ወልቃይት፤ አዲስ አገር የማዋለጃ ማሃጸን (ፊልጶስ)

ምዕራቡ ዓለም የማሃራ ልዩ ኃይል ከምዕራባዊ ትግራይ ወልቃይት ይውጣ “‘ ሲሉ ለቀልድ አልነበረም። በአንድ ልዋአላዊ አገር የውስጥ ጉዳይ መግባታቸው ጠፍቷቸውም አይደለም። ኃያል ስትሆን አይደለም በውስጥ ጉዳይ መገባት መብራትና ኢተርኔት በአስቸኳይ ቀጥልተብለህም ቀጭን ትዕዛዝ ትሰጣለህ፣ እኛም እንቀበላለን። የቁም ሞቱና ውድቀቱም የሚጀምረው ከዚህ ነው።

ብዙ ኢትዮጵያዊ ልብ ያላላለው ግን ገና መከላከያ መቀሌን ሲቆጣጠር ኦዴፓ/ብልጽግና ነበር የአማሃራ ልዩ ኃይል ከወልቃይትና ከራያ ይውጣ።በማለት ለአሜሪካ ማመልከቻውን ያስገቡት። ታዲያ የወልቃይት ጉዳይ የዓለም አቀፍ ጉዳይ ሲሆን ከጀርባውትግራይ” የምትባል አገር ለማዋለድ ብቻ ሳይሆን ኦሮሚያየምትባልም ለማዋለድ ነው።

ያለወልቃይት አገረ ትግራይ እንደማትወለድና ወያኔና አማሃራ እርስ በርሱ ካልተባላ ኦሮሚያየምትባለው አገር እንደማትወለድ ምዕራባዊያን ብቻ ሳይሆኑ ኦዴፓ/ ብልጽግናም ጠንቅቆ ያውቃል። በርግጥ ግብጽና ሱዳን ግን ሶስተኛ ቢንሻንጉል የሚባል አገር ይወለድ እያሉ እየወተወቱ ነው፤ አባይን ለመቆጣጠርአገረ ትግራይ እና አገረ ኦሮሚያመወለድ ብቻ በቂ አይደለም፣ ኤሪትራን ስናስገነጥልና ኢትዮጵያ በር አልባ ስትሆን አዳክመን የጨረስናቸው መስሎን ነበር፤ እናም ድጋሜ ስህተት መስራት የለብንም፤ ኢትዮጵያ ዳግም እንዳትነሳ አድርገን መበታተን አለብን በማለት ያስረዳሉ።

ታዲያ አሁንም ብዙ ኢትዮጵያኖች አፍጥጦ የመጠውን ሃቅ ተቀብሎ ምን እናድርግ?” ብሎ ለመፍትሄ ከመሻትና ለማይቀረው ትግል ራስና ከማዘጋጀት ይልቅ ፤ እንደ ሰጎን ጭቅላታችን አሸዋ ውስጥ ከተን ምክንያትና ትርጉም ፍለጋ እንደፍቃለን። ሰበብ ፍለጋ እንኳትናለን፤ ራሳችን ለራሳችን አገር ተጠያቂ መሆናችን እና ሙሉ ኃላፊነቱ የእኛ መሆኑን ዘንግተን የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝን በአገር ላይ እንጫወታለን።

ብዙ ሃተታ ሳናበዛ ዱቄትሆኗል የተባለው ወያኔ ዛሬ መላው ትግራይን እንዲቆጣጠር ለምን ተፈቀደለት ? ብለን ብንጠይቅ በቂ መልስ እናገኛለን። ባለፋት ወራቶች አሜሪካ ኢምባሲ ሲመላለሱ የነበሩት እነ አቶ መራራ ጉዴና ኦፌኮ ፓርቲያቸው ከኦነግ ጋር በመሆን ለምን በዚህ ሰዓት የኦሮሚያ የሽግግር መንግስት መሰረቱ ? ብለን ብንጠይቅ ኢትዮጵያዊ ለሆነና መስኪን አገራችን ለመታደግ ለሚፈልግ መልሱ እንደ ተሰያት ጸሃይ በታየው ነበር።

አሁንም ከተባበርን እና ከተናበብን ኢትዮጵያችን መታደግ እንችላለን። ኢትዮጵያ ብዙ መከራዎችንና ጠላቶችን እየተጋፈጠች ከዚህ የደረሰች አገር ነች። ግዛቷ እሳት ውስጥ እንደገባ ፕላስቲክ እየተሸበሸበሽ ከዚህ ለመድረስ የበቃችው በእኛ ድክመትና ጠላቶቻችን ጠንቅቀን ያለመዋቅና ከማን ጋር ቅድሚያ መታገል እንዳለብን ያለመገንዘብ ፤ ትግሉ የሚያስፈልገውን መሰዋአትነት ለመክፈል ዝግጁ ባለመሆናችን ነው።

መንግስት ከትግራይ ለቆ የወጣው ከወያኔ የከፋ ጠላት ስላለብን ነው።ብሎናል። የሚያሳዝነው በአሁኑ ሰዓት ምዕራባዊያንም ሆኑ ግብጽና ሱዳን ኢትዮጵያን ለማጥቃት የሚጠቀሙት ወያኔን ብሎም ኦነግና ኦነጋዊያንን መሆኑ፣ አሁንም ለዚህ የበቃነው በእነዚህ ቅጥረኞች መሆኑን ለማወቅ መጸሃፍ ማገላበጥ እንኳን አያሻም።

ጥያቄው ግን እነሱ በቅጥረኛነት ለእኩይ ዓላማቸው የመንግስትን መመበር እስከማያዝ ደርሰው የገዛ አገራቸውንና ወገናቸውን ብሎም ኢትዮጵያን የሚያክል አገር ማፍረስና መበታተን ሲችሉ፤ እኛ ኢትዮጵያ! ኢትዮጵያ ! የምንል ኢትዮጵያዊያን ለተቀደሰ ዓላማችን እና ለአገራችን አንደነት እንዴት በአንድነት ቆመን አገራችንን እና ወገናችን መታደግ ተሳነን??

የጠላትህ ጥንካሬ የአንተ ድክመት ነውየሚባለው ብሂል ተምራን ዛሬም ሌሎችን መወንጀሉንና ማሳበባችን ትተን በጋራ ለጋራ አገራችን ከታገልን ከተዘጋጀልን ወጥመድ ወጥተን ኢትዮጵያን መታደግ እንችላለን።

ሞት እንደሆን ላይቀር በዚህ ቢሊት በዚያ

እንዴት አገር ይጥፋ የሌለው መተኪያ።

ለሚጠይቀው መሰዋአትነት ራሳችን ማዘጋጅት የግድ ይላል። በአገር ላይ ምንም ምን ቢሆን ተስፋ አይቆረጥምና ከተስፋ በላይ ያለችውን አገራችን እያሰብን፣ የሁላችንም መዳኛ ለሆነችው ኢትዮጵያ ዘብ እንቁም። ለመነታረክና ለመጠቋቆም አሁን ግዜ የለም፤ አዎ! ግዜ የለንም ኢትዮጵያ እየተማጸነችን ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች!!!

——–//——

ፊልጶስ

ሰኔ/2013

1 Comment

  1. Ato Philipos, I can see and admire your concern over the fate of Ethiopia. Asking all concerned to be vigilant is a worthwhile effort. But how ? I am surprised to witness that such an issue is being tackled by a government official of minor position. Anyway we have to start talking about measures to be taken. May God be with us to keep our country safe and sound. In anticipation of hearing a sound platform from you.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.