January 19, 2021
27 mins read

በጣም ሊታሰብባቸው የሚገቡ ጉዳዮች – ሰርፀ ደስታ

  • የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩና በተለይም ሕዝበ ሙስሊሙ ከክርስቲያኑ ጋር ያሳየው መተባበር የሚመሰገን
  • የኦሮሞነት አካሄድ፣ እውነት ከሆነ የሽመልስ አብዲሳና ብርሀኑ ጁላ ከሱማሌ መንግስት ጋር ተወያዩ የሚለው ዜና አደገኝነት
  • የዲያስፖራ ትግሬ ወያኔዎች በትግራይ ሕዝብ ገንዘብ በመሰብሰብ ለወያኔ ማደራጃነት ሊጠቀሙ እንደሚችሉ ማሳሰቢያ፡፡ በሱዳን አበበ ተክለሐይማኖት የተባለው ሰው ይሄን እየሰራ መሆኑ እየተነገረ ስለሆም ጭምር፡፡
  • በረሐብና በአረመኔዎች ለተጎዱ ወገኖች እርዳታ የገበታ ለሐገር ብሎ የዓላማ ውል ለሌላቸው ጉዳዮች ገንዘብ ከማባክነ ገበታ ለወገን በሚል ለወገን እርዳታ ማሰባሰብ ቢቻል፡፡ በውጭ የምትገኙም በታማኝ አሰባሳቢዎች ተመሳሳይ ሥራ ቢሰራ
  • ለዘለቄታው መንግስት ማሰብ ከቻለ እስከወዲያኛው ረሀብ የሚባል በአጭር ጊዜ ከኢትዮጵያ ለማስቀረት የሚቻልበት እውቀትና ዝግጅት ከባለሙያዎች መኖሩ የሚሉት በዚህ ጽሑፍ የማንሳቸው ናቸው፡፡

ዛሬ የጥምቀት በዓል በተከበረባቸው ቦታዎች በብዙ መልኩ ከዓምናው የተሻለና የሕዝብም ትብብር የታየበት ነው፡፡ በተለይ በብዙ ቦታዎች የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ከክርስቲያኑ ጋር ያላቸውን አብሮነት ያሳዩባቸው ክስተቶች ይበል የሚያሰኝ ናቸው፡፡ እኔ ተወልጄ ያደኩት ሙስሊም በሚበዛበት አካባቢ ነው፡፡ እኔ ባደኩበት አካባቢ የዛሬን አያድርገውን እኔ ተወልጄ ያደኩበትን አጥቢያ ቤተክርስቲያን ከክርስቲያኑ ጋር ያሰሩት ሙስሊሞች ናቸው፡፡ ይሄን እኔም አይቻለሁ፡፡ በእርግጥም ለመስኪድ ማሰሪያም ክርሲቲያኖቹ ሲያዋጡ ነበር፡፡ አሁን ሳስበው ይገርመኛል፡፡ ይሄ አሁን ሲናገሩት ለብዙዎች እውነት አይመስላቸውም፡፡ የእኛ ቤተክርቲያን በአካባቢው ቀደምት ከሚባሉት በመሆኑ እንደውም እንደተነገረን በንጉሱ ጊዜ ጥምቀት ሁለት ቦታ ይከበር ነበር፡፡ ይሄ በተራ ነው፡፡ አንድ አመት አንዱ ጋር ሌላው ጊዜ ሌላው ጋር ነበር፡፡ እነዚህ ቦታዎች በአጋጣሚ በአንዱ በኩል ሙስሊሞች ብቻ የሚኖሩበት ሲሆን በሌላው በኩል ክርስቲያኖች የሚበዙበት ነው፡፡ እና በሙስሊሙና በክርስቲያኑ መካከል ብዙ ጊዜ ወደ እኛ በኩል ታቦት ካልወጣ ፉክክር ነበር፡፡ እና በአንድ ወቅት እንደውም በሙስሊሞቹ በኩል መንገስ ሲገባው ወደ ክርስቲያኖቹ በኩል ሊሆን ነው ተብሎ ትልቅ ውዝግብ ተፈጥሮ ነበር፡፡ ይሄ ዛሬ ሲወራ ተረት ይመስላል፡፡ በታሪክ የሆነ እውነት ነው፡፡ የሚገርመው ከክርስቲያኖቸ በላይ ሙስሊሞች ታቦቱ ወደነሱ በኩል እንዲወጣ የማያደርጉት ጥረት የለም፡፡ ያለተራቸውም፡፡ የምርም ታቦት ወደነሱ በወጣ ጊዜ በጣም ደስተኞችና ሰብላቸውም ከብቶቻቸውም በጣም የሰመረ ዘመን እንደሚሆንላቸው ያምኑ ነበር፡፡ ደግሞም ይሆንላቸውም ነበር፡፡ ይሄ አሁን ለብዙዎች አይገባቸው ይሆናል፡፡ የቁሉቢን ገብርኤል ቅልብ ሰንጋ ስለት የሚያጨናንቀው እስከቅርብ ጊዜ ድረስም የሐረርጌ ሙስሊሞች ነበሩ፡፡  በነገራችን ላይ ከላይ የረሳሁት እኔ በልጅነቴ ከፋሲካ በኋላ የአክፋይ የሚያመጡልን ሙስሊም ጎረቤቶቻችን ናቸው፡፡ ሞሊዲ ሲሆን እነሱ ጋር ሄደን በቅቤ የተሰሩ የተለያዩ ነገሮችን ለመብላት እንሄድ እንደነበር ትዝ ይለኛል፡፡

በአንድ ወቅት አፈንዲ አንድ የአርሲ ሙስሊም ባላባት ኃይለስላሴ ጋር ድረስ መጥተው  ታቦት እና ቄስ እፈልጋለሁ እንዲሰጠኝ ሲሉ አመልክተው ነበር ሲል አስነብቦናል፡፡ ንጉሱ አንተ ሙስሊም ታቦት ምን ያረግልሀል ሲሉት በእኔ ግዛት ጥቂት ክርስቲያኖች አሉ ሰው ሲሞትባቸው ለመቅበር ብዙ ርቀት ሄደው ነው የሚቀብሩት ስለዚህ በዛው ታቦትና ቄስ ቢኖራቸው ከዚህ ሁሉ ደካም ያርፋሉ ሲል አሳምኖ ታቦትና ቄስ አስፈቅዶ ነበር ሲል አፈንድ ጽፎልን ነበር፡፡ ይሄ ዛሬ ላይ በጥላቻና ዘረኝነት ለተመረዝንው ለእኛ ከቶውንም ሊሆን የማይችል ነው፡፡ አባቶቻቸውን በዚህች አሀር ሲኖሩ በዚህ መልኩ ነው የኖሩት፡፡ የአንዱ መኖር ለሌላው አስፈልጎትና አንዱ ለሌላው መኖር ኖሮ፡፡ ይሄን የመሰለ የሕዝብ ትስስር ነው በ60ዎቹ የተነሳ የተረገመ ትውልድ አጥፍቶ ዛሬ በ21ኛው ክፍለዘምን ከእንስሳም ባነሰ አረመኔ የሆነ ትውልድ ተፈጥሮ ወገኑን እያረደ ያለው፡፡

በዛሬው እለት የሠላም ሚኒስቴሯ ሙፈሪያት በጃን ሜዳ ነበረች ሲባል ሰምቻለሁ፡፡ በእርግጥም ሙስሊም ወንድሞች ለሕዝቡ ዳቦ ሲያድሉ ሁሉ ታይቷል፡፡ የሠላም ሚኒስቴሯ ላለፉት ሦስት ዓመታት ሥራዋ መሆን የሚገባው እነዲህ ነበር፡፡ ሚኒስቴሩ ልዩ የሆኑ ፕሮገራሞችን በማዘጋጀት አሁንም ሕዝቡን በሚዲያዎች ማቀራረብና መርዛማ ትርክቶች ከትውልዱ ማጥፋት ይጠበቅበታል፡፡ ሥራውም ይሄው ነበር፡፡ ሸፍጥና ሴራን የሚነዙ ሚዲያዎችን በልዩ ሁኔታ በተለይ የምግስት የሆኑትን በማስገደድ ጭምር በሚኒስቴሮ የሚዘጋጁ የተለያዩ ፕሮገራሞችን ማቅረብ ግድ ይላል፡፡ መፍትሄው ከባድ አደለም ችግሩ ቁርጠኝነት የጠፋበት፡፡ ይልቁንስ ሸፍጥና ሴራን አሁንም በሕዝብ ላይ የሚሰሩ ስለበዙ እንጂ፡፡ በትግሉ ወቅት 27 ዓመት የተሰራበትን ዘረኝነት በራሱ ጊዜ አፍርሶ አንድ የሆነን ሕዝብ ነው በአለፉት ሦስት ዓመታት ወደለየለት አረመኔነት የተቀየረው፡፡ ለዚህ ደግሞ ወያኔ እየተባለ ከለላ ቢሰጠውም ዋናኛው የኦሮሞ ዘረኝነት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ አሁንም የኦሮሞ ዘረኝነት፣ ጥላቻና የበታችነት ስሜት አገር እያጠፋ እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል፡፡ እውነቱን ልንጋፈጥ ግድ ይላል፡፡ የኦሮሞ ፖለቲካ በጸረ-ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የመጣ ከወያኔ የከፋ አደገኛ አረመኔነትን በሕዝብ ዘንድ እያሰረጸ ያለ ነው፡፡ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነትና የኢትዮጵያ ከሆነ ነገር ሁሉ ሙልጭ ብሎ እንዲወጣ እያደረገው ነው፡፡ አሁንም ብዙ ነገሩ ተበላሽቷል፡፡

ልብ በሉ ኦሮሞነት የመጣው ከኦነጋውያን ጋር እንጂ ኦሮሞ የሚባል ቃል ራሱ በአብዛኛው ዛሬ ኦሮሞ በሚባለው ማህበረሰብ አይታወቅም፡፡ ይሄ በእኔ እድሜ ነው የምላችሁ፡፡ ጅማ ኦሮሞ አልነበረም፣ አርሲ፣ ሐረር፣ ባሌ፣ ቦረና እነዚህ ሁሉ ኦሮሞ አልነበሩም፡፡ ይሄን ስል አሁን ሰው ሊያምን አይችልም፡፡ ኦሮሞነት ከወለጋ አካባቢ ሲሆን መጀመሪያ በኦነጋውያን ወደ ሐረር ከዛ እንደ ወረርሽኝ አገሩን አጥለቀለቀው፡፡ የማወራው ስለ እውነት ነው፡፡ ለብዙዎች ኦሮሞ የሚባለው ቃል ብዙ ዘመን ያስቆጠረ ይመስላቸዋል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃሉን የተጠቀመው በወለጋ ሆሮጉዱሩ አካባቢ ለጉብኝት የመጣ አነቶኒዮ አባዲ የተባ ፈረንሳዊ ነው፡፡ ዘመኑ በ1860ዎቹ ይመስለኛል፡፡ እንደሚገባኝ የሆሮ ሰዎች ነጮቹን ኦርማ እያሉ ይጠሯቸው ስለነበር እነሱ መልሰው ኦርማ ለማለት ኦሮሞ በሚል የተፈጠረ ቃል ነው፡፡ ዛሬ በኬኒያ ያሉ ቦረናዎች ኦሮሞ ስለሚባለው ቃል ገና እየሰሙ ነው እንጂ አያውቁትም፡፡ ይሄ የኦሮሞነት ዘመቻ  ከ70ዓመት ወዲህ ነው ወደሌሎች እየተሰራጨ ዛሬ ያለበት ሕዝቡን ሁሉ ከማንነቱ አውጥቶ ባዶውን እያስቀረው ያለው፡፡ አዝናለሁ እውነቱ ይሄ ነው፡፡

የወለጋው ኦሮሞነት ዋና ተጽኖው ደግሞ የሚሲዮናውያን ስብከት ችምር ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የፕሮቲስታነት እምነት ቀደምት በዚህ ቦታ ነበር፡፡ ሲጀምር ጀምሮ በጸረ-ኦርቶዶክስ ነው፡፡ ዛሬ በኢትዮጵያ የመንግስት ስልጣን ላይ አብዛኛው በሚባል ሌላ ቀርቶ ከ80 በመቶ በላይ ኦርቶዶክስ ሲቀጥል ሙስሊም በሆነበት አማራ ክልል ሳይቀር አብዛኛው የካቢኔ አባል የጴንጤ እምነት ተከታይ ነው፡፡ የዚህ እምነት ተከታዮች በኢትዮጵያ ያላቸው ባሕሪ እንደሌሎች አገር የፕሮቴስታነት እምነት ተከታዮች አደለም፡፡ በዚህ ጉዳይ ከዚህ በላይ ብዙ ሊባሉ የሚችሉ አደጋዎች አሉ፡፡ የሆነ ሆኖ ግን የኦሮሞን ሕዝብ አንዱ ከኢትዮጵያዊነት ለማምከን የተጠቀሙበት ሂደት ነው፡፡

ኦነጋውያን ዓላማቸው ሁሉ ኦሮሞን ከኢትዮጵያዊነት ማውጣት ስለሆነ በኢትዮጵያ ታሪክ ትል ቦታ የነበራቸው ቀደምት የኦሮሞ አባቶች ለዛሬው ኦሮሞ ነኝ ለሚለው ትውልድ በሚያሳዝን ሁኔታ እንደ እርኩስ ነገር ነው የተሳሉለት፡፡ ይሄም በመሆኑ የዛሬው የኦሮሞ ትውልድ የእኔ የሚለው ታሪክና መሠረት እንዳይኖረው አድርገውታል፡፡ ዛሬ የኦሮሞ እያለ የሚያናፍሳቸው ባሕላዊ እሴቶች እውነቱ የኦሮሞ ሳይሆኑ የቦረናና የሸዋ ናቸው፡፡ እነገዳና ኢሬቻ የቀሩት በቀድሞው ዘመን ትልልቅ ቦታ በነበራቸው በእነዚሁ የሸዋና ቦረና ሕዝብ ነው፡፡ ሌላው ኦነጋውያን ስልት በቀደመው ታሪክ ለማጠልሸት የሚፈጥሩት ትርክት ነው፡፡ በተለይ ስለሚኒሊክ ለትውልዱ እየተነገረው የመጣው አሁን ጭራሽ ወደ አእምሮ በሽተኝነት እየቀየረው ይመስላል፡፡ ምንም ነገር እንዳያስተውል ተደርጓል፡፡ ገዳንም ሆነ ኢሬቻን ለዛሬ ያቆዮት የሚኒሊክ ወዳጆች የነበሩት ሸዋና ቦረና ነው፡፡ አርሲ፣ ጂማ፣ ባሌ፣ ሐረርጌ በእስልምና ምክነያት ሁለቱንም ባሕሎች ትቷቸው የነበረ ቢሆንም ተከሳሹ ግን ሚኒሊክ ናቸው፡፡ ዛሬ እንደገና በኦሮሞነት ብዙ ሙስሊሞች በማይመለከታቸውና በማያምኑበት በኦሮሞነት አጀብ የኢሬቻ ተከታይ ሆነዋል፡፡ እንዲህ ያለ አከሄድ አደገኛ ነው፡፡ ኦሮሞነት አደገኛ የአእምሮ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ ብዙ ሰው ልብ ያለው አለመሰለኝም፡፡ ዛሬ በአፍሪካ ሕብረት የሴኩሪቲ ኃላፊ የተደረገው ኃይሉ ጎንፋ ሚኒሊክ ስሜን ቀይሮት እንጂ ኃይሉ አልባልም ነበር ሲል እየሰማን አደጋው ካልታየን አሁን ጫፍ ላይ ስለደረሰ ነገ ነገሮች ሁሉ ከተበላሹ በኋላ ማጠፊያው እንደሚቸግር አትጠራጠሩ፡፡ በዚህ እድሜና ሊያውም በውትድርና ጀነራል የተባለ ሰው እንዲህ ከሆነ ሌላው ምን ይሁን? ይሄው ግለሰብ በቅርቡ አርፋችሁ ተቀመጡ ፊንፊኔ ውስጥ አትኑሩ ያላችሁ የለም  የሚል መልክት ሲያስተላለፍ ነበር፡፡ በሱ ቤት የአዲስ አበባ ሕዝብ የሚኖረው ኦሮሞ ስለፈቀደ ነው፡፡ ሁኔታዎች ከወዲሁ እልባት ከላገኙ ይልቁንስ ተቃራኒው ክስተት ያስፈራል፡፡ ዛሬ ማንም ከኦሮሞ ጋር መኖር አይፈልግም፡፡ ጉሙዝና ሲዳማ እነሱም ለጊዜው ነው እንጂ፡፡ እውነቱ እየሆነ ያለው ይሄ ነው፡፡ ሕዝቡን በጥላቻ፣ ዘረኝነትና የበታችነት ለዘመናት አብሮት ከኖረው ሕዝብ ጋር በሰላም እንዳይኖር አድርገውታል፡፡ አዝናለሁ፡፡

በነገራችን ላይ ሰሞኑን ሽመልሽ አብዲሳ ከብርሀኑ ጁላ ጋር ወደ ሱማሌ ሄዶ ነበር አሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ጤነኞች ስላልሆኑ የሚያደርጉት የሚያውቁ አይመስለኝም፡፡ ይሄ አይደረግም አይባልም፡፡ ከዚህ በፊት ለማ የሚኒሶታን ኮንሲላ ለመክፈት ተገኝቶ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ለማ በወቅቱ በሕዝብ ዘንድ ይወደዳል፡፡ ሆኖም ከአሰራር አንጻር ስህተት ከመሆኑም በላይ ችግሩ የነበረው የኦሮሞነት ልክፍት ነበር፡፡ አሁንም ሽመልሽ አብዲሳ ወደሱማሌ ሄዶ ከሆነ ቀጥሎ ሊመጣ የሚችለውን ከወዲሁ መገመት ጥሩ ነው፡፡ በሱማሌ ወረራ በሚባለው ጦርነት ከሆነው ጋር ተመሳሳይነት ያለው ጉዳይ በመሆኑም ትልቅ የደህንነት ችግር እንደሆነ ኢትዮጵያውያን ሊረዱት ይገባል፡፡ ለመሆኑ ሽመልስ ይቅርና የታማጆር ሹሙስ ቢሆን ሄዶ ከሆነ በምን ምክነያት ሊሄድ ይችላል? በኦሮሞነት የማይሰራ ወንጀል የለም፡፡ ይሄ ጉዳይ እንዲህ በቀላሉ ሊታለፍ አይገባም እውነት ከሆነ ማለት ነው፡፡  ሚዲያዎች ስለ አገር ደህንነት ስለማይረዱ ይሁን ወይም አዚም ተደርጎባቸው በትግራይ ተገኙ ስለተባሉት ሱማሌ ወታደሮች ምናምን ሲሉ ሰምቻለሁ፡፡ ሲጀምር ስለሱማሌ ወታደሮች ሽመልስ አብዲሳ ምን አገባው? የታማጆር ሹሙም በዚህ ጉዳይ ሱማሌ ሄዶ ባለስልጣን ማናገር ያለበት አይመስለኝም፡፡ አገሪቱን የሚውክል ሥልጣን ያለው አካል እያለ፡፡ ይሄ ነገር እውን ሆኖ ከሆነ ሽመልስ ልዩ ሐይል እያለ እስከዛሬ ሲያመርት የነበረውን ቅልብ ኦነጋዊ ሰራዊት ተጠቀሞ ሌላ የአገር ደህንነት ሴራ ሊሰራ እንደሆነ ብዙም መጠራጠር አይገባም፡፡ ይህ ጉዳይ ከመንግስ ከሚባለው በኩል ማብራሪያ ሊሰጥበት ይገባል፡፡

ሌላው በአሁን ወቅት የትግራይ ጉዳይ ብዙ እየተባለበት ነው፡፡ ሌላ ተመሳሳይ ታሪክ እንዳይፈጸም እፈራለሁ፡፡ የኦሮሞ ብዙ ትውልድ በኦሮሞነት ሲበከል የትገሬ ብዙ የሚባል ደግሞ በወያኔ አረመኔያዊ ባሕሪ ተበክሏል፡፡ እምነት፣ የማህበረሱብ እሴቶች ሁሉ የተወ አደገኛ ትውልድ ተፈጥሯል፡፡ ከብዙ ሚዲያዎች እንደምሰማው የትግራይ ሕዝብ ለችግር እየተጋለጠ ነው፡፡ አውቃለሁ ብዙ ሕዝብ ይኖር የነበረው በእርዳታ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ የጦርነት ወቅት ብዙ ቀውስ ሊፈጠር እንደሚችል፡፡ በውጭ የሚኖሩ ትግሬ ነን የሚሉ እየተናገሩ ያሉት በጣም አሳዛኝ ነው፡፡ እነዚህ የትግራይ ሕዝብ ሁሉ ቢያልቅ ደንታቸው አደለም፡፡ የእነሱ ሞት የሆነው የወያኔ መሞት ነው፡፡ አሁን በሕዝቡ ሥም ገንዘብ ከሰበሰቡ በኋላ አንልክም ብለዋል አሉ፡፡ ድሮም እነሱ ለተቸገረው የትግራይ ሕዝብ እርዳታ ያደርጋሉ ብሎ ማሰብና ምን አልባትም የትግራይን ሕዝብ ይረዳሉ ብላችሁ ገንዘብ ያዋጣችሁ አዝናለሁ፡፡ ይሄን ገንዘብ ለወያኔ መልሶ ማደራጀት እንደሚያውሉት አትጠራጠሩ፡፡ ከጅምሩም ወያኔ አንድ ሚሊየን የትግራይ ሕዝብ በረሐብ ሲያልቅ በእርዳታ ያገኘችውን ገንዘብ ለጠር መሣሪያ መግዣ እነዳዋለችው ታሪክ ያስታውሳል፡፡ አሁንም ታሪክ እራሱን ሊደግም እንደሚችል አትጠራጠሩ፡፡ ለሕዝቡ ግን ሁሉም ወግን ያስብበት፡፡ እኔ በዛ ያሉ ሁኔታዎች እረዳለሁ፡፡

ዛሬ ሥልጣን ላይ ያሉት የሚሰሙ ከሆነ ዛሬም አሳስባለሁ፡፡ አትቀልዱ፡፡ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አገርን ወደከፋ ሁኔታ እየወሰዳት ይመስለኛል፡፡ ሕዝብና አገር አደጋ ላይ እያለ ቅድሚያ እስካሁንም ቅድሚያ ሲሰጥ የምናየው የመናፈሻና የችግኝ ተከላ ነው፡፡ ሰሞኑን 8 ቢሊየን ችግኝ አፍልተን ለጎረበት አገሮች ጭምር እንሰጣለን የሚል ቀልድ ሰምቻለሁ፡፡ እንዴት እንሚታሰብ አልገባኝም፡፡ ይሄ ሁሉ ሕዝብ በረሐብና በተለያዩ የደህንነት አደጋ ላይ ተጋልጦ እያለ ችግኝ ማፍላትን ቅድሚያ መሠጠቱ ሳያንስ ሊሆን የማይችል የ8ቢሊየን ችግኝ እቅድ ሊያውም ለጎረቤት አገር ሁሉ የሚሰጥ ማውራት በአውነት አሳፋሪ ነው፡፡ ዛሬ አገራት ዜጎቻቸውን ከመጣው ወረርሽኝ ለመታደግ ምን ያህል ወሳኝ ፕሮገራማቸውን እንዳዘገዩ ጥሩ ትምህርት በሆነ ነበር፡፡ አሁንም እላለሁ ቀልዱን አቁማችሁ ሕዝብን ወደመታደግ ሥራ ግቡ፡፡ ገበታ ለአገር የሚለውን ቁማር ዛሬ ለምን ገበታ ለወገን አይባልም? የሕዝብ ጉዳይ ከስብዕና ይልቅ የቁማር ማትረፊያነትም ሲውል እያየን ነው፡፡ አባ ገዳ ለትግራይ ረዳ ምናምን ብሎ ሌላ ቁማር ለመስራት፡፡ እባካችሁ አገር እንዲህ ባለ ቁማር አይመራም፡፡ አሁንም እላለሁ ከወያኔ ትንሽ እንኳን ተማሩ፡፡

በውጭ የምትገኙ በተቻላችሁ አቅም በታመኑ የገንዘብ አሰባሳቢዎች ለማሰባሰብ ሞክሩ፡፡ ለነገሩ የውጭው ሰው እየሰለቸው ነው፡፡ እነሱ ያፈናቀላሉ የወጭው ነዋሪ ገንዘብ ይልካል፡፡ በዚህ ላይ የጎፍንድሚ አጭበርባሪው ብዛት፡፡ ለማንኛውም አሁን ወሳኝ ጊዜ በመሆኑ ሁሉም ወገን ይረባረብ፡፡ ለከርሞው ዛሬ ሥልጣን ላይ ያሉት ወይ ከተወገዱ ወይ ልብ ከገዙ ይታሰብበታል፡፡ በአንዳንዶቻችንማ ሐሳብ የዛሬ ሶስት ዓመት ለውጥ ሲባል ሁለተኛ ረሀብ የሚባል ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳይሰማ ብዙ አቅደን ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ራሷን አይደለም ምስራቅ አፍሪካንና ከፍል መካከለኛውም ምስራቅ አረብ አገራትን የመመገብ እድል ነበራት፡፡ ይሄ ደግሞ ተዓምር በመስራት ሳይሆን በትክክል በማቀድና በመሥራት የሚመጣ ነው፡፡ ይሄን ኃላፊነት ሙሉ የፖሊሲ መቀየር ቁርጠኝነት ኖሮት መንግስት ለባለሙያዎች ቢሰጠው በሦስት አመት ባልሞላ ጊዜ ሊከወን የሚችል ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ በቂ አውቀትና የሐሳቡም ንድፍ አለ፡፡ ዛሬ መቶ ሚሊየን ዪሮ ለመስጠት ይሄን ካለደረጋችሁ ይህን ካልፈጠራችሁ የሚሉንንም ከእነጭርሱም አንፈልጋችሁም ማለት በቻልን፡፡ ለዚህ ቁርጠኛ የሆነ መንግስት ባለመኖሩ አዝናለሁ፡፡ አሁንም ግን ልብ የሚገዙ ከሆነ እጠይቃለሁ፡፡ ኢትዮጵያ ከዘመነ ኃይለስላሴ ጀምሮ በረሀብ እንጠራለን፡፡ ሁሉም አገራት በሆነ ወቅት ረሀብን አይተዋል፡፡ ሆኖም ሁለተኛ እነዳይመጣባቸው በመስራታቸው ዛሬ ሁሉም ከራሳቸው አልፈው ለሌሎች ሆነዋል፡፡ እነ ሕንድ ይሄን የሚህል ሕዝባቸውን መግበው ያድራሉ እንደኛው በሚመስል መሬታቸውና የሕዝብ አኗኗራቸው፡፡ ምክነያቱ የእቅድ አሰራር እንጂ ተዓምር አደለም፡፡ ኃላፊነት ያለበት መንግስት በመኖሩ ማለት ነው፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop