March 4, 2023
5 mins read

አገር ሲሞት እያየ ከማያይ በላይ ኃጢያተኛ እና ወንጀለኛ ምን አለ ?

abiyኢትዮጵያ እና ህዝቦቿ ለሶስት አስርተ ዓመታት ክህደት እንደተፈፀመባቸዉ እና ይህም እንደሚሆን ቀድመዉ የነቁ እና የበቁ ኢትዮጵያዉያን ዕዉነት እና ፍትህ ተነፍገዉ በሞትም ፤በስደትም ተለይተዋል ፡፡

ይህ ሁሉ በምድር ላይ ታይቶ ማይታወቅ  ዜጎች በማንታቸዉ እና ኢትዮጵያዊ መሆናቸዉ እንደ ወንጀለኛ ሆነዉ የዘር ፍጂት ፣ ስደት  እና ዕንግልት ሲደርስባቸዉ በራሳቸዉ አገር እና ቅየ ለምን ያለ አልነበረም ፡፡

ይህም ዕዉነት ተናጋሪ  ለዕምነት አዳሪ ሲጠፋ ፀረ -ህዝብ እና ኢትዮጵያ ጠሎች ከለላ እና መከታ የማግኘት ያህል ሲሰማቸዉ በህዝብ እና አገር ላይ ያደረሱት በደል እና ክህደት ሊጠየቁ ሲገባ በዝምታ መታለፉ ዛሬ ላይ ለሆነዉ ሁሉ ትክክለኛነታቸዉን በመታቀብ ቄሱም ፤መፅሀፉም አይቶ ባላየ አልፏቸዉ በማን አለብኝነት በዜጎች ህይወት እና በአገር ጉዳይ ላይ ፈራጂ መሆናቸዉን ከዚህ ከዘመናችን ትዕይንት በላይ አስረጂ አይኖርም ፡፡

ማንነትን ፣ዕምነትን እና አመለካከትን እየነጠሉ በጥላቻ እና በበታችነት መንፈስ ኢትዮጵያዊነት ሆነ ዓማራነት የማራያም ጠላት አድርጎ ለሶስት አስርተ ዓመታት የመከራ ቋጥኝ መናድ  ኢትዮጵያን ከነገናና ታሪኳ  በነበር ለማስቀረት በተደረገ ሁሉንአቀፍ  የጥፋት ርብርብ  አንድም ተቋም የፖለቲካ፣ የኃይማኖት ሆነ የማህበረሰብ ተቋም ተዉ ባይ አለመሆን  በአገር ክህደት እና በህዝብ ዕልቂት መታቀብ ኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ተቋማት የተለማመዱት በመሆኑ ዛሬ ላይ በቱርክ ርዕደ መሬት ቢያንስ አንድ ሠዉ ሳይሞት አይቀርም ብሎ የሚያስተጋባ መገኛ ብዙኃን ኢትዮጵያ ላይ ሲደርስ ጥቃት እና ግጭት ማለት ተአቅቦ(አድር ባይነት) በእጂጉ የእኛ ጊዜ ወረርሽኝ መሆኑን የሚረዳ አለመኖሩ በመከራ ላይ መከራ ጫንቃችን ለምዶታል ፡፡

በራሳችን እና በአገራችን ጉዳይ ዕየሞትን አለን የሚል የቁም ቅዠት  ተአቅቦ ከኢህአዴግ መማራችን እኛ እና አድርባይነት አጥፊ እና ጠፊ ሆነን ዛሬ ላይ ለይቶልን ካለፈ ታሪክ እና መከራ መማር አቅቶን ምፅአተ ጥፋት እና ሞትን በዕንቅልፍ ለማሳለፍ በቀቢፀ ተስፋ ሰክረናል፡፡

ከ1983 ዓ.ም ኢትዮጵያን የማጥፋት ሽግግር ጊዜ አስካሁን የደረሱትን እና እየደረሱ ያሉትን የአገር እና የህዝብ የመከራ ምዕራፎች ብናይ የሽግግር እና ህገ ኢህአዴግ ፤ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ፣ የ1997 ዓ.ም  ምርጫ ፣ የ2010 ዓ.ም ህዝባዊ የለዉጥ ጥያቄ  እና የ2013- አስካሁን የህወኃት ኢትዮጵያን በተለይም የሰሜን ምዕራብ እና ማዕከላዊ የኢትዮጵያ ግዛቶችን መዉረር እና መመዝበር ….ከዚህ በላይ በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት በጠላት እና ግብአበሮች ጥርስ ዉስጥ መግባታቸዉን እና ይህም ጠላት እንደማይተኛ አለማወቃችን የትናንቱን ረስተን የዛሬ እና አዲስ ማድረግ የዝገት ምልክት ፡፡

ለአገር ሉዓላዊነት  እና ለህዝብ ነፃነት ዋጋ የከፈሉት የመከራ እና የዕስር ደሴት በሆነች አገር ሠላም እና መረጋጋት እያሉ ተደናግሮ መደነጋገር ሞት እና መከራ በሚፈራረቁባት ምድር እየኖሩ በሠዉ ልጂ ደም እና ህይወት ከመሳለቅ በላይ ኃጢያትም ወንጀልም አይኖርም ፡፡

አንድነት ኃይል ነዉ !

Allen Amber !

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ ¹⁵ የምድርም ነገሥታትና መኳንንት ሻለቃዎችም ባለ ጠጋዎችም ኃይለኛዎችም ባሪያዎችም ጌቶችም ሁሉ በዋሾችና በተራራዎች ዓለቶች ተሰወሩ ፥ ¹⁶ ተራራዎችንና   በላያችን ውደቁ በዙፋንም ከተቀመጠው ፊት ከበጉም ቍጣ ሰውሩን ፤ ¹⁷ ታላቁ የቁጣው ቀን  መጥቶአልና ፥ ማንስ ሊቆም ይችላል ? አሉአቸው ። ራእይ 6 ፤  15_17 ይኽ የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ። የኢየሱስን ልደት ሰናከብር የየሐንስ ራእይን ማንበብ ጠቃሚ ይመስለኛል ። ምክንያቱም በመጨረሻው ዘመን

ከኢየሱስ የፍርድ ቀን በፊት በህሊናችን ውስጥ ፍቅርን ለማንገስ እንጣር 

የምጣኔ ሀብታዊ ፍጥ፣ የፖለቲካ፣ የእውነትና የሰብአዊ መብት ታጋይ፣ የአመኑበትን ነገር ለመናገር እንደ ፖለቲከኛ በቃላት ሳያሽሞነሙኑ ቀጥታ የሚናገሩት የሀገሬ ኢትዮጵያ ታላቅ ሰው ነበሩ “ዘር ቆጠራውን ተዉት፤ የአባቶቻችሁን ሀገር ኢትዮጵያን አክብሩ!”  አቶ ቡልቻ ደመቅሳ

ሀገር ወዳዱ አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

January 6, 2025
ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ? ዛሬ፣ 2025 ዓ/ም ላይ ብንገኝም በዝንጋታ ገመድ ወደ ሞት እየተጎተትን እንደሆነ አናውቅም። (ሁል ጊዜ የሚሞተው የገነዝነው ይመስለናል። ) “ገብርዬ ነበረ

ግን ይህ ሁሉ ወጣት የት ገባ?

January 3, 2025
Go toTop