February 21, 2022
24 mins read

ጥሪ ለኢትዮዽያ እውነተኛ አፍቃሪዎች – ጥሩነህ.ገ

Unite 1አንድ ያላት እንቅልፍ የላት ነውና የምንወዳት ሃገራችን የቁልቁል ጉዞዋም ከመቸውም በላይ እየተፋጠነ ነው: ውስጧ እየተቦረቦረ ነው፤ይጠብቋታል ያልናቸው በአቅም ማነስም ይሁን ፍላጎት በማጣት  የሃገራችንን ትርምስ ለማስቆም አልቻሉም። ከወያኔ ያላነሰ የኦሮሚያ ብልፅግና/ ኦነግ ሃገርን በማፍረስ ላይ ፅኑ እምነት እንዳለው እያየን ነው: በአማራ ላይ የሚደረገው የማያባራ እልቂት ጅማሮው እንጂ የመጨረሻ ግብ አይደለም: ሁሉም በየተራ ይደርሰዋል: ኦነጋውያንም ጭምር ሃገር ያጣሉ ግን ለጊዜው በረጥባ የሚታደላቸውን ገንዘብ ይዘግናሉ:

ወገን ለወገን የሚደርስበት እንደ እንድ ኢትዮዽያዊ ሆኖ ሃገር የሚያድንበት ወይም ኢትዮዽያዊ እንደሆነ የሚሞትበት ወቅት ላይ ደርሰናል:

ይህችን ሀገር እንደሃገር ማቆየት የሚቻለው የተሰጠንን ማደንዘዣ የዳቦ የክልል ስም ወደጎን ትተን በጋራ በመቆም የወያኔ_የኦነግን/ የኦሮሞ ብልፅግናን መመከት  ስንችል ብቻ ነው:: ይህ ማንነትን አይገዳደርም የሚገዳደረው ማንነትንም ሆነ ሃገርን የሚያጠፈውን ነው: መንግስት ይደርስልኛል ብሎ መጠበቅ ሃገራችን ያለችበትን እውነታ አለመገንዘብ ነው: አማራንና አፋርን ማየት በቂ ነው። የመሪወቹ priority የት ላይ እንዳለ የሚያሳይ አጉሊ መነጸር ነው። ካንሰሩ በሰውነት ውስጥ ገብቶ እየተስፋፋ  ነው ሃኪሙ መንግስትም የተስፋ ቃል ከማውረድ በስተቀር መድሃኒት ቢኖረውም ሊጠቀምበት ፈቃደኛ አለመሆኑን ከዝምታው በላይ የሚነግረን የለም::

ኢትዮዽያን ለማዳን ከሰሜን እስከደቡብ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ ያሉ ወገኖች በአንድ ላይ ከመሰለፍ  ሌላ አማራጭ የለንም: ልዩነቶች ከሃገር ህልውና በሁዋላ የሚፈቱ ናቸው:

ዛሬ ለጥቅም ሲሉ ከሃገር ጠላቶች ጋር የተሰለፉ የምንም ዘሩ ይሁኑ ከሃዲወች ናቸው::

አገር አፍቃሪው ሶማሌ ከአፋሩ ክጋምቤላውና ከደቡቡ ህዝብ ከትግሬውና ከኦሮሞ  ህዝብ ጋር ተሳስሮ ኦነግን/የኦሮሞ ብልፅግናንና ወራሪው ትግሬን ለማንበርከክ  አሁኑኑ መቀናጀት ያስፈልጋል::

በዘመነ መሳፍንት መግቢያ ላይ ዳግማዊ ተክለሃይማኖት ንጉስ ነበር: ከ1769 እስከ1855 የሰፈነው ስራዓት አልበኝነት ወይም ዘመነ መሳፍንት ተብሎ የሚታወቀው ከተክለሃይማኖትም በሁዋላ ቢሆን ደካማ ነግስታትን አጥቶ አያውቅም: አባታጠቅ ካሳ ኢትዮዽያን አንድ እስካደረገ እስከ 1855 ድረስ እየተልፈሰፈሰ የቀጠለ “መንግስት”ነበር:: ሿሚና ሻሪ የመንደር ጀብደኞች ነበሩ፤ ከነዚህ ዋናው የትግሪው ሰዑል ሚካኤል ይጠቀሰላ: ዛሬም በአሜሪካ ጀርባ ታዝለው ይህን ለማድረግ የተዘጋጁት ወያኔወችና እነሱው የፈለፈሏቸው ጋሻጋግሬወቻቸው እያደረጉ ያሉትን ስንገነዘብ ታሪክ እራሱን እየደገመ እንደሆነ እናያለን:: የመንግስት መዋቅሩ ያለይምሰል እንጂ ዋናውን የሰው ልጆችን ደህንነት የመጠበቅ አቅም ወይም ፈቃድ የለውም፤ ለዚህ ነው

ዛሬ በሁለተኛው  የዘመነመሳፍንት ዋዜማ ላይ እንዳለን የሚሰማኝ: የህዝብን ሰላም የሚጠብቅ መንግስት የለንም: አድላዊነት እያፈረካከሰን እንደሆነ እየታየ ነው: ሁሉም ጎራውን ይዞ እየተሰለፈ ነው: ከዳግማዊ ተክለሃይማኖት እስከ ቴወድሮስ የነበረው ቀውጢ ጊዜ ከበራችን ላይ ነው:: ማዕከሉ ሲዳከም ወይም በወገንተኝነት ተሸብቦ ለሁሉም መሆኑ ሲቀር ሁሉም ትናንሽ መንግስታትን ይፈጥራል: ያለነው ከዚያ አስፈሪ ሃቅ ላይ ነው::

ሃገርን የሚታደግ ፌደራላዊም ሆነ የክልል መንግስት ማግኘት ከባድ ሆኗል።እንዲያውም ስማችን ተጠራ ብለው የሚቆዝሙ፤ ያዙን ልቀቁን የሚሉ መኳንንቶችን እያየን ነው:: ሰው የገደሉትን ወደፍትህ ከማምጣት ይልቅ ለክብራቸው ንጹሃንን ያስራሉ።

ያም ሆኖ እምነቴ ኢትዮዽያ አሁን ባሉት መሪዎቿም ባይሆን የቁርጥ ቀን ልጆች ይዛ እንደምትመጣ ነው: ከመቶ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ይዛ ይቅርና ከትቂት ሰዎች መካከልም እንደ ቴወድሮስ ያሉ በሃገር ፍቅር የነደዱ ጀግኖችን አፍርታለች:: ለጊዜው ያሰብነው እድገት ሊዘገይ ይችል ይሆናል  ጀግና ወደፊት መውጣቱን ግን መጠራጠር አይቻልም’፤አሳዛኙ ግን እስከዚያው  የአያሌወች ደም መፍሰሱ ነው።

የሰው ልጅ ህይወት እየተቀጠፈ ስደትና ሞት በሰፈኑበት ዘመን ምንም ሰላም በሌለበት ሰላምን ብቻ መስበክ ምን ያህል ባዶ ጩኸት እንደሆነ የሚያሳይ ነው።

የሰው ልጅ እንደ ገና በግ እየተጎተተ በሚታረድበት ሃገር ምን ሰላም ይኖራል?

ብዙ ምርጫ የለንም፣ የሚያሳድዱን ሰዎች በእንቅልፍም ሆነ በእውናቸው  የሚያዩት እኛን ከምድረ ገጽ ማጥፋት ነው፣ ይህን ግባቸውን እውን ለማድረግ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይወጡት ዛፍ የማይሻገሩት ወንዝ የለም። ሽማግሌ የለባቸውም ሁሉም አንድ ናቸው። እንድምታውቁት በታሪካችን በደሎች ነበሩ ሆኖም የሽማግሌ ድሆች አልነበርንምና በእርቅ ይፈታ ነበር። ዛሬ ያ የለም። ሃገር ሲጠፋ ጃርት ያበቅላል እንደሚባለው ሃገር እየጠፋ እንደሰው ማሰብ የማይችሉ ጉድ ፍጡራን ሃገራችንን እየውረሱት ነው። የሰው ልጅ በራሱ ማሰብ ቀርቶ ሌሎች የሰጡትን ተሸክሞ ከሰውነት ወርዶ በመንጋ የሚነዳ ክብት እየሆነ ነው።  ማሰብ ደካማነት፣መጠየቅ ወላዋይነት፣ አንድነት አፍራሽነት፣ፍቅር ሞኝነት የሆነበት ዘመን ላይ ነን። ጠላቶቻችን በውጭም በውስጥም በደስታ ብርጭቋቸውን ያጋጫሉ። ሰዎች ሲሞቱ፣ ሲንገላቱና  ሲሳደዱ የተፈጥሮ ህግ እንድሆነ አድርገው  ሊያቀርቡት ይፈልጋሉ። የነሱ ህልውናና እድገት ከእኛ ውድቀት ጋር አያይዘው ደባ እየሰሩብን ነው። ታዲያ ስንቱ ነው ይህን የሚገንዘበው? ወገኖች ከባድና አስቸጋሪ ችላ፣ ተብሎ የማይታልፍ ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ጾም ጸሎት ብቻ የሚፈታው አይደለም። ነፍስ ይማር እርካሽ ቃላት እየሆኑ ነው።

ዙሪያውን ብታዩት የቀውጢ ዘመን እንደሆነ እያየን ነው፣ ሞትና ስደት የየቀኑ ዜና ነው። ታዲያ አንዳንዶች እነሱጋ ስላልደርሰ ይህን አይኑን ያፈጠጠ ችግር አያዩትም፣ እንዲያውም አንዳንዶች ከፍርሃትም ይሁን ካድርባይነት ችግሩን ሊያስተባብሉት ይሞክራሉ፣ሌሎች ደግም ስር የሰደደ የመደራጀትና የመከላከል ስራ በመስራት ፋንታ በየሜዳው ውጤት የሌለው እምቧ ከረዩ ሲሉ ይታያሉ። አዎ መልሱ መደራጀትና እራስን ማዳን ነው፣ ሌላ አማራጭ አላይም፣ ጠላቶቻችን ይህን አረጋግጠውልናል። መፈናፈኛ እንዳይኖረን ከውጭ ጠላቶቻችን ጋር በመጣመር እየከበቡን ነው፣ ዛሬ አዚያ ማዶ መንደር ነገ ድግሞ እዚህ ነው።

በሚገባ ከመረመራችሁት ዘረኛ ጥላቻ እንጂ በውስጡ ፍቅር አያውቅም። ይህ ደግሞ የኛ የሚሉትንም ህዝብ የሚጨምር ነው። ዛሬ ጠላት የሚሉት ከነሱ ዘር ውጭ የሆነውን ነው ማቆሚያ ግን የለውም። ይህ የዛሬው ምኞታችው ቢሳካ ነገ ትንሽ እራቅ ካሉ ከራሳቸው ዘር ጋር ይፋለማሉ ያም ቢሳክ ደግሞ ቀረብ ካለው ጋር ይጋጫሉ። ነገሩ የጊዜ ጉዳይ እንጂ በጥላቻ የተለከፈ ሁሉንም ነው የሚለክፈው።

በተናጠል መሞት እንችላለን መዳን የምንችለው ግን አንድ ስንሆን ብቻ ነው።

መደራጀት ግድ ነው. እራስን ለማዳን ጥቃትን መከላከል የተፈጥሮ ህግ ነው፣ ከማንም የማይማሩት በደም ውስጥ የሚገኝ የህልውና ክፍል ነው፣ ይህ ደግሞ በሰው ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ነፍስ ያላቸው ፍጡራን ሁሉ የታደሉት ነው። ሞትን ጥቃትን ይሁንብን ብሎ የሚቀበል ፍጡር የለም፣ እየተፈራገጠ አቅሙን በጉልበተኛ እስከሚነጠቅ ድረስ እራሱን ለማዳን ይከላከላል ባልሞት ባይ ተጋዳይነት የሌላውን ህይወትም ያጠፋል። ይህ ተፈጥሮ ነው ማንም ሊቀይረው አይችልም።  ከሁሉም አስቀድሞ በአንድነት ለመኖር ልዩነትን በውይይት መፍታት የሰው ልጅ ባህሪ መሆን አለበት፣ ይህ ደግሞ በአንድ ወገን ብቻ ተግባራዊ አይሆንም ባንድ እጅ አይጨበጨብምና ሁሉንም የጉዳዪ ባለቤቶች ይመለከታል። አጥቂና ተጠቂም የሚፈጠረው አንዱ በራሱ እምነትና ፍላጎት ላይ ተመስርቶ የሌላውን ሲያጣጥልና አልፎም ወደ እብሪት ሲሸጋገር ነው። አሁን በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ችግር በውይይት የማይፈታ ሆኖ ሳይሆን በታሪክ የውሸት ትርክት ላይ የተመሰረቱ የሃገር ጠላቶች በፈጠሩት የተጎድቻለሁ ለቅሶ ነው። ጉዳቱ ከምን ላይ እንደሆነና አንዴት እንደሚታረም እንኳ ወደ ውይይት እንዳይመጡ እንደጭቃ አቡክተው የሰሯቸው ወያኔዎች አይፈቅዱላቸውም።  አራሳቸውን የሌሎች ትርክትና ጥላቻ አጋሰስ ከሆኑ በኋል ለልጆቻቸውም ይህኑ ነው ያወርሷቸው። ግራና ቀኝ ማየት ተስኗቸው አእምሮቸውን ተሰልበው የገድል ማሚቶ ሆነዋል። የሞቱት እንሱ ብቻ ሳይሆኑ ትውልዱን ጨምረው ነው የገደሉት።

ዛሬ በየአካባቢው በተለይም በኦሮሚያ የሚደረገው አጉራ ዘልለ ድንፋታ ለማንም አይጠቅምም። ሁሉም ዘሩን እንደየዘ ከኢትዮጵያዊነቱ ጋር አይጋጭበትም። ሁሉም በጉያው የተወሸቁትንና የሚያጋጩትን ጽንፈኞች፣የፖለቲካ ደላሎች፣ የውጭ የአፍራሽ ፈረሶችን መንጥሮ ማውጣት ለአብሮነታችን ትልቁ የስራ ድርሻ ነው።

ሃገራችን በተላያዩ የታሪክ ወቅቶች ፈታኝ የሆኑ የውጭ ጠላቶች ገጥሟታል፣ በየዘመኑ የነበሩት የታሪክ ባለአደራወች እንዳመጣጡ ተዋድቀው ለቀጣዩ ትውልድ አሸጋግረዋል። ትግሉ መስዋትነትን መዳረሻው ያደረገ በመሞት ህይወትን እየሰራ የዘለቀ ነው። ከወጣት እስከሽማግሌ ከወንዶች እስከሴቶች ሃይማኖትን ሳይለይ ዘርን ሳይቆጥር በየደኑና ሸንተረሩ በአቀበቱና በሸለቆው ባንድ ላይ ክልትም ብለው የቀሩትን ታሪክ ብቻ ነው የሚቆጥራቸው። እንደዚህ እየሆነ ነው አንዱ ትውልድ ሞቶ ለሌላው ህይወት እየሆነ ትውልዱን ቀጣይነይ እንዲኖረው ያደረገው። በእርግጥ በታሪክችን በመካከላችን ግጭቶች ነብሩብን ግን ሁልጊዜ መፍትሄው በሽማግሎቻችን ስለነበረ ዙረን እንታራቃልን። ከሁሉም በላይ ምንም አይነት የርስ በርስ ንትርክ ውስጥ ሆነነም የውጭ ጠላት ጦር ስብቆ ድንበር ጥሶ ሲመጣ ቀፎው እንደተነካበት ንብ ግር ብሎ ጠላቱን መደረሻ ሲያሳጣው እንደነበረ የታሪክ ማህደራችን ጉልህ ምስክር ነው።

የዛሬ ችግራችን ግን ለየት ያለ ነው፣ የውጭ ጠላትን ስራ አስፈጻሚ የውስጥ ጠላቶች ተነስትውብናል። ከነበሩብን ችግሮች በላይ ነው፣ እንዳባቶቻችን የውጭውን ጠላት ለምቋቋም ስንጥር ከውስጥ እየሰረሰሩን ነው። ዛሬ የውጭው እንድድሮው ድንበር ጥሶ አይመጣም፣ እዚያው ካለበት ሆኖ የኛኑ ጉዶች በመሳሪያም በገንዘብም ያስታጥቃቸዋል አፍራሽ ሃሳቦችንም በጨቅላ ጭንቅላታቸው ይጽፈዋል። በውሸት ትርክት ተበድላችኋል ተነሱ አመጽ ፍጠሩ ህይወት ባመጽ ነው ብሎ ይስብካችዋል። እኒህ የታሪክ ድኩማን ሰላም ያማቸዋል ነጻነት ያንገፈግፋቸውል። የውጭ ገንዘብ ከነጻነት፤ ከእኩልነት ገዝፎ የታያቸዋል እንድማግኔት ይስባቸውል። የወላጆቻቸው ባህል በነሱ ላይ ቅንጣት ያህል አይታይም እንዲያውም ይንቁታል። መቻቻልን እንድደካማነት ነው የሚረዱት፣ የጋራ ጥቅም የጋራ  ሃገር ለህልውና በአድ ቋንቋ ናቸው።  ሁሉም የኛ የሚል የስግብግብ አባዜ ስለሚያሽከረክራቸው ሌላውን ከሌላው ጋር አብሮ መኖር ይቅርና ማየት እንኳ አይፈልጉም። ለዚህ ነው የዛሬውን ችግራችንን ከባድ የሚያደርግብን።

አለም እየጠበበች የአንዱ ሃገር የሌላው ጓሮ በሆነበትና በተቀራረበበት ዘመን መለያየትን ይሰብካሉ። የአለም የተሳሰረ ኢኮኖሚ አንድ ሃገር ብቻዋን እራሷን በማትችልበት ይባስ ብለው ሃገርም መከፋፈል አለበት ይሉናል። በዘር ላይ የሚረጩት የጥላቻ ትምህርት ወጣቶችን ደንቆሮ አድርጎ ማሳደግ ብቻ ሳይሆን ከጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር፣ከዩጎስላቪያ፤ ከሩዋንድ አለመማራቸውን ውይም ለመማር ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ነው የሚያሳየው። በሁሉም ትልቅ እልቂት ተካሂዷል። በሁሉም ጉዳት እንጅ አትራፊ አልነበረም። ዛሬ የእኛወቹን የተለየ የሚያደርገው ምንም አይነት ሂሳብ አይኖርም።

ትልቁ ነገር ደግሞ ይህ ሰው እኛን አይመስልም ከምድረ ግጽ ይጥፋ የሚሉት የዘር ደላሎች በዚያች ቁርጥ ቀን አለመገኘታቸው ነው። ለአሳት የሚማግዷቸውን ወጣቶች አድንቁረው ጥያቄ እንዳያነሱ አድርገው ፈልፍለዋቸዋል። እንደናዚ ወጣት ምልምሎች ሂዱና ተማገዱ ሲሏቸው አይናቸውን ሳያሹ የሳት እራት ለመሆን አዋቅረዋቸውል። ከሰውነት ውጭ ስብከታቸው ወደ ከብትነት ቀይረዋቸዋል።

እንደአርያን ዘር ንጹህ ዘር መሆን አለብን ከሚል የበታችነት ስሜት ተቃጥለው የአንዱ ዘር ከሌላው አንዳይጋባ አስከማለት ደርሰዋል። አብደዋል አንዳይባል መጀመሪያውን ለማበድ የሚታመም ጭንቅላት ይጠይቃል፣ ይህ ጭንቅላት በሌለብት ሁኔታ ከሰው አኳያ አብደት ሊኖር አይችልም። አንደውሻ ተለክፈዋል ያስኝ ይሆናል። ውሻ የሚያስብ ጭንቅላት የለውም ግን ያብዳል/ይለከፋል ወደሰውም ያስተላልፋል።

በግልጽ ወጥተው የዘር ቅስቀሳን በይፋ የማያደርጉትም ቢሆን ውስጥ ውስጡን ለአሸባሪወች ድጋፋቸውን ከመስጠት ተቆጥበው አያውቁም። ከአንድ ዘረኝነት ጉድጓድ የተቀዳ ውሃ ነውና የጠጡት በደም ስራቸው የሚንካባለለው ያው የተመርዘው ደም ነው። በመንግስት መዋቅር ተሰግስገው መረጃ በማቀበል ሰዎችን ያስገድላሉ ያፈናቅላሉ ሃብት ያስዘርፋሉ። ስለዚህ በጨዋነት ድንኳን የተገለሉ አሸባሪወች ቁጥር ትንሽ የሚባል አይደለም። ቀን ቀን የህዝብ ስራ የሚሰሩ መስለው ደፋቀና የሚሉ ጸሃይ ስታጋድል ደግሞ የለበሱትን ማስምሰያ ልብስ አውልቀው ከመሰሎቻቸው ጋር ደባን ሲጎነጉኑ ያድራሉ።

ከኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አንጻር ወያኔና ኦነግ አዚህ ግቡ የሚባሉ ሆነው አይደለም፤ ከብዙሃኑ ይልቅ ባፍራሽነት ፍላጎታቸው የጠበቀ ግንኙነትና ዲሲፕሊን ስላላቸው ነው። የብዙሃኑ ትብብር ጎልቶ አልመውጣቱ ምቹ ሆኖላቸዋል። የአማራ ብቻ ኢትዮጵያ የለችም፤የኦሮሞም ብቻ ልትሆንም አትችልም። ኢትዮጵያ ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ናት። ነገር ግን ይህን ተርድቶ በአንድ ላይ በመቆም ፋንታ ሁሉም በየጎራው ተደብቆ የሌሎችን ግፍ በሩቁ ይመለከታል። ነገሩ የቅደም ተከተል ጉዳይ እንጂ ከዘርኞች ጎራዴ የሚተርፍ አይኖርም። የኦነግ ጉራዴ የአፋሩንም፤ የሶማሊወንም የወላይታውንም የጋምቤላውንም አንገት ሳይቀላ ወደ አፎቱ አይመለስም። የዛሬው የወያኔና የኦነግ ጦር በአማራ ላይ ያነጣጥር እንጂ ድግሱ ለሁሉም ነው። ለአማራ ያልሆነች ኢትዮጵያ ለሌሎች አትሆንም። ለዚህ ነው በተናጠል በየጊዜው ከማልቅ የተከፈተብንን የዘረኞች ጥቃት በህብረት መመከት ያለብን።

 

ኢትዮጵያን የሚያፈርሰው የጥቂቶች ጩኸት ሳይሆን የብዙሃን ዝምታ ነው።

ጥሩነህ ገ

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop