ሰበር ዜና ጦርነት መጀመሩ ታወቀ – የጠ/ሚ አብይ መግለጫ

ሰበር ዜና ጦርነት መጀመሩ ታወቀ –  የጠ/ሚ አብይ መግለጫ

ተጨማሪ ያንብቡ:  በሀረሪ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ የወንጀል ድርጊት መባባስ በስጋት እንድንኖር አድርጎናል ሲሉ የክልሉ ነዋሪዎች ገለጹ

2 Comments

  1. ጦርነት ማንም አይፈልግም፤፤ ባይሆንም ይመረጥ ነበር፤፤ እንዳለመታደል ሆኖ ገብተንበታል፤፤ ተወደደም ተጠላ ምርጫው ጆርጅ ቡሽ እንዳለው “You are either with US or your are with THEM”. መሃል መንገድ የለም!! እንደ ኢትዮ360 ማምታት አይቻልም፤፤
    ወያኔ በምንም ተአምር ሊያሽንፍ አይችልም፡፡ ልክ ሻቢያ በባድሜ ጦርነት እንደሆነው የወያኔ የጦርነት “አሸናፊነት” false pride አከርካሪው መሰበር አለበት፤ ይሰበራልም!! ከድሮም አማራና ሻቢያ ነበሩ አራት ኪሎ ያደረሷቸው፤፤ አሁን ጭራሽ ከእነሱ ተጣልተው ምን ተማምነው እንደሆነ ይታያል፡፡ አንቀጽ 39 ብለው የጻፏትም ማስፈራሪያ ብቻ እንደሆነ ግልጽ ሆኗል፤፤
    ሚሊዮኖች ከእርስዎ ጋር ነን ዶ/ር አቢይ!
    Ethiopia shall prevail!

  2. አይ እናንተ ደግሞ የምን ጦርነቱ መጀመሩ ታወቀ ነው፡፡ ወያኔ እኮ ለዘመናት ሲዋጋ ነው የኖረው፡፡ ደ/ር አብይ ከእንቅልፉ ነቃ ብትሉ አይሻልም እንዴ? በመቀሌ ፉከራው፤ ማሰልጠኑ፤ ምሽግ በተለያዪ ስፍራዎች መቆፈሩ፤ መከራ ብቻ የሚዘንብበት የትግራይ ህዝብ ገንዘብና እህል አዋጣ መባሉ ያ ወያኔ ለጦርነት እንደሚዘጋጅ እና ዶ/ር ደ/ዪንም እናሸንፋለን ማለታቸው ወያኔ ማበድን እንዴት ጠ/ሚሩ ዘነጉት፡፡ አሁን ውጊያው ተጀመረ መባሉ የወያኔን ሁለት ዋና ባህሪያት ያሳያል፡፡ ሌብነትና ጠብ ጫሪነት፡፡ መጋዝን መዝረፉ፤ ሃገር በሚጠብቀው ከመላው የሃገሪቱ ክፍል በተወጣጣው ሰራዊት ላይ ያልተጠበቀ ተኩስ ከፍቶ ሰው መጨረሱ ምን ያህል አረመኔዎች እንደሆኑ ያሳያል፡፡ ከዚያው ከወታደሩ ውስጥ ሆነው የወያኔን ስራ የሚሰሩ ለመኖራቸው ተሿሚውን ጄ/ ወያኔ አልቀበልም ብሎ መመለሱ ራሱ መልክት ነው፡፡
    ቆም ብለን ከአለፈ ታሪካቸውና አሁን ከሚቆፍሩት ጉድጓድ የምንማረው ወያኔ ለራሱ ለመኖር ሰው መማገድ ሃገር ማተራመስ የዛሬ 60 ኣመት ጀመሮ የተካነበት ሙያው ነው፡፡ ልብ ያለው አሁን ረጋ ብሎ በኢትዮጵያ መሬት የተሰገሰጉ የወያኔ ተላላኪዎች አንዳንዶች በፌዴራልና በክልል ባለስልጣን የሆኑ ሊያደርጉ የሚችሉትን ካለፈ ተግባራቸው በመረዳት በአይኔ ቁራኛ መጠበቅ አለባቸው፡፡ ከወያኔ ስልቶች የሚከተሉት ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡
    ሀ. በጦርነት ግንባ የሚያስቀድመው የትግራይ ተወላጅ ያሆኑትን ሲሆን ከጀርባ እንዳይሸሹ የትግራይ ተወላጆች የጠብቋቸዋል። ስለሆነም መንግስት ማንኛውንም ተዋጊ በሰላም እጁን እንዲሰጥ በየጊዜው መጠየቅና መልዕክት ማስተላለፍ አለበት።
    ለ. የወያኔ ሌላው መሳሪያ ሁሉን ነገር በከተማም ሆነ በገጠር በኣሳት ማጋየት ነው። አዲስ አበባ እንደገቡ በተከማቸ መሳሪያ ላይ የለኮሱት እሳይ እልፎችን ገድሏል። በጎንደር፤ በአዲስ አበባ፤ በሃረር፤ በመቱ በሌሎችም ገቢያዎችን፤ የመሰብሰቢያ አዳራሾችን በእሳት ለኩሰዋል። ወያኔ እሳት ከውጊያ መሳሪያው
    ሐ. በምግብ በውሃ እና በተለያዪ ተሽከርካሪዎች ላይ መርዝ መጨመር፤ ቦንብ ማጥመድ፤ በገቢያ ላይ ማፈንዳት (ይህ በራሳቸው በትግራይ ህዝብም ላይ ሌላ ነው ያደረገው በማለት) ህዝቡን ለማነሳሳት የሚጠቀሙባቸው ብልሃቶች ናቸው።
    መ. በትምህርት ተቋሟት እሳት በማስነሳት የመማሪያ ክፍሎችን፤ የህክምና ማእከሎችን ማውደም ነው። በጦርነት እናሸንፋለን የሚሉት ዝም ብሎ ቱልቱላ ነው። ህዝብን ለመከራ ለምዳረግ፤ ረሃብና ጉስቁልና ለማላበስ እንጂ እነርሱ በዚህ በዚያም ሰርቀው በውጭና በሃገር ባጠራቀሙት ፈጥጠውም ተደብቀውም ይኖራሉ። የእነርሱ ልጆችና ዘመዶች እኮ በሃገር ውስጥ የሉም። ሁሉም ውጭ ናቸው። የሚገርመው ወያኔ አታስፈልጉንም ብሎ ያባረራቸውን የቀድሞ ታጋዮች አሁን ኑና እህል እየሰፈርንላችሁ ተዋጉ ብሎ በእርጅና ለጦርነት ማዘጋጀቱ እብደቱ ጣራ ላይ እንደ ደረሰ ያሳያል። ከወያኔ መካከል ጀግና የለም። ወንድምና እህቱን ገድሎ ጀግና የሚባል እብድ ብቻ ነው። የውጭ ወራሪን ተጋፍጦ ሃገርና ድንበርን አስከብሮ ቢሆን ኑሮ ጀግንነት ጥሩ በሆነ። ራሱን እያቆሰለ፤ ከውስጥ ተፍረክርኮ በጊዜው የፓለቲካ ወጀብ ተንገዳግዶ ከ 17 የመከራ አመታት በህዋል እንደ ሮም የተፍረከረከው ደርግ በራሱ ስህተትና ከላይ ባመላከትኩት የአለም የፓለቲካ አሰላለፍ ለውጥ ፈረሰ እንጂ ሻቢያም ሆነ ወያኔን አፍ ሞልቶ ጀግና የሚያሰኝ ነገር የለውም። እኔ ደርግ መልካም ነበር እያልኩ አይደለም። አረመኔ እንደነበር ታሪኩ ይናገራልና! ማለት የተፈለገው በየአመቱ ክራርና ከበሮ አስይዞ በነጻነት ስም ባርነትን አላብሶ “የነጻነት ቀን” እያሉ ማክበሩ ጅልነት ነው እያልኩ ነው።
    አሁን ፈንዳ፤ ተጀመረ፤ ተቀጣጠለ፤ አንድ ፈረጠጠ ሌላ ሞተ እያሉ ሚዲያዎች የሚያናፍሱት ወሬ ሁሉ ወሬ ብቻ ነው። በጦርነት የመጀመሪያዋ ሟች እውነት ናት። የሚገርመው የአለም ሁኔታ እጅግ አስፈሪ እየሆነ ነው። አዎን የአሜሪካው ምርጫ ገና ከፍጻሜ አልደረሰም። የገረመኝ ግን ውሸታሙ፤ ጉረኛው፤ ዘረኛው፤ ሲሰኛው ትራምፕ ከዲሞክራቱ ተፎካካሪ ጋር ጎን ለጎን እየተፋለመ መታየቱ የአሜሪካ ህዝብ በተለይም የነጩ ህዝብ እይታ ከዚሁ ናዚ እይታ ካለው ጉረኝ ፕሬዚደንት ጋር መጋጠሙን ያሳያል። ሰውየው በ 77 አመቱ በሰራቸው ወንጀሎች እስር ቤት መቀመጥ የሚገባው ሆኖ ሳለ ዳግመኛ ለመመረጥ አንድ ደቂቃ መቅረቱ አሜሪካ ከመሰረቷ የተናጋች ሃገር መሆኗን ያሳያል። እኔ ሁለቱም ፓርቲዎች የማይረቡ ናቸው ነወ እምነቴ። ይህን ከወያኔና ከሃበሻው ሰራዊት ፍልሚያ ጋር ምን አገናኘው ብትሉ እኮ ረጋ ትራምፕ አይደል እንዴ ለግብጽ ግድቡን እንድታፈርስ አረንጓዴ መብራት የሰጣት። ጠብቁና እዪ። የሃገሪቱ ችግር ጀመረ እንጂ አላለቀም። የአማራውም ደም እንደ ውሃ ይፈሳል፤ መግለጫም ይንጋጋል፤ ጦርነቱም ይቀጥላል። ወያኔ ተራ በተራ አፈር ይመለስበታል። እንይ! በቃኝ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share