አነጋጋሪው ሰባተኛው ንጉሣችን አቢይ አህመድ ዘብሔረ ኦሮሚያ – ግርማ በላይ

ግርማ በላይ (gb5214@gmail.com) ዳንሳ

ይህችን ማስታወሻ ልጫጭር ስነሳ በቅድሚያ ስለውሸትና ውሸታሞች ጥቂት ነገር ለመዳሰስ ሞከርኩ፡፡ እንዲህ ያደረግሁት የአቢይ አህመድን ውሸታምነት ለመፈረጅ በመቸገሬ ነው፡፡ በሥነ ልቦናው ዘርፍ እንደሚታወቀው Pathological liar እንዳልለው የአቢይ ውሸት ዓላማና ግብ ያለው በመሆኑ በዚያ ስም መፈረጅ ከበድ አለኝ፡፡ የመዋሸት ሥነ ልቦናዊ ደዌ የተጠናወተው ሰው አለ ተጨባጭ ምክንያት ይዋሻልና ከአቢይ ዓይነቱ ቦጥራቃ ውሸታም ለየት የሚል ይመስለኛል፡፡ የሚመሳሰሉበት አጋጣሚም ሊኖር ይችላል፡፡ አንዳንዴ ተሰሚነትን ወይም ተደማጭነትን ለማግኘትም ሲባል ሰዎች ከሜዳ ተነስተው ያለ በቂ ምክንያት ሊዋሹ ይችላሉ፡፡ “attention seekers” ብዙውን ጊዜ በዚህ ይታማሉ፡፡

በመሠረቱ መዋሸት አንደኛው መጥፎ የሰው ባሕርይ ነው፡፡ መዋሸት ወንጀልም ኃጢኣትም መሆኑን ብናውቅም ለተለያዩ ዓላማዎች የምንዋሽ ሰዎች አለን፡፡ “እኔ በፍጹም አልዋሽም” የሚል ሰው ካለ እርሱ የመጨረሻው ጉረኛ ነው፡፡ ይነስም ይብዛም እንዋሻለን – ለውሸታችን ግን ምክንያት ልንሰጥ እንችላለን፡፡ “ሰውን ከሰው ላለማጣላት፤ ሰውን ለማስታረቅ፣ የሰው ስሜት ላለመጉዳት፣ ሥራየን ላለማጣት፣ ላለመቀጣት፣…” ወዘተ. የመሳሰሉ ሰበቦችን እየሰጠን ለውሸታችን ቅድስና ልንሰጥ ብንዳዳም ውሸት ያው ውሸት ነውና ዞሮ ዞሮ ስንተኛ ስለቀኑ ውሸታችን መጨነቃችን አይቀርም – ኅሊና አለን የምንል ወገኖች ለዚያውም፡፡ ኅሊናቢሶች ግን መተዳደሪያቸው ውሸት ራሱ ነውና ሲዋሹ አድረው ሲዋሹ ቢውሉ ጉዳያቸው አይደለም – እንደ ዶክተር አቢይ ያሉት ቆርጦ ቀጥሎች፡፡ ግን ታድለው!

ስለውሸት ዳሰሳ ሳደርግ አንድ ጠቃሚ ጽሑፍ አገኘሁ፡፡ ይህ ጽሑፍ ውሸትንና ውሸታምነትን በሰባት ቦታ መድቦ እንደሚከተለው ያስቀምጠዋል፡፡ ማን ወደየትኛው እንደሚያዘነብል መርምሩ፡፡

  1. Error—a lie by mistake. The person believes they are being truthful, but what they are saying is not true.
  2. Omission – leaving out relevant information. Easier and least risky. It doesn’t involve inventing any stories. It is passive deception and         less guilt is involved.
  3. Restructuring—distorting the context. Saying something in sarcasm, changing the characters, or altering the scene.
  4. Denial—refusing to acknowledge a truth. The extent of denial can be quite    large— they may be lying only to you just this one time or they     may be lying to themselves.
  5. Minimization—reducing the effects of a mistake, a fault, or a judgment call.
  6. Exaggeration—representing as greater, better, more experienced, more successful.
  7. Fabrication—deliberately inventing a false story.
ተጨማሪ ያንብቡ:  ታዋቂነት እኮ ሁሉን ማወቅ ማለት አይደለም! - ጠገናው ጎሹ

ሀሰትን መናገር ፈጣሪ አምርሮ ከሚጠየፋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱና ዋናው ነው፡፡ ማስረጃችንም አሠርቱ ትዕዛዛት ውስጥ ስምንተኛው ትዕዛዝ “በሀሰት አትመስክር” የሚለው ነው፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለሀሰት ንግግር መጥፎነትና ኃጢኣትነት በብዙ ቦታዎች ተጠቅሷል፡፡ እነአቢይና ወንድሙ እስራኤል ዳንሳ ግን ምድባቸው ከሌላ በመሆኑ እውነትን ሲረመርሙና ሀሰትን ሲያነግሡ በዚህ ጠያፍ ተግባራቸው ይኮሩበታል – እንጀራም ይበሉበታል – ቆሻሻ ዝናም ያተርፉበታል እንጂ አያፍሩበትም፡፡ ጊዜው በክርስቶስ ላይ የሚቀለድበት ሆነና የአቢይ ዲቃሎች እነእዩ ጩፋ ሴኔኒዝምን በግልጽ የሚያስፋፉበት ሆነ፡፡

ለወትሮው ሀሰትን የሚናገር ሰው በቀላሉ ይታወቃል፡፡ ከፊት ገጽታው፣ ከሰውነት እንቅስቃሴውና ከአንደበቱ መርበትበት ማወቅ ይቻላል፡፡ እንዲህ የሚሆነው ግን ውሸታሙ ሰው ብዙ የመዋሸት ልምድ ከሌለው ነው፡፡ እንደ አቢይ ዓይነቱ የፍየል ዐይን በጨው ቀቅሎ የበላ ከሆነ ግን ራሱ በገደለው ሬሣ ላይ ቀብር ተገኝቶ ፊቱን በባና ቢነጭ አምኖት አብሮት የሚያለቅስ አያጣም፡፡ በሀገራችን እየሆነ ያለውም ይሄው ነው፡፡ ደግነቱ አሁን አሁን ለመድነው እንጂ አቢይ ሲዋሽ ልናውቅበት የሚያስችለን አንደበታዊም ሆነ ዐይነ ውኃዊ ፍንጭ የነበረን ለመሆናችን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ያገሬ ገበሬ ይህን ዓይነቱን ሰው “ኮኬ!” ይለዋል፡፡ እውነቴን ነው የምለው እኔ ልዋሽ ብል ከንፈሬ ይደርቃል፣ ትናጋየ ይለጎማል በብርድ ቆፈናም ወቅት ሳይቀር ነጭ ላብ ያልበኛል፡፡ ተፈጥሮ ለአንዱ ሌላ ለሌላው ደግሞ ሌላ ናት፡፡ መዋሸትም ቁም ነገር ሆኖ ከአቢይ ለየችኝ – ይቺ በአድልዖ የተመላች የማትረባ ተፈጥሮ! አፈር ደቼ ትብላ፡፡

ለማንኛውም ከአቢይ ውሸቶች መካከል ጥቂቶቹን ለአብነት ያህል ላስታውስና ልሰናበት፡፡

  1. ኢንጂነር ስመኘው ራሱን መግደያ ቦታ አጥቶ መስቀል አደባባይ ላይ ተገድሎ ሲገኝ አቢይ ከውጭ መጥቶ ኢንጂነሩ ራሱን በራሱ እንደገደለ በሚዲያ ተናገረ፡፡ አንድ በሉ፡፡
  2. የተወሰኑ ወታደሮች ወደ ቤተ መንግሥት ሄደው “ፑሻፕ” አሰርቷቸው ሲያሰናብታቸው ለሆነ ጥያቄ እንደመጡ ከተናገረ በኋላ ትንሽ ቆይቶና ሁኔታዎች ሲረጋጉ ለመፈንቅለ መንግሥት እንደተላኩ ተናገረ፡፡ ይህ አይደለም ዋናው ነገር፡፡ በወቅቱ የመፈንቅለ መንግሥቱን ዜና ለሕዝብ ለምን ይፋ እንዳላደረገ ሲጠየቅ እጅግ የሚገርም መልስ ነበር የሰጠው፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አፍንጫው ሥር የነበርን ሰዎች ምንም ሳንሰማ “የሰላሌና የሸኖ፣ የባሌና የበደኖ ኦሮሞ ፈረስ ጭኖ፣ ጋሻ ወድሮና ጦር ሰብቆ እየመጣ እንዴት ብዬ ሰውን ላስጨርስ ብዬ እምቅ አድርጌ በሆዴ ችዬ ሳልናገር ተውኩት” ብሎ ጥቂት ብልኆችን በሣቅ ገደለ፡፡ ያኔ በወረት ፍቅር ስለነበርን ጉዳዩን ከቁም ነገር ሳንጥፍ አሳለፍነው፡፡ የሚገርም ቲያትረኛ ነው፡፡ ከተሜው ሳይሰማ ገጠሬው መስማቱ አጃኢብ ያሰኛል፡፡ ከዋሹ አይቀር ደ’ሞ እንዲህ ነው፡፡ ሁለት በሉ፡፡
  3. በአንድ ስብሰባ ላይ ስለኦሮሞ ሁሉንም የሀገር ሥልጣን ለብቻ መቆጣጠር ሲጠየቅ “በኔ የሥልጣን ዘመን ኦሮሞ የተለዬ ጥቅም አግኝቶ ከሆነ ሥልጣኔን በ24 ሰዓት እለቃለሁ” በማለት በሕዝብና በሀገር ላይ ተዘባበተ፡፡ ከነደረጀ የበለጠ ኮሜዲያን አይደል? ሦስት በሉ፡፡
  4. አዲስ አበባ አካባቢ የተሾሙ የኦሮሞ ባለሥልጣናት አማራውንና ደቡቡን ከየመኖሪያው እየመነጠሩ ሲያባርሩና ሲያፈናቅሉ አጅሬ አውቆ እንዳላወቀ “አልሰማሁም” አለ፡፡ በቡራዩና በለገጣፎ ጋሞዎችና አማሮች በአክራሪ ኦሮሞዎች ሲያልቁ፣ የአዲስ አበባ መሬት በቄሮዎች እንደልብ ሲዘረፍ፣ ድሆች ከመናኛ ገቢያቸው አጠራቅመው ያሠሩት ኮንዶምንየም በነጃዋር ልጆች በጠራራ ፀሐይ ሲቀማ … በቺንዋ አቼቤ አገላለጽ a man of the people አቢይ አህመድ አሊ “አልሰምቼም” አለ፡፡ ተበዳዮች ወደርሱ ሄደው አቤት ቢሉ “ይህ ጉዳይ ክልሉን እንጂ እኔን አይመለከትም” በማለት አበሻቅጦ አባረራቸው፡፡ የሕዝቡ ሰው መልኩ ሁለት ነው – አንዱ ለታይታ የሚቅለሰለስ ሌላው የክቱ ጊንጣዊ ዐመል፡፡ ለማንኛውም አራት በሉ፡፡
  5. ሰኔ 15/2011 ባህር ዳር ላይ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ የአማራ ባለሥልጣናትና የፌዴራል ጄኔራሎች ግድያ ከመፈጸሙ በደቂቃዎች ልዩነት በፋቲክ ልብስ ቲቪ ላይ ቀርቦ “በአማራ መንግሥት መፈንቅለ መንግሥት ተካሄደ” በማለት አንጀቱ ለጋ ቅቤ ጠጥቶ በፊት ገጽታው ግን እጅግ ያዘነ በመምሰል ለምቦጩን ጥሎ ዐወጀ፡፡ ኦፕሬሽኑ የተካሄደው በርሱ አመራር መሆኑ አለባበሱና ከመብረቅ የፈጠነ የዕለት እንቅስቃሴው አፍ አውጥቶ ይናገር ነበር፡፡ ከዚያ በኋላ የሚታየው የአማራው አካባቢ ድንዙዙ እንቅስቃሴም የዚያው ኦፕሬሽን ታሳቢ ውጤት ፤መሆኑ አፍ ቢክደው የማንም ኅሊና አይስተውም፡፡ ራሱ አቅዶ ራሱ ባከናወነው ግድያ ሰበብም ንጹሓን ዜጎች በተለይም ከጉዳዩ ጋር በአጋምም በቀጋም የማይገናኙ የአብን አመራሮችና አባሎች ታስረው እስካሁንም እየተሰቃዩ ነው፡፡ አምስት በሉ፡፡
  6. የታገቱት የአማራ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከእገታው እንደተለቀቁ ከአንዴም ሁለቴ በቃል አቀባዩ አማካይነት እንዲነገር አደረገ፡፡ ውሸታም መዋሸቱን እንጂ የውሸቱ ውጤት ምን ይሁን ምን ማሰብ አይፈልግምና ልጆቹ ግና እስካሁንም የት እንዳሉ አይታወቅም፡፡ … ማለቂያ ስለሌለውና መጠነኛ የዳሰሳ ጥናትም ስለሚያስፈልግ ወደሰሞኑ ልምጣ፡፡ ግን ውሸታም ካልሆኑ ለካንስ መንግሥት አይኮንም?
  7. በነዚህ ሁለት ቀናት ይህ ጎበዝ ቲያትረኛ ወደ ዐረቡ ዓለም ጎራ ብሎ የተለመደ አፍዝ አደንግዙን በማሳደስ ላይ ይገኛል፡፡ ለወትሮ መተት የሚታደሰው ጳጉሜ አምስት ወይም ስድስት መስከረም ከመግባቱ ትንሽ ቀደም ብሎ ነበር – ባዲሱ ዓመት መባቻ እንዳይሽር ወይም እንዳይከሽፍ፡፡ አትርሱኝ ባዩ አጅሬም ሕዝብን በማስጨብጨብ የተለመደ ደንቃራውን ሊጥል ወጣ ብሏል፡፡ ሰሞኑን ሰዎች ቀድመው ያበሰሉትን እንጀራ ከምጣዱ በማውጣት ራሱ አቡክቶ እንደጋገረው ሀፍረትን በማያውቀው አንደበቱ እየወሻከተ ነው፡፡ የድል አጥቢያ አርበኛው አቢይ በሰው ደንደስ መወደስን ሥራየ ብሎ ተያይዞታል፡፡ ይሁን ግዴለም፡፡ ግን ስለ ጄኔራል አሣምነው ጽጌ ሲጠየቅ የሰጠው መልስ ብዙ ትችቶችን እያጎረፈበት ነው፡፡ አቻምየለህ ታምሩ እንደጻፈው ከሆነ አሣምነው ሲፈታ አቢይ ማንም የማያውቀው ድብቁ ሰባተኛ ንጉሥ ነበር፡፡ አቢይ ሥልጣን እንደያዘ ሣምንት ሳይሞላው አሣምነውን እንዳስፈታ በሀሰት ቢመሰክርም በአሣምነው መፈተታትና በአቢይ መሾም መካከል የቀደመ የአንድ ወር ከ14 ቀን ጊዜ እንደነበረ የሚያውቁ እየመሰከሩ ነው፡፡ ዐይነ ፈጣጣው አቢይ ግን ሰውን ከመጤፍ ስለማይቆጥር ይህንን ገሃድ እውነትም ሽምጥጥ አድርጎ ይዋሻል፡፡ ስድስት በሉ፡፡
  8. አሁን በቅርቡ ዘሀበሻ ዩቲዩብን ስመለከት ደግሞ አቢይ የመሪዎችን የውሸታምነት ሪከርድ የበጠሰበትን አስገራሚ ነገር ሰማሁ፡፡ እሱም ሰልፊና ሱኒ የሚባሉ ሙስሊሞች በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ መስጊድ የሰገዱት በእርሱ ሽምግልናና እርሱ አመጣሁት ብሎ ከሚኩራራበት ለውጥ በኋላ መሆኑን አንዳችም ሳያፍር ተናገረ፡፡ ሳዲቅ አህመድና አንድ ሌላ ታዋቂ ሙስሊም እንደተናገሩት ይህ የአቢይ ንግግር ነጭ ውሸት ነው፡፡ ለምን እስከዚህን እንደሚወርድ ለማንም ግልጽ አይደለም፡፡ ከዚህኛው ውሸቱ አኳያ የሥነ ልቦና ችግር እንዳለበት መረዳት አይከብድም፡፡ ስለዚህም የህክምና ዕርዳታ ያስፈልገዋል፡፡
  9. ለወደፊቱ እነዚህን ውሸቶች ከአቢይ እንጠብቅ፡፡
    • ቀንና ሌሊት የሚፈራቁት በርሱ ፈቃድ ብቻ እንደሆነ
    • ምድርን ያለካስማ የዘረጋው፣ ሰማይን ያለባላ ያቆመው እርሱ እንደሆነ
    • ኢትዮጵያውያን ያለርሱ ፈቃድ መውለድ አይደለም መሞትም እንደማይችሉ
ተጨማሪ ያንብቡ:  " የሚሰማ ጆሮ ያለው የሰማል ። የማይሰማም አይሰማም ። ዓዋቂ ሰውም  ጥፋትን  እያየ " ዝም አይልም ! " መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

“ዕድሜ ለጓድ ናፖሊዮን፣ በርሳቸው አብዮታዊ አመራር በሣምንት ሦስት ዕንቁላሎችን ከመጣል ስድስት ዕንቁላሎች ወደ መጣል ከፍ ብያለሁ” ነበር ያለችው ያቺ በጆርጅ ኦርዌል ምናብ ተፈጥራ “Animal Farm” በሚባል መጽሐፍ ውስጥ የምትገኝ ዶሮ?

“The truth always comes out in the end, no matter how hard anyone tries to hide it or stop it. Lies are just a temporary delay to the inevitable.” (Anonymous)

“The trust of the innocent is the liar’s most useful tool.”  (Stephen King)

 

5 Comments

  1. በአለማችን ላይ የማይዋሽ መንግሥት የለም። ግለሰብ ይዋሻል፤ ሰባኪው ይዋሻል፤ ሃኪሙ ይዋሻል ሁሉም ይዋሻል። ውሸትና የሰው ልጅ ተለያይተው አያውቁም። አሁን ኢትዮጵያ ባለችበት የፓለቲካ እሰጣ ገባም ሆነ ያለፈው ታሪካችን በያዘው ጥለፈው የተቃመሰ እኔ ከእነዚያ እሻላለሁ በማለት የከፋን ያፈለቀ ታሪክ ነው ያለን። አሁን ከወያኔ ቋጠሮ አፈትልከው ሃገር ወዳድና አስደማሪ የሆኑት ጠ/ሚ አብይ ደግሞ የገጠማቸው ሃበሳ ብዙ ነው። ኦሮሞዎቹ አማራ አቅፎ እያደረ የኦሮሞን ህዝብ መብት ማስጠበቅ አይችልም ሲሉት፤ የቀድሞ የትግር አጋሮቹ ወያኔና ተለጣፊ ደርጅቶች ውስጥ የነበሩት ጠ/ሚሩን አፈር ለማልበስ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። ሶተኛ የፓለቲከኞች ሾትል ደግሞ በሚዲያ የተሳሳተና አልፎ አልፎም እውነት አዘል የሆነውን ወሬ እጅግ በማጋነን ተንኮልን የሚዘሩ የሙታን ስብስቦች ናቸው። ሰውን ገድለው አስከሬንና የአረድበትን ቢለዋ ሶሻል ሚዲያ ድህረ ገጾች ላይ የሚለጥፉትም ሰው ከሰው እንዲገዳደል ከተሰጣቸው ተልዕኮ ጋር የተገናዘብ ነው።
    ትላንት ክህግ ውጭ እልፍ ሰዎችን መቃብር ያወረደው ወያኔ አፉን ሞልቶ ህገ መንግሥቱ አልተከበረም፤ የሰዎች መብት ተገፏል የሚለን ራሱ ገርፎ ራሱ እንደሚጮኽው ጅራፍ ሆነው ነው። በመሰረቱ ወያኔ ሃገሪቱና የጠ/ሚሩ ስልጣን እንዲዳከም የማያደርጉት ሙከራ የለም። ሁሉም ነገር በይፋ ያልተገለጠበት ምክንያት በወያኔ የተነሳ የትግራይ ህዝብ በጅምላ እንዳይጠላ በማሰብ እንጂ የተንኮል ዶሲያቸው ሰፊ ነው። ግን የጠ/ሚ ህግን ለማስከበር አርጩሜ እንኳን አለማንሳት ብዙዎችን እንዳሳሰባቸው እንሰማለን። ከማሰብም አልፎ የሚያሳዝን ጉዳይ ለመሆኑ በየጊዜው በሃገሪቱ ውስጥ የሚፈጸሙት ወንጀሎች ያሳያሉ። ግን ሁኔታው የተበላሽው የክልል ልዪ ሃይል፤ የክልል ፓሊስ እየተባለ በተሰመረ የደንቆሮዎች የፓለቲካ ዜይቤ ነው። ሁሉ በዘሩና በቋንቋው ተሰላፊ በሆነበት ምድር ላይ ፍትህ ይኖራል ብሎ መገመት አብሮ መወስለት ነው። አዲስ አበባ ለኦሮሞዎች ብቻ የሚለው ተልካሻው የወያኔ የአስረሽ ምቺው ፓለቲካ ዛሬ ላይ የኦሮሞ ፓለቲከኞች አናት ላይ ወጥቶ ቤት ሲያስፈርስ፤ በእጣ የተገኘ የመኖሪያ ቤትን ሲቀማ፤ መጤ እያለ ሌላውን ሲገፋ ማየት የኦሮሞ ፓለቲካ ያለቅጥ ሸፋፋ እንደሆነ ያሳያል። በፈጠራ ታሪክ በአጼዎቹ ዘመን ተበድለናል የሚሉት እነዚህ የሙት ፓለቲከኞች ዛሬ ላይ የሰው አንገት በጠራራ ጸሃይ እንደ ከብት ሲታረድ ጎበዝ ይህ ነገር አይበጅም አላሉም። እንዲያውም በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ አበጃቹሁ የሚሉ ነው የሚመስሉት። በቀለ ገርባና ጃዋር የሚለፉት ብቻ ምን ያህል መማር ድንቁርና እንደሆነ ያሳያል። እነ ህዝቅየልና መራራ ያሉትም እይታቸው ለኦሮሞና ለራስ ብቻ በመሆኑ ብዙሃነትን እና አብሮ መኖርን በየቀኑ ከሚናገሩት እየናድት እንደሆነ እንሰማለን።
    እኔ ዶ/ር አብይን 7ኛው ንጉስ ወይም ዘብሄረ ኦሮሞ ብቻ አድርጎ መሳልም ተገቢ አይመስለኝም። ሰውን በሚዛን ላይ ለማስቀመጥና ለመመዘን መጀመሪያ የሚዛኑ ትክክለኛነት መረጋገጥ አለበት። በመሆኑም ከአለፉት የሃገሪቱ መሪዎች ጋር ሲነጣጠር ብዙ የተሻሉ እይታዎች ያለው መሪ ነው። ግን በኦሮሞና በክልል ፓለቲካ እየተናወጠ እንደሆነ ደግሞ ከላይ የተዘረዘሩት የፍትህ እጦትና የሰቆቃ ብዛት መረጃ ናቸው። ኢትዮጵያ ውስጥ ትላንትም ፍትህ የለም ዛሬም ፍትህ የለም። እንዲያውም ዛሬ የሚሰራበት አንዳንድ አሰራር ከወያኔ መጽሃፍ የተቀዳ ይመስላል። የታገቱት ተማሪዎች የት ደረሱ? በየክልሉ ሆያ ሆሄ የሚጫወቱት የክልል ፓለቲከኞችና የዘር ተቆርቋሪዎች ለምን የወለጋን መከራ አይገድቡም፤ ለምን አማራ ነኝ የሚለው ስብስብ በተለያዪ የሃገሪቱ ክፍል በቀንና በሌሊት ሰዎች ሲዘረፉ፤ ሲገደሉ ያን ለማቆም አይታገልም። ወያኔ መቀሌ ላይ መሽጎ ከተማዋን በፓለቲካ ስብሰባና መግለጫ ሲያጥለቀልቃት 27 ዓመት የት ነበሩ አሁን የትግራይ ህዝብ ለትግራይ ህዝብ የሚሉት ብሎ መጠየቅ የሚችል የትግራይ ህዝብ ተቆርቋሪ የጠፋው? ፓለቲካ የውሸተኞችና የገዳዮች ስብስብ ነው። ሌላም ምንም ትርጉም የለውም። ለመኖር ትገላለህ፤ ትዋሻለህ፤ ትሰርቃለህ። አሁን በሃገሪቱ ላይ ያለው የመጻፍ፤ የመናገር፤ የመሰብሰብ (በአመዛኙም ቢሆን) መብት መልካም ጅመራ ነው። ይህ ጅመራ ሌሎችንም የፍትህና የትምህርት የመከላከያ የመሳሰሉትን ተቋማት እንዲያጠናከር ለዶ/ር አብይ ድጋፍ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ይህ ሰው ከስልጣን ከወረደ ሌሎች ጭራቅን የበሉ ጭራቆች ከስልጣን ላይ ከወጡ በሃገሪቱ ላይ የሚከተለውን የመከራ ዶፍ ማሰፍ ያስፈልጋል። ለውጥ እናመጣለን ብለው ሃገራችን እንደፈራረሰው የዓረብ ሃገሮች አይነት ነው የሚሆነው። ስለሆነም የምናቀርባቸው ነቀፋቸውም ሆነ ድጋፍ እውነት ለበስ ሆነው ሚዛናዊነት እንዲኖራቸው ግድ ይላል። ሃገርን ዘርና ቋንቋን ሃይማኖትን ሳንደገፍ እንወዳለን የምንል ሰዎች የቡድን ፓለቲካን አክ እንትፍ በማለት ጠ/ሚሩ ፍትሃዊ እርምጃ በህዝባችን ላይ በደል በሚያደርሱ ማንኛውም ሃይሎች ላይ እንዲወስድ ማሳሰብ መልካም ነው። እይታችን ኢትዮጵያዊ፤ ሃገራችን በሁሉም፤ ቋንቋንችን የምናውቀውና የማናውቀውን ለመማር ዝግጅ ሆነን ከቀረብን የምድሪቱ የወደፊት እድል ፈንታ ቦግ ብሎ የሚታይ ይሆናል። በየጎጡ የሚውለበለቡ የጎሳና የክልል ፓለቲካዎች እንዲሁም የክልል አጥርና የሃይል አሰላለፍ እስካልተቀየረ ድረስ ሃገሪቱ ለህልውናዋ የሚያሰጓት ጭብጥ ነገሮች ይታዪኛል። የሃገሪቱም መፈራረስንም አይቀሬ ያደርገዋል። በመሆኑም በጠ/ሚሩ ላይ የስድብና የፓለቲካ አትካራ ከማውረዳችን በፊት እርሳቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽሙ ከእስራቸው እሳት የሚለኩሱትን የዘርና የጎሳ ፓለቲከኞ ደባ ማጋለጥ ተገቢ ይመስለኛል።

  2. አንዳንዴ ሳስበው እንዲህ ሆነን መቅረታችን እጅጉን ልብ ይሰብራል። እነ ጁዋር በግልጽ በሚፈነጩበት ሀገር፣ ወያኔ ዛሬ አርባአምስተኛውን የሙት አመቱን ፍሪዳ ጥሎ ዴሞክራሲ አገር ላይ ጠፋ እያለ በሚሳለቅበት ዘመን፣ አይምሮ ነበራቸው ያልናቸው እነመረራ ጉዲና ገለባ በሆኑበት ዘመን፣ ከልቡ ለናት አገር ፊቱ ከሰል እስኪመስል ድረስ የሚታክተውን ጠ/ሚር ማንጓጠጥ ምነኛ ያሳዝናል። በዚች ፈተና ጊዜ ፣ እስከ “ውሸቱ” አቢይ አህመድን የመሰለ ለኢትዮጵያ እፈልገዋለሁ። ሌላው ቢቀር እስከ ምርጫው እንኳ። ምናለ ጥይታችሁን በከንቱ ባታባክኑ? ማን ይምጣላችሁ በዚች ምጥ ሰአት? የተባበሩት የፌዴራሊስት አክራሪ ሀይሎች በህውሀት አጋፋሪነት ይምጡላችሁ? ይህው እኮ ጦር እየሰበቁ አቢይ ኢትዮጵያችንን ገደለብን፣ እንበቀል እያሉን ነው። የጥንት ሰንበቴ ጓዶቻቸውን እነስዬን ሁሉ ኒሻን እያለበሱ። የኢትዮጵያ አምላክ በላይህ ላይ ድንጋይ ይድፋብህ ፣ ደሞ በላይ ይባልልኛል። የ አቢይን አቃቂር ማውጣትና ጉድፍ ከመልቀም ለምን ጉልበትህን በእውነተኛ የኢትዮጵያ ጠላቶች ላይ አታሳርፍም? ማን ይሙት አቢይ አህመድ ነው ባሁኗ ሰአት ለኢትዮጵያችን ስጋት? ይህን ሁሉ ከውስጥም ከውጭም እሳት እየለኮሰ የሚያባላን አቢይ ነው? እውነትን ባትፈሩ ፈጣሪን እንኳ ፍሩ እንጅ ።

  3. I understand what Tesfa says.I take it as it is a diplomatic way of opposing my views.I wish my points were false to please some people like Tesfa. But they are stark truths. If they are not true, let others disprove them point by point.
    We may love people and their way of acting but as the same time we have to admit their loopholes and should try to help them correct their wrongs. Abiy might be doing good things but the misdeeds mentionedin my piece are also true. Whois going to be blame for those wrongs doings? If not he, who else then? In whose charge is Ethiopia now? Who is responsible for the mess and the chaos in our nation? Why should Christian Tadele, for example, be in prison while Jawar is at large doing what wishes to do to the extent of killing innocent citizens NONCHALANTLY? Who has made him accountabale for those 86+ people who died by the mob in favor of Jawar? There are so many questions a blind support could by no means answer.

    • You’ve got me wrong brother. i was not saying your points were false. i am simply saying let us give time to the prime minster to resolve many of the issues you have raised.. he maybe the last hurrah for the Ethiopian people. the rest of the crowd is scary to say the least!

  4. አባወረቱ፣ “አንዳንዴ ሳስበው እንዲህ ሆነን መቅረታችን እጅጉን ልብ ይሰብራል” አልከን!? ልብ ዬት አለና!! ሌላውን እንተወዉና መዋሸት ጠባዩ ቢሆንበት ነው እንጂ ምንም ነገር ሳያስገድደው ስለ አሳምነው ጽጌ ነጭ ዉሸት መዘላበድ ለምን አስፈለገው?? ሰውዬው እኮ እንኳን ስለኢትዮጵያ ያለፈው ታሪክ እና ፖሊቲካ ቀርቶ ዛሬ በአፍንጫው ስር ምን እየተካሄደ እንዳለ የሚያውቅ አይመስልም፣ (ከቤተመንግስቱ ግቢ ዉጪ ማለቴ ነው *ስንት ጽገረዳዎች ደረቁ” …. ወዘተ!) ህዝብ በጅምላ እየተጨፈጨፈ፣ እየተራበ፣ እየተሰደደ ዝም የሚል፣ እሱ ጠቅላይ አዛዥ የሆነበት መከላከያ ሲቪሎችን ገድሎ ሬሳቸው ላይ ቆሞ ፎቶ ሲነሳ “ሰላም እያስከበሩ ነው” የሚል፣ ለምሳሌ እዚያው ቡራዩ የሱ ቡችሎች የሚዘዉሩት ፖሊስ ያለምክንያት አርቲስቶችን በአደባባይ ሲቀጠቅጥ፣ መንግስት ተብዬ የተቃዋሚ ደጋፊዎችን በጅምላ እስርቤት ሲያጉር፣ “የቀበሌ አቢዮት ጠባቂ አይደለሁምና አያገባኝም” የሚል “ጠቅላይ ሚንስትር” ኢትዮጵያ እንኳን ኖሮአት፣ ሰምታም አታውቅም ነበር! እንዳንተ አይነቶቹ የአቢይ ልጋግ ላሾች ግን ልብም ህሊናም ስላልፈጠረባችሁ ምኑም አይታያችሁም! መሬት ላይ ያለው እውነታ የማይታየው፣ በአስመሳይ ደጋፊዎች የተጋረደ እዉር መሪ መጨረሻው ገደል ነውና በርቱ!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share