በምሥጋናና አድናቆት ልጀምር፡፡ ሰው በሚሠራው መጥፎ ተግባር ከተወቀሰ በሚያበረክተው በጎ አስተዋፅዖም ሊመሰገንና አድናቆትም ሊቸረው ይገባል፡፡ ያስቸገረን የከንቱ ውዳሤ ሰለባዎች መብዛትና በጭብጨባ ናላቸው የሚዞር ባለጊዜዎች በወር ተራ የሚሰነዝሩብን ያልተገባ እርግጫ ነው፡፡
ዛሬ ዕለቱ ሰኞ ነሐሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም ነው፡፡ ባሳለፍኳት ሌሊት ኢትዮ360 ዩቲዩብ ላይ ከአንድ ዕውቅ ኢትዮጵያዊ ለዶክተር አቢይ የተላከ ግልጽ ደብዳቤ ሲነበብ ሰማሁ፡፡ ሰሚ ቢገኝ ድንቅ ወቅታዊ መልእክት ነው፡፡ “ምክር የድሃ ነበርሽ፣ ማን ቢሰማሽ” ይባላል፡፡ ድህነት ሲባል ደግሞ የሀብት ብቻ አለመሆኑን ልብ ይሏል እዚህ ላይ፡፡ ቤት ሙሉ ገንዘብ እያለህም በአንድ ወይ በሌላ ነገር ድሃ የምትሆንበት አጋጣሚ ሞልቷል፡፡ … ያ ታዋቂ ሰው በኔ የልጅነት ዘመን እጅግ መሳጭ የፕሮቴስታንት መዝሙሮችን ሲያሰማንና ወደ እግዚአብሔር መንገድ እንድንታደም ሲጋብዘን የነበረው በአሁኑ አጠራር ዘማሪ ዶክተር ደረጀ ከበደ ነው፡፡ ዶክተር አቢይ ብዙም ሳይረፍድበት ይህን ደብዳቤ አንብቦ ማድረግ የሚችለው ነገር ካለ ቢሞክር የምትቀርቡት ምከሩት፡፡ ለራሱም ነው፡፡
የዶክተር ደረጃ ከበደን ጦማር በአርምሞ አድምጬ ከጨረስኩ በኋላ ስለግለሰቡ ይበልጥ ለማወቅ ኢንተርኔት መጎርጎር ያዝኩ፡፡ በአንድ አስፈንጣሪ ወደ አንድ የትግርኛ ማኅበራዊ ሚዲያ ተጓዝኩ፡፡ ቃለ መጠይቁ በትግርኛ የተጻፈ ነው፡፡ አነበብኩት ፤ ግሩም ነው፡፡ “ይህ ሰው በነካ እጁ በፕሮቴስታንት እምነት ውስጥ የተሰገሰጉ የቀን ጅቦችን ምናለ ልክ ልካቸውን ቢነግርልኝ!” ብዬ አስቤ ስለነበር በዚያ ቃለ መጠይቅ ውስጥ የልቤን አድርሶልኝ አገኘሁት፡፡ በዚያም ምክንያት ምስጋናየንና አድናቆቴን ልሰጥ ወደድኩ፡፡ ሰው ማለት እንዲህ ነው፡፡ አንድ ሰው ወደ አብርኆት (enlightenment) ደረጃ ሲደርስ ወይም ሲቃረብ የእውነትን ችቦ ከፍ አድርጎ ያበራል፡፡ በእውነትም ብርሃን ይጓዛል፡፡ በማስሎው የሰውነት መለኪያም አንድ ሰው self-actualization የሚሰኘው አምስተኛው የንቃተ ኅሊና ደረጃ ላይ ሲደርስ ከራሱ አልፎ ሕይወቱን ለሌሎች እስከመስጠት በአስተሳሰብ ያድጋል፡፡ ዓለምን የናቀና ስብዕናን ያከበረ አንድ ዜጋ ወደዚያ የልዕልና ደረጃ ሲደርስ በመንጋ እያሰበ ንጹሓንን በሜንጫ አንገታቸውን አይቆርጥም፤ ለሥልጣን ዕድሜ መራዘም ሲል ከፀሐይ በታች የሚገኙ ዕኩይ ሥልቶችን አይጠቀምም፡፡ ያ ዓይነቱ ማህተመ ጋንዳዊና ማዘር ቴሬሣዊ ስብዕናን የተላበሰ ሰው ከዘረኝነት፣ ከሃይማኖታዊ ጽንፈኝነት፣ ከፖለቲካዊ ሸፍጥና ሤራ፣ ከመንደርተኝነት፣ ከጎጠኝነትና ከመሳሰለው ኅሊናንና የአእምሮ ጤንነትን ከሚያቃውሱ የትንሽነት መከለያ አጥሮች ይወጣል፡፡ ዶክተር ደረጀን ያየሁት በዚህ መነጽር ነው፡፡ ልጅ ይውጣለት፡፡ ቀሪ ዘመኑ የተባረከ ይሁን፡፡
በጦር መሣሪያ ከመፋለም ባልተናነሰ ወያኔንና ተረኛ ጽንፈኛ ኦሮሞዎችን ሌት ተቀን የሚዋጉ የሚዲያ ሰዎችን በእግረ መንገድ ማመስገንና ማድነቅ ወደድኩ፡፡ የዩቲዩቡንና የድረገፁን የጹሑፍና የምስል ዝግጅት ስንመለከት አንዳንዶቹ በተለይ “እነዚህ ሰዎች በውነቱ የመተኛና የመመገቢያ ጊዜ ይኖራቸው ይሆን? ለቤተሰባቸውስ በቂ ጊዜ ይሰጣሉ? “ ብለን እስክንገረም ድረስ ያለ ዕረፍት ለምሥኪን ሀገራቸው ሲዋትቱ እናስተውላለን፡፡ የሚለፉባት ሀገራቸው ነፃ ወጥታ ለእናት ሀገራቸውና ለኑሯቸው ያብቃቸው ከማለት ውጪ ምንም አልልም፡፡ “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር” እንደምንለው እነእንቶኔ በአውስትራሊያና በአሜሪካ ከነልጆቻቸው ዝንጥ ያለ ኑሮ እየኖሩ በቀጭኑ ሽቦ በሚያስተላልፉት ትዕዛዝ ግን ቁርስ እንደምንም ቀምሶ ለእራት የሚጨነቀውን ድሃ ሕዝብ እርስ በርስ ያስተራርዱታል – ከሲዖል ያመለጡ ሽፍቶች ማለት እነሱ ናቸው፡፡ ዋጋቸውን እስኪያገኙ ብዙ ዋጋ ቢያስከፍሉንም ታሪክና የውሻን ደም እንኳን በከንቱ የማያስቀረው እግዚአብሔር ይቅር አይሏቸውም፡፡
… የዶክተር አቢይ ኢትዮጵያና የኛ ኢትዮጵያ የሰማይና የምድርን ያህል እንደሚለያዩ በተለይ ሰሞኑን በሚገባ ተረድቻለሁ፡፡
ያለፈው ቅሜዳ ነው፡፡ ከሥራ ወጥቼ ወደ ሰፈር አቀናለሁ፡፡ እንደልማዴ ወደ አንዱ የማታ ትምህርት ቤት ጎራ ብዬ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ጉንተላ ለማካሄድ የዘወትር ጓደኞቼ ወደሚገኙበት ግሮሰሪ ጎራ ብል ሁሉም ፀጥ ረጭ ብለው የዶክተር አቢይን ዘጋቢ ፊልም በተመስጦ ይመለከታሉ፡፡ አንድም ሰው የኔን መግባት አላስተዋለም፡፡ ሌላ ጊዜ አቢይንም ሆነ የፌዴራል ተብዬ መንግሥቱን መረጃና ማስረጃ ላይ ተመርኩዤ ስደሰኩር አፉን ከፍቶ ያዳምጠኝና እንዲያውም አላናግር እያለ ተጨማሪ ማብራሪያና መረጃ ይሰጥ የነበረው ቱልቱላ ሁሉ ዛሬ በተራው በአቢይ አፍዝ አደንግዝ አፉ ተሸብቦ የአካፑልኮ ቤይ ፊልም እያዬ ይመስላል፡፡ የአቢይ በዚህን ወቅት ያን ፊልም ማቅረብ ዓላማውም ይሄው ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ በሀገር ውስጥ አንድ አሳዛኝ ክስተት ሲፈጸም አንድም አቢይ በሀገር ውስጥ የለም ወይም አንድ ሌላ የትኩረት ማስለወጫ አጀንዳ ተከፍቶ እንንጫጫለን፡፡ ያኔ ባቢሎን በኢትዮጵያ ይሆንና እነአቢይ በሰላም ያሻቸውን ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ፡፡ በቀደም ለት ታዲያ በንዴት ብንጨረጨር ማን ገብቶት! የሚገርመው ነገር ተማረ የተባለውም፣ ያልተማረውም እኩል ደንቁረናል፡፡ ይቺን ቀላል ዘዴ እንኳን ማወቅ ተስኖን ስንጃጃል ማየት እጅግ አሣፋሪ ነው፡፡
አቢይ ፈረንጆቹ smart የሚሉት ዓይነት ሰው ነው፡፡ መደነቅ ይገባዋል፡፡ አንድ ሰው ለቆመለት ዓላማ ሙት ሲሆን ይበል ያሰኛል፡፡ “ሰው በወደደው ይቆርባል” መባሉም ለዚህ ነው፡፡ እናም አቢይ ለምንም ዓይነት ዓላማ ይጠቀምበት እንደዚህ ያሉ ሕዝብን የማነሁለያና የተክለ ሰውነት ገጽታን የመገንቢያ የልማት እንቅስቃሴዎችን ልዩ ልዩ ወሳኝ ወቅቶችን እየጠበቀ ባለማቋረጥ ማስመረቁና የሕዝብን የትኩረት አቅጣጫ ማሰቀየሩ ጉብዝናውን ይጠቁማል፡፡ ይህን አካይስታዊ ባሕርይ አለማድነቅ ሲበዛ ንፉግነት ነው፡፡
በመሠረቱ አቢይ የሠራው የመናፈሻ ሥራ እጅግ የሚደነቅ ነው፡፡ ያልተለመዱ ይህን መሰል ሥራዎችን መሥራቱ በታሪክም በትውልድም ሲያስወድሰው ሊኖር የሚችል ነበር፡፡ አንድ መሪ ሀገሩ ገነት እንድትመስል መጣሩ ያሸልመዋል እንጂ አያስወቅሰውም፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ ደግሞ ይህ ፊልም መቅረብ የሚገባው ወቅቱ አሁን አልነበረም፡፡ ይህን መግለጽ ደግሞ የሀገራችንን ተጨባጭ ሁኔታ ከመረዳት በመነጨ ቀጣይ ሥጋቶችን ለመጠቆም የተደረገ ሙከራ እንጂ እንደሚባለው የቅናት ወይም በ“ሰውዬው ስኬታማነት” የመመቅኘት ጉዳይ አይደለም፡፡ የሚባለው ሌላ የሚደረገው ሌላ መሆኑን ተረድተን እውነቱን ብንመሰክር ቢያንስ የኅሊና እፎይታን እናገኛለን፡፡
አቶ ሽመልስ አብዲሣ በተናገረውና የአቢይና የታከለ ኡማ መንግሥታት በስፋትና በጥልቀት በአጭር ጊዜም ውስጥ እየተገበሩት ያለው የ1968ን የወያኔ የደደቢት ማኒፌስቶ የሚመስል ዲስኩር በሰማን ሰሞንና ሕዝበ አዳም በንግግሩ ግሥላ ሆኖ የሚያደርገው ጠፍቶት ሳለ ይህን ዘጋቢ ፊልም ማቅረብ በውነቱ ከሊቀ ሣጥናኤል ከራሱ የተላከ ምክር ካልሆነ በስተቀር በሰው ልጅ አእምሮ ሊታሰብ የሚችል አይደለም – ባጭሩ ይህ ሸር ከአቢይ አቅም በላይ ነው፡፡ ሰውዬው ባህር ዳር ሄዶ ደንገጡሩን ብአዴንን እንደድመትና ውሻ ማጅራታቸውን አሻሸና ሊነሳ ይችል የነበረን ተቃውሞ አበረደ፡፡ ጥሩ ነው፡፡ ጥሩነቱ ግን እንዳለፈው ዓመት የደም ግብር አፍስሶ አለመምጣቱ ነው፡፡ ከዚያም ሳያርፍ ሽመልስንና ድንዙዙን ተመስገን ጥሩነህን ጎን ለጎን ጎልቶ እንደቴፕ የተሞሉትን እንዲያቀነቅኑ አደረገ፡፡ ሽመልስ ይቅርታ ይጠይቃል ሲባል ይቅርታ መጠየቅም ቁም ነገር ሆኖ፣ “ይቅርታ ተሳስቻለሁ” ማለትም ኦሮሞን የሚያዋርድ ሆኖ ተገኝቶ በተለመደው የቅጥፈት ሥልታቸው አድበስብሰው አለፉት፡፡ ከዚያም ራሱ ጠ/ሚኒስትሩ የሚተውንበትን ድራማ ማቅረቡን ጀመረ፡፡ መንግሥቱ ኃይለ ማርያም ፈላስፋ፣ የህክምና ዶክተር፣ የጦር መሪ፣ ኮከብ ቆጣሪ፣ ሁለገብ አርቲስትና ደራሲ እንደነበር አሁን ትዝ አለኝ፡፡ አንዳንድ መሪዎች ተመሳስሏቸው ያስደንቃል፡፡ የሚገርም ጠቅላይ ሚኒስትር እኮ ነው ያለን ግን! ብቻ ይህም ለበጎ ነው፡፡
የሆነ ሆኖ ሰውዬው በብአዴን ውስጥ ያስቀመጣቸው ሰዎች ቀላል አይደሉም፡፡ ይሁዳ ክርስቶስን በ30 አላድ እንደሸጠው ሁሉ ብኣዴናውያንም የአማራን ሕዝብ በፊት ለወያኔ አሁን ደግሞ ለኦህዲድ እንዳወጣ ሽጠው በገንዘቡ እየተምነሸነሹ ነው – በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ኅሊናቸው ተመልሰው ሊጸጸቱ ይችላሉ ብሎ ማሰብም ከንቱ ነው፤ አፈጣጠራቸው ለዚህ የታደለ አይደለም፡፡ በወያኔና በመሰል ፀረ አማራ ኃይሎች ሻጥር በቁጥር በሁለተኛነት የተቀመጠውን እንደ እውነቱ ግን በቡድን ካልሆነ በተናጠል ማንም የማይስተካከለውን የአማራ ሕዝብ እነማን እየመሩት እንደሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን፡፡ የነሱን ማንነት በመዘርዘር ጊዜ አላባክንም፡፡ ትልቁ የሚገርመው ጉዳይ ግን ዋና ዋናዎቹ ባለሥልጣናት ክልሉን በሪሞት ኮንትሮል የሚያስተዳድሩ መሆናቸው ነው፡፡ ይህ ለአማራ ሕዝብ ውርደት ነው – ክፍለ ዘመናዊ ታላቅ ቅሌት፡፡ የሶማሌው ሙስጠፌ የት ሆኖ ነው ክልሉን የሚመራው? የትግራዩ ደብረ ጽዮንስ? የአፋሩስ? የቤንሻንጉሉስ? የጋምቤላውስ? የደቡቡስ? በውድ ወጪ ከአዲስ አበባ በአየር እየተመላለሱ ነው እንዴ የእነዚህ ክልሎች ፕሬዝደንቶች ሕዝባቸውን የሚያስዳድሩት? ደብረ ጽዮን በኦሮሞ አንጋች ይጠበቃል? ምን ዓይነት ቀልድና ዕንቆቅልሽ ነው? አቢይም ሆነ ደንገጡሮቹ ብዙ የሚያወራርዱት ዕዳ እንዳለባቸው አዘውትረን የምንገልጽላቸው ይህን ሁሉ የአደባባይ ምሥጢር ስለምንረዳ ነው፡፡
ስለሁለቱ ኢትዮጵያዎች ትንሽ ልበል፡፡ የአቢይ ኢትዮጵያ ፍትህ ርትዕ የሰፈነባት፣ የሚራብና የሚጠማ የሌለባት፣ ዘረኝነትና ጎሠኝነት ከሁለት ዓመታት ተኩል ገደማ በፊት ጠፍቶ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ያበበባት፣ ስደትና እንግልት ቀርቶ ሕዝቧ በድሎት ተቀማጥሎ የሚኖርባት፣ ላዕላይና ታኅታይ መዋቅሮች ሙሉ በሙሉ ተሟልተው ሕዝብ እፎይ ብሎ የሚንፈላሰስባት ናት፡፡ ቁሣዊና ማኅበራዊ ችግሮቿ ተወግደው አሁን ኢትዮጵያን የሚያስፈልጓት የዐይን ማረፊያ የሚሆኑ አውሮፓዊ መናፈሻዎች፣ ዐረባዊ የከተማ ውበት፣ አማዞናዊ የደን ልማት፣ ሎንዶን ወፓሪሳዊ የአካባቢ ጽዳት፣ ላስቬጋሳዊ የመንገዶች መብራት፣ ወዘተ. እንደሆኑ በመሪዎቿ የሚታመንባት አምሳለ ገነት የሆነች የመንግሥተ ሰማይ ግልባጭ ናት፡፡ (ለማያቃቸው ይታጠኑ!)
እነዚህ በአቢይ አፍዝ አደንግዝ ፓኬጅ ውስጥ የተካተቱ የትኩረት አቅጣጫ ማስለወጫ የሽፋን ተኩስ መሰል ቴክኒኮች በራሳቸው ጥፋት የለባቸውም፡፡ ቀድሞ የመቀመጫውን እሾህ የነቀለ አንድ ሕዝብ በሂደት ሊያገኛቸው የሚገቡ ድንቅ ነገሮች ናቸው፡፡ ጽድቁ ቀርቶበት በቅጡ መኮነንን ለሚፈልገው እንደ ኢትዮጵያ ላለ ሕዝብ ግን እነዚህ ነገሮች ቂጥ ከፍቶ ክንንብ እንደምንለው ወይም ራሷ ሄዳ ሽንፍላ የከለከሏት ‹ምላስ ሰምበር በሰው ላኩልኝ› አለች እንደተባለላት ቅንጡ ድመት መሆን ነው፡፡ ስናሳዝን! ፈጣሪን ምን ብንበድለው ይሆን ለነዚህ ዓይነቶቹ ቁጭ በሉዎች አሳልፎ የሰጠን? ደግሞስ በነዚያኞቹ አይበቃንም ነበር? ከእሳት ወደ ረመጥ!
የኛ ኢትዮጵያ ተረኛ ጽንፈኛ ኦሮሞ የሚዘውረው አስመሳይ የፌዴራል መንግሥት ያላትና በዚያም ምክንያት ሁሉም የጥቅምና የሥልጣን ቦታዎች በባትሪና በሻማ እየታደኑ ለኦሮሞ የሚሰጡባት፣ አማራና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተ ክርስቲያን እንደገባች ውሻ በተገኙበት እንዲቀጠቀጡ በብዛት በሰለጠኑ የኦሮሞ ልዩ ኃይል ተብዬዎችና በቄሮዎች አንገታቸው በጭካኔ የሚቆረጥባት፣ ገና ለገና አማራ ወንድ ልጅ ይወልዳሉ ከሚል ፍርሀት በዐረመኔዎች ቢላ እርጉዞች ሆዳቸው የሚዘከዘክባት፣ በሁለት ዓመታት የተረኝነት አጭር ጊዜ ውስጥ ብቻ ከ50 ሽህ በላይ የመንግሥት ቤቶችና ጭቁኖች በላባቸው ባገኙት አነስተኛ ገንዘብ የሠሯቸው ኮንዶሚኒየሞች ለኦሮሞ የተሰጡባት፣ አንድ ኦሮሞ የመንግሥት ሠራተኛ የሚያከራየውና የሚኖርበት ከሁለት ሦስት በላይ ቤቶች የሚያገኝበት፣ በአዲ አበባ የምትገኝ ባዶ ቦታ እየታሰሰች ለኦሮሞ ብቻ የምትሰጥባት፣ ከቀበሌና ወረዳ ጀምሮ ሁሉም የኃላፊነት ቦታዎች ቢቻል በኦሮሞ ባይቻል በሽመልስ ትዕዛዝ መሠረት ኦሮሞ የሚቆጣጠረው ቅን ታዛዥ ተጎል በስልክና በብጣሽ ማስታወሻ ጽንፈኛ ኦሮሞ የሚጫወትባት፣ የዘረኝነት ልምሻ የኮደኮደው ኦሮሙማ የተባለ የገዳ ሥርዓት አራማጅ ኃይል መላዋን ሀገር ለመሰልቀጥና ወደ ኦሮሞ ለመለወጥ ቀን ከሌት ዘመቻ የሚጧጧፍባት፣ የሀገሪቱ የጋራ ዕሤቶች በሻማ እየተፈለጉ ያለርህራሄ የሚቆራረጡባት፣ ካለሙስና እስትንፋሳቸው ቀጥ የሚልባቸው ቴክኖክራችና የመንግሥት ሠራተኞች የሚፈነጩባት፣ ለሀገር ማሰብ ዕርም የሆነባት፣ ማንኛውም ዓይነት የጥራት ጉድለት የሚታይባት፣ ወደፊት ቀርቶ የኋሊት የምትነጉድ … ጉደኛ ሀገር ናት(“ንገሪኝ ካልሽማ…” ብሎ የዘፈነው ማን ነበር?)፡፡ በበቀደሙ የአቢይ አፍዝአደንግዝ መተታዊ ዘጋቢ ፊልም ኅሊናችሁን ስታችሁ በፍቅሩ የወደቃችሁ ከንቱዎች ይህንንም ካዱና እንደልማዳችን አስቁን፡፡ የገረመኝ ነገር መጀመሪያ ገብቼበት ከነበረው ቤት ወጥቼ ሌላ ቦታ ብቀይርም ሁሉም በመተተኛው አቢይ ነፍልሏል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ አቢይ ጥቂት የማይባሉ ወራትን እንደዚህ እያምታታ ሊኖር እንደሚችል ገመትኩ – ወራትን ነው ያልኩት፡፡ አቢይና አክራሪዎቹ እየተናበቡ በሚሠሩት ፊንታ (ማጭበርበር) ብዙ ዋጋ መክፈላችን አይቀርም – ለይምሰል እስር ቤት ውስጥ ያሉትም ሳይቀሩ በዚህ የኦሮማይዜሽን ሂደት ስለመሳተፋቸው መጠራጠር የለብንም ፡፡ ደግነቱ ድብቅ ነገር ስለሌላቸው የሞታቸው ፍጥነትም በዚሁ ልክ ነው፡፡
ሁሉን ቢያወሩት አያልቅም፡፡ መሰነባበት ሊኖርብን ነው፡፡
አንዳንድ ጥቆማዎች አሉኝ፡፡ “ይህን ሰሞን ለምን የኮሮና ተያዥ ዜጎች ቁጥር ጎላ አለ?” ብሎ መጠየቅና አንዳች ነገር መጠራጠርም ክፋት የለውም፡፡ ገንፎ ብቻ ሳይሆን የአቢይ መንግሥትም ስንጥር በስንጥር ሆኗልና ሁሉንም እንቅስቃሴ ብንጠራጠር ለሃሜት እምብዝም አንዳረግም፡፡ እናም በተለይ ባለፉት ሦስትና አራት ቀናት ከተለመደው ዘገባ በተለዬ ሁኔታ በቀን እስከ 1600 ሰዎች ድረስ መያዛቸው ተነግሯል፡፡ አዎ፣ እውነቱንና ውሸቱን አንድዬ ብቻ ነው የሚያውቀው፡፡ ነገር ግን አእምሮን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ ልምድ ያላቸው አውሮፓውያንና አሜሪካውያን በዚህ MC (Mind Control) በሚሉት ቴክኒክ የዜጎቻቸውን አስተሳሰብ እስከማዛባትና እስከመቀየርም እንደሚደርሱ ይታወቃልና የኞቹ የነሱ ግርፎችም እንዳቅሚቲ በዚህ ብልኃት እየተጠቀሙ ያሻቸውን በማድረግ ላይ እንደሚገኙ መገመት አይከብድም፡፡ የሚቆጨው ግን የትናንትና ኩታራ ሽመልሶችና አቢዮች በዚህች ጥንታዊትና ታሪካዊት ሀገር ላይ ይህን የመሰለ ትብታብ አይሉት ብልጠት በአደባባይ ማከናወናቸውና ከምሁር እስከማይም የሚያታልሉት ሕዝብ ብዛት አስደንጋጭ መሆኑ ነው፡፡ ሌላው ይቅርና ሽመልስ በዚህን ወቅት በትንሹ ማረፊያ ቤት ውስጥ መገኘት ሲገባው እየታዬ ያለው ድራማ ነገን በብርቱ የሚያስናፍቅ ነው፡፡
ብዙ ነገሮችን እየጠቃቀሱ መቆላጨትና መናደድ ይቻላል – ትርፉ ኪሣራ ነው እንጅ፡፡ ሰሞኑን የሰማኋትን የወያኔን ግፈኛና አድሎኣዊ ሥርዓት የምታስከነዳ ይህችን አሰቃቂ ኦነግ-ኦህዲዳዊ የግድያ ሤራ ሳልናገር መቅረት ግን ኩነኔ ነው፡፡ አንድ የሌተናል ኮረኔል ማዕረግ ያለው ወታደር ለግል ጉዳዩ አቧሬ በሚገኘው የሽመልስ አብዲሣ ቤት አካባቢ መኪናውን ያቆማል – ልጁን ለማሳከም ከባለቤቱ ጋር ነበር ወደዚያ አካባቢ የሄደው – ጎጃሜ ነው አሉ፡፡ የሽመልስ ቤት ጠባቂዎች ያንን ሰው ደብድበው ይገድሉታል፡፡ የተገደለው በዘሩ ይሁን በሌላ አላውቅም – ከግምት ባለፈ፡፡ ምናልባት በቋንቋ አልተግባቡም ይሆናል፡፡ ይህ የሚያሳየን ግን ምንም ሆንክ ምን ከኦሮሞ በስተቀር ማንንም መግደል መብትህ መሆኑን ነው፤ በእምነቱ ምክንያት እርሱ ባይቀበላቸውም ደጋፊዎቹ ግን ጽላት ማስቀረጽ እስኪዳዱ ድረስ የሚንሰፈሰፉለት ጠ/ሚኒስትር አቢይ የሚኩራራባት ኢትዮጵያ እንግዲህ ይህች ናት፡፡ በደርግ ዘመን አውቃለሁ – ሰውን የገደለ ይታሰራል፤ ይፈረድበታልም – ሰውነት ዋጋ ነበረው(በቀይና ነጭ ሽብርም ቢሆን በዘር ሳይሆን በአመለካከት ነው የነበረው ግድያና እሥር፡፡) አሁን ግን ዘመን ተለወጠና አንድ ሰው ሲገደል “ገዳዩ ማን ነው?” “ሟች ማን ነው? ተብሎ ከተጠየቀ በኋላ ተረኛው ዘረኛ መንግሥት ከርሱ ወገን በሌላ ወገን ተገድሎ ከሆነ ገዳዩ ወዮለት! የርሱ ወገን የሌላ ወገን ገድሎ ከሆነ ግን ቁንጫ የገደለ ያህልም አይቆጠርም – ግፋ ቢል ወንጀሉን ከሠራበት አካባቢ ዘወር እንዲልና መኖሪያ ቀየ ወይ የሥራ ቦታ እንዲቀይር ነው የሚደረገው፡፡ ለቤት ቀጋ ለውጭ አልጋ የሆነው አቢያችን በሚያስተዳድራት አንድም ሁለትም የሆነች ኢትዮጵያ ውስጥ የምናየው ኹነት ይህን ይመስላል፡፡ ፍትህና እኩልት፣ ነፃነትና ዴሞክራሲ የመጻሕፍት ቃላት ናቸው፡፡ ትያትር መሥራትና ሀገርን በፍትህ ርትዕ ማስተዳደር ለዬቅል ናቸው፡፡
ችግርን ተናግሮ ብቻ መለያየት ደግ አይደለም፡፡ ዕድሜ ለቄሮዎች ዐረመኔያዊ ጭፍጨፋዎችና ለሽመልስ አብዲሣ የዕብሪት ንግግር የአቢይ ዘመን እየተጠቃለለ ቢመስልም መጪው ጊዜ እጅግ አደገኛ መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ አክራሪዎች እንዴት እንደሚያጠፉን ብዙ ተግባራዊ ልምምድ እያደረጉ ነው፡፡ ፌዴራል መንግሥቱም ከነሱ ጋር ነው፡፡ የክልል መንግሥታት ብዙዎቹ ቤታቸውን ዘግተው ለሆነ ነገር እየተዘጋጁ ናቸው – ያ የሆነ ነገር ደግሞ የሚያስነጥስና የሚያስለቅስ እንጂ የልደት ድግስ እንዳይመስልህ፡፡ ሁሉም በየአጥሩ ውስጥ ተከርችሞ ጎራዴውን እየሣለ ነው፡፡ በተለይ ገዳዮች በቂ ዝግጅት አድርገዋል – በውጭም በውስጥም አሉ የተባሉ ፀረ ኢትዮጵያ የጥፋት ኃይሎች ስለሚያሰማሯቸው የስንቅና ትጥቅ አቅርቦት ችግር የለባቸውም፡፡ በዚያ ላይ አእምሯቸውን ስለተነጠቁ ከነሱ ርህራሄ መጠበቅ ፍጹም የዋህነት ነው፡፡ የራስን ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ መጠቆም እወዳለሁ፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይነት ደግሞ የነበረ ነው፤ ኦህዲድ ግን ይሀን አይፈቅድምና ዝግጅታችን በተቻለ መጠን ከነሱ ዕይታ ውጪ ይሁን፡፡ እንዲህ ስል ለመግደል ተዘጋጁ እያልኩ አይደለም፡፡ ጊዜው ሲደርስ ጥጋበኞችን አይቀጡ ቅጣት የሚቀጡ ለመግደል የተዘጋጁ ራሳቸውን ለመስዋዕትነት ያዘጋጁ ወገኖች በሌላ ሥፍራ አሉ – እንዲህ የምለው እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው፤ የት እንዳሉና ስንት እንደሆኑ ደግሞ ከፈጣሪ በቀር ማንም አያውቅም፡፡ እነዚያ ወደኛ እስኪመጡ ግን ጭዳ እንዳንሆን ቢያንስ መንጋን በኅብረት ሆኖ መከላከል ህጋዊም ተገቢም ነው፡፡ ሌላው ቢቀር ቤት ያለን አንቂ ኃይለኛ ውሻ ይኑረን፤ በየአካባቢያችን እየተሰባሰብን እንመካከር፤ ዱላ ይዘን ሠፈራችንን በየተራ እንጠብቅ፡፡ ሲመጡብን እንጩህና በጋራ ሆነን ራሳችንን፣ አካባቢያችንንና ሀብት ንብረታችንን እንጠብቅ፤ በእስካሁኑ የአጥፊዎች ድርጊት ከተጎዱ ወገኖቻችን እንማር፡፡ አንዱ ቤት ሲጮህ የኛም ቤት እንደሆነ ካልቆጠርን በየተራ ይጨርሱናል፡፡ በዕድሩም፣ በጽዋውም፣ በዕቁቡም፣ በሰንበቴውም፣ በአብሮ አደግም፣ በፉካውም … በሁሉም ማኅበሮቻችንና ስብስቦቻችን ይህን ጉዳይ እንነጋገርበት፡፡ የአካባቢያችንን መግቢያ መውጫ መንዶች ከተቻለ በር እንሥራላቸው፡፡ የተጣላን እንታረቅ – ከአንጀት እንታረቅ፡፡ ጠብና ግጭት ለጠላቶቻችን አሳልፎ የሚሰጠን መጥፎ ደንቃራ ነው፡፡ በዘርና በጎሣ መቧደንን እንተው፤ የመጣብን ጠላት ማንንም የሚምር አይደለምና ሃይማታኖችንንና የኑሮ ዘይቤያችንን ሳንመረምር ከመንጋዎች ጋር በቋንቋ ብቻ ስለተመሳሰልን ልባችንን በማሸፈት ቀሪ ወንድሞቻችንን ለመጉዳት አናስብ፡፡ ከወያኔ እንማር፡፡ ሕወሓት መቀሌ ሄዶ ሲሸጎጥ በሚሊዮን የሚቆጠረው ትግራዋይ ግን እዚሁ አለና በዘረ ልክፍት ተነሳስተን ወንድምና እህቶቻችንን ለጉዳት አንዳርግ፡፡ ውጤቱ ከትዝብት ያለፈ ትልቅ አደጋ ሊያመጣ እንደሚችል እንገንዘብ፡፡ በያካባቢያችን ያሉ ወጣቶቻችንን እናንቃ፤ እናደራጅ፡፡ አመራርንና መሣሪያን ሥልጠናንም ጨምሮ መንጋዎቹ በመንግሥት የሚደራጁና ጃዝ የሚባሉ ናቸው – ያለጥርጥር! እኛ በፈጣሪ የምንመካና አዳኛችን(የሚጠብቀን) ከላይ መሆኑን አምነን ከልብ እንጸልይ፡፡ መጽሐፉ “ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም” ይላልና በዕብሪተኞች የሰውና የመሣሪያ ብዛት አንሸበር፡፡ እነሱ ዓላማቸውንና ፍላጎታቸውን ቀድመው ስላሳወቁን፣ የክፋታቸውን ልኬት አልባነትም ስለተረዳን ከእንግዲህ ወዲያ ለምንወስደው ጥንቃቄ ብዙ ትምህርት አግኝተናል፡፡ የነዚህ ሁቱዎች ፍላጎት በነሱ አምሳል እንደ አዲስ ጠፍጥፈው በሚሠሯት ኢትዮጵያ ውስጥ ከኦሮሞ ውጪ ሌላ ሰው እንዳይኖር እንደመሆኑ በግማሽ ሰዓት የሽመልስ ንግግር ብቻ የአማራውን ቁጥር ከ40 እና 50 ሚሊዮን በቀጥታ ወደ 80 እና 90 ሚሊዮን አስገብተውታል፤ በዚህ የግምባር ሥጋነታቸው ሊመሰገኑ ይገባል፡፡ ይህን እውነት ደግሞ ከአሁን በኋላ ሊያስቀይር የሚያስችል ዕውቀትም ሆነ ጥበብ እንዲሁም ፍላጎት የላቸውም፡፡ እዚህ ላይ የምናገረው ነገር ቅኔ ወይም ዕንቆቅልሽ የሚሆንበት ሰው ካለ ትንሽ ለማብራራት ያህል – አክራሪ ወይም ጽንፈኛ ኦሮሞዎች እስላም ያልሆነን ዜጋና እንደጊዜያዊ የትግል ሥልት ደግሞ ጴንጤ ያልሆነን ኦሮሞም ሆነ ኢ-ኦሮሞ ዜጋ በአንድ ዐይን ነው የሚያዩት፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ኢ-ኦሮሞ ኦርቶዶክስና አማራ እንዲሁም ለዘብተኛ ኦሮሞና እስላምም ቢሆን ሌላው ዘውግ ሁሉ የሚካተተው ከጠፊዎቹ ጎራ ነው ማለት ነው፡፡ ያለው ብቸኛ አማራጭ አማራ ጉራጌ፣ ትግሬ ከምባታ፣ ጋምቤላ ሽናሻ …. ሳንል በአንድ ላይ በመሆን ይህን የጥፋት ግሪሣ ተደራጅተን መከላከል ነው፡፡ የአማራውን ቁጥር አበዙት የምለው እንግዲህ በሆነ የመግደያ ርዕስ – ለምሣሌ በኦርቶዶክስነት ወይም በሞጋሣና በጉዲፈቻ ኦሮሞ ለመሆን ባለመፈለግ ሰበብ – ነገ ወይም ከነገ ወዲያ በጽንፈኞች የሚገደል ተጠባባቂ ተረኛ ከመሞቱ በፊት ዛሬውኑ ከአማራ ጓደኞቹ ጋር ተደራጅቶ የወል ጠላቱን አቅል በማስገዛት የጋራ ሀገር እንደሚገነባ በማመን ነው – ኢትዮጵያን ከበርካታ የዕልቂት ድግሶች አትርፎ ለዚህ ዘመን ያበቃት ይህ ዓይነቱ አንተ ትብስ አንቺ ትብሽ ትብብርና መተሳሰብ ነው፡፡ ስለነዚህ ጉዶች መጨረሻ አንዳንድ ነገሮችን መናገር እችል ነበር – ግን እንዳይደነግጡብኝ ይቅርብኝ፡፡ ከመሰናበታቸው በፊት የሚያደርሱት መከራና ዕልቂት እጅግ ከባድ በመሆኑ ግን የተነገረን ማለዘብ እንጂ ማስቀረት የሚቻል ባለመሆኑ በተለይ ከፈጣሪ ጋር በቶሎ መታረቁ ለአመክሮው ይበጀናል፡፡ አዲስ አበባንና ሌሎች ትላልቅ ከተሞቻችንን ወደሦዶምና ገሞራ እየለወጧት የሚገኙ የኖኅና የሎጥ ዘመን ሰዎችን ሃይ እንበላቸው – መምህር ደረጀ ነጋሽ የተባልክ ሰው እግዜር ይባርክህ በዚህ አጋጣሚ፡፡ … የእምነት ቤቶቻችንም አብረው ስለጠፉ ደጋግ እረኞችን ማግኘቱም አስቸጋሪ ነው፡፡ ብዙ የደከሙ ይህን ወቅት ቢሻገሩ ደስ ይለኛል፡፡ ለማንኛውም ሰላም ሁኑልኝ፡፡ በሁሉም አቅጣጫ የጨለመ ቢመስልም ተስፋችን እርሱና በርሱም ነውና ኢትዮጵያችን በቅርብ ወራት ሙሉ ነፃነቷን ትጎናጸፋለች፡፡ ከዚያም ስደት ወደ ኢትዮጵያ ይሆናል የሚለው ቀዳሜ ትንቢት እውን ይሆናል – እዚህ ላይ አንተ ወይ እኔ ለዚያ ወርቃማ ዘመን ብንደርስ ወይ ባንደርስ ሌላ ጉዳይ ነው፤ እንደምንደርስ ግን እንመን፡፡ አቢይ መንገድ ጠራጊ ይመስለኛል – ባይሆንና የተነገረለት እርሱ ቢሆን በወደድኩ፤ አያያዙ ግን ሌልኛ በመሆኑ እርሱ የባለሦስት ዓመቱ ከመሆን የሚዘል አይመስልም፡፡ ልፋቱ ግን ያሳዝነኛል – በውነት! በፍርደ ገምድል ጃውሳ ቁማርተኞች ተከብቦ እርሱም የባሰ ጃውሳ ቁማርተኛ ሆነና አረፈው፡፡
ይነጋል በላቸው ([email protected])