በሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት ፈፀመ

በሁመራ አቅራቢያ “ማይካድራ” በተባለ አካባቢ የህወሓት ልዩ ኃይል ባልታጠቁ ዜጎች ላይ አሰቃቂ እልቂት መፈፀሙ ብዙዎችን እንዳሳዘነ ዜጎች በተለያየ መገናኛ ዘዴዎች የገለፁ ነዉ።”በማይካድራ የተፈፀመው ጭፍጨፋ አማራን መሰረት ያደረገ የዘር ማጥፋት ወንጀል” ሲል የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ድርጊቱን ኮንኖአል።
–የኢትዮጵያ አየር ኃይል በትግራይ ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን አስታወቀ። የትግራይ ክልል በበኩሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዉጃለሁ ማለቱ ተሰምቶአል።
–በትግራይ የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ በርካቶች ወደ ሱዳን ሊሸሹ ይችላል ተባለ። የዓለሙ የሰብዓዊ ጉዳዮች ድርጅት በክልሉ የሰብዓዊ ርዳታ በተቻለ ፍጥነት እንዲደርስ እንፈልጋለን ፤ ምግብ እና ነዳጅ በፍጥነት ሊደርስ ይገባል ሲል ጥሪ አቅርቦአል።
–በዩናይትድ ስቴትስ ረት በ 24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ 202 ሺህ ሰዎች በኮቪድ 19 መያዛቸዉ ተነገረ። በአንድ ቀን ብቻ 1535 ሰዎች በኮቪድ መሞታቸዉም ተዘግቦአል። አሜሪካ ከዓለማችን በኮሮና ወረርሽኝ የተጠቃች ቀዳሚዋ ሃገር ናት።
ዜናዉን በዝርዝር አዳምጡ !
DW
ተጨማሪ ያንብቡ:  Ethiopia freezes Nile agreement

1 Comment

  1. ይህ ግፍ የሚያሳየው በተለያዪ የሃገራችን ክፍል በገንዘብና በመሳሪያ እየተደገፉ በኦሮሞ ስም ሰው ሲያርድ የነበሩት የወያኔ ተላላኪዎች መሆናቸውን ነው። በመሰረቱ ወያኔ አማራን ይጠላል። ለዘመናት ሲተረኩት የኖሩት የፈጠራ ፓለቲካ ባህር ማዶም ተሻግሮ ሰው ከሰው ያላትማል። ወያኔ ማለት እንስሳ ማለት ነው። አሁን ጠ/ሚ በቲዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መረጃ መሰረት ሽራሮ ላይ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት “እጅና እግራቸው ታስሮ ተረሽነው ተገኝተዋል” ይሉናል። ታዲያ ፈጥኖ ከመቅበር ይህን ጉድ በቪዲዮ በመቅረጽ የድረሱልኝ ጥሪ ለሚያሰሙት የክፍያ ቡችላዎችና የአለም የጤና ጥበቃ ሃላፊ የሆነው የወያኔ አሽከር እንዲያፍር ለሚደውልላቸው ሰዎች ግፉን መላክ ነው። የዛሬ 30 ዓመት ገደማ በ Ethiopian Review (Hard Copy) የተጻፉ ሁለት መጣጥፎችን አግኝቼ ስመለከት እጅግ ተገረምኩ።
    የትግራይ ልጆች ምን ይላሉ የሚልና ተሳቢ መቀሌ በሚሉ በእነዚህ ሁለት አርዕስቶች ሥር በአንድ ገጽ የሰፈረው ጉዳይ ዛሬ የምናየውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል። እኔን እጅግ የሚያሳዝነኝ እንዴት የአጋዚ ሃይል መሪ የነበረን ሰው የወታደሩ የመገናኛ ዋና ሃላፊ አርጎ ሰው ይሾማል? የስንቶችን ደም የጠጣ? አሁን ማን ይሙት ለሃገር ለወገን ይቆማል? ግን እብደቱ ከውስጥም ከውጭም ስለሆነ ከወያኔ የዘር ቆጠራና ጥናት ሌላ የሰሜኑ እዝ ሃገሬ ወገኔ ብሎ በወያኔና በወያኔ አፍቃሪዎች ክፋት ወጥመድ ውስጥ መግባቱን በውል አልተረዳውም ነበር። የሚያስቀው የወያኔ አመራር አካላት ያለመከሰስ መብታቸው ተነሳ ይሉናል። በሃገር ሰራዊት ላይ ጭፍጨፋ የፈጸመን ቡድን እዚያው መደምሰስ ነው። እልክ አስጨራሽ ውጊያ በማድረግ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን አፈር ማልበሰ ነው። ወያኔ ተሸንፌአለሁ ብሎ በሰላም እጅን ሰጥቶ በሰላም መኖርን አያውቅበትም። ስረ መሰረቱ በተንኮል የተገነባ የክህደት ቡድን ነው። የት አለ 1.3 ቢሊዪን ብሩ ለባንክ የተላከው? ለምንድነው ወያኔ የወታደሩ ስንቅና ደመዝ በመጣበት ቀን ውጊያ የከፈተው? እነማን ነበሩ ከአዲስ አበባ በስልክ ነገሮችን ያስተላልፉ የነበሩት? ለምን ብር የጫኑት አውሮፕላኖች መቀሌ ካረፉ በህዋላ ተኩሱ ተከፈተ? ለምንስ ነበር ከዚያ ቀደም ብሎ እባቡ ዶ/ር ደ/ዪን ገንዘቡ እንዲላክ ለጠ/ሚሩ የደወለው? ይህን ሁሉ የሴራ ገመድ አገጣጥሞ ኑና ግጠሙኝ እያለ ያቅራራ የነበረን ሃይል ወጥመድ አለማየት ጠ/ሚሩም ሆነ አማካሪዎቻቸው፤ የስለላ ክፍሉም ሆነ ሌሎች የፓሊስና የደህንነት ክፍሎችን ቂልነት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል።
    በማይካድራ ሰዎችን በግፍ መገደላቸው የወያኔን ጭካኔ ያሳያል። ሌሎችም እንዲሁ ይገደላሉ። ወታደሩም ሆነ ሲቪሉ እጄን ለወያኔ ሰጥቼ ከሞት እተርፋለሁ ብሎ የሚያምን ደንቆሮ ነው። ጭራሽ ከሰው ባህሪ ውጭ ናቸው። ገና ብዙ ጉድ እንሰማለን። በመቀሌ ያሰሯቸውን ሁሉ ይገድላሉ። ጦሩ ቶሎ ገስግሶ ቀድሞ አፈር እስካላለበሳቸው ድረስ ከወያኔና ከደጋፊዎቻቸው ሌላ ቀሪ ሰው አይኖርም። ካላመናቹሁኝ ጠብቁ እና እዪ! በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share