June 22, 2022
3 mins read

ልበ ደንዳና፣ አንገተ ወፍራም መሪ ፕሮፋይል እና ከቨር ፎቶ መቀየር ውስጥ ይደበቃል – ዩሀንስ ሞላ

287613935 3037034889940244 2713958192887927026 nሕዝብ ሲቆጣ ማስቀየሻው ፎቶ መቀየር ነው። ምናልባት እንደ ተራ ፌስቡከር ላይክ ለቀማ? (በጭብጨባ ስለመጣ መጽናኛው ይሆናል) ወይ ደግሞ ለራሱም “I’m alright” የሚልበት መንገድ። ወይስ “ምን ታመጣላችሁ? ተዘቅዘቁ” የሚልበት መንገድ?
ብቻ ከዚህ ቀደም ለመጨረሻ ጊዜ ፎቶዎቹን የቀየረው January 11 እነ ስብሀት ነጋ ይፈቱ በተባለ ማግስት “እነ ስብሀት ነጋ ይፈቱ ሲባል፣ እኔም ደንግጫለሁ” ብሎ ያላገጠ እና ሕዝብ የተቆጣ ጊዜ ነበር።
289231832 7623360881038494 8116964725364439940 nይኸው ስንትና ስንት ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ተጨፍጭፎ ሲታዘን፣ ምን ታመጣላችሁ በሚመስል መልኩ ፎቶዎቹን ቀይሯል።
ይኽ ድርጊቱ እስከዛሬ ካደረጋቸው በላይ፣ ስለታየው እና ስላልታየው ማንነቱ በደንብ የሚያሳይ ነው።
ሕዝብ ፕሮፋይሉን በጥቁር ሲለውጥ፣ የሚመገበው ደም ደም ሲለው፣ ምድር ላይ ቀይ የደም አሻራ ታትሞ ሲለቀስ፣ እሱ አረንጓዴ አሻራ ብሎ መለጠፉን ታሪክ ይቅር አይለውም። የጎረቤት ለቅሶ እንኳን ይከበራል። በየትም አገር አስከሬን በክብር ያልፋል። ለእሱ ምናልባት የሰው ልጅ ዋጋ ከእንጨትም በታች ነው።
በዚህ ልክ እንዴት ልበ ደንዳና መሆን ይቻላል?
ለማንኛውም “እንደ እኔ የተሰደበ የለም” ብሎ እልሁን ቢዘረግፍም፣ እንደሱ የተደገፈ የለም።
ሕዝብ ካናቴራ አሰርቶ የድጋፍ ሰልፍ ካደረገ፣ ዛሬ አራት አመቱ።
ቦንብ ያፈነዱበት ሰኔ አስራ ስድስት ዛሬ አራት አመቱ።
ቴሌቪዥን ላይ ቀርቦ “የቀን ጅቦች” ካለ አራት አመቱ።
ይገርማል ብቻ። ያኔ fbi መጥቶ ያጣራ ሲባል እንኳን ለምን ማለት አይቻልም ነበር።
ዛሬ እንጠይቅ እስኪ። ከሌላው ግድያ ምን ለይቶት ነበር ኤፍቢአይ ያጣራ የተባለው? ውጤቱስ ምን ነበር? ማን አፈነዳው? የውጤቱን ማለቴ እንጂ ውስጥ ውስጡን ተብሎ ያለቀውን ማለቴ አይደለም።
በዚያ ድንጋጤ ውስጥ ዘና ብሎ ሆስፒታል ድረስ ወስዶ ያስጠየቀው “አዛኝነቱ” ዛሬ የት ገባ?
ያኔ የቆሰሉት ግን ደህና ናቸው?
ብቻ ይኽም ቶሎ ይረሳል።
ያም ሆነ ይህ ግን የደነደነ አንገት ሁሉ መሰበሩ አይቀርም!

\

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

ጥር 2 ቀን 2017 ዓ/ም   January 10, 2025  በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡ ቤተ ሰብ፡ ወዳጅ ዘመዶቻችሁን ያጣችሁ: ልጆቻችሁን የቀበራችሁ፡ አካልችሁን ያጣችሁ፡ የተሰነዘረውን ብትር በመከላከል ላይ ያላችሁ፡ያለፈቃዳችሁ በመንግሥት ተጽእኖ ወደመግደልና

በኢትዮጵያዊነታችሁ፡ በኦርቶዶክሳዊ እምነታችሁ፡ በአማራነታችሁ፡ በአማረኛ ተናጋሪነታችሁ፡ በተሰነዘረባችሁ ብትር፡

January 10, 2025
Go toTop