ሃጫሎን ማን ሊገድለው ይችላል ለምን?

በእኔ እምነት የአርቲሰቱ ሞት የታላቁ የእዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን ከማደናቀፍ ሴራ ጋር በእጅጉ የተጋመደ ነው።ኢትዮጵያ የአፍሪካ የውኃ ማማ ናት።አፈሯም በዓለም ደረጃ ለም ከሚባሉት የሚመደብና የሰጡትን የሚያበቅል ነው። ነገር ግን ኢትዮጵያውያን ተፈጥሮ የለገሰችንን ሀብት መጠቀም እንዳይችል በግብጽ ታላቅ ደባ ሲፈጸምብን ኖረናል። ግብጾች ሲመቻቸው በቀጥታ ወረራ በማካሄድ ጦርነቱ ሲሳናቸው በእኛ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባት እያሰናከሉ የኢትዮጵያን የተፈጥሮ ሀብት በዋናነት ሲጠቀሙበት ኖረዋል።

ግብጽ በሜዲትራንያን እና በቀይ ባሕር የተከበበች አገር ብትሆንም ውኃው ጨዋማ ስለሆነ ለመጠጥም ሆነ ለእርሻ አትጠቀምበትም። የግብጽ ሕዝብ የሕይዎት መሰረት የሆነውና አገሪቱንም በዓለም ደረጃ በግብርና በቀዳሚነት ከሚሰለፉት አገሮች ተርታ እንድትመደብ ያደረጋት በአባይ ወንዝ አማካኝነት  ከኢትዮጵያ  ታጥቦ በሚሄድላት አፈር ነው። በዚህ ከቀጠለ በተለይ አባይ የሚመነጭበትና አብዛኛው የአባይ ገባር ወንዞች የሚፈልቁበት የአማራ ክልል አካባቢ ከጥቂት ትውልዶች በኋላ አፈርና ውኃ የሌለው፣ ለሕይዎት የማይስማማ፣ ያገጠጠ ተራራ ብቻ መሆኑ አይቀርም።

እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ልጥቀስ ፣ደቡብባዊ  የአፍሪካ ክፍል ሌሶቶ የምትባል 2 ሚሊዮን ህዝብ ብቻ የሚኖርባት በጣም ትንሽ  አገር አለች። ። የህዚች አገር የውጭ ምንዛሬ የሚገኘው ከተራሮቿ የሚፈሰውን ውኃ በዙሪያዋ ላሉ አገራት በመሸጥ ጭምር ነው። ኢትዮጵያውያንም  ካሁን ወዲያ የተከፈለው መሷዕትነት ተከፍሎ ከሌሶቶ ልምድ በመቅሰም  ውኃቸንን የገቢ ምንጭ ማድርግ  ይገባል።

እስራኤል እና የተባበሩት የአረብ ኢሚሬቶች ብዙ ቢሊዮን ዶላር አፍስሰው ጨዋማውን የሜዲትራንያን እና የሕንድ ውቅያኖስን ውኃ ጨውን በማጣራት ለእርሻና ለመጠጥ ይጠቀሙበታል።  ግብጾች ግን  አንድ ሳንቲም ሳያወጡ ከኛው ከቂሎቹ፣ አገር የሚሄድላቸውን አፈርና ውሃ ይጠቀማሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ:  የበድር አመራሮችን አስመልክቶ የወጣ መግለጫ - ከፈርስት ሂጅራ ፋውንዴሽን

በነጻ መጠቀማቸው አልበቃ ብሏቸው እንዲያውም የእኛኑ ደም የአባይን ውኃ የእኛነው፣ ከተጠቀማችሁበት ውርድ ከራሴ እያሉ እኛኑ መልሰው ያስፈራራሉ። ግብጾች በጦርነት እንደማያሽንፉን ጠንቅቀው ያውቁታል። የሚያሸንፉን ተናንት የሄዱበትን መንገድ በመከተል ነው። እሱም ትናንት ሻብያን፣ ወያኔንና ኦነግን አስታጥቀው እርስ በርስ በማዋጋት ከልማት ስራችን እንድንደናቅፍ እንዳደረጉን ሁሉ ዛሬም መሰል የሃገር ጠላት ባንዳዎችን በገንዝብና በቁሳቁስ እየደገፉ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ በማስገባት የእዳሴ ግድቡ የውሃ ሙሌት ብቻ ሳይሆን ጭራሽ ግድቡ በጅምር እንዲቀር ማድረግ ነው ተቀዳሚ አላማቸው።

ለዚህም በአለፈው ሳምንት ሞኝ ከእራሱ ብልህ ከሌላው ይማራል በሚል እርዕስ እንዳስነበብሁት  ህዋሃትንና ኦነግ ሸኔን እንዲሁም ስብናቸውን ለጥቅማቸው ታሪካቸውን ለሆዳቸው የሽጡ አክቲቪስትና ፖለቲከኛ ነን የሚሉ ባንዳዎችን በመመልመል አገራችን ላይ ትርምስ ፈጥረዋል። የአርቲስት ሃጫሎ ግድያም የእነሱ የእጅ ስራ ውጤት መሆኑን ለማዎቅ የግድ ነብይ መሆን አያስፈልግም።

ግብጽ፣ህ.ዋ.ሃ.ት፣ ኦነግ ሸኔና አንድ እግራቸውን ሰላማዊ ትግሉ አንድ እግራቸውን ከሽብር ቡድኑ ጋር በማድርግ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የሚነግዱ አክቲቪስትና ፖለቲከኛ ነን ባይ ባንዳዎች ቅንብር በመጀመሪያ አርቲስት ሀጫሎ ሁንዴሳ ምኒልክን እንዲሰድብ ተደረገ። በቀጣይ ምኒልክን ሰለሰደበ አማራው ገደለው እንዲባልና አማራውና ኦሮሞው ጎራ ለይቶ እንደሩዋንዳ ሁቱና ቱክሲ ጎሳዎች ሲጨፋጨፍ ህ.ዋ.ሀ.ት ወደ ስልጣን መመለስ እንዲችል ታስቦ አርቲሰት ሃጫሎን እራሳቸው ገደሉት።

በሩዋንዳው የዘር ጭፍጨፋ ልክ እንደ እኛው ሁሉ እልቂቱ እንዲፈጽም በትጋት የሚሰሩና ከስልጠና እስከ ትጥቅ  ድረስ ሚሰጡ የውስጥም የውጭ ሀይሎች ነበሩ ። እንደ ጃዋሩ ኦኤም ኤን ሁሉ አንተ ካልቀደምከው ሊያጠፋህ ነው፣ በለው ግደለው ይሄን የምታደርገው ለነፃነትህ ስትል ነው>።እያሉ የሚቀሰቅሱ ሚዲያዎች ስለነበሩ ለዘር ማፅዳቱ ትልቅ አስተዋፅኦ ነበራቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ትህነግ ከትግራይ ትውጣ!በትህነግ ስብዓዊ ጋሻነት የተያዘው ትግራዋይ ነፃ ይውጣ!የኢኮኖሚ አሻጥር ይብቃ

ለሰላም የተስማማው የሩዋንዳ የወቅቱ መሪም የተገደለው አመጹን ለማነሳሳት በሚፈልጉ፣ እንደ እኛዎቹ ህውሃቶች የራሳቸውን ስልጣን ማደላደልን ታሳቢ አድርገው በሚንቀሳቀሱ  ወገኖች ነበር። ይህ ህልማቸው ተሳክቶ  ህዝቡን ስሜታዊ በማድረግ ለዕልቂት ድግሳቸው ተቋዳሽ አድርግውታል።

ይህ እቅዳቸው ግቡን መትቶ በሩዋንዳ ሰው  እንደ ቅጠል ረገፈ ፣ ደም እንደጎርፍ ፈሰሰ፣ ብጥብጡን ያነሳሱትም  ሌሎችን እሳት ውስጥ ማግደው ራቅ ብለው ወላፈኑን እየሞቁ ዓለም ለዚያ እልቂት ትኩረት እንዳይሰጥም አደረጉ።  በመጨረሻም በነሱ ሰቀቀን  ፊልም ሰሩባቸው ። በየቦታው ምሳሌና ማጣቀሻ እንዲሆኑ አደረጓቸው ፣ ባለመሰልጠናቸው ተሳለቁባቸው።ዛሬ በሰቀቀኑ አንገቱን ሚደፋው መላው የሩዋንዳ ህዝብ ነው።

ይህ  የቅርብ  ጊዜ ታሪክ. ለኛ ምንድነው የሚያስተምረን? የኛ እርስ በርስ መባላት ፣ መገዳደል ፣ ሽኩቻ ሰርግና ምላሽ የሚሆንላቸው ጠላቶቻችን ግብጽ ህ.ዋ.ሃ.ት፣ ኦነግ ሸኔና ባንዳዎቹ እሳቱ እንዳይበርድ እንደሚቆሰቁሱት እርግኛ ነን። ለዚህ አላማ ብቻ የተቋቋሙ እንደ ጃዋሩ ኦ.ኤም.ኤን አይነት ሚዲያዎችም መቼም ፍቅር አይሰብኩንም ።

ከእኛ ከእውነተኛ ኢትዮጵያውያን የሚጠበቀው ነገሮችን በእርጋታ መቃኘት ነው። ባለፈው ጽሁፌ አሁንም ሌላ እድሪስ ሞሐመድ፣ ሌላ ኢብራሄም ሱልጣንና ሌላ ወልድ.አብ ወልደ.ማርያምን ከመካከላችን በመመልመል እያዘጋጁ ስለሆነ ልንጠነቀቅ ይገባል ብየ ከላይ የተጠቀሱ ኤርትራውያንን አስታውሽ ነበር። ስጋቴ እውን ሆኖ አንድ ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ይኽው ወንድማችንን አርቲስት ሃጫሎን ገድለው አማራ ነው የገደለላችሁ በማለት የእርስ በርስ ግጭት ውስጥ ከተውናል። አሁንም አልረፈደም አውቀንባችኋል ልንላቸው ይገባል።

ከዚህ አንጻር የአርቲስት ሃጫሎ ሁንዴሳ ገዳዮች ያለጥርጥር ከላይ ስማቸውን የጠቀስሁት የተባበሩት አሸባሪዎች ማለትም ግብጽ፣ ህ.ዋ.ሀ.ት.ኦነግ ሸኔና ካሃዲዎቹ አንዳንድ አክቲቪስትና ፖለቲከኛ ነን ባዮች ናቸው እንጅ አማራ ሊሆን አይችልም የሚል ድምዳሜ ላይ ለመድርስ የሚግድ ነገር ያለ አይመስለኝም።

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሃይ ሊባሉ የሚገባ ወገኖች - ሰመረ አለሙ

መንግስትም ጅል ዳኛ ያማታል ጅል ..… ያፋታል እንዲሉ እንዳይሆንና እንደ እሩዋንዳ ወደመተላለቅ እንዳንገባ ከውጭም ከውስጥም በመፈላለግ ተባብረው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በዘመቱት። በእነ ግብጽ ህ.ዋ.ሃ.ትና ኦነግ ሸኔ እንዲሁም አንድ እግራቸውን ሰላማዊ ትግሉ ሌላ እግራቸውን ከአሽባሪው ቡድን ላይ እርግጠው ሌት እንቀልፍ ቀን እርፍት አጥተው በሚሰሩ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ የማያዳግም እርምጃ ወስዶ ማሳየት አለበት እላለሁ።

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይጠብቅ

አሜን

ማተቤ መለሰ ተሰማ

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share