” Hobbes argues that men are naturally equal in mind and body . As to strength of the body , the weakest has enough strength to kill the strongest. either by assassinating him secretly or by aligning himself with others for the purpose .
Thomas Hobbs remarks cynically is proof that men are equal rather than unequal .
………
john Locke in the Hobbes state of nature he said that, there is no natural law only natural rights each individual doing as he sees fit his preservation and enhancement of power .
ለዚህ ይመሥላል micoolo Machiavelli “The rules of power have priority over those of ethics and morality. ያለው። “Dynamics of illegitimate power .”ይሉሃል ይሄ ነው።
የማጥፋት ኃይል ሁሉም ሰው በተፈጥሮ ተሰጥቶታል።ይህንን ተፈጥሮ የሰጠቺውን ኃይል በሰኘው ጊዜ ሊጠቀምበት ይችላል ።በዚህ ኃይሉ በመጠቀም ሰው በግልና በተናጥል አምሳያውን ለማጥፋትም ይችላል ። በግልፅ ና በሴራ። አሥልቶ ፣በጥልቅ አሥቦ ግዜ ወሥዶ ፣ ትክክለኛ ጊዜ ፣ ቦታ ና ሁኔታ ውሥጥ ታዳኙ ሲያጋጥመው ፤ ኃይለኛውን ግለሰብ ወይም ቡድን ደካማ የተባለ ግለሰብ ወይም ቡድን እንደሚያጠፋው ታሪክ ደጋግሞ አሳይቶናል።
ሆብስም ሆነ ጆን ሎክ በዚህ አሳብ ይስማማሉ። በሞራል አሥተምህሮት በሎጂክ በመጠቀም አሥደማሚ እውነቶችን ለደቀመዛሙርቶቻቸው ያካፈሉት ሆብሥም ሆኑ ሎክ እያንዳንዱን ግለሰብ የአሁን አቅሙን በመመልከት ብቻ አኮስሶ ማየትና መጨቆን ተገቢ እንዳልሆነ ይመክራሉ። የጠሉት ሊወርስ ይችላል። የናቁትም ሲነግሥ በማየት ሞትን ሊያሥመርጥ ይችላል ።
” የሰው ልጅ በኃይልህ ፈፅሞ አትመካ
አንድ አምላክ አለና በኃይሉ ኃይልን የሚለካ ” ሥትል አንድ የፈጣሪ አመሥጋኝ ፣ የኦ/ተ/ቤ / አማኝ መዘመሯንም ላሥታውሥህ።
እናም በኢትዮጵያም ሆነ በመላው አፍሪካ የምናሥቸውለው የመንግሥት ሥልጣንን ለመቆናጠጥ የሚደረግ ትግል ኢ ዴሞክራሲያዊና ዜጋውን ተጠቃሚ ለማድረግ ፣ በህዝብና በፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የሚደረግ ግልፅ ፣በእውነት ላይ የተመሠረተ ፍትሐዊ የሥልጣን ሰጪ ና የሥልጣን ፈላጊ ፖለቲካዊ ሂደት አይደለም።
የሥልጣን መተካካት ሲደረግ የነበረው ፣ ሥልጣንን ይዞ ፣ ሥልጣን ያሥገኘለትን ጥቅም ፣ ማለትም የተቀናጣ ኑሮ እና ይህ ነው የማይባል ምቾት ላለማጣት ፣ በተቻለው አቅም ሥልጣኑንን ላለመልቀቅ በያዛቸው መንግሥታዊ ማውቀሮች ከለላ እና እገዛ በሚፋለም እና ይሄንን በከንፈር ሽንገላ የሚያምን የሆዱ ችግር አንቆ የያዘውን ህዝብ በሠላ ምላሴ አደናግሬ ፣በማይተገበር ፖሊሲዬ አማልሌ ሥልጣንን አግኝቼ እኔን እና የፖርቲ አባላቶቼን ሥልጣን እንደያዘው መንግሥት ተጠቃሚ አድርጋለሁ በሚል መካከል ነው።
ሥልጣንን ለማግኘት ፣ከገዢው ፖርቲ ጋር ወደፖለቲካ ግጥሚያ ውሥጥ የገቡት ተቀናቃኝ ፖርቲዎች ፣ ሁሉም ሰው በሚመለከተው የመንግሥት ችግር እንጂ በድብቁ የመንግሥት ውሥጣዊ ችግር ላይ አያተኩሩም። ይህ ጠለቅ ያለ ፖለቲካዊ ትንታኔ የሚጠይቀውን ችግር በመፈተሽ ፣የገዢው ፖርቲ ችግር በተፈለገው መጠን በእድገት እንዳንራመድ አድርጎናል አይሉም። የገዢውን ፖርቲ ውሥጣዊ ችግር በማጋለጥ ፣የተሻሉ ፖሊሲዎች ሰንጃለሁና እነዚህን ለህዝብና ለአገር የሚጠቅሙ ፖሊሲዎቼን ተግባራዊ ለማድረግ እንድችል የመሪውን ወንበር ፍቀዱልኝ አይሉም።በእውነት ና በቅንነት አገለግላችኋለሁ ሲሉ ከቶም አይደመጡም።የሚመሪበትን የመንግሥታቸውን ርእዮትም በግልፅ አያስቀምጡም። መንግሥታቸው ቅይጥ ርእዮተ ዓለም ይኑረው ፣ዴሞክራሲያዊ ይሁን ሞናርኪያዊ ፤ ሌበራል ይሁን ኮሚኒሥት ግልፅ አይደለም። ለምሳሌ በመጨረሻ አገራችንን ሲመራ የነበረው የኢትዮጵያ መንግሥት ” አብዮታዊ ዴሞክራሲ ነው ርእዮተ ዓለሜ ። ልማታዊ መንግሥት ነኝ። ” ሲለን ነበር።እንዲህ ሲል ኮሚኒሥትም ነኝ።ቡርዣም ነኝ።ማለቱ ይሆን ? በበኩሌ አልገባኝም።
ዛሬሥ? ዛሬ ኢትዮጵያ እየመራት ያለው አሻጋሪ መንግሥት ነው።ይህንን መንግሥት በቅንነት መረዳት ያሥፈልጋል።
በቅንነት መርዳት ሥል ምን ማለቴ ነው? ወደ ሥልጣን ሲመጣ ያነሳቸውን ሃሳቦች በወጉ ተረድቶ ፣ እውነተኛ ፣ ያልተወናበደና ያልተጭበረበረ ዴሞክራሲያዊ የሥልጣን ሽግግር መድረክ እንዲፈጥር ለአገሪቱ ፖለቲካ ፖርቲዎች የሚጠቅም ሃሳብ በማዋጣት ሽግግሩን አመርቂ ማድረግ-ማለት ነው። ይህንን ግን በማድረግ ቀና ትብብር የሚያደርጉት የበዙ አይደሉም። የሚበዙት “እጅግ የበዛ ቅዠት የሰፈረባቸው ፣ ሰማይ ቅርባቸው የሆኑ ናቸው። እና አሉታዊ የሆኑ እኩይ ሃሳቦችን በየሚዲያው ሲነዙ ይሥተዋላሉ።
እንዲህ አይነቶቹን ሰዎች የኢትዮጵያ እንቁ ልጅ እንዲህ በማለት ከደእኩይ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይመክራቸዋል።
” በማንኛውም ቡድንም ሆነ ግለሰብ ባህሪ ውሥጥ የኢትዮጵያዊነት የባህል ብቃት ና የመንፈስ ኩራት ያለውን ቡድን ወይም ግለሰብ በነገር ቀደም ተከታትሎ መልከፍ ና ማሥለከፍ ፣ በመሠሪ መውጋትና ማስቆጣት ወደሥህተት መግፋትና ማዘናጋት ፣ብሎም ማዋረድና ዋጋ ማሳጣት ሁልጊዜም በተከታታይና ያለመሰልቸት የሚደጋገም የጥፋት ዓላማ ነው። …”
ሎሬት ባለቅኔ ፣ፀሐፊ ተውኔት ፣የቋንቋ ተመራማሪና ሊቅ ፀጋዬ ገብረመድህን
ይህ ለአገርና ለህዝብ ደንታ ቢሥ የሆነ አውዳሚ አሥተሳሰብ ነው። ማንም ግለሰብ ሆነ ቡድን የማጥፋት ኃይል እንዳለው ከላይ የጠቀሥኳቸው ፈላሥፎች ከረዢም ዓመት በፊት በሚሥብ ቋንቋ አሳውቀውናል። መጠፋፋት ለማንም አይበጅም።ዛሬ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚያሥፈልገው ፍቅር ኘው።አንድነት ነው።ህብረት ነው። የእገሌ ዘር ፣ የእገሌ ክልል እያለ ለመብላት መንግሥት አያሥፈልገውም። ለመብላት ብቻ ለመኖር ብዛ ቢል እረኛ ነው የሚያሥፈልገው። እረኛ ብቻ እንዲኖር ደግሞ ከተፈለገ ፖርቲዎችን በጉልበት ማጥፋት በቂ ነው።ያን ጊዜ በብትሩ ሃይ እያለ ሐሆድ ብቻ የሚያኖር መንግሥት መፍጠር ይቻላል ።
የግለሰብ ሥብሥብ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብለት ብቻ ለመኖር ፣ በሴራ ና በጡንቻ ብቻ ተጠቅሞ ለመበልፀግ ለሚፈልገው በር ለመክፈት ከመቸውም ጊዜ ይልቅ ዛሬ ዝግጁ እንዳልሆነ ለሥልጣን የሚፋለሙ ፖርቲዎች ከወዲሁ ቢገነዘቡ መልካም ነው።
አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዜጋ ፣ ለአገሪቱ መበታተን ትልቅ ሚና የጫወታል ተብሎ በውጪ ኃይሎች ትልቅ ግምት ተሰጦት ከነበረው የትህነግ ሠራዊት ድንገተኛ ውድቀት ትልቅ ትምህርት በማግኘቱ የዘረኝነት አመለካከቱ ተቀይሮ እንዲህ በማለት መዘመር ጀምሯልኔ !!
የሰው ልጅ በኃይልህ ፈፅሞ አትመካ( 2)
አንድ ዓምላክ አለና በኃይሉ ኃይልን የሚለካ (2)