መንግስት የፖለቲካ ምህዳሩን ቢያሰፋም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ፈር እየለቀቁ ነው – ብሮድካስት ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን መንግስት የሃሳብ ነጻነት በዴሞክራሲያዊ መንገድ እንዲያድግ የፖለቲካ ምህዳሩን ቢያሰፋም አንዳንድ መገናኛ ብዙሃን ፈር እየለቀቁ እንደመጡ መመልከቱን ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጿል።

የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንደሰን አንዷለም እንዳሉት፥ ተቋሙ በሁሉም ዘርፍ የሚዲያ ነጻነት እንዲረጋገጥና የዴሞክራሲ ግንባታ ሂደቱን ለማገዝ ኢ ፍትሀዊ ሀሳቦች ሲተላለፉ በተለያየ መንገድ ለመፍታት እየጣረ ነው።

ባለፉት ስድስት ወራትም ለ49 የመገናኛ ብዙሃን ግብረ መልስ መሰጠቱን ጠቅሰው፥ ለአራት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ የማስጠንቀቂያ መልዕክት በስልክና በደብዳቤ እንዲደርሳቸው ተደርጓል ብለዋል።

በሂደቱ የተወሰኑ ለውጦች ቢታዩም ከህገ መንግስቱም ሆነ ከብሮድካስት ባለስልጣን አዋጅ ተጻራሪ በሆነ መንገድ የሚጓዙ መገናኛ ብዙሃን መኖራቸውንም አንስተዋል።

አያይዘውም ባለስልጣኑ ከአንድነት ይልቅ ልዩነት ላይ ያተኮሩ እና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ መገናኛ ብዙሃንን እንደማይታገስ አስረድተዋል።

ከዚህ አንጻርም ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩና ቁርሾ የሚፈጥሩ ሃሳቦችን በሚያስተላልፉ መገናኛ ብዙሃን ላይ በአዋጁ መሰረት እርምጃ መውሰድ እንደሚጀምርም ተናግረዋል።

ትናንት በኦ ኤም ኤን የህዝቦችን አንድነት የሚሸረሽርና ቁርሾን የሚፈጥር መልዕክት ሙሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ባለስልጣኑ እንደደረሰውም ገልጸዋል።

አሁን ላይ መልዕክቱ በባለሙያዎችና አመራሮች እየተገመገመ ሲሆን፥ በአጭር ጊዜ መረጃውን በማጥራት ውጤቱ ይፋ እንደሚደረግም አውስተዋል።

በማጣራት ሂደት ውስጥ የሚገኙ ውጤቶች የሚያስጠይቁ ሆነው ከተገኙም እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

ምንጭ፡- ኤፍቢሲ

3 Comments

 1. አሁን የጭፍን ዘረኝነት ስካር ወደ ለየለት እብደት መኝታ ቤታችንን ማንኳኳት አማረው። ይኼ ነው የቀረኝ አሉዋሉ .. የነፃነት ትርጉም ያልገባቸው በሞቅታ ረግረግ ወስጥ ተዋጡ። መንግስት የሚለውንና የሚያደርገውን በአርምሞ ብንጠብቅም አኛ ግን አንፈታም አንፈታም ።(አንደኛው “ፈ” ጠበቅ ተደርጎ ይነበብ።)

 2. A Mother of two from Ethiopia got shot and killed in San Francisco California USA by two males this year in January 2020 , even though the killers admitted to the killing of the 32 years old mother of two from former state of Ethiopia , of Eritrea while Eritrea was under Ethiopia, no charges are filed against the killers by the USA government authorities . The international communities should know that denying Ethiopians water and their chance of being self reliant with food got so many unforseen negative consequences not only to Ethiopia but to the whole world since Children who grow up malnourished witnessing starvation related disasters got less stamina throughout their lifetime .

  A former Ethiopian famine victim as a little child who witnessed the death loosing of her parents to the Ethiopian famine starvation in the state of Eritrea who is now an independent country , who later got adopted and moved to USA later ended up having two children of her own got shot and killed by two male individuals a couple of months ago in San Francisco , California USA , ingniteing one of the most controversial legal conflicts since the killers are not charged with murder but charged the admitting killers with only gun charges since these Ethiopian lady was a former famine victim in the former Ethiopian State of Eritrea who terrorized the two males that were charged with only gun charges even if they admitted to killing the 32 years Ethiopian who was born from Eritrean family , the two men claimed they feared for their life before they shot and killed Emma Hunt so no murder charge is being filed for this 32 years old Ethiopian mother of two despite the Ethiopian Eritrean Community continuous outcry to charge the killers with murder the prosecutor is inclined to not charge them with murder saying she acted threatening towards the two male individuals exhibiting her African sides of when she grew up fending for herself and her younger sister homeless in Ethiopia after her parents died of starvation famine .

  News Break › … › San Francisco
  Web results
  SF District Attorney declines to file murder charges in Tenderloin shooting of mother

 3. እርምጃ መወስድ ግድ ይላል፡፡ በአለም ላይ ለተሰሩ ከባድ ወንጀሎች፣ ህዝብ ከህዝብ ለሚያጣሉ ጥፋቶችና ብሎም አገራት መፈራረስ ሚዲያዎች ትልቁን ሚና ሲጫወቱ እንደነበረ መማር ያስፈልጋል፡፡ አንድ ሚዲያ ተቋም ከግለሰብ፣ ቤተሰብና ማህበረሰብ አይበልጥም እኮ፡፡ ስለዚህ አፈጣኝ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል፡፡ ሆን ተብሎ በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ሳናውቅ ቀጥታ ስርጭት ስለሆነ ነው ማለት ማፈሪያ ነው፡፡ ከተናገሪያዋ ጀምሮ ሲስቁና ሲሳለቁ የነበሩ በሙሉ ማፈሪያ ናቸው፡፡

  እንደው በተከበረ የሴቶች ቀን ላይ ማፈሪያ የሆነች ሴት ተናጋሪ ይህንን ማቅረብ የሴቶችን የአለምና የአገር ለውጥ ጥረት በቆሻሻ መልክት መገለፁ ማፈሪያ ነው፡፡ በዚህ ትልቅ ፕሮግራም ላይ መቅረቡ ምን ያህል የወረደ አመለካከት እንዳለ ነው፡፡ ለሊት ለሊት አማራ ወይም ሌላ ብሔር የሆነች ሚስታቸውን እያቀፉ ሌላ የወረደ ነገር መናገር ሰዎች ምን ያህል የወረዱ እነደሆነ ነው፡፡ እነዚህ ለልጆቻቸው ምንድን ነው የሚያስተምሩት፡፡ ተናጋሪዋም ተጠያቂ መሆን አለባት፡፡ መዋደድና መፋቀርን ሰው ስለፈላገ እኮ አያለያየውም፡፡

  ፍቅርና መዋደድ ስለፈለጉት ብቻ የሚሆን አይደለም፡፡ በዓለም ላይ ባለ ግንኙነት አገር አቋርጦ ፈረንጅ ወይም የሌላ አገር ዜጋ በማግባት ምን ያህል ፍቅር እንደሚያሻንፍ ይታወቃል፡፡

  አረ በስንቱ ነው ማፈር!!!!!!!

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.