የአገራችን ኢትዮጵያ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ውስጥ ቀዳሚና ቁጥር አንድ የአገር ጠላት በሆነው ወያኔ ጋር እየተመሳጠሩ አገራችንን ለማጥፋት እየተረባረቡ ይገኛሉ፡፡ ወያኔ ከኢትዮጵያ ህዝብ ለ27 አመታት ዘርፎ በውጭ አገራት ባከማቸው ቢሊዮኖች ዶላሮች ክፍያ እየተገዙ የእምዬ ኢትዮጵያ ጠላትነታቸውን ቀይ መስመር በማለፍ ጭምር አሰላለፋቸውን ብቻ ሳይሆን በአድርጎታቸው ጸረ ኢትዮጵያነታቸውን በተግባር እያሳዩን ነው፡፡ ተከፋዮቹ የምእራባዊያን ዋና ዋና የዜና አውታሮች፣ ጋዜጠኞች ፣የአለም አቀፍ ልዩ ልዩ ድርጅቶች ሀላፊወች ….. ወዘተ በኢትዮጵያ ላይ ያላሴሩት ሴራ ፣ያልጎነጎኑት ተንኮል ፣አገሪቱን ለማጥፋት ያልክፈነቀሉት ድንጋይ የለም፡፡ ኢትዮጵያ ሰላሟን አጥታ፣ በውስጥ ጦርነት ዳሽቃ፣ ለውጭ ወራሪወች ደካማ ሆና፣ ህዝቧም እርስ በእርስ ጦርነት እንዲጠፋፋ ብሎም አገሪቱ እንደ ሶሪያ፣ የመንና ሊቢያ የወደቀች አገር (failed state) እንድትሆን አበክረው እየሰሩ ነው፡: እስካሁን በጸረ ኢትዮጵያ አሰላለፍ ውስጥ ከታዩት የውጭ ሀይሎች ቀጥታ ጥልቃ ገብነቶች ውስጥ ይበልጥ የከፋው ሀምሌ 6 ቀን 2021 በአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል የወጣው መግለጫ ነው፡፤ መግለጫው በእንግሊዝኛ መሆኑና ከአሜሪካ መሰማቱ እንጅ በወይን ጋዜጣ ላይ ከመቀሌ የወጣ የህወሀት ማእከላዊ ኮሚቴ መግለጫ ነው ቢባል ቅንጣት ማጋነን አይሆንም፡፡
የመግለጫውም ገራሚ ክፍል እንዲህ ይነበባል፡፡ complete withdrawal of ….. Amhara forces from Tigray ….. and an affirmation that neither the internal nor external borders of Ethiopia will be changed by force or in contravention of the constitution …
ይህ መግለጫ ሱዳን ኢትዮጵያን ስለመውረሯ ምንም ነገር አይልም፡፡የመግለጫው እንቆቅልሽ ሲመነዘር ብዙ ገጽታ አለው፡፡ይህንን መግለጫ በወይራነቱ ካየነው መግለጫው የሚለው ወልቃይት ፣ ራያ፣ ጠገዴና ጠለምት የወያኔ ናቸው ነው፡፤ የዙሪያ መሄድ አያስፈልግም፡፤ አሜሪካ ለዚህ እውን መሆን ጠባቂውም አስፈጻሚውም እኔ ነኝ እያለችን ነው፡፡ አለቀ፡፡ ከዚያ ውጭ ያለው እንቶ ፈንቶ ነው፡፤ በሌላ መልኩ ይህ ምን ማለት ነው?? ይህ ማለት ወያኔ ወልቃይትን ወስዶ ወደሱዳን መውጫ መግቢያ በርን ይቆጣጠራል ማለት ነው፡፤ ይህ ማለት ወያኔ የራያና የሁመራ ለም የአማራ መሬቶችን ይወስዳል ማለት ነው፡፡ ከዚያስ?? ከዚያማ በነአብይ አህመድ ላይ በአሜሪካ የተጣለው ማእቀብ ይነሳል ማለት ነው፡፡ ከዚያ በኋላም የአብይ አህመድ ሚስትና ልጆቹ ወደ አሜሪካ ወደነበሩበት ደንቨር ኮሎራዶ መመለስ ይችላሉ ማለት ነው፡፤ ከዚያ በኋላስ?? ከዚያማ በኋላ የፈረደበት የወልቃይት ፣ ራያ ፣ጠለምትና ጠገዴ የአማራ ህዝብ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለዘለአለም ከርስቱ ተነቅሎ ይባረራል ማለት ነው፡፤ ወያኔ ወልቃይትን ይዞ ወደሱዳን መውጫ መግቢያ በርን ተቆጣጠረ ማለት በኢትዮጵያ ጉረሮ ላይ ማረጃ ካራ አረፈባት ማለት ነው፡፡ በአሁኑ ፖለቲካና የሀይል አሰላለፍ ይህንን በሰፊው ካየነው ወደ ሱዳን መውጪያ መግቢያ በር የሆነው ወልቃይት በወያኔ ቁጥጥር ስር ሆነ ማለት የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች የዘመናት ያልተሳካ ሙከራቸውን በድል አጠናቀቁ ማለት ነው፡፡ ይህም ማለት ከአጼ ቴወድሮስ ጀምሮና አጼ ዮሀንስን ይዞ በየዘመናቱ ህይወታቸውን ለኢትዮጵያ አንዲነት የገበሩ ታላላቅ የአገሪቱ የጦር መሪወች ፣ጀግኖች አርበኞችና የህዝቡ የአርበኝነት ታሪክ በአሁኑ ዘመንና በተናጠልም በአብይ አህመድ አመራር በሚያሳፍርና በሚያሳቅቅ ሁኔታ አፈር ዲሜ በላ ማለት ነው፡፤ አገሪቱም እንደተፈራው ፈረሰች ማለት ነው፡፡ሁሉን አቀፍ የርስበርስ ጦርነት እውን ሆነ ማለት ነው፡፤
አብይ አህመድ ይህንን በመርዝ የተቀመመ መደለያ ተቃውሞ አሜሪካ በዚህ አይናውጣነት ደረጃ በአገራችን ጉዳይ ፈላጭ ቆራጭ መሆን እንደማትችል በግልጽና በይፋ በአስቸኳይ ወጥቶ ካልተቃወመ የሚነፍሰው ንፋስ ልክ ነው ማለት ነው፡፡አብይ ይህንን ካላደረገ ያልተገነዘበው ጉዳይ አለ ማለት ነው፡፤ ይህም በዚህ ስራው ራሱ ከባድ የአገር ክህደት የፈጸመ መሆኑንና እልፍ ሲልም ይህ የክህደት ስራ በድምር ውጤቱ መጨረሻ ላይ ራሱንም ቤተሰቡንም ሊያድን አለመቻሉን ነው፡፡ እዚህ ላይ ጀግናው በላይ ዘለቀ ልጁና ሚስቱ በወራሪው የጣሊያን ጦር ተማርከው ለእነርሱ ሲል እጁን እንዲሰጥ ሲጠየቅ የሰጠውን መልስ ያስታውሷል!!
አብይ ለፓርላማው እንዳስረዳው ”መደብ ላይ ተኛ ብባል የለመድኩትና ያደግኩበት ስለሆነ አይገደኝም” እንዳለው ሁሉ የኢትዮጵያ ህዝብም የቀረው ይቅር እንጅ ነጻነቱ ይበልጥበታልና ባርነትንና ለጠላት ማጎብደድን ፈጽሞ አይቀበልም፡፡ በአገር ደረጃም ሆነ በእስካሁኑ መሪወቿ ደረጃ ኢትዮጵያ የዚህ አይነት ታሪክ የላትም፡፡ ስለዚህ አብይ አህመድ ሆይ፦ የአገሪቱ የወቅቱ መሪ ስለሆንክ በቃል የምትለውን በተግባር ሁነህ ተገኝ!!! ሁሉም እንደ ጎርፍ ያልፋል፡፤ አገርና ህዝብ ግን ለዘለአለም ይኖራሉ፡፡አገራችን ባለው የወቅቱ የአገራት ፖለቲካዊ አሰላለፍ የወሳኝና ጠንካራ የውጭ አገራትን ድጋፍ በአስተማማኝ አላት፡፡ በአለም አቀፍ ግንኙነት የሁለት ሀያላን ጎራወች መኖር ሚዛኑና አዋችነቱ ቢለያይም ለደካማ አገሮች ጥቅሙ ወሳኝነት አለው፡፡ አብይ ሆይ፦ በአገር ውስጥም ሙሉ በሙሉ ሰፊ የህዝብ ድጋፍ አለህ፡፤ ስለዚህ መልመጥመጡ ለምንድን ነው?? ለተልካሻ ነገር ያለአግባብ ይህንን ያህል ወርዶ ሸብረክ ማለት አያድንህም፡ አያዋጣህም፡፤ አገሪቱንም ይገድላታል፡፡ የሚያዋጣህ ፣የሚያድንህ የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ነው፡፡ ምክንያቱም በእስካሁኑ ዝምታህና በሚጠረጠረው አድራጎትህ ከገፋህበት አገር ጎድተህ ትእዛዛቸውን ለጊዜው ብትፈጽምም ጠላቶችህ አንተን ካላጠፉ አያርፉምና በመሀል ሊደልሉህ በሚሞክሩ የውስጥም የውጭም ሀይሎች አትሞኝ፡፡ በእውንም ከኦሮሙማ የጸዳህ ከሆንክና በሙሉ ኢትዮጵያዊነት በእምነትና በስሌት የምትጓዝ ከሆነ በውስጥ ለእነማን ጋሬጣ እነደሆንክ ራስህም ሰፊው የኢትዮጵያ ህዝብም ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፤ ምክንያቱንም የነዚህ ጋሬጣወች የውጭ ገፊ ሀይል ከጀርባ ማን እንደሆነ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ቁልጭ ብሎ ይታያልና፡፡ከውጭ በኩል ያሉትም የማይቀመሱ የሚመስሉ ገፊና ደላላ ሀይሎች/አገሮች ለጊዜው መተንፈስ ያስችሉህ ይሆናል እንጅ እነርሱ በአለም ውስጥ በገቡባቸው አገራት ሁሉ ታሪካቸው የሚያሳየው ታክቲካል አጋር ያደረጉትንም ሀይል (ግለሰብ) ከማጥፋት አይመለሱምና፡፤ በተለያዩ አገሮች ውስጥ በፈጸሟቸው የፖለቲካ ቁማሮች የጠላትነት ልምዳቸው፡ ታሪካቸው የሚያሳየው ይህንኑ እውነታ ነው፡፡ስለዚህ በአጭሩ በአገራችን ላይ የመጡ ጠላቶችን ለመቃውም፤ እምቢ ለማለት፣ ለመመከትና ለማስወገድ ፍጹም አታወላውል፡፤ ህዝቡ ከአንተ ጋር ነውና፡፤ ይህንኑ በሚመለከት አንድ ወርቃማ የአገራችንን አባባል አለ፦
እልም ነው ጭልጥ ነው ዉሀ አይላመጥም
ጠላት ወዳጅ ላይሆን አልለማመጥም