March 31, 2020
12 mins read

 ‘ያልታረሙ አንደበቶች ሀገርን ያዘቅጣሉ!’ – ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ

ፀጋዝአብ ለምለም ተስፋይ- የኢኮኖሚክስ መምህርና ጸሓፊ

(ሸክም የበዛበት ትውልድ፡2009 እና የምሥራቃዊት ኮከብ፡ 2010 መጻሕፍት አዘጋጅ)

ንግግር በሰው ልጆች ያለፉ፣ ያሉና የሚኖሩ ኹለንተናዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መሰተጋብሮች ውስጥ የማይተካ ሚና እንዳላቸው የሚታወቅ ሃቅ ነው፡፡ ንግግር ስሜትን፣ ሃሳብንና ምኞትን የሚገልጽ ከመኾን ባሻገር ከአንዱ ወደ አንዱ የማስተላለፊያ – ትልቅም ተጽዕኖ የመፍጠሪያ ዐቢይ መሣሪያ ስለመኾኑ ማንም በመኖር የሚያውቀው ዕውነት (Truth) እና እውነታ (Reality) ነው፡፡

በሀገራችን ባህል፣ ወግ፣ ልማድና ኹለንተናዊ መስተጋብር ውስጥ ንግግር ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ከመኾኑም ባሻገር ሰዎች እርስ በራስ የሚተያዩበትን አውድ ራሱ የወሰን ኃይል አለው፡፡ በሥነ ቃሎቻችንም ቢኾን ብዙ ብዙ ተብሏል፡፡

ለአብነት፡- “ከንግግር ይፈረዳል – ካያያዝ ይቀደዳል፤” የሚለውን እናገኛለን፡፡

ይህም ከግለሰብ/ቦች፣ ከቡድን/ኖች እና ተቋማት/ቶች መልዕክትና ገለጻ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው፡፡ በተለይ ከማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል በላቀ – በተሻለና አርዓያነት ባለው መንገድ ከምሁራን፣ ከኪነ ጥበብና የሥነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከመሪዎች፣ ከገዥዎች፣ ከባለሙያዎች፣ ከጋዜጠኞች፣ ከእድሜ ባለጸጋዎች – – –  ወዘተ የሚጠበቁ ነገሮች አሉበት፡፡

አንድ ሰው የሃይማኖት አባት ኾኖ እንደአንድ ሥነ ምግባር የሌለው ወጣት የሚጠቀምበትን የንግግር ዘዪ ተከትሎ ቢናገር ከንግግሩ በላይ “ከአንድ የሃይማት አባት የማይጠበቀ” እየተባለ የሚወቀስበት ነጥብ ሚዛን የሚደፋ ኾኖ እናገኘዋለን፡፡

ከንግግር ይዘት፣ አይነትና መጠን ብሎም አቀራረብ አንጻር በባህሪያዊና ጠባያዊ መገለጫዎቹ የተነሳ ንግግር መልካም ብቻ ሳይኾን መጥፎ፤ የላቀ ብቻ ሳይኾን የዘቀጠ፤ ምርቃት ብቻ ሳይኾን እርግማን፤ ምክር ብቻ ሳይኾን ስድብ፤ ቁም ነገር ብቻ ሳይኾን ቧልት – – – ይቀርብበታል፡፡ በውጤቱም ማስደሰት ብቻ ሳይኾን ያሳዝናል፤ አንድ ማድረግ ብቻ ሳይኾን ይከፋፍላል፤ ፍቅርን ብቻ ሳይኾን ጥላቻን ማስፋፊያ ይኾናል፤ – – –  ከመቀራረብ ይልቅ ያራርቃል፤ ከፍ ሲልም ጦር ያማዝዛል፡፡

በሀገራችን ዛሬ ዛሬ በአደባባይ እንደሚስተዋለውና በየሚድያዎቹ እንደሚስተጋባው ንግግሮችን በተለይ የጋዜጠኞችን፣ የምሁራንና የገዥዎችን ስንመለከት ዕውን የያዙትን ኃላፊነት የሚመጥን፣ የሚገባና አርዓያነት ያለው ነውን?

በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበትና የህዝብ ተወካዮች ባሉባቸው ቦታዎች የሚነገሩ ንግግሮችን ስንመለከት፡

1ኛ. ከይዘት አንጻር እጅግ የተፋለሰ፤

2ኛ. በአመክንዮ ያልተደገፈ – በስሜት የተሞላ – ማስመሰልና ሴራን ማዕከል ያደረገ – መነሻውና መዳረሻውን ፕሮፖጋንዳዊ ዓላማና ግብን ብቻ ያደረገ ትርጉም አልባ አስተያየቶች የተበራከቱበት፤

3ኛ. አሽሙርና ስድም አለፍ ሲልም በዘለፋ ላይ የተመረኮዙ  – ህልውናቸውንም በዛ ላይ ያደረጉ፤

4ኛ. በቃላት አጠቃቀም እጅግ የወረዱና የዘቀጡ፤

5ኛ. አርዓያነት የሌላቸው – እጅጉን በአደባባይ ሃሰት የተሞሉ፤ ከአንድ ትልቅ የኃላፊነት ደረጃን ከያዘ/ዙ ግለሰቦችና ቡድኖች የማይጠበቁ በርካታ ንግግሮችን በየሚድያውና በየስብሰባ አዳራሹ መስማት እንደአንድ ጀብዱ የሚቆጠርባቸውን ኹነቶች እጅግ በተደጋጋሚ ታዝበናል፡፡

ተናሪው ስለሚናገረው ሀሳብ ዕውን ለምን? እንዴት? መቼ? የት? በምን ኹኔታ ውስጥ ትውልዳዊና ኃላፊነታዊ ግዴታን እወጣለው ብሎ ከማሰብ ይልቅ እጅግ በስሜት የተሞላ፣ ከነባራዊ እውነታ እጅጉን የራቀ፣ በተራ የቃላት ድርደራ የተሞላ፣ ከንቱ መታበይ የተሞላበት፣ በልቅምቃሚ ጥቅሶች የተጥለቀለቀ፣ በጥቃቅንና አነስተኛ አጀንዳዎች የተሞላ፣ ጥላቻን የሚዘራ መልዕክት የተበራከተበት፣ ጭብጨባን ማዕከል ያደረገ፣ ከመድረኮቹ ዓላማ እጅጉን የራቀና የተቃረነ – – – ብዙ ህዝብ በተሰበሰበበት ተራ የግለሰብና ቡድኖች የርስ በራስ የፕሮፖጋንዳ ጦርነት አውድማ የኾነበትን አጋጣሚ በብዙ መንገድ ከመመልከታችን ባሻገር መሻሻሎች ሳይታዩበት እየቀጠለ ይገኛል፡፡

ዕውን የኢትዮጵያ ህዝብ የሚመጥነውን ንግግር እየሰማ ነውን? ዕውን የሚያስፈልገው ኹለንተናዊ መልዕክት እየተላለፈለት ነውን? ዕውን በየመድረኮቹ የምንታዘባቸው እጅግ የዘቀጡና የወረዱ የአንደበት ንግግሮችን አሉታዊ ተጽዕኖ ኹለንተናዊ ዋጋ ማን ይከፍላል? ማንስ ይጠየቃል? ዕውን በኢትዮጵያ ውስጥ ላልታረሙ አንደበቶች ልጓም የኾነው ምንድነው? ያለአሽሙርና ስድብ ንግግር ማድረግ የሚችሉ የማይመስላቸው – ኾን ብልው አስበውና አሰላስለው በመግለጫ፣ በመልዕክትና በመልሳቸው ላይ የሚከቱ ገዥዎች አልተበራከቱምን?

ባዶ ፍሬ ከርስኪ የኾነ ንግግር በማቅረብ በጭብጨባ የሰከሩና ጭብጨባን ማዕከል ያደረጉ እንቶ ፈንቶዎች በየቦታው የሚሰሙ አይደሉምን? የተጠየቀውን ጥያቄ በቀጥታ ከመመለስ ይልቅ ምንም የማይያያዝና ያልተጠየቀ ጥያቄ ራሱ ጠይቆ ራሱ የሚመልስ ትዕቢተኛ አልተበራከተምን? ለአንደበታቸው ሥርዓት፣ ወግና ግብረ ገብነት የሚባል ከቶ ያልፈጠረባቸው – ምሁራዊ ባህሪያትን ከአመክንዮ አንጻርና ከሀሳብ ጥልቀት አንጻር ከቶ የማያቀርቡ በርካቶች አይደሉምን?

የያዙትን ኃላፊነት የማይመጥኑ ከሚጠበቅባቸው እጅግ ወርደው፣ ዘቅጠውና ኃላ ቀርተው የሚገኙ ኾነው ሳለ ህዝብን  – የሚፈልገውን – ይፈልገዋል የሚባል – ያልኾነውንና ሊኾን የማይችለውን ውዳሴ በመንገርና በስሜት በማስከር አልያም በንግግራቸው ፍጹም ከተነሱ ኹለንተናዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መሠረታዊ ጥያቄዎች እጅግ የራቀ ተረት ተረት፣ ፍሬ ከርስኪ ቀልድና ቧልት አለፍ ሲልም ሃሰት በመጨመር የሚከናወኑ ተግባራት አልተበራከቱምን?

ዛሬ ዛሬ በሃገራችን ንግግሮች እጅጉን በሃሰት የተሞሉና ወደ መሬት የማይወርዱ እጅግ በርካታ ጉዳዮችን አልታዘብንምን? የህዝብን ትኩረት ለመሳብ ሲባል በሀገር ደረጃ ግለሰቦች ብቻ ሳይኾን ቡድኖችና ተቋማት ህዝብን ተደራጅተው፣ አስበውና አስልተው የሚዋሹበት –  የውሸት ዜና፣ መልዕክትና ዶክመንተሪዎች በእጅጉ አልተበራከቱምን? ሃሰተኝነትን የማንነታቸው አካል ያደረጉ – ሲዋሹ በአደባባይ ምንም የማይመስላቸው ነውረኞች አልተበራከቱምን? ሃሰተኝነታቸው ሲታወቅና ሲጋለጥ የበለጠ ውሸት በመዋሸት የሚዳክሩስ በርካቶች አይደሉምን? ሃሰተኝነትን ዋነኛ የስብዕናቸው መገለጫ ከማድረጋቸው የተነሳ ደሞ መጡ የሚባሉ በርካቶች አይደሉምን?

ዕውን ዛሬ ዛሬ የሚታመኑ ገዥዎች እነማን ናቸው? በንግግሩ የሚታመን ባለሥልጣን ማን ነው? እንኳንስ ህዝብ ሚስቱና ልጆቹ የሚያምኑት ባለሥልጣን ማን ነው? ሃሰተኛነትን የስብዕናው አካል ያላደረገ ማን ነው? ቃሉን የሚያከብር ጀግና ኢትዮጵያ አላትን?

“ያልታረሙ አንደበቶች ካልታረሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ሲወጡ – የታረሙ አንደበቶች በአንጻሩ ከታረሙ ግለሰቦችና ቡድኖች ይወጣል፡፡”

ንግግር በባህሪው በሰው ልጆች ኹለንተናዊ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስተጋብሮች ውስጥ ዘር ኾኖ በሰዎች አዕምሮ የሚቀር እያደገ ሲሄድም በዕይታ፣ በምልከታ፣ በአስተሳሰብና በአመለካከት ሂደት ውስጥ እጅግ የላቀ ሚናን የሚጫወት ታላቅ መሣሪያ ስለኾነ ያልታረሙ አንደበቶች እንዲታረሙ ኹለንተናዊ ሥራ መስራት ያስፈልጋል፡፡ ያልታረሙ አንደበቶች ሀገርን፣ ህዝብንና ትውልድን ወደ አዘቅጥ ሲወስዱ የታረሙ አንደበቶች በአንጻሩ ወደ ከፍታ ይወስዳሉ፡፡ ፈጣሪ ሀገራችን ነጻ ፍቃድን የኹሉ ነገር ማዕከል ወደ ሚያደርግ የዕሳቤ ሂደት ትገባ ዘንድ ይርዳን!

ቸር እንሰንብት!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop