business and Economics Department of Cooperative Studies, The Role of Cooperatives In Unlocking Potentials of People with Disability: The Case of Tigray War Veterans in Mekelle, By Tesfahunegn Hailemariam Degefu/ September, 2011

2 Comments

  1. Amahara is gonna be in trouble . please leave Tigray and return where you come from. devastating damage coming soon. It is not threatening message but an alerte.You cannot overcome the indomitable powers by sending farmers . Donot masacre your own people.

    • Feed ur people first before u worry about Amahras which is non of ur business. Amharas r among their people who were snatched away in 1992. There has never been Tigrai west of Tekeze river . Ethiopian defence forces will protect people of Raya and Wolqaite.

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share