May 6, 2014
17 mins read

(የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ) ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት!!

ከኢትዮ ተዋሕዶ

ህሊናዬ ያለእረፍት ይናጣል በሃሳብ ቅብልብሎሽ አድማስ ይሻገራል፡፡መቸም ህሊናችን አንድ ግዜ ክፉውን ሌላ ጊዜ በጎውን ማውጠንጠኑ የተለመደ ገቢር ቢሆንም ህሊናዬን በቁጣና በቁጭት ያደነቆረኝን ነገር በልቤ አብሰልስዬ በአንደበቴ መስክሬ የእርካታ ጣሪያ ላይ መድረስ አልተሳነኝምና ቁጭት ያቀረረ ብእሬን አንስቼ በጦማር ልፋለመው ገባሁ፡፡በቅድሚያ ክቡር ንዑድ የሆነ ሰለምታዬ ይድረሳችሁ፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ለዘመናት በሊቃውንት አባቶች ከታላቁ መፃህፍ ከመፅሐፍ ቅዱስ በተጨማሪ ህገ መንፈሳዊ በሆኑት ፍትሃ ነገስት(The Law of the Kings)፣ቃለዓዋዲ፣ ሐይማኖተ አበው እና ሌሎችም አዋልደ መፃህፍት በመታገዝ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቅዱሳን አባቶች ስለ እውነት ብለው እንደ ስንዴ ተቆልተው እንደ አክርማ ተሰንጥቀው በዱር በገደል እንዲሁም በበረሀ ተቅበዝብዘው ቅጠል በልተው አፈር ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው የቤተክርስቲያንን ህልውና ከፀና ሰርዓቷ ጠብቀው አኖረዋል፡፡

የጉድ ሃገር ገንፎ እያርደ ይፋጃል” እንዲሉ አለማዊ ክብርና ዝናን ለመላበስ በመሻት ከሙሽራው ክርስቶስ ውዳሴ በላይ የኔ ስምና ክብር ይቅደም በማለት በበዓለ ሆሳዕና ቅዳሴ የተስተጓገለበትን የሚኖሶታው ደብረ ሰላም መድሐኒያለም በአርምሞ ማለፍ ከህሊና ጋር መቃቃር እንዲሁም የልቦና መባከን ስለሆነብኝ ትንሽ የግሌን የአስተሳሰብ ልኬት እና ግንዛቤ ከመንፈሳዊ ህግ ጋር በማዋሃድ ላወጋችሁ ወደድኩ ፡፡ሆሳዕና በልዩ ሁኔታ የሚከበር ጌታችንን ክርስቶስ በእየሩሳሌም ከሚጠቡ ህፃናት አንደበት አንስቶ እሰከ ቤተፋጌ ድንጋዩች ድረስ “ሆሳዕና በዓርያም በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ አርሱ ብሩክ ነው″ ብለው ያመሰገኑበት ተዓምራታዊ እለት እና አንደኛው አበይት በዓል ነው፡፡ እናም በዚህ እለት ኢትዮጳያ ካለው ቅዱስ ሲዲኖዶስ ለኒዮርክና አካባቢዋ የተላኩት አቡነ ዘካሪያስ በስርዓተ ቅዳሴው የእኔን ስም በመግለፅ ሊቀደስ ይገባል ካለሆነ ቅዳሴው ተስተጓግሎ ቤተክርስቲያኒቷ እንድትዘጋ የሚል ትዕዛዝ አስተላለፉ፡፡ለሃያ አመታት በዚህ ስርዓት ሲተዳደሩ የነበሩ ህገ እግዚአብሄርን የሚያከብሩ ካህናትና ዲያቆናት ከህዝበ ክርስቲያኑ ጋር ጌታን ሲያመሰግኑ ዋሉ፡፡ የነገስታቱ ምድራዊ ጥንካሬና ጉልበት ያስፈራቸው ካህናት ቅዳሴውን ትተው ምድራዊውን ንጉስ ሊያመስግኑ ከሆሳዕና ተለዩ ከፈሪሳዊያንም ጋር አበሩ፡፡ከሙሽራው በላይ መድመቅና መክበር የፈለጉ ሚዜዎች መሆን ፈልገው እንጂ ከማያልፈው የክርስቶስ ክብር የእነሱን ዘለቄታ የለሽ ዝና ማስቀደም አልነበረባቸውም(የመንግስት ቀኝ ክንፍ ካለሆኑ በቀር) ደግሞም ቤተክርስቲያን ስለአለም ሁሉ የምትማልድ እንጂ ለህዝብና አህዛብ፣ ለቤተክርስቲያን ኃላፊዎችና ለቤተመንግስት ባለስልጣን አልያም ላለው ለሌለው ብላ እግዚኦታ የምታስብል አይደለችም፡፡ ለቤተክርስቲያን አገልጋይም በተለየ መልኩ በማዕረግ ፀሎት መደረግ አለበት ከተባለ በስርዓተ ቅዳሴው “ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ጳጳሳት፣ ኤጲስ ቆጶሳት፣ ቀሳቀወስት ወዲያቆናት” በሚል ሀረግ ይማልዳል፡፡

ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- “የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ”፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን “አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡
(የሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ) ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት!! 1
ደግሞም እኮ በድርጊት እንጂ በስም ሰማዕትነትን የተቀበለ የሰው ዘር የለም (መብራቱን እስከ ዘይቱ የያዘም አይደል ከሙሽራው ጋር ሰርጉን የሚታደም?)፡፡

ከታሪክ የማይማር ታሪክን ይደግማል እንዲሉ ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን በሆሳዕና እለት ህዝቡ የዘንባባ ዝንፃፊ እና የለበሱትን ልብስ በማንጠፍ ጌታ በውርንጭላይቱ ላይ ሆኖ እንዲያልፍ በማድረግ “ሆሳዕና በዓርያም በእግዚበሔር ስም የሚመጣ አርሱ ብሩክ ነው″ ብለው ሲያመስግኑ ለእነሱ አልተዋጠላቸውምና መምህር ሆይ ለምን ዝም በሉ አትላቸውም አሉት ምስጋና የባህሪ ገንዘቡ ነበርና እነሱ ዝም ቢሉ የቢታኒያ ድንጋዮች ያመሰግኑኛል አላቸው፡፡ እውነትም ድንቅ ነበር የቤተ ፋጌ አለቶች ድምፅ አውጥተው አመሰገኑት ዛሬም ይሄ ነው የተፈፀመው ፈሪሳውያንና ሰዱቃዊያን አናመሰገንም ሲሉ በበዓለ ሆሳእና በደብረ ሰላም መድሐኒያለም የቤተ ፋጌ አለቶች ድመፅ አውጥተው አመሰገኑት (ከቢታኒያ ድንጋይ ከማነስ ይሰውረን)፡፡ አቡነ ዘካሪያስም መፅሐፍ ቅዱስ በማይፈቅደው ከቤተክርስቲያን የህግ መፅሐፍ ከሆነው ከፍትሃ ነገስት ጋር በሚጣረስ መልኩ የግዝት ትዕዛዝ አስተላለፉ (እንደማስተባበያ ሥልጣነ ክህነታቸው ተያዘ እንጂ አልተወገዙም የሚል ጉንጭ አልፋ ምክንያት እንደ ምክኒያት ቢቀርብም &እዚች ጋር አንድ ቀልድ ቢጤ ትዝ አለችኝ ሰዎቹ በሰውዬው ሀብትና አውቀት እጅጉን ይቀኑና ህይወቱን እስከማጥፋ የሚደረስ ቅናት ያድርባቸዋል እናም በሚመላለስበት ቦታ አዘውትረው ይጠብቁት ነበርና አንደ ቀን አድፍጠው በሚጠብቁበት ሰዓት የሰውየው የበኩር ልጅ ያገኛቸዋል ወትሮውንም አባቱን ሊያጠፉት እንደሚፈልጉ ይሰማ ነበርና የያዙትን ስለት በማየት አባቴን ልትገሉት ነው አይደል ሲላቸው አንደኛው ፈጠን ብሎ አይደለም ባክህ የእናትህን ባል ነው አለው፡፡ግዝትና ክህነትን መያዝ ምን አለያየው ሁለቱም ግልጋሎትን የሚከለክሉ አይደሉም እንዴ ቂቂቂቂቂ)

ግዝት በቤተክርስቲያን ሃይማኖትን ለካዱ እና በነውር ለተገኙ ሰዎች በተለይም በካህናት ላይ የሚተላለፍ የመጨረሻው የፍርድ ውሳኔ ነው።ይህ አንድን ካህን(ሰው) ከማኅበረ ክርስቲያን የመለያ ውሳኔ የሚተላለፈው ደግሞ ተጨባጭ የሆኑ የኃይማኖት ክህደትና የምግባር ብልሹነት ሲቀርቡ ብቻ ነው።
ስለውግዘት መፅሐፍ ቅዱስ (መፅሐፈ ሔኖክ ምዕራፍ 36 ቁጥር 15) እንዲህ ይላል፡- “የማይገባ ግዝትን ለምትፈፅሙ ለናንተ ወዮላችሁ ስለ ኃጢያታችሁ ድህነት ከናንተ ይራቀ እንደስራችሁ መጠን ፍዳውን ትቀበላላችሁና ለባልንጀራችሁ ክፉ ምላሽ ልምትመሱ ለናንተ ወዮላችሁ”፡፡ በፍትሃ ነገስትም ላይ እንዲህ የሚል ኃያል ቃል እናገኛለን “አለቃው ህዝቡን የሚመክራቸው በውግዘት ያይደል በመስቀል የሚያስራቸው ይሁን በማይገባ አያውግዝ፡፡ሰዎችን ሊያሳዝናቸውና ፈርተው እንዲገዙለት ፈልጎ በማይገባቢያወግዝ እርሱ ከእግዚአብሐየር ዘንድ የታሰረ የተወገዘ ይሁን፡፡ ካህናትም በእውነት ይቋቋሙት ይላል፡፡ በተፃራሪ ለግል ክብርና ዝና ውግዘት ማድረግ ተገቢ አይደለም ተደጋጋሚ ምክር ሳይደረግ ሊቃውንተ ቤተክረስቲያን ጉባዔ ሳይቀመጡ ውጉዝ ከመዓርዮስ ማለት ወፈ ገዝት እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ይናገራሉ፡፡ሰለስቱ ምዕት(318ቱ ሊቃውንተ ቤተክርሰቲያን) አርዮስን በተደጋጋሚ መክረውና ዘክረው በነቂያ ጉባዔ እንዳወገዙት ልብ ይሏል ይህም የሆነው ለግል ክብርና ዝና ሳይሆን ከባድ ሐይማኖታዊ ክህደት በመፈፀሙ ነው፡፡

መቸም ዲያብሎስ በእድሜ እንጂ በተንኮል የማይበልጠን ተመፃዳቂ ለምድ ለባሽ ተኩላዎች ስለሆንን እንጂ ከእውቀትና ከመንፈሳዊ ብስለት ጋር የማይስማማ ቅዱሳን በመንፈስ ቅዱስ ተመርተው ከፃፏቸው የህግ መፅሕፍት ጋር በሚጣረስ መልኩ ባልተባረከነ በአራቱም የቤተክርስቲያኑ አቅጣጫ በቅብዓ ሜሮን ባልተባረከበት ብዙ ተገቢ ስርዓተ ቤተክርስቲያን ባለተፈፀመበት አዲስ ቤተክርስቲያን ከሶስት ሳምንት በላይ ስርዓተ ቅዳሴ መፈፀም ምን ይባላል? ደግሞስ ለብዙ ዘመናት የጌታ ስጋና ደም ሲፈተትባት የነበረችን ቅድስት ቤተክርስቲያን ይሄንን በረት አሳማ አርቡበት ብሎ ናቡከደነፆራዊ ድፍረት የተሞላበት ስድብ መሳደብ መቸም ሚኒሊክ ቤተመንግሰት ካሉት ነገስታት የተላከ እንጂ ከሰማዩ አባት የተወረሰ መንፈሳዊ ብስለት አይደለም፡፡

ሌላው አስነዋሪ ክስተት አላዋቂ መካር የፍዳ ማከማቻ መሆኑ ያልተረዱት የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የበላይ አሰተዳዳሪ አባ ዘርዓ ዳዊት በትንሳኤ ሌሊት አለም ከአመተ ፍዳ ወደ አመተ ምህረት በተሸጋገረበት አዳም ከዲያብሎስ እስራት ወጥቶ በክርስቶስ እቅፍ በዋለበት በዚያች የድህነት ብስራት በሚበሰርበት የምህረት እምቢልታ በሚለፈፍበት የነፃነት ነጋሪት በሚጎሰምበት ትንሳኤ ክርስቶስ በሚዘመርበበት እለት የአስታራቂነት ሚና ከሚጠበቅበት መንፈሳዊ አባት ቤተክርሲቲያኗ ግልፅ ያልሆነ በጉባዔ ባለተወሰነ የካህናቱና ዲያቆናቱ ምግባር ፅድቅ ይሁን ኩነኔ ባልተለየበት ለማህበረ ምዕመኑ የካህናቱንና የዲያቆናቱን ውግዘትና የስልጣነ ክህነት እስር መለፈፍ ምን ይሉታል? (እስራት የባህሪ ገንዘቡ ከሆነው የኢትዮጵያ መንግሰት ካልተላኩ በቀር)፡፡ እናም ቅዱስ አባታችን የቀደመውን አስቡ እግዚአብሔር ለሁለት አምላክ መገዛት አትችሉም በማለት ቀናተኛ አምላክ መሆኑን በአውደ ምህረቱ ትሰብኩልን የለ እናንተም ወይ ምድራዊ ክብራችሁን አልያም በመስቀል ላይ የዋለውን አምልኩ አልያ ከወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት ሆኖ በቤተክርስቲያን መክበር አይቻልም፡፡
ናቡከደነፆራዊ ድፍረታችሁን ትታችሁ የቀደመውን አስቡ!!!

እግዚአብሔር ለቤተክርስቲያናችን ህብረትን ፍቅርን አንድነትም ይስጥልን!!!

Latest from Blog

ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop