February 14, 2020
3 mins read

 ባፈሙዝ ተናገር – ታዛቢው

ቀድሞ የማናውቀው ፣ ባገር ያልነበረ ፣ ጨካኝ አረመኔ
የባዕድ ቅጥረኛ ፣ የአረብ ተላላኪ ፣ ወኔ ቢስ ምስለኔ
አገር የሚያሸብር ፣ ደንቆሮ አሰማርቶ ፣ መንጋና ቦዘኔ
ቃሊቻ ኩራቱ ፣ ዛፍ ቅቤ የሚቀባ ፣ ሰጋጅ ላደ ሸኔ
መቅደስ የሚያቃጥል ፣ ካህናትን የሚያርድ ፣ በግፍ በጭካኔ
ዕንብርት አልባ ፍጥረት ፣ ዐይኑ ያየውን ሁሉ ፣ አምጡ የሚል የኔ
ከሳት ወደ ረመጥ ፣ የርጉም የበኽር ሽንት ፣ የዚያች የወያኔ ።

በዓለም ያገነናት ፣ ከሁሉም ከፍ ብላ ፣ እንድትታይ ቆማ
አጥንቱን ከስክሶ ፣ ከወራሪ ጠላት ፣ ተዋድቆ የደማ
እንደ ባዕድ ሲታይ ፣ ባቀናት ምድር ላይ ፣ ባቀናት ከተማ
በግፍ ሲያሳድዱት ፣ በገዛ ሐገሩ ፣ መብቱ እየተቀማ
እንዴት ያስችለዋል ፣ ተሰፍሮ የማያልቅ ፣ ግፍ እየተሰማ
ቡሃ ላይ ቆረቆር ፣ አይበጅም ብሎ እንጂ ፣ እናት ሐገር ታማ
እዚያ ቤት ያለ እሳት ፣ እዚህም እንዳለ ፣ ንገሩት ከሰማ ።

በዘመናት ገድሉ ፣ ስመ ጥር የሆነ ፣ ገኖ የከበረ
እጆቹን አጣምሮ ፣ ልጁን ከፎቅ አፋፍ ፣ እያስወረወረ
በነጋ በጠባ ፣ ትውልዱን እርስቱን ፣ ጭዳ እየገበረ
ከእንሰሳት አንሶ ፣ ወገን ከነነፍሱ ፣ እየተቀበረ
የትላንቱ ወይራ ፣ ዶግ ሆኖ ይታያል ፣ ዘመን ተቀየረ
ያለፈው ሲገርመን ፣ ያሁኑ ይባስ ሆነ ፣ ዛሬም አልተማረ ።

ባበዳሪው ትዕዛዝ ፣ በዶላር ለጋሹ ፣ ፍላጎት ተልዕኮ
ጦር እያዘጋጁ ፣ ሐገርን ለማፍረስ ፣ ሰራዊት አምልኮ
በነ ስም አይጠሬ ፣ ምሽግ ቆፋሪዎች ፣ በወያኔ ምርኮ
በያስራምስት ቀኑም ፣ እልፍ ቢያመርት ፣ ቡኮ
መች አጣነው ልኩን ፣ ነገ ሊደረመስ ፣ ልክ አንደ ኢያሪኮ ።

ከቃኤል ጀምሮ ፣ ሲወርድ ሲዋረድ ፣ ዝንተ ዓለም የሚኖር
በሩጫ አያመልጡት ፣ በሃብት አይጋርዱት ፣ ሺ ጦር ቢደረደር
ሰራዊት አይደለም ፣ ኃይል የፈጣሪ ነው ፣ ምንድነው መሸበር
ከአፅናፍ እስከ አፅናፍ ፣ ዘር እየቆጠረ ፣ ግፍ ሰልጥኖ ባገር
መቶ ዓመት ላትኖር ፣ በፍርሃት መራድ ፣ መቼም ከሞት ላትቀር
ወተት ይሸፍታል ፣ እንኳን የሰው ፍጥረት ፣ ሲበዛበት ቀንበር
እንደ አባቶች ገድል ፣ ማይጨውና አድዋ ፣ በድል ለመሻገር
እንደ ውሻ አትሙት ፣ አይኖችህ እያዩ ፣ በቁም አትቀበር
ዝናርህን ታጥቀህ ፣ አንተም ጫካ ገብተህ ፣ ባፈሙዝ ተናገር ።

ታዛቢው
February 14, 2020

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Go toTop