November 4, 2020
12 mins read

ሰሞነኝነት እና  አድር ባይነት ከእኛ ይራቅ ! – ማላጂ

አገራችን እና ህዝቧ ያላስተናገዱት የመከራ እና የሰቆቃ ዓይነት እንዳልነበር እየታወቀ ለዚህ ምንጭ እና ከምንጩ ማድረቂያ መድሃኒት ላይ ከማተኮር ይልቅ ሰሞነኛ በመሆን መጠመዳችን ለተመሳሳይ እና ድግምግም ችግር ዳርጎናል ፡፡

እንደ ክፉ ደዌ አመም ፤አገም እያለ በአገራችን የሚከሰት የተቀናጀ እና የተደራጀ የግል እና የቡድን  ሴራ መነሻዉን ክፋት ፤መዳረሻዉን ጥፋት ላይ  በማለም ሲንቀሳቀስ በተለይም ከ1960’ዎች  ጀምሮ የነበረዉ  ብሄር ተኮር የቡድን እና ጠናጠል ተልዕኮ “በነጻ አዉጭነት ” ስም የሌለ የጭቆና እና ባርነት ታሪክ በመፍጠር ከዚያ አስካሁን ዋና የመሸሸጊያ እና የማጥቂያ መሳሪያ በማድረግ እንደሚገለገሉበት ይስተዋላል ፡፡

ህዝብን ከህዝብ በመነጠል አባሪ እና ገባሪ በማድረግ እንደ አገራችን የዘመን አቆጣጠር ከ ግንቦት 20 ቀን 1983 ዓ.ም. ጀምሮ ከህዝብ በተከፈለ መስዋዕትነት ለመንበረ ስልጣን ከወጡበት ጊዜ አንስቶ ድንበር መናስ፣ ህዝብ ማስለቀስ እና ደም ማፋሰስ ዋና የስልጣን ማስጠበቂያ ዘዴ አድርገዉ እንደሚወስዱት ከስረ መሰረት ማዎቅ እና ታሪክን ማጠየቅ ይህ በጥፋተኞች ህጋዊ እና ትክክለኛ ሆኖ አድርጎ የመዉሰድ ልማድ እንደነበር መገንዘብ ከሰሞኘኝነት አስተሳሰብ እንድንወጣ ያግዘናል ፡፡

በዓለም ታሪክ  የአንዲት ሉዓላዊት አገር የሚያስተዳደር አካል እና መንግስት (ኢህዴግ) የራሱን ህዝብ እና አገር በጥላቻ፣ ስጋት ፣ ንቀት እና ፍርሃት በመታጠር አንድን ህዘብ ጠላት እና ወዳጅ ብሎ በመፈረጅ ከፋፋይ አስተዳደር  በማሰፈን የተጀመረዉ የማሳደድ ተግባር አሁን ባለንበት ዘመን መቀጠል ምክነያት የሰሞነኝነት እና የአድር ባይነት እንክርዳድ ፍሬ ዉጤት ነዉ ፡፡

በራስ አገር ምድር የራስን ህዝብ እና አገር እንደጠላት የመቁጠር እና ከልክ ያለፈ መጠራጠር አገሪቷን በግዞት ፤ህዝቡን በባርነት የግል መሳሪያ ማድረግ የተለመደ መሆኑን በመረዳት ለመከላከል በጋራ አለመቆም ሌላዉ የአድር ባነት እና ሰሞነኝነታችን ችግር ዉጤት ነዉ ፡፡

ከጅምሩ አገሪቷ የባህር በር ባለቤት እንደነበረች እያወቅን የባህር በር ማሳጣት፣ ኢትዮጵያዊነትን እና የዜግነት መብትን  ከፖለቲካ ስልጣን እና ማንነት በታች የማየት፣ ማጥላላት ፣ ታሪክ ማሳካር ፣ለዘመናት ህይዎት እና አካል ዋጋ የከፈሉትን  ቀደምት ጀግኖች የተጋድሎ ታሪክ ማዛባት እና ማጥላላት ፣ብሄራዊ እና ህዝባዊ ጦርን አፍርሶ “ብሄር ተኮር ”ጦር ኃይል ማቋቋም፣ በኢትዮጵያዊነት እና በግል ብቃት እና ማንነት የተገኘን ድል መታሰቢያ ማሳነስ / ማስቀረት እና መተካት (ለአብነት የመኮንኖች ማሰልጠኛ ሆለታ ማዕከል ጀ/ል ሙሉጌታ ቡሌን ፣ የቀድሞዉ የኢትዮጵያ መሪ ኮ/ል መንግስቱ  ኃይለ ማርያም……) መታሰቢያ እንዲኖር አለማድረግ ፣ ማናቸዉም ቅርስ ዉርስ እንዳይቀጥል ወይም እንዲፈርስ ማድረግ የመሳሰሉትን ለረጅም ዓመታት ካየንዉ እና ከቀዳሚ ታሪክ አለመማር በራሱ ዘላቂ እና የማያዳግም አገራዊ የችግር መድሃኒት እንዳናፈላልግ እንቅፋት ሆኖብናል ፡፡

ይህ በግዴለሽነት እና ቸልተኝነት የተጀቦነ  አድር ባይነት  እና ሰሞንኛነት እንደ ህዝብ  ለተደጋጋሚ እና ተመሳሳይ ችግር ተጋላጭ አድርጎናል ፡፡

በዚህ ሳምንት እንኳን የምንሰማቸዉ የጥፋት እና ሞት ምኞት ናፋቂዎች ድርጊት( በምዕራብ ወለጋ ጎሊሶ ወረዳ እና ትናንት በመቀሌ ጦር ኃይል ሠፈር) ከብሄራዊ እና ህዝባዊ ዕይታ ይልቅ ብሄረሰባዊ ካባ ተላብሶ በብሄር የመብት ጥያቄ አንጋቢነት እና መልስ ሰጭነት በእነርሱ መዝገበ ቃላት “ነፃ አዉጭነት” ጭንብል ከስድሳ እና ሠባ አመት በፊት የዘራ እንክርዳድ በመስከር በህዝቡ መካከል የጥላቻ እሾክ እየተከሉ ይገኛሉ ፡፡

ከ1983 ዓ.ም .ጀምሮ (ከ27 ዓመት በፊት ) ነጻ ወጣን ያሉ ነጻ አዉጭዎች ካላቸዉ ህዝባዊ ንቀት እና ጥላቻ የተነሳ ለስልጣን ዕድሜ መግዣ በዳግም ነጻ አዉጭነት ስም ተደጋጋሚ የህዝብ ሞት እና እንግልት ድግስ እያዘጋጁ በህዝብ ዉድቀት እና የአገር ድቀት የሚደሰቱት በቃችሁ የሚለቻዉ ባይኖርም ግፍ አይፈር መሆናቸዉ አሁንም ድረስ በፍርሃት እና ስጋት ድባብ ዉስጥ መኖራቸዉን የጥፋት ተግባራቸዉ ምልክት ነዉ ፡፡

ዛሬ ህዝብ ፣አገር እና መንግስት እንዲነጣጠሉ ጉድጓድ ለሚምሱ እና ቅጠል ለሚበጥሱ ትናንት በህዝብ መስዋዕትነት በተገኘ ድል በስልጣን ኮርቻ የነበሩት እና ጥገኞች የስልጣን ጥመኞች አንድ በሚያደርጓቸዉ የአገር እና ህዝብ ጥላቻ ላይ ቆመዉ ለሚያራምዱት የጥፋት ስልት ለመከላከል ከአድር ባይነት እና ሰሞንኛ  አስተሳሰብ ወጥተን በህብረት እና አንድነት በሚቻለዉ ሁሉ ለአገር ህዝብ የሚደግሱት የትፋት ወጥመድ  እና ግብዓተ መሬቱ የነሱ እንዲሆን በአንድነት በትብብር መትጋት እና መስራትን ይጠይቃል ፡፡

በያዝነዉ ሳምንት በምዕራብ ወለጋ የሆነዉ አንድን ማሀበረሰብ ለይቶ እና ነጥሎ ማጥቃት እና  ማጥፋት እንዲሁም በመቀሌ የጦር ኃይል ሠፈር የተከጀለ ጥቃት  በአገር እና ህዝብ ላይ የተሸረበዉ የጥፋት ሴራ ለዓመታት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የታየ ሲሆን ይህም ከ1980’ ዎች  አስከ ቅርብ ዓመታት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች የሆነ የትፋት አካል ነዉ ፡፡

ይህ ተደጋጋሚ ጥፋት እና ማን አለብኝነት የኢትዮጵያ ህዝብ ከ27 ዓመታት ጀምሮ እንዲሁም መንግስት ከሁለት ዓመት በፊት ችላ ያሉት  የለየለት ህዝባዊ ንቀት እና ጥላቻ  ዉጤት ነዉ ፡፡

አበዉ  “ቁጭ ብለዉ የሰቀሉት ቆሞ ለማዉረድ ያዳግታል”  የሚለዉ  ብሂል ለእኛ አገር ችግር መደራረብ ሁነኛ ማሳያ ነዉ ፡፡

በአገር እና ህዝብ ላይ ጥልቅ እና የማይታረቅ ጥላቻ ፣ ንቀት እና በቀል ለተሸከሙት ከሰንኮፉ መንቀል እና መቀልበስ ሳይሆን ሰንኮፉን ከመሰረቱ ማጥፋት እና እንዳልነበር ማድረግ ከዳግም ጥፋት የሚታደግ በመሆኑ በመቀልበስ ስም የሚታይ መለሳለስ ከድጥ ወደ ማጥ ስለሚከት የዚህችን አገር ስጋት ምንጭ ማድረቅ ያስፈልጋል ፡፡

አንድ ነገር መንስኤ እና ፍጻሜ በጥሞና ተመልክቶ ሳይቃጠል በቅጠል ማለት አገርን ከጥፋት፣ ህዝብን ከሞት እና ስደት ፣ መንግስትንም ከታሪክ ተጠያቂነት እና ከትዉልድ ጎደሎነት የሚያድን እና የሚከላከል ይሆናል፡፡

የአንድ አገር ህዝብ አንድነት እና ደህንነት የሚረጋገጠዉ አስመሳይ እና አድርባይነት በእዉነተኛ ማንነት እና በቁርጠኛ እርምጃ ላይ የተመሰረተ ህዝባዊ አመራር ሲኖር ብቻ ነዉ ፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊ/ ት በራሱ እና በአገር ፣ወገኑ ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ስጋት አስቀድሞ በመረዳት እና በመገመት መከላከል እና ከድንገቴ ሰሞንኝነት እና አድር ባይነት በማላቀቅ በድግምግሞሽ ከገጠመን ድርብርብ ችግር እና የኋላ ታሪክ ድርሳናት በመማር ራሳችንን እና አገራችንን ከዳግም ጥፋት ለመታደግ መንቃት እና መዘጋጀት ይኖርብናል ፡፡

በመጨረሻም ዉድ እና አይተኬ ክቡር ህይታቸዉን ከትናት አስከዛሬ በግፍ ለተገደሉ፣ለተጨፈጨፉት የአገራችን ህዝቦች እና ወገኖቻችን መድኃኒት ዓለም ነፍሳቸዉን በገነት ይቀበልልን ፣ ስማቸዉን ከመቃብር በላይ ዉሎ ለተዉልድ ሲተላለፍ እና ሲዘከር እንዲኖር በታሪክ ማህደር  እንዘክራቸዉ ፤ከሞት ለተረፉት እና ለቀሰሉት ጨርሶ ይማራቸዉ ፤ ለአገራቸዉ እና ህዝባቸዉ እዉነት መስካሪ ታሪክ ሰሪ ለመሆን ያብቃቸዉ ፡፡

 

እናት አገር ምንጊዜም ትኑር !!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop