June 9, 2013
10 mins read

አንድነት ፓርቲ የሰኔ አንድን ሰማእታት ዘከረ

ኔ 1 ቀን 1997 ዓ.ም በመንግስት ሀይሎች በግፍ የተጨፈጨፉ የሰላማዊ ትግል ሰማዕታትን ለመዘከር አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የአዲስ አበባ ዞን ያዘጋጀው መርሀግብር  ተካሄደ፡፡ቀበና አካባቢ በሚገኘው አንድነት ፓርቲ ዋና ጽ/ቤት ሰማዕታቱን ለማሰብ በህሊና ፀሎት በተጀመረው በዚሁ መርሀ ግብር ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርቲው ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ሲሆኑ ከሳቸው በመቀጠል የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን ሰብሳቢ አቶ ትዕግስቱ አወሉ ዕለቱን የሚመለከት ንግግር አድርገዋል፡፡ ከ300 በላይ ታዳሚዎች በተሳተፉነት በዚህ መርሀግብር ላይ ዕለቱን የተመለከቱ ግጥሞች በገጣሚ መላኩ ጌታቸው ቀርበዋል፡፡ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ኃይሉ ዕለቱን አስመልክቶ የነበረውን ትዕውስታ ለታዳሚው አካፍሏል:: የመርሀግብሩ አዘጋጆች ሰኔ አንድ በግፍ ከተገደሉ ዜጎች መካከል 42 የሚሆኑትን ስምና የአገዳደል ሁኔታ በመቀንጨብ አቅርበዋል፡፡ የታሳሪዋ ጋዜጠኛ ርዕዮት አለሙ አባት አቶ አለሙ ጌቤቦ የመዝጊያ ንግግር ካደረጉ በኋላ በቅርቡ በማዕከላዊ ታስሮ ድብባና እስር ሲፈፀምበት በነበረው ወጣት ብርሀኑ ተክለያሬድ የተመራ የጧፍ ማብራት ስነስርአት ተካሂዶ መርሀግብሩ ተጠናቋል፡፡

የአቶ ትእግስቱ አወሉ የአንድነት ፓርቲ አዲስ አበባ ዞን ም/ቤት ሰብሳቢ ንግግር
ሰኔ 1 ቀን 2005ዓ.ም   አዲስ አበባ

ታሪክ መፃፍ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ሰለመንግስታት አነሳስና አወዳዳቅ ብዙ ተዘርዝራል ወይም ተብላል፡፤ አንዳንዶቹ ትልቅ ስለመሆናቸዉ ያረጋገጡት በረጅም ጊዜ ሲሆን ብሄራዊ ነጻነታቸዉ ሳይቀር ባጭር ጊዜ ከእጃቸዉ ሲወጣ ተስተዉላል፡፡ ብሄራዊ ፍልስፍናቸዉንና ተልእኮአቸዉን አጉል መስዋእትነት የሰጡበትም ጊዜ አልፉዋል፡፡ ዉድቀትም ተከትሎአቸዋል፡፡ የዚህ አይነት አደጋ ሰለተደጋገመ ሄግል የተባለዉ ጥንታዊ ፈላስፋ “ከታሪክ የምንማረዉ ነገር ቢኖር አለማመራችንን ነዉ” ሲል ሌላዉ ፈላስፋ ሳንታያና ደግሞ “የታሪክ ትምህርቶች ለመማር የማይችሉ እንዲደግሙት ይገደዳሉ” ብሎአል፡፡

እኛ ኢትዮጵያዊያን ከረጅም ጊዜ በፊት ትልቅ ነበርን ፡፡ ከረጅም ጉዞ በኃላ ደግሞ በሁሉም ረገድ ከሁሉም አገር በሚባል ደረጃ ከበስተጀርባ ተደብቀናል፡፡ አገራችንን አልታደግናትም፡፡ እራሳችንንም አላዳንም፡፡ ለኢትዮጵያ ታማኝና አብሮነታችን ለፈጠረዉ አንድነታችን መገለጫ መንገዳችን አደጋ ላይ ነዉ፡፡ አቡነ ጴጥሮስ በባለ ቅኔ ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ትያትር ገፀ ባህርይ እንደጠቀሱት “ኢትዮጵያን ረሳናት” ብለዋል፡፡ አዎ ኢትዮጵያን ረሳናት ምክንያቱም ከመገንባት ይልቅ አፈረስናት እንጂ፡፡ እኛ አትዮጵያኖች ከጥንት ጀምሮ መንግስትን እንደ ጣኦት የማየትና የማምለክ ዝንባሌ ስለነበረን በእኛ ስም እየማሉ አገር ለሚያፈርሱ ገዥዎች ታዝዘናል፡፡ በየዘመኑ አትዮጵያን ያፈረሱም ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ በታሪካችን ካየናቸዉ በተለየ ሁኔታ እያፈረሱን ነዉ፡፡ አገር ማፍረስ ከደም ማፍሰስ ጋር የሚሄድ ብሄራዊ ወንጀል ነዉ፡፡

ህዝብ ማለቅ የለበትም ብሎ መስዋእትነት የከፈለ፤ እትዮጵያን መጠበቅ አለብን ብሎ የተሰየፈ፤ ዛሬም ሰብአዊና ዴሞክራሳዊ መብቶቻችን መረገጥ የለበትም ከማለት ባሻገር ከወያኔ ኢህአዴግ ጋር ፊት ለፊት የተፋጠጠ ማን ነዉ? እኔ አለሁ የሚልም ካለ ይህ ሰዉ ወይም ድርጅት ጀግና ነዉ፡፡ ኢትዮጵያዊ ከብርና ሞገስ ይገበዋል፡፡ የዛሬ ስምንት አመት በዛሬዋ ቀን በአምባገነን ገዥዎች ትእዛዝ የተረሸኑትን ወገኖቻችንን የምናስታዉሳቸዉ ለሰብአዊና ለዴሞክራሳዊ መብቶች በተደረገ ትግል ዉስጥ የተከፈለ መስዋእትነት በመሆኑ የህዝብ ሰማእታት ናቸዉ፡፡ ለጀግኖች የሚሰጠዉን ክብር እንሰጣቸዋለን፡፡

ዛሬ ዛሬ በአለማችን አንባገነኖችም ዴሞክራቶችም ምርጫ ያካሂዳሉ፡፡ ሁለቱም ጫፎች ምርቻዎችን ነፃና ዴሞክራሲያዊ ብለዉ ይጠራሉ፡፡ ነገር ግን የሰማይና የምድር ያህል ልዩነት የሚመጣዉ ምርጫዎች በሂደት እስከ ዉጤት በሚታዩት ሁኔታዎች ዉስጥ ነዉ፡፡ እነዚህ የዛሬዋ ቀን የነፃነት ሰማእታት በአምባገነን የተጨፈጨፉት፤ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎቻችን በእስር የተገላቱት ወያኔ ኢህአዴግ “ምርጫዉ እንከን የለሽ ነዉ” እያለ የዘፍንለት የነበረዉ 1997ዓ.ም ምርጫ ዉጤት በኃላ “ድምፃችን ይከበር ” በማለታቸዉ ነበር፡፡

በዛሬዋ እለት በህሊናችን የመናስታዉሳቸዉም ሆኑ ከእነርሱ በፊትና በኃላም ለፍትህና ለነፃነት መስዋእትነት የከፈሉና እየከፈሉም ያሉ ታጋዮች አሉ፡፡ እነዚህ የህዝብ ታጋዮች ኢትዮጵያ አትፈርስም፤ ህዝብም አይበተንም በማለታቸዉ የዴሞክራሲና የነፃነት ጠበቆች ናቸዉ፡፡ እኛ በኢትዮጵያ አምላክ የምንጠየቀዉ እነዚህ ሰማእታት በደም የዋጁለትን ህዝባዊ አላማ ቸል ብለን ኃላፊነታችንን እርግፍ አድርገን ትግሉን የሸሸን እነደሆነ ነዉ፡፡ ኢትዮጵያዊያን ብሄራዊ ፈተናዉን የምንወደወቀዉ እዚህ ላይ ነዉ፡፡

የአምባገነንነት አደገኛ ባህርያት ዛሬ በሥልጣን ላይ ከአለዉ መንግስት በግልፅ በማየት ሁላችንም ስንጮህና በተገኘዉ አለም አቀፍ መድረክም ጭምር ድምፃችንን ስናሰማ ቆይተናል፡፡ ገዥዎቻችን የዜጎችን ሰብአዊ መብት በመርገጥ ወደ አዘቅት እየወሰዱን መሆኑን ያልተስማማንበት ጊዜ አልነበረም፡፡ ምናልባትም ከዚህ የከፋ ሁኔታ አገራችንን እንዳይጎበኛት ምን ማድረግ እንደሚገባን መጠየቅ ካለብን ከመቼዉም በበለጠ ጊዜዉ አሁን ነዉ፡፡ ከተግባባን መፍተሄዉ በኢትዮጵያዊያን እጅ ይገኛል፡፡ አማራጮቹም ሁለት ይመስሉኛል፡፡ አንዱ ያለዉን ሁኔታና መጪዉን ሁሉ አሜን ብሎ ተቀብሎ አርፎ መቀመጥ ፡፡ ሌላዉ ደግሞ ይህን ሸክም አዉርዶ መጣል፡፡ ሁለተኛዉ አማራጭ ሲታሰብ ግን የተዘጉትን በሮች ከሩቅ አይቶ ወይም ከታጠረዉ ግንብ ጋር ተጋጭቶ መመለስ ሳይሆን በአሉት ቀዳዳዎችና ጭላነጭሎች ገብቶ መታገል የግድ ይሆናል፡፡ የሠላማዊ ትግሉ አንዱ አማራጭ ይህ ነዉ፡፡ የጊዜ ጉዳይ እንጂ የጠብመንጃ መንግስት የዘለቀበት የታሪክ አጋጣሚ የለም፡፡

በመጨረሻም በዚህ ታላቅ ዝክረ ሰማእታት የተገኛቸሁትን ሁሉ በአዲስ አበባ ዞን አንድነት ፓርቲ ምክር ቤት፤ በዝግጅቱና በራሴ ስም አመሰግናለሁ፡፡ የሰኔ አንድ ሰማእታት አላማ የሚከበረዉ በተጠናከረ ህዝባዊ ትግል ነዉ፡፡

ዘላለማዊ ክብር ለነፃነት ሰማእታት

2 Comments

  1. Surely, the morning is on the coming. The morning when humane Ethiopians stand tall and proudly erect the monument. Till then, a virtual version of this memorabelia should flash on pages …

Comments are closed.

Pen 4
Previous Story

“ትግሉ ኑረምበርግ ደርሷል”

brother africa ethiopia
Next Story

ስለቤቲና የወሲብ ጉዳይ – ኣብርሃ ደስታ (ከመቀሌ)

Latest from Blog

አስቸኳይ ህዝባዊ ጥሪ

July 24, 2024 ዓለማቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት Global alliance for the Rights of Ethiopians (GARE) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት የብዙ ወገኖቻችንን ህይዎት ማለፉን
Go toTop