ኦነግ ሸኔ ብሎ ነገር የለም ። ያለው ሥለ ገንዘብ ብሎ ሰው የሚያርድ የአውሬ ስብስብ ነው ። ያለው በግፍ በጭካኔ እና በስርቆት ሥለሚሰበሰብ ሀብት እና ንብረት የሚጨነቅ የአውሬ መንጋ ነው ። ያለው እየተዘረፈ ሥለሚበላ ሥጋ ብቻ የሚያሥብ ለሆድ ብቻ የሚኖር ከአውሬና ከእንስሳ ጎራ የሚመደብ ፀረ ሰው ፣ ፀረ ህብረተሰብ ፣ ፀረ አገርና ትውልድ ” በለዔ ሰብ ” ቡድን ነው ።
ይህንን ፀረ ሰው እና አገር አፍራሽ ” በላዔ ሰብ እና መንጋ ቡድን ” መሐል ከተማ ሆነው ( በመላው አትዮጵያ በተለይም በኦሮሚያ ክልል ውሥጥ ሆነው ) የሚመሩትና የሚደግፉትም ትላንት ምንም የሌላቸው ዛሬ በለባንክና ባለፎቅ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው ። እነዚህ ግለሰቦች ከግብፅ ፕላን ቢ ጋር በመቀናጀትም ” የአሸባሪ ተግባር በመፈፀም የኢትዮጵያን ህዝብና መንግሥት እንዳይረጋጉ ማድረግ ። ” የሚለውን ዕቅድ በማስፈፀም ላይ ናቸው ። ትላንት በአረብ በረሐዎች አይሲስ አንገት ይቀላ ነበር ። ዛሬ ደግሞ በኦሮሞ ሥም ተደራጅቶ አንገት የሚቀላ የግብፅ ተላላኪ አውሬ ቡድን ፈጥረወልናል ።
ምናልባትም የሰውን አንገት ማረድ እንዴት ቀላላ እንደሆነ የሚያሰለጥን ሤጣን በከፍተኛ ብር ክፍያ ከዚህ ኦነግ ሸኔ ተብዬ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ እና የሽብር ቡድን ጋር እንዳለም ጠርጥሩ ። ትላንት በህውሃት ቤት ነበረ ። ዛሬ ደግሞ በኦነግ ሸኔ ተብየው ቤት ሥለታም ቢላውን ከፍ አድረጎ ይዞ እብድ እብድ እየተጫወተ ነው ። ይህንን የእብድ ተግባሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ያላሰለሰ ድጋፍ የሚያደርጉለት የጥቅም ተጋሪዎቹ በመንግሥት ማዋቅር ውሥጥ የተሰገሰጉ ምናልባትም ከፍተኛ አመራራ የሆኑ ሆዳም ግለሰቦች ሊሆኑ እንደሚችሉ ህዝብ ከጠረጠረ ቆየ ። ለዚህ ዋቢ የሚሆነን ደግሞ በኃቅ ህዝብን የሚያገለግሉ የኦሮሚያ ክልል አመራሮች በእነዚህ አውሬዎች በግፍ ና በጭካኔ መገደላቸው ብቻ ሳይሆን ፣ አያሌ የኦሮሚያ ፖሊሶች እና ልዩ ኃይሎች ለግዳጅ መሰማራታቸው አሥቀድሞ ለአውሬው እየተነገረ በአሳዛኝ ሁኔታ በጉዞ ላይ ሳሉ በድንገተኛ ጥቃት ማለቃቸው ነው ። ይህ የሚያሥረዳን ” ኦነግ ሸኔ ” የተሰኘ ቡድን ያለመኖሩን ነው ። ያለው ከላ እስከታች በኔት ዎርክ የተደራጀ ፣ አገር አፍራሽ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳይ አውሬ ቡድን ነው ። ይኽ ቡድን ለዘረፋ ፣ በጭካኔ ለማረድ እና ለመግደል በጠላቶቻችን የተፈጠረ ሆኖም ሆዳም እና ህሊና ቢሥ ምሁራን ፣ ትልቅ የሚባሉ ግን ″ የትኋን አሥተሳሰብ ያላቸው ″ ፖለቲከኞች እና ባለሥልጣናት ፣ በብርቱ የሚደግፉት በመሆኑ መሐል አገር ድረስ ዘልቆ የጭካኔ ተግባር ይፈፅማል ።ይኽንን እኩይና ኩንን ተግባር በግልፅ እና በአደባባይ በፀሐይ ብርሀን ሲፈፅምም ሃይ የሚለው የጠፈውም በዚህ ምክንያት ነው ። የግል ሀብታቸውን እያደራጁ፣ ዶላራቸውን በውጪ እያሳበጡ እና እጅግ የተቀናጣ ኑሮ በሸገር እየኖሩ እንዴት ብለው ከጠላቶቻችን የሚያገኙትን ገንዘብ ከላዩ ላይ እየቆነጠሩ በመሥጠት ፣ ለዚህ ያበቁትን እና እነሱን ቱጃር ያደረጋቸውን የአውሬ ቡድን እንዴት ተው ! ይበቃል ! እረፍ ! ሰውን በመግደል እንደ አውሬ መኖርህ ይብቃ ሰው ሁን ! ይሉታል ። መጀመሪያ ራሳቸው ሰው ሳይሆኑ ሌላውን አውሬ አምሳያቸውን ወደ ሰው ለመቀየር እንዴትስ ይችላሉ ?
በነገራችን ላይ የፌደራል መንግሥቱ በፀጥታ ኃይሉ ውሥጥ የተሰገሰጉ በመጥፎ ሱስ የተበከሉ ፣ ለሱሳቸው ሲሉ አገር ከመሸጥ ወደኋላ የማይሉ በፀጥታ አካላቱ ውስጥ ያሉ አባላቱን ለማጥረት ፣ ልዩ ኦፕሬሽን ወይም የማጋለጫ ውይይት ″ በጎድ ደረጃ ″ ሳይዘገይ ማካሄድ እንዳለበት አስባለሁ ። የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ወታደራዊ ዲሲፕሊኑ ከብረት የጠነከረ መሆን ይገባዋልም ። እንደ ብረት የጠነከረ ዳሲፕሊን ላለው የመከላከያ ሠራዊትም ኢትዮጵያ ከማንኛውም የመንግስት ሠራተኛ የተሻለ ደመወዝ ልትከፍለውና ልትንከባከበውም እንደሚገባም አምናለሁ ። የአገር ሠላም ዋሥትና የመከላከያ ሠራዊቱ ፣ የፊደራል ፖሊሱ እንዲሁም በየክልሉ ያሉ ኃቀኛ ፖሊሶች እንደሆነም አበክረን መረዳት ይኖርብናል ። በእነዚህ ህግ አሥከባሪ ፣ አገርና ህዝብን ጠባቂ ተቋሞችም ውሥጥ ያለው ″ ንቅዘት ″ እሥካልተወገደ ድረሥ የኢትዮጵያ ሠላም አሥተማማኝ አይሆንም ።
ትላንት ፣ የህውሃት ጀነራሎች የግል መኖሪያ ቪላ ብቻ ቢሰሩ ኖሮ አይገርመንም ነበር ። የንግድ ፎቅ ሠርተው ሲያከራዩ ግን አይተናል ። ይህ ምን ማለት ነው ? ይህንን የሚሰማ በዝቅተኛው እና በመካከለኛው አመራርና በተራ ወታደርነት ያለው በደመወዙ ብቻ የሚተዳደረው ፣ ከዓመት እሥከዓመት ኑሮው ባለበት የሚረግጠው ዓባል ምን ይሰማዋል ? በእውነቱ ወደ ታችኛው እና የበዛ መሰዋትነት ወደ ሚከፍለው ለውይይት ስትሄድ ውድ ኮትህን ወደ ርካሽ \ ጃኬት መቀየሩ ከቶ ምንም ዋጋ እንደማይኖረው መገንዘብ አለብህ ። መጀመሪያ እራስህ በእውነት ከሥግብግብነት እንደተላቀቅህ ራስህን ጠይቅ ። ሥግብግብ ሰው ህሊና ቢሥ ነው ። ማሥተዋልም ከቶም አይችልም እና ይህንን ፍራ ፡፡ …
ዛሬ ፣ ዛሬ ሥግብግቦች አና ከራስ በላይ ነፋስ ባዮች በመንግሥት ማዋቅር በከፍተኛው አመራር ውሥጥ በመብዛታቸው ነው ፣ ተራ ነፍሰ ገዳይ አውሬዎችን እንኳን ማጥፋት ያልተቻለው ። ከተማ ሲገቡ ድምፅን አጥፍቶ በመመሸግ እምሽክ ማረግ ሲቻል ፤ ” እኛ በዚህ ሥፍራ ተሰባሥበን ቁጭ እንላለን እናንተ ገብታችሁ ዝረፉ ። ” በማለት ይመስላል ወደ ወለጋ ከተሞች እየግቡ ያለፍርሃት ዘርፈው ወደ ጨካቸው የሚመለሱት ። አሥቀድሞ ይህ ከፍተኛ ባለሥልጣን ( ወታደራዊም ሆነ ሲቪል )ከአውሬዎቹ ሥንት ሚሊዮን ብር ቢቀበል ነው ፣የፀጥታ መዋቅሩን ″ አርፈህ ቁጭ በል ። ″ ብሎ ቀጭን ትዕዛዝ የሚሰጠው ? በዚህ ዓለም እኮ ለፅድቅ ተብሎ ዘረፋ ፣ ግድያ እና ሰው ማረድ ይከናወናል እንዴ ?! …
በዚህ ዓለም ላይ፣ ሁሉም ጦርነት ለጥቅም ሥለ ጥቅም ነው የሚከናወነው ። ጥቅምህን ሲያሳጡህ ጦርነት ትከፍታለህ ። ያልተገባህን ሆኖም የቋመጥክበትን ጥቅም ለማግኘት ጦርነት ተከፍታለህ ወይም ታሥከፍታለህ ። እንዲህ ዓይነቱ ጠርነት ነው ፣ ዛሬ በዓለማችን እየተከናወነ ያለው ። በእኛ አገርም እንዲሁ ።
ኦነግ ሸኔ የሚባል የሌለ የሽፋን ሥም ይዘው ፣ በባርነት ያልተያዘውን የኦሮሞ ማህበረሰብ ነጻ እናወጣለን በማለት አላማቸውን የማይደገፈውን ሁሉ ፣ ቋንቋ እና ጎሳ ሳያመርጡ ጦርነት ከፍተውበት ፣ ጭካኔ በተሞላ መንገድ የሚገድሉ ፣ የአውሬ ሥብሥቦች ፣ በአገር ውሥጥ ያሉ ትሆን ፐለቲከኞችን ወደሥልጣን ለማምጣት አንደሆነ ግን መታወቅ አለበት ። እነዚህ ትሆን ፖለቲከኞች ፓርቲ መስርተው በሰላማዊ መንገድ እንቀሳቀሳለን የሚሉ አስመሳዮች ናቸው ፡፡ በውጪ ፀረ ኢትዮጵያ ጠላቶቻችን በገንዘብ እንደሚደገፉ የታወቀ ነው ። በእርግጥ ፀረ ኢትዮጵያ ኃይሎች የቋመጡለትን ጥቅም ለማግኘት የሚችሉት ኢትዮጵያን በማፍረሥ ነው ። ( አንባቢ ሆይ ልብ በል ፤ እንደ ቴዎድሮስ ጸጋዬ አይነቱን ልበ እውር ፣ በገንዘብ ቀጥረው የጥላቻ ጥሩንባ ቢያስነፉ አይገርምህ ) ።
ዛሬ የኢትዮጵያ ጠላቶች ኢትዮጵያን ለማፍረስ በፕላን ቢ እየተንቀሳቀሱ ነው ። ፐላን ሲም አላቸው ፡፡ ያንን በጊዜው እገልፅዋለሁ ። ጅማሬው ግን ሀ ተብሏል ። ለጊዜው ዛሬ ፣ ለዕቅዶቻቸው ግብ ያቋቋሙት ፀረ ሰው የአውሬዎች ሥብሥብ በሙሉ ኃይሉ ፣ ሌት እና ቀን ለጥፋት ተግባር እየተንቀሳቀሰ ነው ። ይህንንም እውነት ለመገንዘብ ከፈለክ አፍንጫህ ሥር ምሥረቅ እና ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ የሚታረዱትን ንፁሐን ተመልከት ። የዚህ አሸባሪ፣ አፍራሽ እና አውዳሚ አውሬ ቡድን ሞተር ከአዲስ አበባ እስካልጠፋ ጊዜ ድረስም የዘረኛ አክራሪዎች ፕላን ቢ እና ሲ ይቀጥላል ። …