April 7, 2022
1 min read

የፈተና ሥርቆት ዋነኛ ችግር መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለእንደራሴዎቹ ገለፁ

ውዝግብ ባስነሳው ያለፈው ዓመት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ፈተና ውጤቶች ጉዳይ ላይ መግባባት ላይ መደረሱን የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል ግን ከሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ጋር አለመነጋገሩን ቅሬታና ሥጋታቸውን በይፋ ካሳወቁት መካከል የሚገኘው የሕዝብ እምባ ጠባቂ ተቋም አመልክቷል።
አሁንም ጥያቄዎች እንዳሉ ዋና እምባ ጠባቂው ዶ/ር እንዳለ ኃይሌ ተናግረዋል። የፈተና ሥርቆት ዋነኛ ችግር መሆኑን ፕሮፌሰር ብርሃኑ ለእንደራሴዎቹ ገልፀዋል።

4 Comments

  1. ይሄ ብርሀኑ የሚባል ሰው የነካው ሁሉ ምስቅልቅሉ ይወጣል ማለት ነው? ሲጀመር ህዝብ ያልመረጠውን የጠላውን ስራ ሰርቶ የማያውቀውን ሚኒስቴር ማድረግ ምን ይሉታል? አረጋዊ በርሄንም እንዲሁ። ሰው ጠፍቶ ነዉ ወይስ ዶር አብይ ብቃት የሌላቸውን ሹሞ አገሩን ምስቅልቅሉን ማውጣት ነው እቅዱ?
    ባለፈው በዚሁ ጉዳይ ማርክ ካልጨመራችሁልኝ አሉ ብሎ እነዚህን ልጆች ሲከሳቸው ነበር። የሆነ መሬት ወስዷል ተብሏል እሱ ላይ ቢዝነስ ይስራ አንድ ቀን ክፉ ስራው እስኪጋለጥ እስከዛው ግን ነገር አያወሳስብ፣ አርፎ ይቀመጥ። ምነው እርሶ በሉኝ አለ። እንኳን ዶር ዳኛቸው ጋር ይቅርና ልደቱ ጋር ቁጭ ብሎ በአንድ አርእስት ማውራት ይችላል? እብሪት ጥሩ አይደለም ቀዝቀዝ ቢል ጥሩ ነው መርካቶነት ሁልጊዜም አያዋጣም ውርደትን ያቀርባል።

  2. እንቅልፋም ፓርላማ?
    መቼም አንዳንድ ደፋር በሀገር አይጠፋም
    ፓርላማውን አሉት ድብርታም እንቅልፋም?
    እና ተቀምጦ ጆሮውን ይኮርኩር
    ባሳከከው ቁጥር
    ካድሬ የሚለቀው የሐሰቱ ዲስኩር?
    ይጋደማል እንጂ ጆሮ ፣ ዐይኑን ጨፍኖ
    እሱ ምን ሊጨምር
    በቀረበለት ፋይል ቀድሞ ተወስኖ?
    ኧረ ጎሽ ይተኛ!
    ደንዛዛ ልቡና አምላክ እስከቸረው
    እንቅልፍ አይደለም ወይ ባገር የቸገረው?

  3. Ahoon ጥሩ ተጠብበሀል። መልእክትህ ለብሬ ከሆነ ስለሚቸኩል ብዙም አይገባውም። አሜሪካ አንድ ሎካል ራዲዮ ጣቢያ ከአንድ መልካም ኢትዮጵያዊ ጋር አቅርቦት የብሬ እንግሊዝኛ ሳይገባን ተለያየን። ምንም እንኳን ቢጠላውም ትንሽ አማርኛ የሚሻለው ይመስለኛል ኦሮምኛም ሊናገር ይችላል እኔ ግን አልሰማሁትም በዝግ ስብሰባ ሊያቀላጥፈው ይችላል።

  4. የፈተና ስርቆት አንዱ ዋነኛ ችግር እንደሆነ ከተባለ ቆየ እኮ ለዓመታት ያለ ችግር፡፡ ታዲያ ማነው ይህን ሰንሰለት ሊያስቀር የሚችልና የጠራ አሰራር የሚያመጣ አመራር??? አስቸኳይ መዋቀራዊ ማስተካካየ በትምህርት ሚኒስቴር እና በፈተናዎች ኤጀንሲ ውስጥ ያስፈልጋል፡፡ የፖለቲካ ጨዋታ እና ሙሰኝነትን በማሰወገድ በሙያቸው የሚታመኑ ስንት ባለሙያዎች ስላሉ እነሱን በፍጥነት መመደብ ያስፈልጋል፡፡ጠንከር ያለ የቁጥጥር አሰራር/System/ መዘርጋት፣ ችግር የሚያመጡ ግለሰቦችን ከስራ ማገድ እና በህግ ተጠያቂ ማድረግ፡፡ እንዴት ሰው ይህንን መቆጣጠር ያቅተዋል፡፡ የተዘረጋውን ሰንሰለት መበጣጠስ፡፡ ተወካዮች ምክር ቤት/እንደራዎችስ/ ለለውጥ ምን እያደረጉ ነው?? ትውልድና አገር እየሞተ ዝም ብሎ ማየት ነገ ከተጠያቂነት አያድንም ለህሊናም ጥሩ አይደለም፡፡ አንዳንዱ ልጁን በፈለገው ቦታና አገር በዚህች ደሃ አገር ሀብት ስለሚያስተምር ግድ ላይለው ይችላል፡፡ ግን ለህዝብና ለአገር በዚህች አጭር የምድር ኑሮ ስልጣን ላይ ያለ ሁሉ ምን ሰራው ማለት አለበት?? እስከመቼ የፈተና ስርቆት ችግር ይቀጥላል?? ተማሪው እምነት/Confidence/ እያጣ ነው ዝም ብሎ የሚማረው፡፡ አረ አሳፋሪ ነው፡፡ ፕሮፌሰር ብርሃኑም በዚህ ላይ በቂ እገዛ እየተደረገላቸው ለውጥ ካለመጡ የስልጣን ወንበሩ ቢቀር ይሻላል!!!

    ጥቅማቸው የሚነካ እንደሚጮሁ ሳይታለም የተፈተ ነው፡፡ ምድረ ሆዳም!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!

Leave a Reply

Your email address will not be published.

shimeles
Previous Story

ግልጽ ደብዳቤ ለክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የኦሮሞ ክልል ፕሬዚዳንት – ፓስተር ዲጎኔ ሞረቴው ከሚድ ዌስት አሜሪካ

278112525 5324204964326908 2593143229231615193 n
Next Story

መንግሥት አምነስቲና ሂውማን ራይት ዎች እውነቱን ማወቅ ከፈለጉ በጥልቁ እንዲመረምሩ መከረ

Latest from Blog

“መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የሚለው የዲያስፖራ ከንቱ አታካራ! – ክፍል ሁለት

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) በአንዳንድ ስብሰባዎችና የሕዝብ መገናኛ መድረኮች የሚታየው የአንዳንድ ዲያስፖራዎች  “መነሻችን እዚህ መዳረሻችን እዚያ” የበከተ ከንቱ አታካራ በልጅነታችን ወላጆቻችን ትምህርት እንዲሆነን ይተርኩልን የነበረውን ከጫጉላ ወጥተው ጎጆ ለመመስረት የታከቱ ሁለት ያልበሰሉ ባልና ሚስትን ታሪክ

መነሻችን አማራ መድረሻችን አማራ እና ወያኔያዊ መሠረቱ

የማይወጣ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል። የዛሬን አያድርገውና የትግሬ ልሂቆች “ትግራይ የጦቢያ መሠረት ናት ።  ጦቢያ ያለ ትግራይ፣ ትግራይ ያለ ጦቢያ ሊታሰቡ አይችሉም” በማለት ጦቢያዊ ከኛ ወዲያ ላሳር እያሉ አለቅጥ ይመጻደቁ፣ ይኩራሩ፣ ይታበዩ ነበር። ወያኔ

አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው ወንጀሎች ጥፋተኛ ተባሉ

ለአመታት በእረስር ላይ የሚገኙት  አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱባቸው የጥላቻ ንግግር ማሰራጨት እና የዕርስ በዕርስ ግጭት መቀስቀስ ወንጀሎች ጥፋተኛ መባላቸው ታውቋል፡፡ አቶ ታዲዮስ ታንቱ በተከሰሱበት ክሶች በዛሬ ቀጠሮ የጥፋተኝነት ፍርድ የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ

ከ”ችርቻሮ” ድል አልፎ ለመሄድ የአንድነት አስፈላጊነት – ግርማ ካሳ

በአሁኑ ጊዜ ሁለት የፋኖ አሰላለፎች አሉ:: መኖር ያልነበረበት:: አንከር ሜዲያ ከሁለቱም አሰላለፎች፣ ሁለት ፋኖ መሪዎች ጋር ቃለ ምልልስ አድርጋለች፡፡ ሁለቱን አደመጥኩ፡፡ በሰማሁት ነገር ተደስቻለሁ:: ትልቅ ተስፋ እንድሰንቅም አድርጎኛል:: የአማራ ህዝባዊ ድርጅት የፖለቲካ
Go toTop