ሰሞኑን የአባይን ግድብ አስመልክቶ አሜሪካ በአደራዳሪነት ጣልቃ በመግባት ኢትዮጵያ ላይ ጫና እያደረገች እንደሆነ በሰፊው እየተወራ ነው፡፡ እኔ ጉዳዩን በጥልቀት አልተከታተልኩትም፡፡ ሆኖም ከዚህ በፊት በተመሳሳይ ድርድርድር ወይም የፍትህ ጥያቄ ብዙ የታዘብኩት ነገር አለ፡፡ በአሁኑ ወቅት የአባይን ግድብ አስመልክቶ እየተካሄደ ያለው ድርድር ብዙ ደስ የማይል ነገሩ ይበዛል፡፡ በእኔ ምልከታ የአባይ ግድብ ጉዳይ በሁለቱም አገራት በኩል የሆነ የፖለቲካ ቁማር ያለ ነው የሚመስለኝ፡፡ ግብጽ በኩልም ከውስጥ ያለበትን የፖለቲካ ችግር የሕዝብን ትኩረት ወደ አባይ ለማዞር እንደሚሰራ እታዘባለሁ፡፡ ይሄን ከራሳቸው ከአንዳንድ ግብጻውያንም ሰምቻለሁ፡፡ በኢትዮጵያም በኩል ይሄው አይነት ቁማር ነው ያለ የሚመስለው፡፡
አባይንም ሆነ ሌሎች ሀብቶችን በጋራ መጠቀም የሚያስችሉ ብዙ እቅዶችን በጋራ መሥራት ላይ ትኩረት ከማረግ ይልቅ ነገሮችን ትልቅ ጽንፍ እንዲይዙ በማድረግ የራሳቸውን ድክመት መሸፈኛ እያደረጉት ይመስላል፡፡ አባይ በሰከንድ 2349ሜትር ኩዩቢክ ውሃ የሚተፋ ታላቅ ወንዝ ነው፡፡ እኔ ግድቡ የተከደበበት ቦታ ላይ የሚፈሰውን አባይ አይቼዋለሁ፡፡ ብዙዎች አባይን የሚያውቁት ወደጎጃም ሲሻገሩ ነው፡፡ አባይ ግን እሱ አደለም፡፡ ዳቡስና ዴዴሳ በለስ ከተቀላቀሉ በኋላ ያለውን አባይ የታዘብ የአባይን ታላቅነት ያስተውላል፡፡ እንግዲህ በሰከንድ 2300 ሜትርኩቢክ ውሃ ቢሰጥ ብለን ብናስብና የተባለው ግድብ የጣናን ሁለት እጥፍ ቢሆን ብለን ብናስብና ብናሰላው የሚከተለውን እናገኛለን፡፡ የጣና ስፋት 2156ኪ.ሜትር ስኩዌይር ይገመታል ጥልቀቱ ደግሞ 9ሜትር፡፡ ጥልቀቱን 10 ሜትር እንድርገውና የያዘውን ውሄ ሙሉ ቢሆን 21,560,000,000 (ሃያ አንድ ቢሊየን አምስት መቶ ስድሳ ሚሊየን) ሜትርኩቢክ ውሃ መሆኑ ነው፡፡ ልብ በሉ ይሄ ጣና ሙሉ ከሆነ ነው፡፡ የጣና ሁለት እጥፍ ማለት እንግዲህ በዚህ ስሌት 43,120,000,000 (አርባ ሶስት ቢሊየን አንድ መቶ ሃያ ሚሊየን) ሜትር ኩቢክ ውያ ማለት ነው፡፡ እንግዲህ አባይ በሰከንድ 2300 ሜትርኩዩቢክ ውሃ ከሰጠ በሰዓት 8280000 (ስምንት ሚሊየን ሁለት መቶ ሰማኒያ ሺ) በቀን ደግሞ 198720000 (አንድ መቶ ዘጠና ስምነት ሚሊየን ሰባት መቶ ሃያ ሺ) ሜትር ኩዩቢክ ውሃ መስጠቱ ነው፡፡ በዚህ ስሌት ጣና የአባይን ግድብ ለመሙላት 217 ቀን ብቻ ይፈጅበታል፡፡
ከላይ የሳየሁት አባይ ሙሉ በሙሉ ወደግድቡ ቢመለስ ማለት ነው፡፡ ሆኖም አንድን ወንዝብ ሙሉበሉ መገደብ ሊያውም እንደ አባይ ያለ የብዙዎች ሕወት የሆነ በሕግም በሞራልም ስለማይቻል በአግባቡ የተወሰነው ወደግድቡ ማፍሰስና ሌላውን በመንገዱ እንዲቀጥል ማድረግ ነው፡፡ የአባይን አንድ አራተኛ ውሀ ግድቡ እስኪሞላ ወደግድቡ እንዲፈስ ቢደረግ ግድቡን ለመሙላት 868 ቀናት ገደማ ወይም ሁለት ዓመት ከሶስት ወር ገደማ ይፈጃል፡፡ ይህ በደረቅ ስሌት ሲሆን በትነትና በሌሎች ምክነያት የሚባክን ወሃ ቢታሰብ ከሶስት ዓመት ባልበለጠ ጊዜ የአባይን ግድብ መሙላት ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በክረምት ወራት ወደግድቡ የሚፈሰውን ወሃ ማብዛት ነው፡፡ አንዴ ውሃው ከሞላ በትነትና በሌሎች የሚባክንን ለማስተካከል ካልሆነ አባይ ሙሉ በሙሉ ወደ ታች አገራት መፍሰሱ ይቀጥላል፡፡ ይሄ እንግዲህ ግድቡን ሙሉ በሙሉ በአንድ ጊዜ ለመሙላት ከታሰበ ነው፡፡ ሆኖም ግድቡን ሙሉ በሙሉ ሳይሞላ በፊት ኃይል በሚሰጥበት ደረጃ ከተሞላ በኋላ ቀሪው እንደ አስፈላጊነቱ ሊሞላ ይችል ይሆናል፡፡ የግድቡ የውሃ አጠቃቀም እቅድ ስለማላውቅ ይሄን በትክክል መናገር አልችልም፡፡
እንግዲህ ግብጽ በዚህ የማትስማማ ከሆነ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች ይሄን ማሳመን ካልቻሉ ችግሩ ከዚህ ውጭ በሆነ ጉዳይ ላይ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ነው፡፡ ሰሞኑን የምሰማው አሜሪክ ኢትዮጵያን አስገድዳ ለግብጽ ወግና ልታስፈርም ነው የሚል ነው፡፡ አንዳንዶች ግድቡ በ20ና 30 ዓመት እንዲሞላ ነው እቅዱ የሚሉም አሉ፡፡ ይሄ ሁሉ ከተባለ ድክመቱ ማን ጋር እንደሆነ ታዘቡ፡፡ ግማሾች የአሜሪካውን ፕሬዘደንት ትረምፕን ሊከሱ ይሞክራሉ፡፡ ትረምፕ በአገራቸው ጉዳይ ጠንካራ አቋም ያላቸውን መሪዎች የሚደግፉና በዚህም ለአገሩ ባለው አቋም ለሚበልጠው ሊያደሉ እንደሚችሉ አይካድም፡፡ ስለዚህ እዚህ ጋር ያለው ድክመት ምን እንደሆነ ታዘቡ፡፡ የትረምፕ አስተዳደር ከየትቹም ከኃይለስላሴ ዘመን በኋላ ከመጡ መሪዎች ለኢትዮጵያ መልካም አጋጣሚ የሚፈትር ነው ብይ አምናለሁ፡፡ ሆኖም በተንሸዋረረና የትረምፕን አስተዳደር በጅምላ በሚነዳ ወሬ ባለማስተዋል ለብዙ ኢትዮጵያውያን ይሄ አይታያቸውም፡፡ ተረምፕ ያችን አገር የዳንኳት እኔ ነኝ ሲል ያለምክነያት ይመስላቸዋል፡፡ እውነታው አሁን ያለውን የኢትዮጵያ ሁኔታ በትኩረት እየተከታተለ ያለ መንግስት አለ ከተባለ የአሜሪካ መንግስት ነው፡፡ አውሮፓውያን የዛን ያህል ትኩረት የሚሰጡን አደለም፡፡ እርግጥ ነው የአሁኑ አመሪካ መንግስት አሁን ያለው የኢትዮጵያ ሁኔታ አያስደስተውም፡፡ ለኢትዮጵያ ግን ከማንኛውም ከቀደሙት ይልቅ የትረምፕ አስተዳደር ቀና እንደሆነና በዚህ ወቅት አጋጣሚውን መጠቀም የሚችል አካል ቢኖር ትልቅ ሥራ ሊሰራ ይችል ነበር፡፡ ትረምፕ ከቀደሙት መሪዎች በተለይ ከፖለቲካዊ አካሄድ ይልቅ ተግባርና ውሳኔ ላይ ያተኮረ አስተዳደርን በአገሩ የመሠረተ ነው፡፡ ይሄ ለብዙዎች ከጠበቁት በላይ ሲሆንባቸው በአገሪቱ በተፎካሪነት ለሚገኙ የዲሞክራት መሪዎች ሳይቀር እጅግ ፈተና ሆኖባቸዋል፡፡ ትረምፕ ለዘመናት ቁማር የነበሩ የዓለም የሽብር ቡድኖችን ከምድር ገፅ እያጠፋ ሲሆን በየአገሩ የሚነሱ ግጭቶችንም እያከሰማቸው ነው፡፡ በእነ ኦባማ ዘምን በየቦታው ተፈጥረውና ተስፋፍተው የነበሩ የሽብር ቡድኖች ዛሬ ይት ናቸው? አይሲስ የት ነው? ቦኮ ሀራም፣ አልሸባብ፡፡ የእነዚህና ሌሎች በየአገራቱ የሚነሱ ግጭቶች ዋና የገንዘብ ምንጭ የቁማርተኛ ፖለቲኞች ሴራ ስለነበር ትረምፕ ዛሬ ያ እንዲነጥፍ አድርጎታል፡፡ የሽብር መሪዎችንም እያደነ ማጽዳትን ይዟል፡፡ የሶሪያ እልቂት ዛሬ እየተስተካከለ ነው፡፡ ሌሎችም እንደዛው፡፡ እንግዲህ የዛሬው የትረምፕ አስተዳደር ለሚጠቀምበት እጅግ ወሳኝ የሆነ ምዕራፍ ነው፡፡ ኢትዮጵያም የዚህ አጋጣሚ ተጠቃሚ ልትሆን የምትችልበት እድል ነበር፡፡ የትረምፕ ልጅ ኢቫንካ ኢትዮጵያ ድረስ የሄደቸው፡፡ የጫማ ፋብሪካ ለመገንባት አስባም የነበረው ያለምክነያት አልነበረም፡፡ ብዙ ነገር አቅም እንዳል አስተውላ ነበር፡፡ ከምንም በላይ ግን ስነምግባርን ነው፡፡ በታሪክ ትልቅ ሞገስ ያለው ስነምግባር ነበረን፡፡ ዛሬ ግን ለይቶልን አሳፋሪ ሆነናል፡፡
ወገኖቼ ኢትዮጵያውያን የራሳችንን ድክመት በሌሎች እያመካኘን ጊዜያችን አናባክን፡፡
ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይጠብቅ! አሜን!