በአንድ የደስታም ይሁን የሀዘን ድግስ ላይ ሳይጠራ ወይም ሳይጋበዝ ወደ ግብዣው ቦታ የሚገባና ከታዳሚዎች ጋር ተመሳስሎ የሚበላ የሚጠጣ ሰው በአራድኛ ቋንቋ ድንኳን ሰባሪ ይባላል፡፡ በተለይ በዚህ ዘመን የድንኳን ሰባሪ ቁጥር እያየለ በመምጣቱ ደጋሾች እየተቸገሩ እንደሆነ ይነገራል፡፡ አለባበሱን አሳምሮ የተጠራ በመምሰል አስተናባሪዎችንና ቋሚዎችን ማለትም አሳላፊዎችን አጭበርብሮ ይገባል፤ ከዚያም ቤት ያፈራውን ሁሉ ልክ እንደተጋበዘ ሰው ይስተናገዳል፡፡ “የለማኝ ተጓዳጅ” እንዲሉ ሲስተናገድም ከታዳሚዎች ባልተናነሰ ምናልባትም በበለጠ ስለግብዣው ሁኔታ አቃቂርና ስሞታ የሚያበዛው ደሞ እሱ ነው፡፡ ወያኔንና የወያኔን የትሮይ ፈረስ ብአዴንን አጭበርብሮና አምታትቶ አራት ኪሎን የተቆጣጠረው አቢይ አህመድም ከድንኳን ሰባሪነት ቢበልጥ እንጂ አይተናነስም፡፡ ችግሩ ድንኳን ሰባሪነቱን ረስቶ ሥልጣኑን በህግ አግባብ ያገኘው ይመስል “ኢትዮጵያን መምራት ማለት አንድ ሚሊዮን ጉንዳን እንደመሸከም በመሆኑ ከጉዳት በቀር ትርፍ የለውም” እያለ ምራን ብለን ያስገደድነው ይመስል በተለመደው ስድ አንደበቱ መሳደቡ ነው፡፡ በተፈጠረ ክፍተት ተመሳስሎ ገብቶ ቁም ስቅላችንን የሚያሳየን አቢይ አህመድ እንኳን ኢትዮጵያን የመሰለች ታሪካዊት ሀገር መምራት ይቅርና እንደሰው ሊያስቆጥረው የሚችል አንዳችም ሰብኣዊ ባሕርይ የለውም፡፡ በግሌ አቢይ አህመድን የማውቀውን ያህል እኔንም ሆነ ክብርት ባልተቤቴን አላውቅም፡፡ አቢይ ማለት በተንኮል ሤራ ከሆነ ብቻውን የአንድ ሺህ ሰው ግምት ነው፡፡ በተንኮልና በሤራ ክህነት አግኝቶ የመጨረሻው ጨካኝ ለመሆን ደግሞ ትምህርት ሣይሆን ኅሊናን እንዳወጣ መሸጥ ብቻውን በቂ ነው – ትምህርት ካለ እንዲያውም ተልእኮን መቶ በመቶ ከማከናወን አኳያ መሰናክል ይፈጥራል ተብሎ ስለሚታመን ብዙ መማር በኅቡዓን ድርጅቶች ዘንድ አያስመርጥም፡፡ አቢይም የልጅነት ዘመኑን ቁሣዊ አራራ ወይም ችግር ለመበቀል ሲል ነፍሱን አሲይዞ ለአጋንንቱ የጨለማው ዓለም ኢትዮጵያን ሸጧል፡፡ ለዚህ ዓላማውም ሁን ያሉትን ይሆናል፤ አድርግ ያሉትንም ያላንዳች ማንገራገር ያደርጋል፡፡ ከዚህ አንጻር ካገኘው ሸበላ ወንድ ጋር ሁሉ መተሻሸቱና ዐይኖቹን በፍቅር ርሀብ ማንከራተቱን እንደጽድቅ እንጂ እንደሦዶም ወገሞራዊ ነውር አይቆጥረውም፡፡
አቢይን በጭካኔ የሚወዳደረው እንደሌለ ተነግሮ ያለቀ ቅቡል እውነት ነው፡፡ በዓለም የመንግሥታት ታሪክ እንደነኢዲያሚን ዳዳ፣ አፄ ቦካሣ፣ ሂትለርና ሙሶሊኒን የመሳሰሉ ዐረመኔ አምባገነኖች ታይተዋል፡፡ የኛው አቢይ ግን ከነዚህና ከሌሎቹም ለየት ይላል፡፡ በዐረመኔነቱ አሁን እዚህ ከተጠቀሱትም ሆነ ካልተጠቀሱት አምባገነኖች በእጅጉ የሚበልጥ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ሌላው ልዩነት ሌሎቹ ሀገራቸውንና ሕዝባቸውን ያልካዱ ሲሆኑ አቢይ ግን በምንም ነገር የማይረካው ኢጎው ለፈጠረበት የሥልጣንና የሀብት ፍቅር ሲል ሀገሩን ይቅርና ልጆቹንና ሚስቶቹን ሳይቀር የሚሸጥ መሆኑ ነው፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን የካደና የተጸየፈ ሰው ኢትዮጵያን በጠቅላይ ሚኒስትርነት የሥልጣን ማዕረግ ሲገዛ ማየት የክፍለ ዘመናችን ዕንቆቅልሽ ሆኖ አለ፡፡ ይህ ዓይነቱ በየትም ሀገር ያልተከሰተና ይከሰታል ተብሎም የማይጠበቅ ክስተት በእጅጉ አስገራሚም አሳዛኝም ነው፡፡ ለምሣሌ ኢዲ አሚን ዳዳ ዩጋንዳዊነቱን፣ አፄ ቦካሣ የማዕከላዊት አፍሪካ ሪፓብሊክ ማንነቱን፣ ሂትለር ጀርመናዊነቱን፣ ሙሶሊኒ ጣሊያናዊነቱን …. አይክድም፤ አይክዱም፡፡ አቢይ ግን በኢትዮጵያዊነቱ የሚያፍርና ለሥልጣንና ለገንዘብ ፍቅር ሲል ብቻ በሥነ ልቦና እየተሰቃዬ አራት ኪሎን የሙጥኝ ብሎ የሚገኝ ወላድ አትይህ የሚባል ማፈሪያ ነው፡፡ ኢትዮጵያውያን የሚኮሩበት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ የሚያሳስርና የሚያስገድል የሆነው አቢይ ከመጣ ወዲህ ነው – በመለስ ጊዜ ይህን ባንዲራ ይዞ መገኘት ማሳሰር ካልሆነ በቀር ማስገደሉን አላስታውስም፡፡ ኢትዮጵያዊ ቅርስ በገሃድ እንዲወድም ዐዋጅ ታውጆ የሺዎች ዓመታት የሚታይና የማይታይ ቅርሳችን እንዲጠፋ እየተደረገ ያለው በአቢይ ነው፡፡ የነጭ ውሸት ንግግሩን ሳንጨምር አልፎ አልፎ ለማስመሰል ሲል አቢይ በአፉ የሚናገረው ሌላ፣ በተግባሩ የሚታዬው ደግሞ ሌላ የሆነ አሰለጥና ነውረኛ ሰው መሆኑን በተለይ አሁን ላይ ማንም ያውቃል፡፡ ነገር ግን ይሄ ከተበላ ከአራት ሰዓታት በኋላ ከሆድ ውስጥ የሚጠፋው እንጀራ የሚባል ነገር ሰዎችን እያነሆለለ የዚህ እርኩስ ሰው አሽከርና አጋፋሪ ማድረጉን ቀጥሏል፡፡ ሞት የታወጀበት አንዳንድ ባንዳ አማራ ሳይቀር የአቢይ አሸርጋጅና ለፍርፋሪ ሥልጣን ሟች ሆኖ በሚታይበት በአሁኑ አስጨናቂ የምጥ ቀን ከንፍሮም ጥሬ ይወጣልና ታዬ ደንደኣን የመሰሉ ጀግና ዜጎች ግን ለሕይወታቸው ቅንጣት ሳይሳሱ የአቢይን ውስጠ ምሥጢር በሚዲያ በማጋለጥ የሕዝብን ንቃተ ኅሊና በማሳደግ ላይ ይገኛሉ፡፡ ይህ ተጋድሏቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ በወርቅ ቀለም ተጽፎ ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲሸጋገር ይኖራል፡፡ መስዋዕትነታቸው ደግሞ በቅርቡ ፍሬ እንደሚያፈራ ጥርጥር የለውም፡፡ አማራን፣ ትግሬንና ኦሮሞን (ATO – አቶ – ተብሏል በቅርቡ) በማጋጨትና በማባላት በየትም ሀገር ባልተለመደ ሁኔታ የሥልጣን ዕድሜውን የሚያራዝመው አቢይ አህመድ የወደፊት የትውልድ ሐረጉን አንገት የሚያስደፋ ጭራቅ ሰው መሆኑን የማይገነዘብ ኢትዮጵያዊ ከሀገራችን ታሪካዊ ጠላቶች ተለይቶ እንደማይታይ ደግሞ መታወቅ አለበት፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ “አፌን በምሣሌ እከፍታለሁ” እንዳለ ናርሲሲስቱ አቢይ አፉን የሚከፍተው ከክርስቶስ በተቃራኒ በስድብና በዛቻ እንዲሁም በፀረ ኢትዮጵያ ንግግሩ ነው፡፡ “ማኅበረሰቡ ከዕውቀት የጸዳ ማይም በመሆኑ ያመጣሁለትን ተዓምራዊ ልማትና ብልጽግና ለማየት ዐይኑን መክፈት አልቻለም” የሚለውን የቅርብ ጊዜ ስድቡን ይዘን ወደኋላ ብናይ ይህ አቢይ የተባለ የሣጥናኤል ልዑክ ባለፉት ሰባት ዓመታት ያላዥጎደጎደብን የስድብና የዘለፋ ዓይነት የለም፡፡ የራሱን ማይምነት ወደኛው ለጥፎ ከአራተኛ ይሁን ከሰባተኛ ያቋረጠውን ትምህርቱን የማናውቅለት ይመስል በሸፍጥና በፎርጀሪ በተገኙ የኮሎኔልነትና የዶክተርነት ማዕረጎች ተጀቡኖ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን አድራጊና ፈጣሪ መስሎ ሀገራችንን የምድራዊ ሲዖል ምሣሌ አደረጋት፡፡ ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ መስበሩንም በግልጽ አሳየን፡፡ እሱን መሰል ማይም ደናቁርት ከየጉራንጉሩ ሰብስቦ ዙሪያውን በሰው መሰል ካባ ድንጋይ በማጠር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን የማውደም ዕኩይ ተግባሩን በስፋት ተያይዞታል፡፡ ቶሎ ካላቆምነው አደጋው የሚቀለበስ አይሆንም፡፡ በተለይ ሰሜናውያን ወያኔ ያጠመደባቸውን የተንኮልና የሤራ ወጥመድ በጣጥሰው ወደጋራ አንድነት ካልመጡ በአቢይ የከፋፍለህ አውድም የአገዛዝ ዘዴ መጥፋታቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ አማራ ትግሬ ምናምን መባባሉ ለአቢይ ሠርግና ምላሽ ነው፡፡
ስለሀገራችን ወቅታዊ ጉዳይ የቱን አንስተን የቱን እንደምንጥል ግራ የተጋባን ብዙ ነን፡፡ እርግጥ ነው – ከጥቂት ባለጊዜዎች በስተቀር በዚህ ሥርዓት የማይነካ ባለመኖሩ “ያልተነካ ግልግል ያውቃል” በሚለው ሀገርኛ ብሂል ለመግለጽ ብንቸገርም እጅግ በርካታ ዜጋ ምን እንደተዞረበት በውል ሳይታወቅ ስለሀገርም ሆነ በሀገር መታወክ ምክንያት ስለሚደርስበት ዘግናኝ ግፍና በደል መናገርን አይፈልግም፡፡ ስለዜጎች ዝምታን መምረጥ ብዙ ሰበቦችን መደርደር ይቻላል፡፡ ነገር ግን ዝምታ ጠቀሜታ እንደሌለው አሁን የደረስንበት የኑሮ ሁኔታ ራሱ ምሥክር ነው፡፡ ዝምታና ይሉኝታ ገዢዎችን የልብ ልብ እየሰጠ የስቃይ ጅራፋቸውን ይበልጥ እንዲያኖጉ ረድቷቸዋል፤ ባለቤት ካልጮኸ ደግሞ ጎረቤት አይረዳም፡፡ አትንኩኝ ባይነትና በደልና ግፍን አልቀበልም ባይነት ያስከብራል፡፡ የሕዝብ መብዛትና ማነስ እንደሆነ ዋጋ የለውም፡፡ ባለ 120 ሚሊዮን ሕዝቧ ኢትዮጵያ በሕዝቧ አለመተባበር ምክንያት ወደሲዖልነት ስትለወጥ አጠቃላይ ብዛታቸው ከ5 ሚሊዮን በታች የሆኑ በርካታ ሀገራት ለመብታቸው ተባብረው ስለቆሙ የመጣ የሄደው እንዳሻው አይረግጣቸውም፡፡ እኛ ግን በዘርና በቋንቋም እንበለው ባለውና በሌለው፣ በሃይማኖትና በነገድም እንበለው በጎሣና በጎጥ እየተከፋፈልን ለመጨረሻው ውራጅ የውራጅ ውራጅ የበሻሻ መንደር ሰውዬ ተጋለጥንና አበሳችንን እናያለን፡፡
ይህ መለያየታችን እስከቀጠለ ድረስ ደግሞ የዚህ ወፈፌ ሰውዬ የአገዛዝ ቀምበር መቀጠሉ የማይሸሹት የመከራ ቀምበር ነው፡፡ ከአሁን በኋላ አቢይ ጥፋት የለበትም፡፡ “ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ እንደሚባለው” ምርጫው የኛው ነው፡፡ አቢይ ምንና ማን እንደሆነ በተግባሩ ብቻም ሣይሆን ማንንም ሳይፈራ በየቀኑ በሚወሻክተው የሀሰት ንግግሩ ይታወቃል፡፡ አቦይ ስብሃትን ራሱ ከእሥር ቤት ከለቀቀ በኋላ በዚያ ጎምቱ ሀገር አጥፊ ሰውዬ ካለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከእሥር መለቀቅ ምክንያት ዜጎች መደንገጣቸውን ሲገልጹ አቢይም “እኛም ስንሰማ ደንግጠናል” ብሎ በመላ ኢትዮጵያውያን ንቃተ ኅሊና ላይ ማላገጡ በታሳቢነት ይያዝና ከዚያም በፊት ሆነ በኋላ የሚያሰማን የውሸት ድረታ ሰይጣን ራሱ የሚቀናበት ነው፡፡ ሰይጣን የሚቀናበት አንድ ለእናቱ የሆነ የዓለማችን ቁጥር አንድ ዋሾ ሰው ቢኖር – ሰው ማለቱም አሁን አሁን እየከበደኝ መጥቷል – አቢይ አህመድ ነው፡፡ እንደኔ እንደኔ ሰይጣን ከአቢይ አህመድ ይልቅ ሩህሩህ ነው፤ ሰይጣን ለውሸቱ ለከት አለው፡፡
በነገራችን ላይ ስለውሸትና ውሸታሞች ከልምድ ያገኘሁትን ልጠቁም፡፡ ሁላችንም ማለቱ ቢከብደኝም ብዙዎቻችን ለተለያዬ ዓላማ እንዋሻለን፡፡ ስለውሸት ዓይነቶችና መቼታዊነት አሁን አላነሳም፡፡ ስለዋሾዎች ግን በሁለት ከፍዬ ላመልክት፡፡ የአቢይ ዓይነት ዋሾነት የሥነ ልቦና ህመም ወይም ልክፍት በመሆኑ አቢያውያን ሲዋሹ ቅሽሽ አይላቸውም፡፡ ሲዋሹ እውነታቸውን ነው፡፡ ምን ለማለት ነው – ለምሣሌ አቢይ “በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት በሁሉም ኢትዮጵያውያን ቤት ሮቦት ይኖራል” ሲል – ብሏልም – ለእሱ እውነቱን ነው፡፡ ውሸት እንደተናገረ አያምንም ወይም ማመን አይፈልግም፡፡ ስለዚህም አእምሯዊ የጤናማነት ስሜት እየተሰማው ስለማይሳቀቅ በፊቱ ላይ ምንም ምልክት አይታይበትም፡፡ ይህ ደግሞ ትልቅ በሽታ ነው፡፡ በሌላ በኩል ለምሣሌ እኔ በሁለት መቶ ብር የገዛሁትን ሳልቫጅ ሸሚዝ ለባለቤቴ ወይም ለጓደኞቼ በአምስት መቶ ብር እንደገዛሁት ብዋሽ በጥሞና የሚከታተለኝ ሰው ካለ ውሸቴን መሆኑን መረዳት አያቅተውም፤ ምክንያቱም ከፊቴ አንዳች ምልክት ያሳብቅብኛልና ይታወቅብኛል፤ በዚያ ላይ ጥቂት ለማስመሰልም ቢሆን ልምድ ያስፈልጋል፡፡ ስለዚህ የአቢይ ዓይነት ውሸትና የጤናማ ሰዎች ውሸት ለየቅል መሆናቸውን መረዳት ይገባል፡፡
ስለውሸቶቹ ከማንሳታችን በፊት ስለዚህ ሰውዬ ሥነ ልቦናዊ ማንነት በመጠኑ እንቃኝ፡፡ ከፍ ሲል ለመግለጽ እንደተሞከረው እርሱን የከበቡት ሰዎችም በእርሱ ምርጫ ከየሥርቻው የተለቃቀሙና በትምህርትም፣ በዕድሜም፣ በሥነ አእምሯዊ ደዌም ከእርሱ እምብዝም የማይሻሉ መሆናቸውን ደግሞ በእግረ መንገድ እንረዳ፡፡ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ በግልጽ በአደባባይ እየተሰደቡና እየተወረፉ አብረው አይቀጥሉም ነበር፤ ከማጨብጨብ ባለፈ አንዳችም ተቃውሞ የማያሰሙትም በታኅተ-ስብዕናቸው ምክንያት ነው፡፡ በቅርጽ እንጂ በይዘት ሰው አይደሉምና፡፡ ስለሆነም ሆዳቸውና ጥቅማቸው በልጦባቸው እሱ እስኪገረሰስ ድረስ አጅበውት ይቆያሉ፡፡ ለምሣሌ በአሁኑ ሰዓት ሁሉም ባለሥልጣናትና ሚኒስትሮች ናዝሬት ውስጥ በአንድ አዳራሽ ተከርችሞባቸው ከቤተሰብም ከወዳጅ ዘመድም ተለይተዋል፡፡ ከዓለምም ከኢትዮጵያም እንዲለዩ ተደርገው ሩቅ ብዕሲ ሆነዋል፡፡ ባለሥልጣንነት እሥር ቤት መግባት እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ዕብዱ ሰውዬኣቸው በቁጥጥሩ ሥር አውሎ ከማንም ጋር እንዳይገናኙ እንዳደረጋቸውና በደኅንነት ሰዎች ክትትል ውስጥ ገብተው ሌት ከቀን በሰቀቀን የተሞላ አስቀያሚ ሕይወት እንዲገፉ አድርጓቸዋል እየተባለ ነው፡፡
በሥነ ልቦናው የዕውቀት ዘርፍ የሚጠቀሱ ብዙ የህመም ዓይነቶች አሉ፡፡ እንደመጥፎ አጋጣሚ ሆኖ አቢይ አህመድ ከሞላ ጎደል የሁሉም አእምሯዊ ህመሞች ባለቤት ነው፡፡ ለዚህም ነው አንዳችም ሀፍረት ገጽታው ላይ ሳይታይበት ሁሉንም የሥነ ልቦና ደዌያት የሚያሳየን፡፡ የተወሰኑትን ማየት እንችላለን፡፡
Pathological liar – አቢይ ካልዋሸ መኖር የሚችል የማይመስለው ሆኖ እንደሚሰማው ማመን እችላለን፡፡ ይህን እምነታችንን የሚያዳብርልን ሃቅ ደግሞ አቢይ መዋሸት ሳያስፈልገው ሁሉ ለመዋሸት የሚገደድ መሆኑን ስንረዳ ነው፡፡ ለምሣሌ በሰሜን ሸዋና በጎጃም አካባቢ ዝናብ እንዲጥል ያደረግነው እኛ ነን ማለቱ ለምን አስፈለገው? በ2030 በዓለም ከሚኖሩ ሁለት ኃያላን መንግሥታት አንደኛዋ ኢትዮጵያ ናት ብሎ መወሻከት ለምን አስፈለገው? ማን ሆዱ ላይ ቆመና ዋሽ አለው? ሰሞኑን ደግሞ በ2100 በዓለም ከሚገኙ ሰባት ኃያላን መንግሥታት አንደኛዋ ኢትዮጵያ ናት ማለቱ ምን ይፈይዳል? ማንስ አስገደደው? … ስለዚህ ካልዋሸ መኖር እንደማይችል ራሱን አሳምኖ መሣቂያ መሣለቂያ መሆንን መምረጡን እንገነዘባለን፡፡ ይህ ደግሞ ሥነ ልቦናዊ ልክፍት ነው፡፡ ተሰሚነትን ለማግኘት፣ መድረክ ለመቆጣጠር ወዘተ. ሲሉ አንዳንድ በቅርብም በሩቅም የምናውቃቸው ሰዎች ይህን መሰል በሽታ የሚያጠቃቸው ጓደኞች ያሉን ሰዎች እንኖራለን፡፡ ይህ ጠባይ በተራ ጓደኝነት ደረጃ ቢሆን ጉዳቱ ትንሽ ነው፡፡ በሀገር መሪ ደረጃ ሲከሰት ግን እንደምናየው ሀገርን ገደል እስከመክተት ያደርሳልና አደጋው የከፋ ነው፡፡ የአቢይ ውሸት ከዚህ አንጻር የሚታይ ነው፡፡
Megalomaniac – አንድ ሰው ራሱን ከሚገባውና ከእውነቱም አስበልጦ ትልቅ ቦታ ሲሰጥ በዚህ ህመም እየተሰቃዬ እንደሆነ ይገመታል፡፡ ራሱን የሁሉም ሙያዎች ባለቤት ያደርጋል፤ ከእሱ በላይ ዐዋቂ ላሣር ነው፡፡ በሁሉም የሙያ ዘርፎች የብፁዕነት ስሜት ይሰማውና ልክ እንደ አቢይ አህመድ ፓይለቶችን ሰብስቦ ስለአየር ማብረር፣ ሀኪሞችን ሰብስቦ ስለመርፌ መውጋትና ስለቀዶ ህክምና፣ የጦር ጄኔራሎችንና የመስመር መኮንኖችን ሰብስቦ ስለውጊያ ሥልት፣ መምህራንን ሰብስቦ ስለፔዳጎጂ (ስለማስተማር ጥበብ)፣ የፊዚክስ ሊቃውንትን ሰብስቦ ስለ ማተር (ቁስ) እና ኢነርጂ (ኃይል) መስተጋብራዊ ውጤት፣ ማን ያውቃል የኔቢጤ ለማኞችንም ሰብስቦ ልብን ስለሚያራሩ የልመና ዓይነቶች ሊያሰለጥንና ሊያስተምር ይችላል፡፡ አቢይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጣ ጀምሮ ሲያደርግ የምናየውም ይህንን ነው፡፡ አለመታደል ነው፡፡ ይህ ጠባይ በተራ ዜጋ ቢታይ በከንፈራዊ የሀዘን መግለጫ ታዝኖለት በቀላል በታለፈ፡፡ በመሪ ደረጃ ሲታይ ግን አደጋው ትልቅ ነው፡፡ እያየነው እኮ ነው – ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያምን ቢሮህ ጠርተህ ስለመልክዓ ምድር ማብራሪያ መስጠት ምን ይባላል? ደግሞ እኮ ከአንደኛ ደረጃ የዘለለ ትምህርት ቢኖረው ባልከፋ፤ በጥራዝ ነጠቅም ቢሆን ትንሽ ዕውቀት እንዳለው ይገመትና መታገስ ይቻላል፡፡ ይህ ሰው ግን ፍጹማዊ ማይም ሆኖ ይህን ያህል ድፍረት መላበሱ በርግጥም ሊቀ ሣጥናኤል ቢቀናበት አይፈረድበትም፡፡
Paranoid – ሰዎች ይጠሉኛል ብሎ ማመንና የሚጠሉት የመሰሉትን ማጥፋት ወይም ዕድላቸው ካማረ ከፊት ገለል እንዲሉ ማድረግ፡፡ አቢይ አህመድ አይጥመድህ እንጂ ከጠመደህና ከጠላህ እንጦርጦስ ሳይከትህ ዕረፍት ብሎ ነገር አያውቅም፡፡ እነአምባቸው መኮንን፣ እነአሳምነው ጽጌ፣ እነሰዓረ መኮንን፣ እነጄኔራል ገዛዒ፣ … ስንቱን አንስተን ስንቱን ጥለን … በሚሊዮኖች ከተገደሉት ተራ ዜጎቻችን ጀምሮ ስንትና ስንት የቀለምና የጦር ሜዳ ጀግኖች በዚህ ድውይ ሰውዬ አልቀውብናል፡፡ አንድን ጄኔራልና አንድን የአካዳሚክስ ሰው ትልቅ ደረጃ ለማድረስ ስንት ድካምና ወጪ አለው፡፡ ይህ የሀገርና የሕዝብ ትርጉም ምንነት የማይገባው የዲያቢሎስ አሽከር አራት ኪሎን ተቆጣጠረና ሰው ብቻ ሳይሆን ባህላችንን፣ ሞራላዊ ስብዕናችንንና መንፈሣዊ ሀብታችንን ሁሉ አወደመብን፡፡ በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለማት ጥላቻ የተለከፈው ይህ አቢይ የሚባል ሰውና መላ ጀሌው አራት ኪሎን ከያዙ በኋላ በሀገራችን ላይ የወረደው መቅሰፍት በአሠርት ቀርቶ በምዕት ዓመታትም የሚያነሰራራና የሚመለስ አይመስልም፡፡ መሪዎች ፀረ-ኢትዮጵያ ሆነው ተመሪዎች ደግሞ በኢትዮያዊነታቸው ጸንተው በመሀላቸው በተነሣ የ30 እና የ40 ዓመታት የማያባራ ጦርነት ሀገራችን ያየችው አበሣ የታሪክ መዝገብ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ ነው፤ ደግነቱ ይህም ያልፋል፡፡
Narcissism – ናርሲሲዝም በስፋት የሚታወቅ ራስን ክልክ ባለፈ የማፍቀር በሽታ ነው፡፡ ይህ ሥነ ልቦናዊ በሽታ ስሙን ያገኘው በግሪክ አፈ ታሪክ ራሱን በእጅጉ እንደሚያፈቅርና መልከ መልካምነቱን ለማየት ወንዝ እየወረደ ፊቱን ውኃው ላይ ይመለከት እንደነበር ከሚነገርለት ናርሲስ የተባለ ግሪካዊ ባለታሪክ ነው፡፡ አቢይ አህመድም ምንም እንኳን በመስታወት ቴክኖሎጂ መምጣት ምክንያት ወንዝ ወርዶ ፊቱን እንዲያይ የማይገደድ መሆኑ በታሳቢነት ተይዞ በራሱ ፍቅር የተጠመደና ሌላውን ከእግሩ እጣቢም የማይቆጥር፣ ኩንስንስነትና መቆነጃጀትን አጥብቆ የሚወድ ለቃሉ ይቅርታ ይደረግልኝና ሴታ ሴት ፍጡር መሆኑን መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡ ይህ በራሱ ችግር አይደለም፡፡ ግና ራሱን የሚያፈቅር ሰው ለሌሎች ሰዎች ሃሳብም ሆነ አመክንዮና ፍልስፍና ቁብ ስለሌለው ይህ ዓይነቱ ፍናፍንታም ሰው ትልቅ ሥልጣን ሲይዝ ሀገር የምትበደል መሆኑ ነው ችግሩ፡፡ ስለሌሎች ሥነ ልቦናዊ ህመሞቹ በሌላ ጊዜ እንገናኝ፡፡