ቤቲ ስለተባለች ልጅ (ስላደረገችው ጉዳይ) ስሰማ የሷ ፎቶግራፍ ማየት አማረኝ (ዘመቻ እንደማይከፈተኝ ተስፋ አለኝ)። የወሲብ ነገር ይፋ ሲሆን ‘ያስደነግጠናል’፤ ስለጉዳዩ ማውራትና ማየት ግን በጣም ያስደስተናል። (‘ያስደነግጠናል’ ያልኩት ለወግ ያህል ነው)። ባያስደስተን ኑሮ ስለ ልጅቷና ተግባሯ መላልሰን ባልፃፍንና ባላወራን ነበር።
አንድ ተግባር (ወይ ነገር) ስሜታችን (በጥሩም በመጥፎም) ከነካ ውስጣችን ተመሳሳይ ስሜት አለ ማለት ነው። ስለዚህ አንድ ተግባር ስናወድስ ወይ ስንኮንን የራሳችን ስሜት እየገለፅን ነው። (አለበለዝያማ በቀላሉ ማለፍ እንችል ነበር)። የወሲ…ብ እርካታ ያላገኘ ሰው ስለወሲብ መጥፎነት ወይ ጥሩነት ያወራል።
የቤቲን ነገር ባልደግፈውም፣ አልኮንነውም። ምክንያቱም (1) ወሲብ ሁላችን የምንፈልገው ተሰጥኦ ነው። ወሲብ መጥፎ ስለመሆኑ እኔን ማሳመን ይከብዳችኋል። (2) በባህላችን መሰረት ‘ተሸፋፍኖ’ መደረግ ነበረበት ከሆነ፡ መልካም (እኔም እስማማለሁ)።
‘ሀገር ወክላ ሄዳ አዋረደችን!’ በሚለው ግን አልስማማም። ወሲብ የማያውቅ ሀገር ወይ ህዝብ አለ እንዴ? አንዲት ልጅ ወሲብ ስለፈፀመች ሀገር አይዋረድም፤ የአፍሪካ (እንዲሁም የዓለም መሪዎች) ወደ ኢትዮዽያ መምጣት የሚያስደስታቸው በምን ምክንያት ሆነና ነው??? ደሞኮ ሰዎች ወሲብ ይኮንናሉ እንጂ ወሲብ አይጠሉም።
አንዳንዴ ሰዎች ይገርሙኛል። ወሲብን እያወገዙ በልቅ ወሲብ የሚታወቁ ታዋቂ ሰዎች ያደንቃሉ። አደንዛዥ ዕፅ ጠልተው በአደንዛዥ ዕፅ የደነዘዙ ሰዎች ያደንቃሉ (ስንቶቻችን ነን ዓሺሽ ጠልተን … የቦብ ማርለይ ፎቶ ግድግዳችን ሰቅለን የምናመልከው???!!! ልቅ ወሲብ አውግዘን ብሪትኒ ስፒርስን የሙጥኝ የምንወደው???!!!)
የቤቲን ተግባር ባልደግፈውም ለሀገራችን የሚያመጣው መጥፎ ስም ግን አይኖርም። (አሁን ከሁሉም ሰው በበለጠ ማየት የምንፈልገው … .. ቤቲን ልንመርጥ እንችላለን)።
ከቤቲ ተግባር ይልቅ በጣም ያስደነቀኝ ነገር ስለ ተግባሯ የተሰጡ አስተያየቶች ናቸው። በሚሰጣት አስተያየት ካልተደናገጠች (ቤቲን ነው) ለሷ ያለኝ አድናቆት አድርሱልኝ (ለፈፀመችው ነገር ሳይሆን በሚሰጣት አስተያየት ላለመደንገጧ ወይ ላለመሸማቀቋ)። ከተሸማቀቀች ግን አድናቆቴን መልሱልኝ።
ግብዝነት ይቁም።
It is so!!!