ኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ለሶስት አስርተ ዓመታት ክህደት እንደተፈፀመባቸዉ እና ይህም እንደሚሆን ቀድመዉ የነቁ እና የበቁ ኢትዮጵያዉያን ዕዉነት እና ፍትህ ተነፍገዉ በሞትም ፤በስደትም ተለይተዋል ፡፡
ይህ ሁሉ በምድር ላይ ታይቶ ማይታወቅ ዜጎች በማንታቸዉ እና ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ እንደ ወንጀለኛ ሆነዉ የዘር ፍጂት ፣ ስደት እና ዕንግልት ሲደርስባቸዉ በራሳቸዉ አገር እና ቅየ ለምን ያለ አልነበረም ፡፡
ይህም ዕዉነት ተናጋሪ ለዕምነት አዳሪ ሲጠፋ ፀረ -ህዝብ እና ኢትዮጵያ ጠሎች ከለላ እና መከታ የማግኘት ያህል ሲሰማቸዉ በህዝብ እና አገር ላይ ያደረሱት በደል እና ክህደት ሊጠየቁ ሲገባ በዝምታ መታለፉ ዛሬ ላይ ለሆነዉ ሁሉ ትክክለኛነታቸዉን በመታቀብ ቄሱም ፤መፅሀፉም አይቶ ባላየ አልፏቸዉ በማን አለብኝነት በዜጎች ህይወት እና በአገር ጉዳይ ላይ ፈራጂ መሆናቸዉን ከዚህ ከዘመናችን ትዕይንት በላይ አስረጂ አይኖርም ፡፡
ማንነትን ፣ዕምነትን እና አመለካከትን እየነጠሉ በጥላቻ እና በበታችነት መንፈስ ኢትዮጵያዊነት ሆነ ዓማራነት የማራያም ጠላት አድርጎ ለሶስት አስርተ ዓመታት የመከራ ቋጥኝ መናድ ኢትዮጵያን ከነገናና ታሪኳ በነበር ለማስቀረት በተደረገ ሁሉንአቀፍ የጥፋት ርብርብ አንድም ተቋም የፖለቲካ፣ የኃይማኖት ሆነ የማህበረሰብ ተቋም ተዉ ባይ አለመሆን በአገር ክህደት እና በህዝብ ዕልቂት መታቀብ ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቋማት የተለማመዱት በመሆኑ ዛሬ ላይ በቱርክ ርዕደ መሬት ቢያንስ አንድ ሠዉ ሳይሞት አይቀርም ብሎ የሚያስተጋባ መገኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ላይ ሲደርስ ጥቃት እና ግጭት ማለት ተአቅቦ(አድር ባይነት) በእጂጉ የእኛ ጊዜ ወረርሽኝ መሆኑን የሚረዳ አለመኖሩ በመከራ ላይ መከራ ጫንቃችን ለምዶታል ፡፡
በራሳችን እና በአገራችን ጉዳይ ዕየሞትን አለን የሚል የቁም ቅዠት ተአቅቦ ከኢህአዴግ መማራችን እኛ እና አድርባይነት አጥፊ እና ጠፊ ሆነን ዛሬ ላይ ለይቶልን ካለፈ ታሪክ እና መከራ መማር አቅቶን ምፅአተ ጥፋት እና ሞትን በዕንቅልፍ ለማሳለፍ በቀቢፀ ተስፋ ሰክረናል፡፡
ከ1983 ዓ.ም ኢትዮጵያን የማጥፋት ሽግግር ጊዜ አስካሁን የደረሱትን እና እየደረሱ ያሉትን የአገር እና የህዝብ የመከራ ምዕራፎች ብናይ የሽግግር እና ህገ ኢህአዴግ ፤ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ፣ የ1997 ዓ.ም ምርጫ ፣ የ2010 ዓ.ም ህዝባዊ የለዉጥ ጥያቄ እና የ2013- አስካሁን የህወኃት ኢትዮጵያን በተለይም የሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ የኢትዮጵያ ግዛቶችን መዉረር እና መመዝበር ….ከዚህ በላይ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በጠላት እና ግብአበሮች ጥርስ ዉስጥ መግባታቸዉን እና ይህም ጠላት እንደማይተኛ አለማወቃችን የትናንቱን ረስተን የዛሬ እና አዲስ ማድረግ የዝገት ምልክት ፡፡
ለአገር ሉዓላዊነት እና ለህዝብ ነፃነት ዋጋ የከፈሉት የመከራ እና የዕስር ደሴት በሆነች አገር ሠላም እና መረጋጋት እያሉ ተደናግሮ መደነጋገር ሞት እና መከራ በሚፈራረቁባት ምድር እየኖሩ በሠዉ ልጂ ደም እና ህይወት ከመሳለቅ በላይ ኃጢያትም ወንጀልም አይኖርም ፡፡
አንድነት ኃይል ነዉ !
Allen Amber !