በጦሙ ፈሰኩ! – በላይነህ አባተ

ደሞ እንደ ታች አምኖች ደም እንደጠጡቱ!
አምና በሬሳ ላይ ዙፋን የወጡቱ!
በጎች አሳርደው በጦሙ ፈሰኩ!

ሕዝብ እንደ ሳር ታጭዶ ደም ሲለብስ አገሩ፣
‘ችርስ’ ተባብለው በሸራ ቶን ጠጡ!

ወላጆቹ ታርደው ልጆቹ ሲያለቅሱ፣
ሼኮች ፓስተሮቹ ተአራጅ ጀርባ ታዩ!

ልጆች ተጨፍጭፈው ወላጆች ሲያነቡ፣
አቡኑ ጳጳሱ እንዳላዩ አለፉ!

በአቢይ ጦም ደም ፈሶ ሲፈሰክ እያዩ!
መስቀል ጨባጭ ቄሶች ሳይገዝቱ ቀሩ፡፡

ባለ ዲግሪ ምሁር እነ ሆድ አምላኩ!
አሳራጅ ሲፈስክ አሳላፊ ሆኑ!

ህፃን አራጆቹ አንዲት ሳይደብቁ!
ነፍጠኛን ጨፈጨፍን ብለው ሲደሰቱ!
አለቅላቂዎቹ እሬብ እያማቱ!
የአማራን ዘር ፍጅት አድማሱን አሰፉ!
በዜጋ ድሪቶ እየሸፋፈኑ!

የለበጣ ዜማ እያንቆረቆሩ፣
ዜግነት ኢትዮጵያ እየወሸከቱ፣
አማራን አታለው ተጅብ አፍ ከተቱ!

ወልድ ለወላዲት አማራም ለጦቢያ፣
በከሀዲዎች ሰይፍ ደጋግሞ ተወጋ!

ሳልስት ሰንበት ሲደርስ አብ እንደተነሳ፣
ጊዜውን ጠብቆ ይተማል አማራ !
እንደ ድር አብሮ አግስቶ እንደ አንበሳ!

ያ ቀን እስቲመጣ እግሬ አውጪኝ እስቲሉ!
ህፃን እያረዱ በጦም ይፈስኩ፡፡

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com)
መጋቢት ሁለት ሺ አስራ ሶስት ዓ.ም.

ተጨማሪ ያንብቡ:  አንገት የሚያስደፋ ! - ማራኪ ስዊድን

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share