መግቢያ
WHO THE CAP FIT
SONG OF BOB MARLY .
Man to man is unjust_
Children ya don’t trust
Your worst enemy
Coud be your friend
And your best friend
Your worse enemy.
Some will eat and drink with you
Then behind them su_sopon you
Only your friend know your secrets
So only he could reveal it.
And who that cap fit
Let them wear it .
Said i throw me corn
Me no call no fowl
I saying “cook _cook _ cook _ cluk _ cluk
Same will hate you ,pretend they love you now
Then behind they try to eliminate you , but who Jan bless
No one curse !
Thank God we have past the worse
Hypocrites and parasites
Will come up and take a bite .
And if your night should turn to day,
A lot of people would run a way
And who the cap fit
Let them wear it .
በኢትዮጵያችን በልቡ ውሥጥ ያለውን ንፁህ እውነት በነፃነት መናገር የሚያሣሠርበት እንዲህ በቀላሉ መድረሳችን በበኩሌ እጅግ ግርም ይለኛል ።
የሰለጠነው ዓለም ኮመዲያን በግልፅ በአደባባይ በመንግሥት ባለሥልጣናት ደርጊት ከበሸቀው ህዝብ ጋር በመወገን ፖለቲካዊ የልብ ትርታው አዳምጠው በቀልድ እያዋዙ ባለሥልጣናቶቻቸውን ተው ፣ እረፉ ይኽ ለዚህ ህዝብና አገር አይመጥንም በማለት ይመክራሉ ። ምንም መራራ እና የሚያንገፈግፍ ተረብ ቢደርስባቸው ባለሥልጣናቱ ከሥህተት መንገዳቸው ከማር ባሻገር በቀልድ አሥመሥሎ ሰድቦኛልና ዘብጥያ ይውረድ ብለው ከቶም አያውቁም ። እዚህ አገር አስብቶ ማረድ ፤ ልኩን አሳየው በማለት የራስ ቆዳን በማዋደድ ( ራቁታቸውን እንደተወለዱ ና ራቁታቸውን እንደሚቀበሩ በመካድ ) ዜጎች ተፈጥሮ በሰጣቸው አንደበት ለምን ተናገሩበት ብለው ለእግረ ሙቅ የሚዳርጉ መከሰታቸው እናንተንስ አይገርማችሁም ።
እንዴት በዚች ቅድስት አገር መልካም አንደበት ላይ የተጣመመ ሃሳብ እንዳለ ወይም ከግለሰቡ ዳቢሎሳዊ ሃሳብ እንደወጣ በቅቤ ምላሱ በማሣበቅ ፣ በሥራው ብቻ ታምኖ ንፁሐን ዘብጥያ ይወርዳሉ ? እንዴት የተፈጥሮ አንደበታችን ያሶግረናል ? ( ይላሉ ለእውነት ብለው የታሰሩ ምሁራን ። )
በእርግጥ በኢትዮጵያ ከደርግ የሶሻሊዝም የአብዮተኛ እና የፀረ አብዮተኛ ፍረጃ ጀምሮ ውሸት ነግሷል ። ንፁሐን ያለ ፍትህ ፣ ፍርድ ቤት ሣይቀርቡ ፣ በግለሰቦች የግል ውሳኔ ፣ በነፃ እርምጃ ይገደሉ ነበር ።ያም እኩይ ድርጊት የፍየል ወጠጤ እየተዜመ በሬዲዮ ሞታቸው ይነገር ነበር ። ከደርግ በኋላ ደሞ ፤ መልኩን ቀይሮ ብቅ አለ ። የእነሱ እና የእኛ ቋንቋ ። ሰውን በቋንቋው መከፋፈል ።ሰውን ከፋፍሎ በየቋንቋው መፈረጅ ።ከአንድ ቋንቋ ቤተሰብ የተወለደ ግለሰብን ድርጊት ብትኮንን መላውን የቋንቋውን ቤተሰብ እንደተዳፈርክ የሚቆጠርበት ። ( የእገሌን ልጅ ተናገርክ ፤ ሰደብክ ፤ ነገሩን ፣ ድርጊቱነሰ ኮነንክ ፤ …አንተ እንትን ሥለሆንክ ። የሚሉ የነገር ቅደም ተከተሎችና ወጊዎች የበረከቱበት ።) ማስተዋል የጠፈበት ዘመን ።
አሁንማ ብሶል ። እንደ ኮስ አበደች ሁሉም ቋንቋውን እየጠለዘ ነው ። ኳስ አበደች እንደሚባለው ” ቋንቋ አበደ ” እንበል ?
ከዚህ ” ከቋንቋ አበደ ” የፓለቲካ ጡዘት መቺ ነው የምንወጣው ? የሠለጠኑትን ፣ በዕውቀት የተራቀቁትን አገራት ሰውኛ መንገድ ከመከተል ይልቅ ፣ ” ድንቁርናችን ወርቅነው ። ” እያልን ጭረሻ የማንደማመጥን መንገድን አጠንክረን እየገነባን እኮ ነው ።
ተመልከቱ ፣ ፈጣሪ ያሳያችሁ ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ሆነ ፌደሬሽን ምክርቤት በአማርኛ ሥብሰባውን እያካሄደ ፣ እንደ አንድ አገር ዜጋ አንድ ለመሆን የሚያሥችለንን ፣ በአፍሪካውያን ክብር የሚሰጠውን ፣ የራሳችንን ፊደል አማርኛን ለምን በየክልሉ የሥራ ቋንቀ ለማድረግ እንዳቃተን ይታያችኋልን ?
እኛ ኢትዮጵያዊያን ፣ ዛሬ እና አሁን ያልባነንን መቼ እንደምንባንን ከቶም አይገባኝም ። መንግሥት ህዝብን በሚበጀው ወይም ሁሉንም ተጠቃሚ በሚያደርገው ፣ ዜግነቱን በሚያሶድደው መንገድ ህዝብን መመራት አለበት እንጂ በጠላቶቻችን በሚዘወሩ ኢ _ ሰው እና ፀረ _ፍቅር በሆኑ ባለነፍጥ ፖለቲከኞች ማስፈራርቾ እሥከመቼ ፓለቲካውን እያስታመመ አገርን በተረጋጋ ሁኔታ ማሥተዳደሩን በወከባ ይቀጥላል ?
የበለፀጉት አገራት ታሪክ የሚነግረን ጠንካራ መንግሥት ለመገንባት በወታደራዊ ህግ ብቻ የሚመራ መከላከያ ሠራዊት እና የአገርን ጠላቶች አሥቀድሞ በማነፍነፍ የሲቪሊና ወታደራዊ ደህንነት አሥቀድሞ መገንባት ያሥፈልጋል ። ( ዛሬም የተጠናከረ የደህንነትና የመከላከያ ተቋም እንዲኖራቸው ለነዚህ ተቋማት የሚያወጡት ወጪ የሠራዊት እንክብካቢያቸው ከፍተኘ ነው ። ) እኛም በአቅማችን ከፍተኛውን በጀት ለመከላከያ ና ለደህንነት ኃይል በመሥጠት መንግሥትን አጠናክረን ፣ በዜጎች ቅቡልነት ያለው ተከታታይ የሆነ ጠንካራ መንግሥታዊ ተቋማ ሊኖረን ይገባል ። ብዬ አምናለሁ ። በዚህ ረገድ የመንግሥት ጥረት የሚያስመሰግነው ቢሆንም ፣ ከፓለቲካው አንፃር ግን ፈቀቅ ያለ ተጨባጭ ለውጥ በበኩሌ አላየሁም ። መንግስት ዛሬ በከፍተኛ “ የማንን ልመን ? “ ጥርጣሬ ውሥጥ የወደቀም ይመሥለኛል ።
ዛሬ እና አሁን መንግሥት እንደግለሰብ ማንን ማመን ማንንስ ያለማመን ጥርጣሬ ውሥጥ ሊወድቅ የቻለው ፣ካለፈው የደርግ አዙሪት ያልወጣ የፓርቲ አባላትን ይዞ ሥለሚጓዝ ነው ። እርግጥ ነው በሥም ፓርቲው ተለውጧል ። በግብር ግን የተለወጠ አንዳች ነገር የለም ። መንግሥት በአንክሮ ከተመለከተ ዘሬም የሚጓዝበት አደረጃጀት ደርግ ከመሠረተው ቀበሌ ና ገበሬ ማህበር የሚነሳ ነው ። ዛሬም የማዘጋጃ ተቋማዊ ሥርዓት የለም ። ዛሬም ፓርቲና መንግሥት አልተለየም ። በመሆኑም በፓርቲ ሥም ከቀበሌ ጀምሮ በሰው ነፍሥ የሚወሥኑ እግዜሮች ቢኖሩ አይገርምም ። ከደርግ ጀምሮ ነበሩና !!!!!!!!
በበኩሌ መንግሥት ወይም ገዢው ፓርቲ ለ21 ኛው ክ/ዘ የሚመጥን የመንግሥት ሥርዓት ለማዋለድ አንድ ብርቱ ዘዴ ካልቀየሰ በታሪክ ተወቃሽ ሊሆን የሚችልበት መሥቀለኛ መንገድ ላይ እንዳለ ይታየኛል ።
በተለይም በትግራይ ያለው ፣ ሰው መሆንን የካደ የሊሂቅ ሥብሥብ አጥፍቶ መጥፋት አላማው ነውና አሁንም የኢትዮጵያ ህዝብ በሆነው መሬት በእኔነው ባይነት በብርቱ ይከራከራል ። ይኽንን ህዝብን ከህዝብ የማጋጨት እኩይ መንገድ እንዳቋረጥ ፣ በኢትዮጵያ ህዝብ ቅቡል የሆነ ልዩ ዘዴ እና ዘላቂ መፍትሄ የሚያመጣ አዲስ የዜጎች እኩልነት መንገድን መንግሥት ሣይዘገይ መቀየሥ ይኖርበታል ብዬ አምናለሁ ። ያ ዘዴም የትግራይ ህዝብ ሰውነትን በካደው ፣ የትግራይ ሊሂቅ ላይ የሚነሳበት እና እሥከወዲያኛው የሚጠራርገው መሆን ይኖርበታል ። ልብ በሉ የትግራይ ህዝብ እንደ ኢትዮጵያዊነቱ የኢትዮጵያ ግዛት ሁሉ አገሩ መሆኑንን በተጨባጭ ከተረጋገጠለት እጅግ የሚያስደንቅ ኢትዮጵያዊነቱን የወያኔንን ግብአተ መሬት በመፈፀም ያረጋግጣል ።
እያንዳንዱ ሰው ፣የራሱ አእምሮ እንዳለውም ተገንዘቡ ። ዛሬ ባለማወቅ ያደረሰው ጥፋት ነገ ወደ ህሊናው ሲመለስ ና ከድንቁርና ሲፋታ ይገባዋል ።
በመጨረሻም ህዝብ ይነቃ ዘንድ እንደ ቦብ ማርሊ ህዝብን በኪነት የሚያነቁ ከያኒያንን እና የጥበብ ሰዎችን ፈጣሪ ያብዛልን ። ከወዳጅ ጠላታችን እንድን ዘንድ በማለት ፅሑፌን እቋጫለሁ ።
………………………