ሻሸመኔ ዳግም የዘር ጥቃት ሰለባ !!! – ተድላ አስፋው

የሻሸመኔ  ከንቲባ ለ VOA አማርኛ ዛሬ እንደነገረን ከተማዋን ለማዉደም የመጣው አሸባሪ የጎሣ ቡድን የተነቃነቀው ከሻሸመኔ ዙሪያ መሆኑን ና ሀያ ሰዎች በቁጥጥር ስር መሆናቸዉን ነግሮናል።
የዛሬ ሁለት ዐመት ገደማ የጃዋር መሀመድ ደጋፊዎች ወጣት ገድለዉ ቁልቁል በመስቀል ከአንገት ቆራጩ ISIS የተሻለ የማሸበር ችሎታቸዉን ያስመሰከሩበት ሻሸመኔ መሆኑን እናስታዉሳለን።
ከንቲባው ንብረት የተቃጠለባቸው ኦሮሞ ያልሆኑ ንብረት እየተመረጠ መሆኑንም አረጋግጥዋል። ሀይሌ ገብረሥላሤ ዘመናዊ ሆቴል የአቶ ዮሀንስ ወልዱ የምዋች ሃጫሉ የስጋ ዘመድ የግል መኖሪያና የግል ትምህርት ቤት ከወደሙት መካከል ይገኛሉ ።
ከተማን ለማሸበር የተደበላለቀው ሻሸመኔ ከተማ ነዋሪዎችን መጠቀም ስለማይቻል በዙሪያ ያለውን ጎሣ ጥፋት ኃይል ማነሳሳት የተለመደ ሆንዋል።
ድሬዳዋ ሀረር ናዝሬት አዲስ አበባ የተደረጉት ሁሉ እንደ ሻሸመኔ በዙሪያ ያለውን ህዝብ በመጠቀም ነው።
አዲስ አበባ የሻሸመኔ መሰል ጥቃት ለመፈፀም እነጃዋር በOMN ገስግሰህ ፊንፊኔ እንገናኝ ቅስቀሳ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ምኒሊክ ሠፋሪ እየተባለ የሚፎከርባቸዉን ሕይወትና ንብረት ለማጥፋት ለማስገበር ነበር።
የ OMN የሃጫሉ ቀብር ጥሪ አዲስ አበባ በፍጥነት የታወጀው ዋናው ዐላማ የኦሮሞ ማህበረሰብ በከፍተኛ ቁጥር ከአዲስ አበባ ዙርያ አስገብቶ የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ንብረት የሰው ህይወት በማዉደም መንግሥት የለም አስብለው ወያኔና ጃዋር አህመድ የሽግግር መንግሥት  ሊመሰርቱ ነበር።
መከላከያዉ አዲስ አበባን እንዳዳነዉ በኦሮሞ ክልል ያሉ ከተማዎች ዉስጥም በፍጥነት መነቃነቅ ነበረበት። ያም ባለመሆኑ ከመቶ በላይ ህይወት ጠፍትዋል።
የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ይህን መሰል አደጋ መምጣት ጠንቅቆ የተረዳዉ  ባልደራስ አሁን ባልደራስ ፓርቲ መሪዎች ዕስክንድር ነጋ ስንታየሁ ቸኮል አስቴር ሥዩም ና የአዲስ አበባ ወጣቶች ማሰር ፊንፊኔ ኬኛዎችን ማባበል በመሆኑ ተቀባይነት የለዉም። ወንጀላቸው የሚሆነው ለምን ህዝቡ እራሱን እንዲጠብቅ ማንቃታቸው ብቻ ነው።
ጃዋር መሀመድ አዲስ አበባን በቀለበት ከበን መንግሥት መቆጣጠር ስንችል ነበር ዉይይት የተቀመጥነዉ ፉከራዉን ተከበብኩ ድረሱ ብሎ አዲስ አበባ ከዛሬ አንድ ዐመት በፊት ከመቶ በላይ ህይወት ዕምነት ቤቶችመኖርያ የንግድቤቶች አጋይትዋል። ባልደራስ ይህን አዉግዞ ወደፊት እንዳይደገም አኩሪ ስራ ሰርትዋል።
የኦሮሞ ክልል ብሔርተኞች የወያኔን ፈለግ በመከተል የኦሮሞ ሪፐብሊክ እንዳይመሠርቱ ዋናው ዕንቅፋት አዲስ አበባ በመሆኑ ከተማዉ ዙሪያ በመከላከያ መጠበቅ ይኖርበታል። ባልደራስ የአዲስ አበባ ህዝብ ማደራጀት መብት የህልዉና ጉዳይ በመሆኑ መደገፍ አለበት።
ሌሎች በኦሮሞ ክልል ያሉከተሞች ለህዝብ ደህንነት ለንብረት ዋስትና ሲባል በመከላከያ መጠበቅ ጥያቄ ዉስጥ አይገባም። የከተማው ህዝብም መደራጀት መብቱ ይከበር።
በኦሮሞ ክልል ለጠፋዉ ህይወትና ንብረት ተገቢዉን ካሣ መክፈል ያለበት የክልሉ መንግሥት ሲሆን የክልሉ ፀጥታ ኃይሎችም መፈተሽ ይኖርባቸዋል።
የሻሸመኔ ከንቲባ ለደረሰው ጥፋት ሀያ ሰው ይዘናል ያለው የማይመስል ነው። ህዝብ ተደራጅቶ ህይወቱን ንብረቱን እንዳይጠብቅ ማድረግ ከ አሸባሪዎች ጎን መቆም ስለሆነ የከተማዉ ከንቲባዎችን አስተዳዳሪዎች ህዝብ በነፃ ይምረጥ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የኢትዮጵያ የምጣኔ-ሐብት ማሻሻያ ምን ይዞ ይመጣል? - እሸቴ በቀለ(DW)

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share