ነፃነት – በ እንደሻው በርጃ

ጻድቃን ያወሩለት ሕያው የሞቱለት
ይሄ ነው ነፃነት የባርነት ጠላት፤
ነፃነት ህብረት ነው መኖር ተፈቃቅሮ
አንዱ አንዱን ሳይጠላው ሳይተፋው አንቅሮ፤
ነጻነት ሸማ ነው ንጹህ ያላደፈ
በድንቁርናና በደም ያልጎደፈ፤
በስርዐት ተመርተን በደንቡ ካልያዝነው
ካለቦታው ሲሆን ነፃነትም ጸር ነው፡፡

ፀርጋዬ መርጊያ

1966 ዓ.ም

ይህን ጠንከር ያለ መልዕክት በ1966 ዓ.ም በመረዋ ድምፁና በጊታር ጨዋታው ያስተላለፈልን ተወዳጁ መምህር ፀጋዬ መርጊያ ነበር፡፡ወቅቱ የኢትዮጵያ አንድነትና ጥንካሬ መገለጫ የነበረው ዘውድ እንደ ዘበት ተሽቀንጥሮ የተጣለበትና ሶሺያሊዝም ቀመስ የጊዜው አብዮተኞች እዚህም እዚያም እንደ አሸን ፈልተው ዙፋኑን ለመቆጣጠር ሀገር እየታመሰች በነበረበት ወቅት ነው፡፡ሁሉም ፖለቲከኛ ሀገር መሪ ለመሆን የ’መጠበትና “ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባበታል” እንዲሉ ታሪካዊ የኢትዮጵያ ጠላቶችም መልካም አጋጣሚ ሆኖላቸው የዋህ ልጆቿን ተጠቅመው እስከዛሬ የምንታመስበትን የጦርነት መሰረት ዳግም የጣሉበት ጊዜ ነበር፡፡

እናም ይህን በአንክሮ የተመለከተው ፀጋዬ ጊዜ ሳያባክን ስንኙን ቋጥሮ ጊታሩን በማንሳት በጥዑም ድምፁ ስጋቱን ለሀገሩ ልጆች ገልጹዋል፡፡ነገር ግን ነቢይ በሀገሩ አይከበርም እንዲሉ፤ይህን መልዕክቱን ልብ ያላሉት የሀገሩ ልጆች የነፃነትን ምንነት ሳያውቁ ነፃነትን በአፍጢሙ ደፍተው፤ ነጻ አውጪ ነን በማለት በያቅጣጫው ወደ እንጀራ እናቶቻቸው ሱዳን፣ ግብፅ፣ የመን፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ጅቡቲ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ጀርመን፣ ቻይና፣ ኢራቅ፣ ፓኪስታን፣ ኩባ ወዘተ ተመሙ፡፡

ከእነዚህ ሀገሮች ገሚሱ ከለላና ፓስፖርት በማዘጋጀት፤ ገሚሱ ፅህፈት ቤት ከፍተው ወታደራዊ ስልጠና በመስጠት ፤ ገሚሱ ትጥቅና ስንቅ በገፍ በማቅረብ በአራቱም ማዕዘናት በሀገሪቱ ላይ አሰማሩባት፡፡

 • የባርነት ጠላት የሆነችውን ነፃነት፣ ነፃ አውጪ ተብዬዎቹ በብርቱ ተዋጓት፣
 • ሕብረት የሆነችውን ነፃነት፣ በዘር ከፋፍለው ነጠላ አደረጓት፣
 • ፍቅር የሆነችውን ነፃነት፣ የበቀል ምንጭ አደረጓት፣
 • በፀአዳ ሸማ የተመሰለችውን ነፃነት፣ ደናቁርት ነፃ አውጪዎች በደም ሸማ አሳደፏት፣
 • በክብርና በስርዐት መያዝ የነበረባትን ነፃነት፣ ትዕቢተኛ ነፃ አውጪዎች ከነሰንደቅ ዓላማዋ ከመሬት ጥለው አዋረዷዋት፡፡
ተጨማሪ ያንብቡ:  ሦስቱ የሰው ዓይነቶች በጥንታዊ የግሪክ ፈላስፋዎች አገላለፅ  (ትርጉም:ዘ-ጌርሣም)

ለዚህ ሁሉ ጥፋቱ ግን ለዚህች ሀገር ነፃነት አንዲት ጠብታ ደምና ስንጥር ታህል አጥንት     ያላዋጡ በስሜት የተነዱ ወጣቶች በገዘፈ መስዋዕትነት በገፍ የተሰጣቸውን ነፃነት በስርዐትና በአግባቡ መያዝ አለመቻላቸው ነው፡፡ ካለቦታው የተሰጠውም ነፃነት ለሀገሪቱ ፀር ሆኖ ማለቂያ የሌለው የጦርነት አዙሪት ውስጥ ከቶናል፡፡ ይህም አልበቃ ብሎን ዛሬም ቅጥ ባጣ ነፃነት ህዳጣን ‹‹ነፃ አውጪዎች›› በያካባቢው ተፈልፍለው ከኔ ዘር በላይ ላሳር በሚል ትዕቢትና ጉራ ተወጥረው ሀገሪቱን የስጋት ቀጣና አድርገዋታል፡፡ እነዚህ ዘመኑን የማይመጥኑ ደናቁርት ዛሬም በነፃነት ስም በሀገሪቱ ሀብት በተገነቡ መገናኛ ብዙሀን ላይ በመቅረብ ፍፁም የለየለት ሀገር አፍራሽ የዘረኝነት ቅርሻታቸውን 24 ሰዓት በህዝቡ ላይ ያቀረሻሉ፡፡

ኢትዮጵያውያን ምን ያህል ለነፃነታችን ቀናዒ እነደነበርን ዓለም የሚያውቀው ነው፤ ነገር ግን እርግማን ሆኖብን ከምድራችን የበቀሉ የነፃነትን ዋጋ ያልተረዱ የዘር ነፃ አውጪዎች ብዙ መስዋዕትነት ተከፍሎ የተሰጣቸውን ነፃነት ከምንም ሳይቆጥሩ በነፃነት ስም ሀገር በማፍረስ ተግባር ላይ ተጠምደዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ግን ማንም የሰው ዘር የሆነ ሁሉ ማወቅ ያለበት ግዙፍ ዕውነታ፤ የዚህች እናት ሀገር ኢትዮጵያን ነፃነት ለማስከበር የፈሰሰው ደም ጣና ሐይቅን፣ የተከሰከሰው አጥንትም ራስ ዳሽን ተራራን የሚገዝፍ መሆኑን ነው፤በዚህ መስዋዕትነት ላይ ማንም እንዳሻው ሊፈነጭበት ከቶም አይገባም!! ዛሬ በዚህ ታላቅ መስዋዕትነት የተገኘውን ነፃነት ፍፁም ለመደምሰስ የሚሯሯጡ ኢትዮጵያውያንም ሆኑ ባዕዳን ዜጎች፤ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች በሀገሪቱ ላይ የሚፈፅሙት አፍራሽ ድርጊት በዚህ የመስዋዕት የደም ሐይቅ ውስጥ እንደ መዋኘት፤ በመስዋዕት የአፅም ተራራውም ላይ ሠደድ እሳት እንደ መልቀቅ የሚቆጠር ነው፡፡

በመሆኑም እኚህ በላዔ-ሰቦች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እያሳሰብን፤ ይህ ሳይሆን ቀርቶ በሀገር አፍራሽ ተግባራቸው የሚቀጥሉ ከሆነ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ለማስከበር የእሳት ዝናብ በላያቸው ማዝነብ የሚችልና፤ እጃቸውን በካቴና አስሮ በፍርድ አደባባይ እያቆመ የማያዳግም ፍትሕ የሚጥልባቸው በአንክሮ እያያቸው ያለ እልፍ ዜጋ እንዳለ ከወዲሁ ሊገነዘቡት ይገባል፡፡ አሁንም ቢሆን መምህሩ እንዳለው….

ተጨማሪ ያንብቡ:  ሰው መሆን ይበቃል (ዘ-ጌርሣም)

በስርዐት ተመርተን በደንቡ ካልያዝነው፣

ካለቦታው ሲሆን ነፃነትም ፀር ነው !!

እንደሻው በርጃ

 

ለጀግናው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ሥላሴ

ለመቀሌ የሽምግልና ኦሎምፒክ ድል የተበረከተ

የሰላም ምንዳ

ለሰላም ዝቅ አለ… ኃይሌ ተፈተሸ
ባንዳ አዋራጅ ነው… ሀገር ያቆሸሸ

የጽናት ተምሳሌት…
የኢትዮጵያ ምልክት…

እግሩ እንኳ ቆስሎ …አምቆ ህመሙን
አየቆጠቆጠው……..ገፍቷል ውድድሩን

የዛሬው ቁስል ግን……ከቀድሞው ይለያል
እግሩን ብቻ ሳይሆን…ልቡን ጠዝጥዞታል
በገዛ ሀገሩ እንደ ባዕዳኑ……… ኃይሌ ተፈትሿል
እጁን አሰቅሎ…………….. ባንዳው አዋርዶታል

ይሄ ነው ሽልማት…….ይሄ ነው ኒሻንህ
ለጀግና የሚሰጥ…የክብር ሜዳልያ…ባንዳ ያጠለቀልህ

በባለጌ መንደር……………….በባለጌ ቡድን
እንዲህ ነው ማዋረድ…..የኦሎምፒክ ጀግናን

አልበገር ባዩ…….ለህዝብ ጥቅም ብሎ…..ኃይሌ እጅ ሰጠ
በመቀሌው ባንዳ…ጀግናው ሲበረበር……….ዓለም ደነገጠ

 

እንደሻው በርጃ

 

 

2 Comments

 1. ወንድሜ እራሱን ያዋረደው ሀይሌ ነው:: በመጀመሪያ አማራ እንደጠላት የሚታይበት መንደር የምን አስታራቂ ሆኖ ሊቀርብ ነው:: አቡኑና የሀይማኖት መሪዎች ስራቸው ስለሆነ ሄደው ይጃጃሉ ሀይሌ አርፎ መቀመጥ ነበረበት:: ህውሁት ዘርፊያ ስለቀረበት አማራን አጥብቆ ይጠላል:: ይህ የማይታየው ጅል አማራ ብቻ ነው

 2. Haile G/Selassie did not degrade himself he rather add respect and wisdom the bible says forgive your brother seven times seventy. he cares for the Tigray Ethiopians not for old guard” bandas” and their cliques. The time will be up for the criminal tigrians and the punishment will be severe. Haile feels the pains and sufferings of his fellow Ethiopians and took the initiative and he deserves with all who went respect and appreciation.
  God bless all true Ethiopians and Ethiopia and protect them.
  Muchfun
  Canada.

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.