ካላመረርን፣ ካልጨከንን እንጠፋለን – ግርማ ካሳ

June 1, 2023
ይህ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነው፡፡ ራሱን መከላከያ ነኝ ብሎ የሚጠራው ኦነጋዊ አሸባሪ ሰራዊት በከባባድ መሳርያና በድሮች፣ ከርቀት ቤተ እምነቶችም፣ ገዳማትን በዚ መልኩ እያወደመ ነው፡፡ መንኮሳት እየሞቱ ናቸው፡፡ይሄ ሉ ሲያደርግ፣ ከደጀን ወደ አማኑእል ባለው መንገድ መንገዶች ታጣቂዎችንና ከባባድ መሳሪያዎች አስጨኖ ፣ ያለ ምንም ችግር በማመላለስ ነው፡፡
ይህ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነው፡፡ ራሱን መከላከያ ነኝ ብሎ የሚጠራው ኦነጋዊ አሸባሪ ሰራዊት በከባባድ መሳርያና በድሮች፣ ከርቀት ቤተ እምነቶችም፣ ገዳማትን በዚ መልኩ እያወደመ ነው፡፡ መንኮሳት እየሞቱ ናቸው፡፡ ይሄ ሉ ሲያደርግ፣ ከደጀን ወደ አማኑእል ባለው መንገድ መንገዶች ታጣቂዎችንና ከባባድ መሳሪያዎች አስጨኖ ፣ ያለ ምንም ችግር በማመላለስ ነው፡፡

የስደት ኑሮ የጀመርኩት ከ30 አመት በፊት ነው፡፡ በ23 ዓመቴ፡፡ ወጣት እያለሁ፡፡ እስከ ምርጫ 97 ድረስ ብዙም በአገር ጉዳይ ትኩረት አልሰጥም ነበር፡፡ በ97 ነው እንደ አጋጣሚ አዲስ አበባ ስለነበርኩ፣ የተግባረ እድ ተማሪዎች በሰደፍ ሲደበደቡ አይቼ፣ እንዲህ አይነት ነገር ኢትዮጵያ ውስጥ እስኪቆም የድርሻዬን አበረክታለሁ ብዬ በአገር ጉዳይ መንቀሳቀስ የጀመርኩት፡፡

350265097 1001688841243353 8769580985828745840 n

ከ97 ጀምሮ በነበረኝ እንቅስቃሴ በሰላማዊ ትግል ብቻ የማምን ሰው ነበርኩ፡፡ ያኔ ወያኔዎች ጋር የነበረን ችግር የፖለቲካ፣ የዲሞክራሲ ችግር ነበር፡፡ በወያኔዎች ጊዜ አንድ ሰው አርፎ ፣ ከፖለቲካው ርቆ ከተቀመጠ ማንም አይነካዉም ነበር፡፡ በወያኔዎች ጊዜ አሁን መብት ይረገጥ ነበር፣ ግን መኖር ይቻል ነበር፡፡ በማንነት ግድያ አልነበረም፡፡ መፈናቀል አልነበረም፡፡ ምንም ዜጋ በማንኛውም የአገሪቷ ግዛት ያለ ምንም ችግር ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ ስለዚህ በሰላማዊ ትግል ለውጦች እንዲመጡ ማድረግ ይቻላል በሚል ሰላማዊ ትግል ነበር የምደግፈው፡፡ህወሃት ወደ መቀሌ የተሰናበተችው በሰላማዊ የ እምቢተኝነት ትግል ነበር፡፡

አሁን የተለየ ነገር ነው ያለው፡፡ አሁን ጉዳይ የፖለቲካ መብትን፣ የዴሞክራሲ ጥያቄን የማከበርና ያለማስከበር አይደለም፡፡ ጉዳዩ የመኖርና ያለመኖር ጉዳይ ነው፡፡ አሁን አራት ኪሎ ያሉት መብት የሚገፉ ብቻ ሳይሆን የሚያስጨፈጭፉ፣ የሚጨፈጭጭፉ አረመኔዎች ናቸው፡፡ በመሆኑም እነዚህ ክፉና ጨካኝ፣ ናዚዛዊና ዘረኛ ቡድኖችን በማንኛውም መንገድ መታገልና ማስወገድ ያስፈልጋል፡፡ ሊገድሉ ሲመጡ መግደልንም ጨምሮ፡፡

“ጸሎት ነው የሚያስፈልገው፣ ጦርነት አያስፈልግም፡፡ ውጊያ አያስፈልግም፡፡ መገዳደል አያስፈልግም፡” ብለው ሞራሊቲንና ሃይማኖትን ሊሰብኩ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ፡፡ “”ሽምግልና፣ እርቅ” የሚሉ፡፡ ገዳዮች ሲገድሉ ዝም ብለው፣ የሚገደለው አልገደልም ብሎ እርሱም መግደል ሲጀምር ፣ስለ ሰላም ማውራት፣ ከገዳይነት በምንም አይተናነስም፡፡ ግብዝነትና አደርባይነት ነው፡፡

350687328 642281544429768 1035737819209520050 n

ክርስቲያን ነኝ፡፡ የክርስትና እምነቴ በህይወቴ እጅግ በጣም ትልቅ ቦታ አለው፡፡ ሰው ሲጎዳ ዝም አልልም በሚል በገር ጉዳይ እሳተፍለሁ እንጂ፣ ከምን ነገር በላይ የሚያስደስተኝ ቤተ ክርስቲያን ሄዶ ቃለ አምላክን ማዳመጥ፣ ቃለ አምላክን ማካፈል፣ መዝሙሮች መስማትና መዘመር ነው፡፡ የሰላምና የእርቅ አስፈላጊነት በሚገባ እረዳለሁ፡፡ ግን ለሁሉም ነገር መርህ ያስፈልጋል፡፡

ለነዚህ ሰዎች አንድ ጥያቄ ላቅርብላቸው፡፡ ቤታቸው ተቀምጠዋል፡፡ መሳሪያ አላቸው፡፡ የታጠቁ፣ የመንግስት ደህንነቶች ነን የሚሉ፣ የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ፣ የቤት በር ሰብረው ይገባሉ፡፡ ወንድ ልጆችን እየደበደቡ ይወስዳሉ፡፡ ሚስቶቻቸውንና ሴት ልጆቻቸውን ለመድፈር ይነሳሉ፡፡ ምንድን ነው የሚያደርጉት ? ጸሎት ማድረግ፣ ሰዎቹን መለመንና መለማመጥ፣ ከዚያ በኋላ ሰዎቹ ያደረጉት ወንጀል ፈጽመው፣ “ወንድ ልጆቼን ወሰዱብኝ፣። ሚስቴንና ሴት ልጆቹእ ደፈሩብኝ” ብሎ ማለቃቀስና እንደ ኢትዮ360 ያሉ ሜዲያዎች ጋር ደውሎ ብሳቶ ማሰማት ነው ???? ቤታቸው ያለውን መሳሪያ ተጠቅመው ሌላው ቢቀር የሚስቲቻቸውንና የሴት ልጆቻቸውን ክብር አያስጠብቁም ???

ቤታችን ቅያችን፣ ሰፈራችን፣ አካባቢያችን፣ በበአሸባሪዎች፣ በዘረኞች፣ በክፉዎች፣ በናዚዎች፣ በጨፍጫፊዎች ሲደፈር፣ መሳሪያ ያለን መሳሪያችንን ወልውለን፣ የሌለንም በእጃችን እየቧጨርን፣ ሌላው ቢቀር ራሳችንን ማዳን ባንችልም፣ ልጆቹን፣ ሚስቶቻችንን አረጋዊ እናትና አባቶቻችን ማዳን መቻል አለብን፡፡

ደግሞ እመኑኝ፣ ሁሉም ሰው በሁሉም ቢታ ካመረረና ከጨቀነ፣ ከተነሳ እነዚህ ጉጅሌ የኦነግ/ኦህዴድ አሸባሪዎች፣ የአብይ አህመድና የኢጆሌ ጁላ ታጣቂዎች እንደ ጉም ነው የሚተኑት፡፡

ይህ ምስራቅ ጎጃም ዞን፣ ደብረ ኤሊያስ ወረዳ ነው፡፡ ራሱን መከላከያ ነኝ ብሎ የሚጠራው ኦነጋዊ አሸባሪ ሰራዊት በከባባድ መሳርያና በድሮች፣ ከርቀት ቤተ እምነቶችም፣ ገዳማትን በዚ መልኩ እያወደመ ነው፡፡ መንኮሳት እየሞቱ ናቸው፡፡
ይሄ ሉ ሲያደርግ፣ ከደጀን ወደ አማኑእል ባለው መንገድ መንገዶች ታጣቂዎችንና ከባባድ መሳሪያዎች አስጨኖ ፣ ያለ ምንም ችግር በማመላለስ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ነገሩ እንዲህ ነው ባሳለፍነው ታህሳስ 15 በተካሄደው ብልጽግና ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ እጃቸውን አውጥተው ተናገሩ እኔ አቅቶኛል የአማራ ክልል ቀውስ ማስተዳደር አልቻልኩም ብለው ተናገሩ በዚህ ጊዜ

“አንተን ለማኝ አደርጋለሁ” አቢይ አሕመድ ለአማራ ክልል ፕረዚዳንት ለአረጋ ከበደ የሰጠው ማስጠንቀቂያ

January 31, 2025
ከቴዎድሮስ ሃይሌ የምናከብራቸው ጀነራል ተፈራ ማሞ ሰሞኑን አደባባይ ወጥተው አድምጠናል:: የጀነራሉ ጤንነትና ደህንነት ሲያሳስበን ለቆየነው ወገኖች ሁሉ በጥሩ ቁመና ላይ ሆነው በማግኘታችን የሕሊና እረፍት ሰጥቶናል:: አሁንም ባሉበት ሰላሞት እንዲበዛ ምኞታችን ዳር የለውም::

እስክንድር ነጋ እና ጀነራል ተፈራ ማሞ ከድል ለዲሞክራሲ እስከ ፉኖ ተሰማራ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) ዛሬም እንደ ትናንቱ አያሌ ምሁራንና ታዋቂ ነን ባይዎች ስለብሔራዊ ሽምግልና እርቅ ይደሰኩራሉ፡፡ ያለምንም ሐፍረት ቅዱሱን ሽምግልናን ከምእራብ ከተሸመተው ኤፍሬም ይሳቃዊ ድርድር ጋር እያምታቱ የአያት የቅድመ አያቶቻችንን የተባረክ የሽምግልና ሐብት ያበላሻሉ፡፡ ሽምግልና በመለኮት

ፍትህ የሌለው ሽምግልናና እርቅ ሥራ እንደሌለው እምነት የሞተ ነው!

Go toTop