ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ (ዘ-ጌርሣም)

ማሳውን ዙሪያውን
ሜዳ ተራራውን
ቆፍረው ቆፋፍረው
ቀንበጡን ቦጥቡጠው
ዘሩንም አጥፍተው
ሌሊት ጩኸታቸው
ልፊያና ድሪያቸው
አላስተኛ እያሉ
አድረው እንዳልዋሉ
ጊዜው ደረሰና
ዘመን ተተካና
ምድሯ ተንቀጥቅጣ
ትራዋን ስትቀጣ
ሁሉም ተጠራርተው
ካዘጋጁት ቦታ ገቡ ጉድጓዳቸው
ኑሮውን ለመልመድ ምንም ቢቸገሩ
በቆፈሩት ግድጓድ በአንድ ላይ ታጎሩ
ዳግም ሳይዳሩ
በጠራራ ፀሃይ አንደውጡ ቀሩ
ለሁሉም ጊዜ አለው
ደረሰ ተራቸው
ጠቢቡ ሰለሞን እንደተናገረው
ጊዜው ባለ ጊዜ ሲቀየር አየነው
ድመቶች ብቅ ሲሉ አይጦች ተደበቁ
የሰበሰቡትን እንደሰለቀጡ
ሆድ የገባ ነገር አይቀርም መውጣቱ
መቆየት ተችሎ ከሰነባበቱ
ማሳው ለመለመ ተመቸው አትክልቱ
አይጦች ጉድጓድ ገብተው ቀሩ እንደታገቱ

ተጨማሪ ያንብቡ:   “የአማራ ኢሊቶች..”? - ጌታችው አበራ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share