የእናት ፓርቲ ተመሰረተ።መስራች ጉባኤውን ዛሬ በአዲስ አበባ ላይ በተሳካ መልኩ አከናውኗል።የተመራጮች ስም ዝርዝር ይዘናል

ጉዳያችን 

የፖለቲካ፣የሰላም እና ደህንነት (Peace and Security) ምሑሩ ዶ/ር  ኃይለየሱስ ሙሉቀን ፕሬዝዳንት፣የምጣኔ ሃብት ምሁሩን ዶ/ር ሰይፈስላሴ አያሌውን ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አድርጎ ጉባኤው መርጧል።

ዛሬ በጠቅላላ ጉባኤ ከቀረቡት አማራጮች ውስጥ የፀደቀው የእናት ፓርቲ ዓርማ

ዛሬ ዕሁድ የካቲት 29፣2012 ዓም በአዲስ አበባ ስድስት ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማዕከል የመስራች ስብሰባውን ያካሄደው አዲሱ እናት ፓርቲ የፓርቲውን ሎጎ በጠቅላላ ጉባኤው ያፀደቀ ሲሆን፣ የስራ አስፈፃሚ አባላትን፣የላዕላይ ምክር ቤት አባላትን፣ የሂሳብ ክዋኔ ኦዲት ኃላፊዎች እና የሕግ ስርዓት ጉዳዮች ኃላፊዎችን መርጧል።የእናት ፓርቲ አደራጆች በዛሬው መስራች ጉባኤ ላይ የፓርቲው መመስረት ያስፈለገበትን ምክንያት ሲያስረዱ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግሮች በሶስት ጉዳዮች ተተብትበው መያዛቸውን እና ለእዚህም በቂ መፍትሄ ፖለቲካው  መስጠት ያለመቻሉን በዋናነት ያስቀምጣሉ። እነርሱም –

1. ፖለቲካዊ ችግሮች፣ 

በሀገራችን የሚታየው የፖለቲካ ስሪት ብዙ የሀገራችንን ችግሮች መፍታት ሲገባው በአሉታዊ መልኩ መገኘቱ። ኅብረተሰቡን በቋንቋ፣ በጎሳ ፣ በሰፈር፣ ወዘተ የሚከፋፍል በመሆኑ በሕዝቦች መካከል አብሮ የመኖር እሴትን መሸርሸሩ።

2. ማኅበራዊ ችግሮች፣

የሀገራችንን ማኅበረሰብ በማኅበራዊ ጉዳይ በፍቅር ፣ በመተሳሰብ ፣ በመቻቻል እና በመከባበር በጋራ ሀገራችን መኖር ሲገባን ግራ በገባው ትርክት ሰዎች መሰደዳቸው፣ መፈናቀላቸው፣ የግለሰቦች ሀብትና ንብረታቸው ከፍተኛ ጉዳት ላይ መውደቁ፣ የሃይማኖት ተቋማት የደኅንነት አደጋ ላይ መውደቃቸው፣ የሰዎች የመኖር ዋስትና ስጋት ላይ መውደቁ፣ በየጊዜው ብዙ ሰዎች መገደላቸው፣ ወዘተ የሀገራችንን ሕዝቦች የማኅበራዊ የሕይወት ትስስር አደጋ ላይ መውደቁ።

3. ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፣

የሀገራችን የኢኮኖሚ ግባት የኢትዮጵያውያን ሕዝቦች ዕለት ተዕለት ኑሮን ለማሸነፍ የማያስችል፣ ከገቢ ይልቅ ወጪን እንዲንር በማድረግ የሰዎችን የመኖር ተስፋ ያቀጨጨ ስለሆነም መፍትሔ የሚያስፈልገው ስለሆነ።
በአጠቃላይ የሀገራችን ፖለቲካ ሦስቱንም (ፖለቲካዊ ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ) ጉዳዮች በጥምረት ለመፍታት የተዘጋጀ አለመሆኑ። እናት ፓርቲን እንዲመሰረት አስገድዷል፣ ይላሉ በምስረታ ላይ ያሉ ወገኖቻችን ።

በእዚሁ ፍፁም ዲሞክራሲያዊ እና የመስራች ጠቅላላ ጉባኤው አባላት በንቃት እንደተሳተፉበት በተነገረው ስብሰባ ላይ አሁን ላሉት የፓርቲው መዋቅሮች ከቀረቡለት ዕጩዎች ክዚህ በታች የተዘረዘሩትን የመስራች ጉባኤው ተሳታፊዎች  መምረጣቸውን ጉዳያችን ከአዲስ አበባ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።በእዚህም መሰረት የፅህፈት ቤት አባላት  –

ተጨማሪ ያንብቡ:  ደብረማርቆስ አዳማ እና ቁጫ ሰኔ አንድ ቀን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች ይካሄዱባቸዋል።

1)  የፓርቲው ፕሬዝዳንት =       ዶ/ር ኃይለየሱስ ሙሉቀን
2)  የፓርቲው ም/ፕሬዝዳንት =  ዶ/ር ሰይፈ ስላሴ አያሌው እና
3) የፓቲው ጠቅላይ ፀሐፊ =  አቶ ጌትነት ወርቁ የተመረጡ ሲሆን እንደ ቅደም ተከተላቸው በደረጃ ተለያይቶ ነገር ግን ሁሉም ከ400 በላይ ድምፅ አግኝተዋል።

በእናት ፓርቲ መስራች ጉባኤ ላይ ከተሳተፉት በከፊል 

በእዚህም መሰረት የፕሬዝዳንቱ፣ም/ፕሬዝዳንቱ እና ፀሐፊው የትምህርት እና የስራ ልምድ ሁኔታ በአጭሩ እንደሚከተለው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

1)ፕሬዚዳንት፡-  ኃይለኢየሱስ ሙሉቀን (ፒኤችዲ)

 ዶ/ር ኃይለኢየሱስ፣ የመጀመሪያ ድግሪ በፖለቲካል ሳይንስ ተመርቀዋል፡፡
 2ኛ ድግሪ peace and security ተምረዋል፡፡
 3ኛ ድግሪ peace and security ተምረዋል፡
 በፓለቲካል ሳይንስ በመምህርነት፣ በተመራማሪ እና በማማከር ሠርተዋል፡፡
 በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ተዘዋውረው አስተምረዋል፡፡
 አትራፊ ባለሆነ ድርጅት በሓለፊነት ጭምር ሠርተዋል፡፡
 አሁን በሓላፊነት፣ በማስተማርና በምርምር ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ፡፡
2) ም/ፕሬዚዳንት፡- ሰይፈሥላሴ አያሌው (ፒችዲ)

 ዶ/ር ሰይፈሥላሴ፣የመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ በኢኮኖሚክስ ተምረዋል፡፡
 3ኛ ድግሪ በኢኮኖሚክስ ሠርተዋል፡፡
 በኢንፎርሜሽንና ኮምኒኬሽን፣ ፕሮግራሚንግ ዓለምአቀፍ ሥልጠናዎችን ወስደዋል፡፡
 GPS ማጎልበትና ማላመድ ሥራ ሠርተው በማጠናቀቅ ላይ ይገኛሉ፡፡
 በተለያዩ ተቋማት በሓላፊነትና በኢክስፐርትነት ሠርተዋል፡፡
 በአሁኑ ወቅት  “መሪ” የሚባል የ GPS ዘዴን ለሀገራቸው አስተዋውቀዋል፡፡
 አሁን GPS እና Navigation company በመክፈት እየመሩ ይገኛሉ፡፡

3)  ጠቅላይ ጸሐፊ፡-  አቶ ጌትነት ወርቁ

 አቶ ጌትነት፣የመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ በሒሳብ ተመርቀዋል፡፡
 ሁለተኛ ድግሪ በኢኮኖሚክስ ተምረዋል፡፡
 በግልና መንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማስተማር በምርምር ሠርተዋል፡፡
 በግል ተቋማት በሓላፊነትና በኢክስፐርትነት ሠርተዋል፡፡
 አሁንም በማስተማር ምርምርና ሓላፊነት እየሠሩ ይገኛሉ፡፡

የሕግ ስርዓት ጉዳዮች  ሆነው የተመረጡ –

ተጨማሪ ያንብቡ:  ምሽት 12፡00 ዜና ሙዳይ ባሕር ዳር፡ ሕዳር 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ)

1)  አቶ ሰለሞን (በአንደኝነት) እና

2)  አቶ ለሜሳ (በሁለተኛነት)

ሂሳብ ክዋኔ ኦዲት

1)  ኢንጅነር ዓቢይ (በአንደኝነት)
2)  አቶ ተመስገን (በሁለተኛነት)

ለሥራ አስፈፃሚ አባልነት የሚከተሉት ተመርጠዋል።

1)   አቶ ፍሬው፣
2)  አቶ ኪሮስ፣
3) አቶ አበበ፣
4) አቶ ማቲያስ፣
5)  መምህር ሳሙኤል፣
6)  ወ/ት ዓለም፣
7)  አቶ ታከለ፣
8)  አቶ ዓይነሰው፣
9)  አቶ ሰለሞን፣

መስራች ጉባኤው ላይ ለመሳተፍ በማለዳ የተገኙ ብዙ ነበሩ።ከአዲስ አበባ ውጪ የተወከሉም እንዲሁ።
 

ለፓርቲው የላዕላይ ምክር ቤት የሚከተሉት ተመርጠዋል። እነርሱም  –

1)  ዶ/ር መሰሉ፣
2)   ወ/ት አስማሩ፣
3)   ዶ/ር ታመነ፣
4)   ዶ/ር ናሁ ሰናይ፣
5)   ዶ/ር ወንድወሰን፣
6)   አቶ መኩርያ፣
7)   ኢንጅነር ማቲያስ፣
8)   አቶ ጌታሰው፣
9)    አቶ ብርሃኑ፣
10)  ወ/ት ጉዳዩ፣
11)  አቶ ሮቤል፣
12)  አቶ ካሳሁን፣
13)  አቶ አሰፋ፣
14)  ወ/ት ናሆሚ፣
15)  ኢንጅነር ደሳለኝ፣
16)  አቶ ተመስገን፣
17) ወ/ሮ ሜሮን  ሆነው ተመርጠዋል።

እናት ፓርቲ በዛሬው የመስራች ስብሰባ ላይ በዋናነት የመጠፋፋት ፖለቲካ በኢትዮጵያ ዳግም እንዳያንሰራራ እና ላለፉት ዓመታት በኢትዮጵያ የኖረው ህዝብን ከህዝብ የሚከፋፋል ”የእኛ እና የእነርሱ” የሚሉት የፖለቲካ አካሄዶች እንዲያበቃ እንደሚሰራ ተወስቷል።

በመጨረሻም ተመራጮች  በሙሉ በታማኝነት እና በትጋት እንደሚያገለግሉ እና የተጣለባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ ቃል ገብተዋል። (ከስር ቪድዮውን ይመልከቱ)

ጉዳያችን ሚድያ፣ኮሚኒኬሽን እና ምክር አገልግሎት 
Gudayachn Multimedia, Communication and Consultant

2 Comments

  1. ጎሽ! ሀገራችንን የፓርቲ ድርቅ መትቷት ሥቃይ ላይ ሳለች ነው አዲሱ እናት ፕርቲ በነፍስ የደረሰላት። ወላድ በድባብ ትሂድ! ደግሞ ፓርቲ ለመመሥረት።
    እኔም “በ1980 ከአ.አ.ዩንቨርስቲ በህግ ትምህርት የተመረቁ የአሁን ወጣት መሣይ ሽማግሌዎች ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ” የሚል አዲስ የፓለቲካ ፓርቲ ለመመሥረት መነሣቴን በዚህ አጋጣሚ ማሣወቅ እፈልጋለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share