የሕግ የበላይነትን ሊያስከብር ያልቻለ መንግስት በሕዝብ እምነት ሊጣልበት አይችልም

መስከረም 09 ቀን 2013 ዓ.ም

የሕግ የበላይነትን ሊያስከብር ያልቻለ መንግስት በሕዝብ እምነት ሊጣልበት አይችልም፡
ከምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

መግቢያ ፡-
የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግድብና የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በሆነውና የተፈጥሮ ሀብት ባለፀጋነት ከሚያረጋግጡት መካከል እምነበረድ፣የፅንሠ- ወርቅ፣ የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማዕድናት፣ ቤዝሜታል፣ የኢነርጅ ሀብት/ ባዩጋዝ፣
የፀሐይና የነፋስ ኃይል/ በስፋት መኖራቸው የሚገለፅላትና የተለያየ ቋንቋ ተናጋሪዎችን በውስጡ ይዛ የሚገኘው ቤኒሻንጉል መንግስት ትኩረቱን ለምን ነፈገው ? የሚለውን መነሻ በማድረግ በሕውሀት እና ብልፅግና ፓርቲ ዘመነ
መንግስት የሚያመሳስላቸውን በመጥቀስ የአቋም መግለጫችንን እንደሚከተለው እናቀርባለን፡፡

1.      የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ (ሰመጉ) ከዚህ ቀደም በቤኒሻንጉልና ኦሮሚያ ክልል አጎራባች አካባቢዎች ብሔርን
መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ያስከተሉትን ከፍተኛ የሆነ የህይወትና የንብረት ውድመት በአካባቢው በመገኘት በባለሙያዎቹ
አማካኝነት በማጣራት የደረሠውን የጉዳት መጠን እና ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች ይፋ አድርጓል፡፡ ለትውስታ
ያህል ሐምሌ 10 ቀን 2000 ዓ.ም የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በኢትዮጵያ በሚል ርዕስ ባወጣው 31ኛ መደበኛ መግለጫ በጉሙዝና ኦሮሞ ብሔረሠብ ዜጐች መካከል በ 09/09/2000 ዓ.ም በተፈጠረ ግጭት 99 (ዘጠና ዘጠኝ)ሰዎች መገደላቸውን፣ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ 108 የሚሆኑ መኖሪያ ቤቶች መቃጠላቸውን፣ እንዲሁም ከ27‚000 (ሀያ ሰባት ሺ) በላይ ህዝብ መፈናቀሉን በማስረጃ አስደግፎ ይፋ ማድረጉ ይታውሳል፡፡ በመግለጫውምመንግስት በአስቸኳይ ዘላቂና የማያዳግም መፍትሄ እንዲሰጥ ቢያቀርብም መንግስት ለኢሰመጉ ጥሪ ትኩረት ባለመስጠቱዛሬም ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃትና ግጭት ሊፈፀም ችሏል፡፡

2.      ብሔርን መነሻ ባደረጉ ጥቃቶች እና ግጭቶች ምክንያት ባለፉት 26 ወራት ብቻ በተለያዩ ክልሎች ከሁለትሚሊዮን በላይ ዜጐች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል፤ በርካቶች ቆስለዋል፡፡ ከዚህም ዘበላይ ዜጐች በገዛ ሐገራቸው በሰላም ወጥቶ የመግባት ዋስትናቸው ጥያቄ ውስጥ ወድቋል፡፡ መንግስት የዜጐችንበሕይወት የመኖር፣ በሐገሪቱ በፈለጉበት አካባቢ ተንቀሳቅሶ ኑሮን የመመስረትና ንብረት የማፍራት ሕጋዊ መብቶችእንዲጠብቅ እና እንዲያስከብር ፓርቲያችን ምክክር ደጋግሞ ጥሪውን በድጋሚ ያቀርባል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኦሮሙማ ፖለቲካ ብሎ ነገር የለም! ኦሮሙማ መነገጃና የራስን ፍላጎት ወይም ኢጎ ማሟያ መሳሪያ ነው!

3.      በተጨማሪም መንግስት በሐገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች እየተፈፀሙ ላሉት ጥቃቶች እና ግጭቶች ተገቢዉን ትኩረት በመስጠት እየተባባሰ የመጣውን ችግር በዘላቂነት ለመቆጣጠር ሕብረተሰቡን እና የተለያዩ የፖለቲካ ኃይሎችን
ያማከለ፣ ዘላቂ፣ ሕጋዊ እና ፖለቲካዊ መፍትሔ እንዲወስድ ምክክር ፓርቲ ያሳስባል፡፡

4.      ግብፅ እና ሱዳን በህዳሴው ግድብ የውሀ አጠቃቀም ታሪካዊ የውሀ ሀብታችን ጠላቶች ናቸው፡፡ ኦነግሸኔ፣ከብልፅግና ያፈነገጡ ሀይሎች ሀገራዊ ህልውናችን ላይ መደራደራቸው ከታሪካዊ ጠላቶቻችን የሚለዩ አይደሉም፡፡
በ 2013 ዓ.ም መግቢያ በቤኒሻንጉል የተፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ግድያና ንብረት ማውደም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪመንገድ የእነዚህ ሀይሎች እጅ እንዳለበት የሚያመላክቱ መረጃዎች ስላሉ መንግስት ጉዳዩን አጣርቶ እርምጃ እንዲወስድ፣ለዜጎችም ጥበቃ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡

5.      መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት ለተጎጂዎችም የምግብ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ፣ የአልባሳትናየመድሀኒት አቅርቦት በአስቸኳይ አለማቅረቡን ስንመለከት ለቤኒሻንጉል ሕዝብ ትኩረት አለመስጠቱንያመላክታል፣በመሆኑም መንግስት ለተጎጂዎችትኩረት እንዲሰጥ አበክረን እንጠይቃለን፡፡

6.      በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልና በአጎራባች አካባቢዎች እየደረሰ ያለው የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶች በአስቸኳይ ይቁም! ለብሔር ተኮር ጥቃቶች እና ግጭቶች ሕጋዊና ፖለቲካዊ ውሳኔ እንዲሰጥ አበክረን እንጠይቃለን፡፡

7.      ትምህርት ሚ/ር በቤኒሻንጉል የኦሮሚኛ ትምህርትን ለመስጠት ለምን ተፈለገ ? በስልጣን ላይ የሚገኘውመንግስት በረጅም ጊዜ እቅዱ ምን አስቦ ይሆን የሚለው በፓርቲያችንና በኢትዮጵያ ህዝብ ዘንድ ጥያቄ ማስነሳቱ
አይቀርም፣ነገ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ የግጭቶች መንስዔ እንዳይሆን የሚል ስጋታችንን የፓርቲያችን ሳይጠቅስ አያልፍም ፡፡
ምክክር ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ

መስከረም 09 ቀን 2013 ዓ.ም

ምክክር ፓርቲ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share