መልካም የመስቀል በዓል – እሳት ወይ አበባ ከ ሎሬት ፀጋዬ

https://youtu.be/edbcClSpxZg

A tribute to my late brother, written some two years ago, now a part of my anthology at amazon:

የወንድም ፍቅር
=============
ዓመታት አልፈው ዘመን ሲተካ፤
ጥሎልን ያልፋል የሃሳብ ዱካ፤
እንድንከተል መንገዱን ሳንስት፤
ሁሌ ስንደክም ሁሌም ስንዋትት፤
ቤት ለመመለስ ከተጓዝንበት፤
ጊዜ ይነጉዳል ፈጥሮ ትዝታ፤ የማይደበዝዝ ህያው ደስታ፡፡

ጓደኛ ወንድሜ የምትኖር በልቤ፤
የማትለየኝ የምትኖር በሃሳቤ፤
ፋናዬ ነበርክ መንገዴ ለዝንተ ዓለም፤
መንፈስህ ይመራኛል፣ አይዞህ ይለኛል ዛሬም፡፡

ያኔ የድሮው የልጅነትህ ፈገግታ፤
አሁንም ደማቅ ነው በሞት የማይገታ፤ በጊዜ የማይፈታ፡፡

ካንድ ማህጸን ወጥተን፣ አንድ ላይ ኖረን፤
አንድ ልብ ይዘን፣ አንድ አካል ሆነን፤
ደስታና ሃዘን ባንድ ተጋርተን፣
አብረን ተምረን፣ አንድ ላይ አድገን፤
ኖረናል ህይወት ስቀን፣ ተጫውተን፣ ተደስተን፡፡

ተማምለን ነበር እንዳንለያይ፤
ቃል ገብተን ነበር በምድር በሰማይ፤
ጨለማ ሳይነግስ ሳትሸሽ ፀሐይ፤
ደግሞም በጨረቃ በከዋክብት ብርሃን፤
ተመርተን ነበር እኛ የተስማማን፤

ዘመኑ አልፎ ባዲስ ሲተካ፤
ከቶ ላይመለስ ጨክኗል ለካ፤
እኛም ጊዜን ስናማ፤
ጊዜም እኛን ላይሰማ፤
እንፀናለን በያዝነው አላማ፡፡

ግና ምነዋ ጊዜ ቢቆም ቢቸከል፤
እንዳይነቃነቅ አንዳይኮበልል፤
እንዳንለወጥ በጊዜ ግፊት በዘመን ርቀት፤
አቁመን ዕድሜን እዚያው ባለበት፡፡

ፍቅርህ ያረጥበኝል፣ እንደሚወርድ ዝናብ፤
ደምቆና ፈክቶ፣ ጎልቶ በምናብ፤
ያፀናኛል፣ ያጽናናኛል ዘወትር ትዝታህ፤
ዘልቆ ህይወትን ያ ሩህሩህ ቃልህ፤
የኔና ያንተ የመንፈስ ውህደት፤
ፀንቶ ይኖራል እንደ አክሱም ሐውልት፤
ሳይነቃነቅ እንደ «ጂብራልታር» አለት፡፡

ፈ.ፉ. (28 May, 2018)

ተጨማሪ ያንብቡ:  ጊምቢ ኤሎሄ ጊምቢ ቶሌ (ከአሁንገና ዓለማየሁ)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share