መኢአድ ላለፉት ፫ዓሥርት ዓመታት ና ከዚያም በላይ በመላ ሃገሪቱ ድርጅታዊ መዋቅሩን ለመላ ህዝባችን ሠላም ደህንነት ዲሞክሪያሢዊ ሥርአት ና ፍትህ ሠፍኖ የህግ የበላይነት ተረጋግጦ በህዝብ ላይ ግፍና ጭቆናን ብሎም አሥከፊ ወንጀሎችን የፈፀሙ ሁሉ በፍትህ አደባባይ ላይ ቆመው የሚጠየቁበትን የማያቋርጥ ህዝባዊ ስርአት እንዲሰፍን ሲል ትግል እያደረገ ያሉ የፅኑአን ድርጅት መሆኑ ይታወቃል በዚህ ታሪካዊ የትግል ሂደት ውስጥ ለጀሮ የሚሠቀጥጡ ለአእምሮ የሚከብዱ ከባባድ ጊዜያትን በፁኑ ትግል አሳልፏል ብዙ መሪዎቹን መስዋእት ሁነዋል ፤ አባላቱንና ደጋፊዎቹንም በአሰቃቂ ሁኔታ አጥቷል። በለውጥ ስም ወደ ስልጣን የመጣው ሃይል ከዘርኝነት ከረጢት ያልወጣና ዜጎችን በአደገበት ዋልታ ረገጥ የማንነት ፖለቲካዊ እሣቤውን ለመሸፈን አገር በሚል ፖለቲካዊ ሸፍጥ ተጀቡኖ ሢያበቃ ልክ እንደ አሣዳጊዎቹ መሥመሩ አንድ አቅጣጫ ብቻ አለመሆኑ ተደማምሮ የትግላችን ሜዳ ከማጥበቡም በላይ ሂደቱን በማወክ በማደብዘዝ በማፈንና ጭራሹን በመዝጋት የምናደርገውን ሠላማይና ህጋዊ የትግል መሥመራችን የማያከብር ከመሆኑም በላይ የአባሎቻችን በየደረጃው የሚገኙ መሪወቻችን በህይወት የመኖር ዋስትና በማሣጣት በምን ምክንያት ና በማን ሊጣስ እንደሚችል ለመገመት እሥክንቸገር የደረሠ ጉዞ ሆኖብን መውጪያ ና መግቢያ በማሣጣት ለአገራችን አንድነት ፍትህ ሠላም ና ድህንነት ለተራበው ህዝባችን በፁኑ መሠረታችን ቁመን የምናደርገውን ወሣኝ ትግል ፈፅሞ ለማሥቆም በመላ አገሪቱ ያሉ አባሎቻችን ና አመራሮች በማፈን ሠበባ ሠበብ እየፈጠሩ በማጎር ና በሌላ ሥልት በማሣፈን ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍና መከራ እንዲደርሥብን በማድረግ የማይቆመውን ትግላችን ለማሥቆም ታቅዶ እየተፈፀመብን መሆኑ ግልፅ ነው : :
ለዚህ ማሳያው የድርጅታችን ወጣት አመራር የሆነው ጓዳችንንና ዘላለም ሌሎች ወገኖቻችንን በመተከል ዞን በሥራ ላይ እንዳሉ በ10/10/2017 ዓ.ም ሸኔ የሚል የዳቦ ሥያሜ በተሠጠው ዘመናዊ መሣሪያን ታጥቆ እንደፈለገ ሠውን የሚያግት የሚሠውር የሚያርድ ና ግፍን አዘምኖ በግፍ እየፈፀመ ያለ ቅምጥል ቡድን አባላችን ከሌሎች ወገኖቻችን ጋር ታፍኖ ተወሥዶ የ
ደረሠበት አለመታወቁን እጅግ ልብ ሠባሪና አሣዛኝ መሆኑን ነገሮችን የበለጠ አጠናክረን የሚከፈለውን ዋጋ ሁሉ ከፍለን የህዝባች ሙሉ ነፃነት ለማረጋገጥ እንድንቆርጥ ሢያደርገን ቆይቷል እንጂ ሠብሮን አያውቅም። ከዚህ ጋር በተያያዘም ላለፉት 50 ዓመታት ሥርአታዊ ና መዋቅራዊ በሆነ ግልፅ የዘር ምንጠራ ሥትራቴጅ ተጠቂ በሆነው የአማራው ወገናችን ላይ የተፈፀመው ና ተጠናክሮ እየተፈፀመ በቀጠለው ፍጅት ከወልቃይት ራእያ አሦቦት ገዳም ወተር ጋራሙለታ በደኖ አርማጉጉ በደራ በሻሸመኒ በዝዋይ በምእራብ ሸዋ በወለጋ (የአማራወች የመታረጃ ቄራ ) በመተከል እሥከ አሁኗ ሠአት የሚፈፀመውን ግፍ በማጠናከር በሠሞነኛው ግልፅ ፍጅት አካል በምሥራቅ ወለጋ በጉቶ ጊዳና ወረዳ በጃርሦ ቀበሌና በሌሎች አካባቢዎች የደረሠው የወገኖቻችን ጅምላ ፍጅት በፅኑ እያወገዝን ዛሬ ባይቻል ነገና ከነገ ወዲያ በቀጥታም ይሁን በተዛዋዋሪ ይህን ወደር የለሽ ግዙፍ ወንጀል የፈፀሙ ና ያሥፈፀሙ አካላትን እንዲሁም የሚፈፀመውን ግፍ የማሥቆም ግዴታ ያለባቸው ሃላፊወች ዛሬ ላይ የሚጠየቁበት ህግ ባይኖርም ነገም ሆነ ከነገ ወዲያ መጠያቀቸው አይቀሬ ቢሆንም ትላንት ለዛሬ ዛሬ ላይ ለነገ ና ከነገ ወዲያ በምናደርገው የማያቋርጥ ትግላችን ልናረጋግጥ እንወደል !
“አንዲት ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!”

ሰኔ 13/2017 ዓ.ም
አዲስ አበባ