የሞትንስ እኛ ነን! – ፊልጶስ

የሞቱትስ ሄዱ፣ ወደ እማይቀረው፣
የሞትንስ እኛ ነን፣ ቁመን ያየነው።
የሞትንስ እኛ ነን፣ እኛ ቀሪዎቹ
ይጣራል ድምፃቼው፣ የእናት የልጆቹ።
“ኤሉሄ! ኤሉሄ! ላም ሰበቅተኒ፣ ያ ሲቃ ዋይታቼው፣
ቀርቷል ከእኛ ጋራ፣ ውሻ የላሰውም ይጣራል ደማቼው።
ኧረ ይብልኝ ለእኔ፣ ኧረ ይብላኝ ለአንተ፣ ኧረ ይብላኝ ለአንች
ለሁሌ ምሾ አውራጅ፣ ለሁሌ አዲስ ሞቱ፣ ለጥቁር ለባሾች።
ሰምተን – እንዳልሰማን
አይተን -እንዳላየን
አውቀን – እንዳላወቅን
ጠርተውን ” ወይ” ሳንል፣ ሲማፀኑን ቀርተን።
ደማቼው እረክሶ፣ ከአባይ ውሃ ጅረት ፣ ከሚሞላው ደለል
ገላቼውም ሳስቶ፣ ንፋስ ከሚወስደው፣ ከላባ-ከቅጠል፤
እኛ ነን የሞትነው፣ የበሰበስነው
የቁም ሞትን ሞተን፣ አለን የምንለው።
ነገስ ምን ይዘናል?
ምንስ አስበናል?
የትላንት መታረድ
የዛሬ መረሸን
ምን አስተምሮናል?

——// ——
ፊልጶስ
e-mail: philiposmw@gmail.com

ተጨማሪ ያንብቡ:  ዕንባም አያብሰው (ዘ-ጌርሣም)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share