የ“ማዕበል ጋላቢ” መጽሐፍ ግምገማ ክፍል 1 – ገምጋሚ መንግስቱ ሞሴ (ዶ/ር)

የመጽሐፉ እርእስ “ማዕበል ጋላቢ” ፀሐፊ ታደለ ገዛኸኝ። አቶ ታደለ ገዛኸኝ የመጽሐፉ ማስታወሻነቱን “በትግሉ ለወደቁ፤ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና በየ እስርቤቱ ለማቀቁ – ለአገር ለወገን ብለው መስዋዕትነት ለከፈሉ ሁሉ እንዲሆን ሰጥተዋል።

መንደርደሪያ

በዚህ ገምጋሚ አተያይ እና በቀጣይ እንደሚታየው አቶ ታደለ ውብ የድርጅት ስራ እንደከወኑ እና የጎጃም-ጎንደር ኢንተርዞንን ከምንም አንስተው መልክ ያስያዙ በተለይም የጎንደር ክፍለ ሐገርን ትልልቅ ሰወች ቀርበው ለኢሕአፓ ደጋፊ እና አባል እንዲሆኑ ያደረጉ ውብ አታጋይ እና አደራጅ መሪ ነበሩ። ያነንም ስራቸውን በመጽሐፋቸው “ማዕበል ጋላቢ” ውስጥ በውብ ቋንቋ አስቀምጠዋል። የዚያን በእውነትም ማእበል ዘመን ታሪክ ለዚህ ትውልድ እና በታሪኩ ለአለፉት የዚያ ተርብ ትውልድ ታጋዮች በ 515 ገጽ ታሪክ አቅርበዋል። ሆኖም ጸሐፊው ለምን የጎጃም ጎንደር ኢንተርዞን እንደሚሉት ምናልባትም ለሚያነብ ሁሉ በልቦናው የሚቀረጽ ጥያቄ ይሆናል ምክንያቱም ብዙም ስለጎጃም ዞናል (ቀጥናወች እና ቀጠና ኮሚቴወች) የጻፉት ባይኖርም ወይንም እንደስሙ በቂ ባይሆንም ምናልባትም ቀደም ያለውን ኮሚቴ ሊሆን ይችላል በልሚ ይህ ምገጋሚ የራሱን ግምት አስቀምጦ አልፎታል።

አንባቢ በጥልቀት ሲያነበው አንዳንድ አቃቂሮች እንደሚያወጣ ደግሞ ልንረዳው ይገባል እናም አንዳንድ ቦታ ላይ ጸሐፊው አሉ አሉን ተጠቅመዋል። ወይንም የቀጥታ ቃለ መጠይቅ አድርገው ታሪኩን ከመዘገብ ይልቅ ምናልባትም ባለታሪኮቹ ስለሌሉም ይሆናል ሦስተኛ አካላትን የአባባሎች ባለቤት አድርገዋል። ይህ ገምጋሚም እነዚያን ለማሳየት ይሞክራል። በተረፈ መጽሐፉ የአንድ ተርብ የሆነ ሐገር አፍቃሪ እና አላማውን ግብ ለማድረስ የትኛውንም ዋጋ የከፈለ ትውልድን ታሪክ እና መሪ ድርጅቱን የሚተርክ ብሎም በህይወት ካሉ ትቂቶች የቀድሞ መሪወቹ ከሆኑት የአንዱን የአቶ ታደለ ገዛኸኝን ትረካ ያቀረበ በመሆኑ ሊነበብ ይገባዋል።

 

የመጀመሪያ ክፍል (1)

——————————————————————————————————————————

መጽሐፉ ባለ 515 ገጽ ከድርጅት ጋር የተያያዘ ግለታሪክን ያካተተ በመሆኑ አንባቢ የዚያ ትውልድ አካል ካልሆነ ገና በማየት ሊያነብ ይሰጋል የሚል ሀሳብ ፈጥሮብኛል። ጸሐፊው ይህን ያክል ጥራዝ የያዘ ከማስነበብ በሁለት ወይንም ሦስት ጥራዞች ቢከፋፍሉት ልክ አቶ ክፍሉ ታደሰ እንዳደረጉት ተነባቢነቱ ከፍ ይላል ብሎ ገምጋሚው አሰብ። ለዚህ ምክንያቴ ብዙ ግዜ አንባቢ ያልሆነ ሕብረተሰብ ሲያዩት የሚያታክት ትልቅ ጥራዝን በማየት ተሰላችቶ ጨርሶ ላይጀምረው ይችላል (የገምጋሚው የግል አስተያየት)። ደግሞም አቶ ገዛኸኝ ኢሕአፓን ከፈጠሩ ስብስቦች የአንዱ የወጣቱ አካባቢ ያወጣ በነበረው ጋዜጣ (አብዮት) በሚባለው ቡድን ውስጥ የነበሩ ብሎም ብዙ ቁልፍ የትግል ቦታወች ላይ የተገኙ፣ በይበልጥም እስከመጨረሻ የዘለቀውን የጎንደር-ጎጃም በይነ ቀጠና ያደራጁ እና ያዋቀሩ በመሆኑ መጽሐፉን ሁሉም ሊያነበው ይገባል። ይህን ስል በ1969-70 ለሁለት አመታት የዘለቀው ቀይሽብር እና ነጻ እርምጃ የተባለው የደርግ አንድ ትውልድን የመተረው ፍጅት ከተካሄደ በኋላ ሁሉም በሀገሪቱ ውስጥ የነበሩት በይነ ቀጠናወች ሲፈርሱ እና ሲጠፉ ይህ የጎንደር-ጎጃም በይነ ቀጠና ግን ሁለት እና ሦስት ግዜ እራሱን እንደገና እያዋቀረ የቀጠለ በመሆኑ ስራቸው ከህሊናዊው ሁኔታ ጋር ያጣመሩ ታታሪ ታጋይ በመሆናቸው ነበር። ጸሐፊው በኢሕአፓ ውስጥ አብዮትን ወክለው በውህደቱ ተለዋጭ የማህከላዊ ኮሚቴ አባል፤ በኋላ ሙሉ የማህከላዊ ኮሚቴ በመሆን ያታገሉ ሰው ናቸው። እንደሚታወቀው አብዮት የተባለው ቡድን በጌታቸው ማሩ መሪነት የተደራጀ ሲሆን። ጌታቸው ማሩ ከሁሉም ወጣት የነበረ የኢሕአፓ ፖለቲካ ቢሮ አባል ሆኖ ለተወሰነ ግዜ ያገለገለ በኋላ ልዩነት በመፍጠር አንጃ በሚል ሀ እና ለ ከሚለው የሚታወቅ ሀ መሆኑን ጸሐፊው ይጠቅሳሉ። አቶ ገዛኸኝ የጌታቸው ማሩ ቅርብ ጓደኛ እና አብዮትን በመመስረት ከአራቱ አንዱ እንደነበሩ ይህ ግለ ታሪካቸው ያስረዳል። ያም ሆኖ ግን አቶ ገዛኸኝ የአንጀኛውን መስመር አለመከተላቸው እና እስከ አራተኛው የማህከላዊ ኮሚቴው ፕሌኒዬም ከዚያም የሁለተኛው ሪጅናል አርሚ ብተና እስከተደረገበት መቀጠላቸ እሳቸው እንዳሉት የስንብት ደብዳቤ መጻፋቸውን ሆኖም ያስገቡት ወይንም አያስገቡት መርሳታቸውን ይጠቅሳሉ። የገምጋሚው አስተያየት ይህን ያህል ዝርዝር ሚኒቶችን የያዘ አንድ መሪ የታገለለትን ድርጅት የስንብት መልቀቂያ ደብዳቤ ማስገባት አለማስገባቱ ተረሳ የሚለው ተቀባይነቱ ሥስ ነው ብሎ ያምናል እናም ባይጠቀስ ወይንም ሳልሰናበት ወጣሁ ቢባል መልክ ይኖረው ነበር (የገምጋሚ)።

ለማነኛውም የገምጋሚው መጽሐፉን ለመገምገም ያሳሰበው ሊነበብ የሚገባ መጽሐፍ  መሆኑን ለማሳየት ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ቢያነበው ከ 1953 የጀመረውን የአገር የነጻነት የዴሞክራሲ ጥያቄ መልኩን እየቀያየረ 51 አመታት ሳይመለስ መዝለቁን የሚያሳይ ስለሆነ እና ከዚያ ትምህርት መውሰድ አንድ እርምጃ ስለሆነ ገምጋሚው በተለይ በታሪኩ ያለፉት እንዲያነቡት እና ተችም እንዲተች ያበረታታል።

አቶ ታደለ ገዛኸኝ ያለነገር አይደለም የመጽሐፉን ማስታወሻነት ለእናት ለአባት ለልጆች ወይንም ለቤተሰብ ያላደረጉት። የሰጡት በልጅነት ተነስተው ህልም ሰንቀው እስከ ትግል ሜዳ ወርደው የታገሉት ለሕዝብ ስለነበር እና ያነን የሕዝብ ፍቅር የገለጹት በውብ ሕልም እውን አለምን ለመፍጠር በመነሳት በቁርጠኝነት ስለነበር። ካልተሳሳትሁ ያ ህልም በአጭር ተቀጭቶ በተስፋ መቁረጥ ተደምድሞ ገና በጠዋት የአፍላ እድሜ እና የወጣት ጉልበት እያለ ወደስደት በመውጣት ደምድመውታል።

አቶ ታደለ ገዛኸኝ እንደማንም ተራ ታጋይ እንዳልነበሩ ሁሉ ተነሳስተው ሜዳ የገቡ ሳይሆን በዚያ ትውልድ ትግል ውስጥ ሁነኛ የመሪ ቦታ የነበራቸው እና ለቋጠሩት ህልም ግብ መምታት የቅድሚያውን እረድፍ የያዙ ታጋይ ነበሩ። የመጽሐፋቸው የመጀመሪያ ቻፕተር “ትግል እና እድገት የአንድ ወቅት ቅንጫቢወች አይደሉም” በሚል ርእሰ አረፍተነርገ ይጀምሩታል። በዚህ የመጀመሪያ ርእስ የሀገራችን እውቀት የመነጨው ከኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን አስተምሮት ጋር መያያዙን በምሳሌነት ልክ እንደአውሮፓውያን የእውቀታቸው ምንጭ ቤተክርስቲያን እንደሆነች እና እነ ኮፐርኒከስን አይነት ጠቢባንንም እንዳወጣች ይዘረዝራሉ። በዚህ ገለጻቸው እድገት ፍለጋን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ተከታታይ ትውልዶች የተጓዙበትን እና የሞከሩትን የእድገት ግብአት ይገልጻሉ። በምሳሌነትም የዘመነ መሳፍንት ጉግ ማንጉጎችን ዘመን በመራር ትግል ያቸነፉትን አፄ ቴወድሮስን በምሳሌነት ያቀርባሉ። አፄ ቴወድሮስ ሐገራችን የከበባትን የጠላት ብዛት እና የሐገራችን ቀጣይነት የሚረጋገጠው እራሳችንን ችለን የራሳችንን ኃይል ዘመን ከሚጠይቀው እውቀት አዋህደን ስንቀጥል መሆኑን የጋፋት ፕሮጀክት ስራቸውን ያሳዩናል።

በዚህ እርእስ ስር የአለቃ ታየን የለውጥ የእውቀት ፈላጊነትን የህይወት ስራወች ያስነብቡናል። በማስቀጠል በገጽ 6 በጣሊያን የተወረረች ሀገራችን በዘመኑ የተማሩ ትቂትም ቢሆኑ ልጆቿ በአለማቀፍ ትግሉ ያበረከቱትን ሰፊ አስተዋጸኦም ይዘረዝራሉ። የጠላት ወረራ በኢትዮጵያ አርበኞች ከተወገደ በኋላ በዘመኑ ተራማጅ የነበሩት ንጉሠ ነገስት ያደረጉትን አስተዋጽኦ በንጉሡ እና በዘመኑ ተንሰራፍቶ በነበረው የመሳፍንታዊ ስርአት መለስተኛም ቢሆን የነበሩ መፋተጎችን ያሳያሉ። የአቶ ታደለ ገዛኸኝ የመጀመሪያ ዕርእስ በእርግጥም ብዙ ሳይጓዝ ወደ የኢትዮጵያ የተማሪ ንቅናቄ እና በቀጣይ ከ1950-60 ወቹ የተወለዱትን የፖለቲካ ድርጅቶች ታሪካዊ አመጣት ውብ በሆነ መንደርደሪያ እና ዳይሌክቲካል ግንኙነቱን ያሳዩናል።

ገጽ 10 እረዕስ 2 የተማሪው ንቅናቄ

የተማሪው እንቅስቃሴ – ይህ እርእስ አሁንም የሚጠቅሰው በቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ የነበረውን የተማሪወች የለውጥ ንቃቄ ነው። በዘመኑ ማለትም የ ቀኃ ሥ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች ንቅናቄ በ 1950 ወቹ በአብዛኛው ከሞራል ጥያቄ ያልዘለለ ነበር ይላሉ የመጽሐፉ ደራሲ። ምን ያህል ይህ አባባል ትክክለኛ ይሁን ባላውቀም (ገምጋሚው) የኢትዮጵያ የተማሪ ንቅናቄ እየተባለ የሚታወቀው በቀዳማዊ አፄ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ (ያሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ) የተጀመረው የ1953 ዓም የንዋይ ወንድማማቾችን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ መሆኑን ብዙ ታሪክ ከታቢያን ይነግሩናል። ፕሮፈሰር ባህሩ ዘውዴ The history of Modern Ethiopia second edition, Oxford 2001 እንደሚያብራሩት የገርማሜ መንግስቱ ነዋይ የግልበጣ ሙከራ ዋና አላማ ተራማጅ ይዞታ የነበረው የህዝብ ኑሮ ይሻሻል በሚል እንደሆነ እና በቀጣይ አመታት የተማሪው ንቅናቄ የንዋይ ወንድማማቾች ያነሷቸውን ጥያቄወች እንዳስቀጠለ እሳቸውም ይጨምሩበታል። አቶ ገዛኸኝ ከንዋይ ወንድማማቾች ጥያቄ አንዱ የሆነው የመሬት ስሪትን አስመልክቶ የተማሪው የ1950 ወቹ መጨረሻ አመታት ጀምሮ በዋና መፈክርነት አስተጋብቶታል። የንግግር፣ የመጻፍ ነጻነቶች እንዲከበሩም ተማሪው የትግል ሀሁ አድርጎታል ይላሉ (የአማረኛው አጣጣል የገምጋሚው ነው)።

እስከ 1960 አመተ ምህረት ድረስ የነበረው ትግል የሚናቅ እንዳልሆነ ጠቅሰው ያልፋሉ። የትኞቹ የጎሉ እንደነበሩ ግን አላብራሩም። ወረድ ብለው የ 1954 ን የተማሪ ትግል መልሰው ያሳዩናል። እናም እስከ 1954 በአየአመቱ ግንቦት ወር ላይ ኮሌጅ ቀን በሚል ይከበር የነበረውን የግጥም ውድድር ንጉሡ ጭምር ይገኙበት ነበር ይላል የመጽሐፉ ደራሲ። በመቀጠል ከ 1954 በሁዋላ ፀረ መንግስት እየሆነ መምጣቱ ንጉሡን እንዳቆሙና ይባስ ብሎ በዚያ ምክንያትም ከ 1955 ጀምሮ አዳሪ ትምህርትቤቱ እንዲዘጋ ሆኗል በሚል ፀሐፊው አስፍሯል።

ገጽ 11 የመጨረሻ ምእራፍ ላይ ጸሐፊው ንቅናቄው እስከ 1955-62 እና 1956-63 ድረስ በሚል የግዜ ሰሌዳ በገባ ንቅናቄው አንዳንድ ጥያቄወች ሲያነሳ ቆይቶ 1957 ዓም ለመጀመሪያ ግዜ መሬት ላራሹ ጥያቄ ተነሳ የሚለውን መቋጫ ሳይሰጡ ዩኒቨርስቲው ውስጥ የክሮኮዳይል የሚባል ቡድን ትልቅ አስተዋጽኦ ማድረጉን እንደሰሙ ይጠቅሳሉ። በዚህ አባባላቸው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ሲነሳ ፀሐፊው ዩኒቨርስቲ እንዳልነበሩ ይጠቁማል። አውሮፓ የነበሩ ተማሪወች በአምስተኛው ጉባኤያቸው ፊውዳሊዝምን ማውገዛቸውን እና ልክ እንደአዲስ ቀ ኃ ሥ ተማሪወች የመሬት ስሪት እንዲሸሻል ለመጀመሪያ በዚሁ በአምስተኛው የ1958 ስብሰባቸው አቅርበዋል ይሉና የሰሜን አሜሪካም ተማሪወች ማህበር በ 13ኛው አመታዊ ስብሰባው ንጉሳዊውን አገዛዝ ፈላጭ ቆራጭ እንደሆነ ኮንኖ የነጻ ሰራተኞች ማህበር መቆቋም ፈቃድ እንዲሰጥም ጥያቄ አቅርቧል ይላል።

ፀሐፊው ዶክተር ባህሩ ዘውዴን አጣቅሰው የ 1956 የሰሜን አሜሪካ ተማሪወች በነሀሴ ስብሰባቸው የመሬት ላራሹ የሚል መፈክር ይዘው መሰለፋቸውን ይጠቁማል። በፀሐፊው አባባል 1957-58 ሁለት አመታት ታላቅ የለውጥ አመላካች ሆኑ ይላሉ። ፀሐፊው በድጋሚ ዶክተር ባሕሩ ዘውዴን በማጣቀስ የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ተማሪወች ማህበር Ethiopian Students Union North America (ESUNA) ይባል የነበረው ማህበር መፈጠር በኋላ በሀገራችን ለመጣው አብዮታዊ ለውጥ ዋና ፈር ቀዳጅ መሆኑን ያጣቅሳሉ።

በገጽ 13 የ ቀ ኃ ሥ ተማሪወች ትግል በ 1960 የበለጠ ማህበር ማደራጀት ላይ አተኩሮ እንደነበር እና በግቢ ብቻ የሚሉት እና በዩኒቨርስቲ ደረጃ በሚሉት መካከል ትግል ተደርጎ በኋላ በዩኒቨርስቲ ደረጃ ያሉት አሸንፈው University Student Union of Addis Abeba (USUAA) ተቋቋመ አሸናፊወቹም በግቢ ብቻ የሚሉትን Restorers በሚል ስም ገለሏቸው ይላል። USUAA (ኦዙዋ)ላንድ እርምጃ ወደፊት ሂዶ በስድስተኛ ስብሰባው ላይ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላት አለማቀፍ ኢምፔርያሊዝም መሆኑ ተስማማበት ይላል። በ 1961 በበለጠ አህጉር አቀፍ የሆኑ ጥያቄወች እና መፈክሮች ላይ ተማሪው ማተኮሩን እና የሮዴሽያ (ዜምባቡዬ) ጉዳይ ዋና ስለነበር ተማሪው በዚሁ አመት እስከ አፍሪካ አዳራሽ በመሄድ ሰልፍ አድርጓል ይላል ገጽ 13 ም-3። በዚሁ አመት ከዚህም ከዚያም በነበሩ የተቃውሞ ትእይንቶች እና የታሰሩ ተማሪወች ይፈቱ በሚል መሪ መፈክር ተሳቦ ዩኒቨርስቲው ለሳምንታት ተዘግቶ እንደነበር ይገልጻል። በጅምላ ሳምንታት የሚለው የጸሐፊው ቃል ወር ይሙላ ይለፍን አያሳይም እና ይህ አይነት የአጻጻፍ ስልታቸው በጸሐፊው በቀጣይ ብዙ ቦታወች ይታያል። ለምሳሌ በዚሁ ምእራፍ እና በገጽ 14 የመጀመሪያ ምእራፍ ተማሪወች ወደ አፍሪካ አዳራሽ ሄዱ፣ ተሰለፉ እንጅ ቀን መቸ እንደሄዱ ለምን እንደሄዱ መቸ እንደተሰለፉ የተያዙ መፈክሮች እና መሪ ተዋነያን እነማን እንደነበሩ ዘርዘር ያለ መጣቀሻ አይሰጥም።

ገጽ 26 በወሰን ምክንያት በጎንደር ክፍለ ሐገር የተነሳው እንቅስቃሴ

በሚለው እርእስ ስር በክረምት ወራት ወደጎንደር ይዘልቃሉ። በአዲስ አበባ የተማሪ ማህበር፣ በአብዮት እና በንቅናቄው ንቁ ተሳታፊ ስለነበሩም ይህን የድንበር ጉዳይ አንድም ጉዳያቸው ስለሆነ ሌላም አንዱ ሕዝብን ለማታገል እና ማሰባሰብ ጥሩ እድል ፈጣሪ መሆኑን ተረድተው በዚያ ላይ አብዮት ከመጀመሩ አመታት በፊት ሕዝብን ማነሳሻ ለማድረግ ችለዋል። በዚህ እርዕስ ውስጥ ያካተቱት ቁምነገር ቢኖር የምእራብ ጎንደር በሱዳን መያዘን አመልክቶ ለያኔው የድርጅት ጓዶቻቸው ለጌታቸው ማሩ እና ለአብዩ ኤርሳሞ ገልጸው እና ተወያይተውበትም እንደነበር በዚሁ በተመሳሳይ ገጽ 26 ያሳያሉ።

ወረድ ብለው በአዲስ ገጽ ጅማሮ ገጽ 27 ምእራፍ 1 ላይ የጎንደርን ጉዳይ አንስተው የተወያዩት በ 1964 ክረምት በጳጉሜ ወደ ጎንደር ሄደው የጎንደርን ሁኔታ ከአቶ ፍስሐ መኮነን ጋር መነጋገራቸውን በዚሁ ገጽ ይጠቁማሉ። አንባቢ እንዲረዳው ማብራሪያ ከ (ገምጋሚው)። 1964 ዓም ከቅድመ የካቲት አብዮት አመት ተኩል በፊት ሲሆን ያ ዘመን ሐገራችን በለውጥ ጎዳና ላይ የነበረችበት – ንጉሳዊው ጥንታዊ ስርአት እጅግ ተንቆ የኮሰሰበት እና በእርግጥም አስቸኳይ ድርጅታዊ ጥንካሬን የሚፈልግበት ግዜ ነበር (ገምጋሚ)። ሆኖም ሕዝቡን አታግሎ ለድል የሚያበቃ የፖለቲካ ድርጅት ባለመኖሩ በሀገር ውስጥ የነበረውን ህሊናዊ እና ነባራዊ ሁኔታ ክፍተት ለመሙላት በውጭ የነበሩት የኢትዮጵያ ተማሪወች ማህበራት እና በይበልጥም በ1962 ዓም የኢትዮጵያን አውሮፕላን ጠልፈው ካርቱም ከዚያም አልጀርስ የገቡት አንጋፋ የተማሪው ንቅናቄ መሪወች ከላይ የተጠቀሰውን የድርጅት አስፈላጊነትን ባዶ ቦታ ለመሙላት የተነሳሱበት ውጤቱም አቶ ገዛኸኝ በመሪነት የታገሉበት በኋላ ድርጅት ኢሕአፓ (ኢሕአድ) በሚል በርሊን የተመሰረተበት አመት ነበር።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Hiber Radio: በእስራኤል የዘረኝነት ጥቃት ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የጠነከረ ተቃውሞ ተከትሎ ባለስልጣናት ዘረኛ እርምጃ የወሰደውን ፖሊስ እናባርራለን ማለታቸው፣ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ያላትን አቋም እንድትመረምር መጠየቁ፣በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን ሞተን ሻማ ከማብራታችሁ በፊት በሕይወት ታደጉን ሲሉ ጥሪ አስተላለፉ፣ዶ/ር መረራ በአገር ቤት ያለው የወጣቱ ሁኔታ ምርጫ 97ን ያስታውሳል ማለታቸው፣ የመኢአድ አባላት እየታፈኑ መወሰድ መቀጠሉ፣ የጦማሪ ሶሊያና ሺመልስ ቃለ መጠይቅ እና ሌሎችም

አቶ ታደለ ገዛኸኝ ከአቶ ፍስሐ ጋር ያደረጉት ልውውጥ ላይ አቶ ፍስሐ የመሳሪያ ትግል መጀመሩን እና አቶ ነጋ የተባለ ሰው ማሰለፋቸውን ገልጸውላቸው እንደነበር በዚሁ ገጽ ይጠቅሳሉ። አዲስ አበባ ተመልሰው ከጓዶቻቸው ከጌታቸው ማሩ እና ከአብዩ ኤርሳሞ ጋር ባደረጉት ውይይት ግን ለዚህ የአርሶአደር የመሳሪያ ጅማሮም ሆነ ድንበሩን የመጠበቅ መነሳሳትን እንደስብስብ መፍትሄ አለመበጀቱን በዝምታ ይዘሉታል። እንዴውም የጸሐፊውን ቃል በቀጥታ ልውሰድ እና እንዲህ ይላሉ።

“ስለድንበሩ ጉዳይ አንስቸ ለጌታቸው እና ለአብዩ ላስረዳቸው ሞከርሁ – አካባቢው ለትጥቅ ትግል አመች የሆነ መሆኑን እና እግራችንን ለመትከል ጥረት ማድረግ እንዳለብን አመለከትኋቸው። ስለድንበሩ ጉዳይ ሳወራቸው በስሜት ነበር የማወራቸው እንደጨረስሁ እራሳቸውን ደፍተው እየነቀነቁ ምንም ሳይመልሱልኝ ቀሩ።” በማለት ድንጋጤአቸውን ገልጸዋል (ገምጋሚ)።

በእርግጥ ነው ይህ የሆነው 1964 ጷግሜ መሆኑ ሳይረሳ ጌታቸው ማሩ እና አብዩ ኤርሳሞ ደርግ የጥረግ አዋጅ አውጆ የኋላው ድርጅታቸው አንዱ በፖሊት ቢሮነት የሚመራው ሌላው በአዲስ አበባ በይነቀጠና አባልነት የሚሳተፉበት አባላት በአደባባይ እየታረዱ ለምን መከላከል የሚል ነገር ታነሳላችሁ። ደርግ ተራማጅ ዝንባሌወች አሉት የጋራ ግንባር ፈጥረን ደካማ ጎኑን እያረምን መሳተፍ ይገባል በሚል እንዳፈነገጡ ይሰመርበት። ይህ የጌታቸው እና የአብዩ ኤርሳሞ የጎንደር ድንበርን እንከላከል የሚለው የአቶ ገዣኸኝ አቋም እንዳልተዋጠላቸው ሁሉ ደርግ ጨካኝ እና ወታደራዊ መንግስት ነው ከሕዝብም ለስልጣኑ ሲል ላይታረቅ ታሪካዊ ባህርይ አለው የሚለውን ኋላም አልተቀበሉም የልቁን የአብረን እንስራ ፕሮፖዛል ከድርጅታቸው በተሰወረ እንዳቀረቡ እና ያ ሳይሆን ሲቀር በድርጅት ውስጥ ድርጅት መሰረቱ የሚለው የኢሕአፓ አመራር ውንጀላ ቀራቢነት እንደሚኖረው ከዚህ ታሪክ ጋር ተያያዥ ይሆናል (የገምጋሚው)።

ምእራፍ 5፡ የዓብዮት እና የኢሕአድ መዋሀድ። ገጽ 50፦ በዚህ እርእሰ ነገር ላይ የመጀመሪያው የተደራጀ ትግል በታሰበበት እና በ1964 ዓም የኢሕአፓ እርሾ የሆነው ድርጅት ኢሕአድ በበርሊን እንደተመሰረተ ሁሉ በአዲስ አበባ ኢትዮጵያ ውስጥ ደግሞ በእድሜ ወጣት የሚሆኑ የ ቀ ኃ ሥ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች የሁለተኛ ደረጃ መምህራን እና ተማሪወችን ያሳትፍ የነበረ አንድ ስብሰብ ተፈጠረ ይላሉ ጸሐፊው። ስብስቡ ከኢሕአፓ ጋር እስከ ተዋኸደበት ግዜ ሁሉ በሚያወጣው በራሪ ወረቀት ስም ይጠራ ነበር እርሱም “አብዮት” በመባል ይላሉ አቶ ገዛኸኝ። ይህን ስብስብ የፈጠሩት መጀመሪያ ጌታቸው ማሩ፣ አብዩ ኤርሳሞ እና ታደለ ገዛኸኝ በአቀራራቢነት ሲሰሩ መቆየታቸውን ያትታሉ። በኋላ ድርጅታዊ መልክ ሲኖረው ጌታቸው አሰፋ፤ ኤርምያስ ሚካኤል እና ስዩም (አራርሳ) በመሆን መልክ እና ቅርጽ ያለው ድርጅት በ1964 የመጨረሻ ወራት ተፈጠረ (ጸሐፊው)።

ከዚህ ግዜ በኋላ ድርጅታዊ ስራ የጀመረው አብዮት ብዙ ወጣቶችን በዙሪያው ማሰባሰቡን እና በድንገት የደረሰው የ 1966 አብዮት ሰሞን ሁለቱ አመራሮቹ ጌታቸው ማሩ እና ታደለ ገዛኸኝ ለእስር መዳረጋቸው በመጠኑም ቢሆን የማደራጀት ስራው እንዲጓተት ሆኗል ይላሉ። በዚህ ገጽ የጌታቸው ማሩን ንቁ አብዮታዊነት እና ታታሪ አደራጅነቱን የእርሱ መታሰር ሁሉንም የአብዮት ስራወች እንዲቆሙ አድርጎ ነበር ባይ ናቸው። አቶ ታደለ የጌታቸው ማሩን ባህርይ ሲገልጹ አንዴ ያለውን ቃል የማይለውጥ እርሱ ብቻ ያለው ትክክል ነው ብሎ የሚያምን ሰው ነው ይላሉ።

ጌታቸው እና ታደለ ከእስር ከወጡ በኋላ ታደለ በቆቃ እና ወንጅ ከላባደሩ እና ማህበራቸው ጋር ግንኙነት እንደጀመሩ ያትታሉ። የአቶ ታደለ ገዛኸኝ ጠንካራ ስራ ወደኋላ በኢሕአፓ ውስጥ እንደታየው ወደጎንደር ያደረጉት ትኩረት ውጤት ሁኔታወች ተለውጠው እና አንጀኝነት እና በታኝነት በድርጅቱ ነግሶ ባጭር ባያስቀረው አፍ ተሞልቶ ውጤት የተገኘበት እንደነበር ይህ ገምጋሚም ከእርሳቸው ባገኘው እና በተግባር በዚያ የጎንደር-ጎጃም በይነ ቀጠና ስር የተንቀሳቀሰ በመሆኑ ምስክር ነው። ትረካውን በመቀጠል ጌታቸው እና ታደለ ከእስር ከተፈቱ በኋላ ሌላው የተሰራው ስራ ከዴሞክራሲያ (ኢሕአፓ) ጋር የተደረገው የመቀላቀል ውይይቶች መጀመር እንደነበር ይገልጻሉ። መቀላቀሉ ለሁለቱም ውብ እድል ወይንም ክፉ ገጠመኝነትን በዚያ ትግል ያለፈ ሁሉ ሊገልጸው ይችላል። በተለይ እንደዚህ ገምጋሚ በቀዩ ሽብር ወላፈን ውስጥ ከምርመራ ሸምቀቆ እስከ እስርቤት እና ከፋሽስቶች መዳፍ ማምለጥን ያየ እና በ ሀ እና ለ የአንጀኝነት ጉዞ የደረሰውን ግዙፍ የህይወት ጥፋት ያነን የሁለቱ ጋብቻ ባይኖር ምናልባት ሰፊው ጥፋት ባንሰ ተለውጦ ብዙ ጭንቅላት የነበራቸው ያለእድሜ የጠፉ ሰማ’እታት ሁነኛ የትግል አቅጣጫን አስተካክለው ያስቀጥሉት እና ይህ አሁን ያለንበትም ሁኔታ ባልኖረ እንድንል ለሐገር ያጎናጽፉ ነበር (ገምጋሚ)።

በገጽ 54፡ አቶ ታደለ ገዛኸኝ ከዴሞ ጋር በሚደረገው የውህደት ውይይት ዴሞወች ሕዝባዊ መንግስት ሲሉ ትክክል ያለመሆኑን ይዘን ቀርበን ነበር ይላሉ። ለዚያ መከራከሪያ አብዮቶች ያደረጉት ሕዝባዊ መንግስት ሊቆቋም የሚችለው በላባደሩ እና አርሶ አደሩ በተመራ አብዮት እንጅ ከሙያ ማህበራት እና ከብዙሀን ድርጅቶች በሚመረጡ ተወካዮች አይደለም የሚል ነበር።

የገምጋሚ አስተያየት፡ እነ ጌታቸው ከዴሞ ጋር ተለየን የሚሉት ይህን ገምጋሚ እንደሚመስለው የላባደሩ እና ጭቁን አርሶአደር ስልጣን የሶሻሊስታዊ ስርአተ መንግስት እንጅ ከፊውዳላዊ ማህበረሰብ ወጥቶ በወታደር ከተያዘ ስልጣን የሚያሸጋገር ሊሆን አለመቻሉን የአረዳድ ችግር ወይንም ያኔ እንደሚባለው ግራ ጽንፈኝነት እና ከጭብጥ ሁኒታ የራቀ አስተሳሰብ በነ ጌታቸው እንደነበረ አመላካች ነበር። “ኢህአፓ ጊዚያዊ ሕዝባዊ መንግስት” ዲዴሞክራሲ ያለገደብ ለሕዝብ ሲል መፈክሩ በእርግጥም ግዜውን የሚመጥን ትክክለኛ መፈክር እንደነበር በኋላ አብዮቶች ተቀብለው እንደተዋሀዱ ያሳየናል።

ከውህደቱ በኋላ እና

ምእራፍ 7 ገጽ 77፦ የመሬት አዋጅ፤ እድገት በሕብረት እና ሶሻሊዝም።

ምናልባት አቶ ታደለ ገዛኸኝን አይነት አብዮተኛ ያኔ ቢኖር እና የያኔውን መጭ ዘመን በተወለደበት አካባቢ እንዲሰራ በትጋት ቢሰራ ኖሮ ኢሕአፓ በጎንደር እና ጎጃም ያገኘውን ተቀባይነት እና ጠንካራ መዋቅራዊ ትሥስር ቀዩ ሽብር ቀርቶ ምንም የሚበግረው የማይችል ድርጅት በሆነ ነበር። ይህ ገምጋሚ እንደሚመሰክረውም የጎንደር ጎጃም በይነ ቀጠና ጠንካራ እንዲሆን ያደረገው እና ድርጅቱም ከትግራይ መጀመሪያ የትጥቅ ትግል ከጀመረበት አካባቢ አሲምባ በጠባብ ብሔርተኛዋ ህወሓት ተገፍቶ ሲወጣ በቀላሉ ወታደራዊ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል አስችሎታል። ያ ብቻ አይደለም በተከታታይ ቀውስ የተመታው ኢሕአፓ በበለሳ (በሦስተኛው ሪጅናል ሰራዊት) የተጀመረው የውስጥ ምንደኞች እና የህወሓት አንጃ ጥምር ያስከተለውን ጉዳት ተከትሎ በሁሉም አካባቢወች ከደረሰበት ጉዳት ለማገገም ወደ ኤርትራ ማፈግፈጉ እና መልሶ ጎንደር ጎጃም ከብተናው በኋላ መመለሱ ድንቅ አስተዋኦ የአቶ ታደለ ገዛኸኝ የቀደምት ነቅቶ መዋቅር ማዋቀር፣ ማደራጀት እና አርሷደሩ በተለይ በእድገት በህብረት የተማሪ ዘመቻ ወጣት ተማሪወች የተላኩበትን ትተው ሕዝብን ማደራጀት ማንቃት በትኩረት ማድረጋቸው ለዚያ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያበረከተው የጎንደር ጎጃም በይነ ቀጠና እና ይህን ቀጠና አሰባስበው እና አደራጅተው ለትግል ላበቁት አቶ ታደለ ገዛኸኝ መሆኑን ማሳየት ያስፈልጋል።

ሆኖም ያነን ያዋቀሩትን በይነ ቀጠናም ሆነ የትግል ሜዳውን በተፈጠረው የጨለምተኝነት ድባብ ትግሉን ትተውት መሄዳቸው ለምን እንዲል ይህን ገምጋሚ አድርጎታል። በቀጣይ ገጾች እንደምመለስበት ሁሉ በበለሳ የጠላት ሰርጎገብነት እና ንጹሐን አባላት እና ምናልባትም የሪጅኑ እመራር አባላትን አስሮ የተካሄደው ድርጅት የማፍረስ ስራንም ሆነ በመስዋ’እትነት የተገነባውን ነጻ የወጣ ቀበሌ መልሶ ለጠላት ለቆ መውጣት እና የዚያ የማፍረስ ድባብ ወደምእራብ ተዛምቶ በድርጅቱ ላይ የደረሰውን ጉዳት በግንባር መመከት ማረጋጋት እንደእሳቸው ያለ ታጋይ መሪ ሊሰራው የሚገ ሆኖ እያለ – ትግል የማስቀጠል የክፉ ቀን ስራን ለሌሎች ጥለው ያደራጁት ያሰባሰቡትን ብሎም ነጻ እንዲወጣ ሁነኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱበትን ሜዳ ባሻው እንደአወጣጡ ይወጣው ብለው ወደስደት መሄድ ምንም እንኳን እንደሌሎች ቢሆኑም የተለየ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ግን በትከሻቸው እንደነበር ያነንም በጽሁፍ በዚህ ግለታሪካቸው አለማሳየታቸው ለዚህ ገምጋሚ ግራሞትን አሳድሮበታል።

በገጽ 78 ጸሐፊው “ዘመቻው አይቀሬ መሆኑን የተረዳው ኢሕአፓ ዘመቻውን ለመጠቀም አንዳንድ ዝግጅቶችን አከናወነ” ይላሉ

እውነታው ምናልባት አቶ ታደለ ገዛኸኝ በአደራጅነት በተሰለፉበት የጎንደር ጎጃም በይነ ቀጠና እንደሆን እንጅ ይህ አበባላቸው በተግባር ተከናውኖ ነበር የማያስብሉ አያሌ ኩነቶችን ማስፈር ይቻላል። ከላይ ለማሳየት እንደሞከርኩት ዘማቹ በብዛት ለቆ የወጣው እና ወደቤቱ የተመለሰው በሰኔ ሐምሌ 1967 ዓም ሲሆን ምናልባት የኢሕአፓ አመራር ሁኔታውን የተረዳው እና ዘመቻው እንዲቀጥል ማበረታታት የጀመረው ከሲዳሞ እና የከፋ ዘማች ተማሪወች አመጽ እስራት እና ግድያም በኋላ ነበር። እናም አንዱ የዘመቻው አባል የነበረው ይህ ገምጋሚም የኢሕአፓ ዘመቻው ቀጥሉ የሚለውን የሰማው ኋላ መሆኑን እንዳጋጣሚ ግን ዘመቻውን ጨርሰው ከተመለሱት መሆኔን በተጨባጭ የማውቀው እንደብበር ሲሆን። ኢሕአፓ ዘመቻውን በበቂ ተጠቅሞበት ነበር ብሎ ለመናገር የሚያስችል በአቶ ታደለ ገዛኸኝ በሚመሩት በይነቀጠና ብቻ እንደነበር ቢባል ምንም ስህተት የለውም። በደቡብ፤ በምስራቅ እና በምእራብ ዘመቻው ምንም እኳን የመሬት ባላቤት የሆኑትን መሳፍንቶች ፊትለፊት የገጠመ እና ጢሰኛውን በሙሉ እምነት ኮጎኑ ያስለፈ ቢሆንም የዚያን የለውጥ ኃይል አጋሩ ከማድረግ ይልቅ የነዘገየ አስፋውን ኦነግ እና የነ ኃይሌ ፊዳ መኢሶንን ከደርግ ጋር እጅ እና ጓንት የነበሩትን የጠቀመ አብዮታዊውን ወጣት የቀደምት የመሬት ላራሹን መፈክር አንግቦ የታገለውን አግላይ እና አርሷደሩ እንደጎንደር እና ጎጃም ትግራይ አርሷደር መጠጊያ ከመሆን ይልቅ ለወታደራዊው መንግስት እና ተከታይ አድርባይ ድርጅቶች አቃፊ እስከመሆን የሄደበት ሁኔታ ተስተውሏል። ለምሳሌ ወለጋ የዘመትነው የኢሕአፓን መስመር ደጋፊ ዘማቾች ሆ ብለን እንደገባነው ሳይሆን ዱላ እና እስር እየቀመስን ተሹለክልከን መመለሳችን የሚታወቅ ነበር።

ገጽ 86፣ ምእራፍ 8 የጎንደር ዞን

ህሊናዊ እና ነባሪ ሁኔታ ግጥጥሞሽ የታየበት ጎንደር መሆኑን አቶ ታደለ እንዲህ ሲሉ አስቀምጠውታል። “ጎንደር የተማሪው እንቅስቃሴ ጉልበት ያገኘው በ 1957 ዓም ጀምሮ ነበር። የተማሪወች ካውንስል ተቋቁሞ ዘዋለ ዘገይየ ሊቀመንበር፤ ሞሐመድ ጣህር፣ ወንድሚነህ ዳኛው፤ ባዬ ንጋቱ፤ ፍርኑስ አስናቀ፤ እና አያና እንየው በአባልነት ሲመረጡ ነበር” ይላል።

ወደዝርዝር ከመሄዴ በፊት – ባዬ ንጋቱ የባሕርዳር ሁለተኛ ደረጃ እና ፖሊቴክኒክ ተማሪወችን ንቁ የለውጥ ደጋፊ እንዲሆኑ እና ትግሉን ከጥቃቅን መፈክሮች አውጥቶ ወደሐገራዊ መፈክሮች ብሎም የትግል አቅጣጫው ሁኋላ ወደ ኢሕአፓ ያጋደለ ስራ ከሰሩት አንዱ እንደነበር የዚህ ገምጋሚ ትውስታ እና የባየ ንጋቱ ተማሪ እንደነበር እና የጎንደር የቀደምት አብዮተኞችን ሰፊ አስተዋጸኦ ይረዳል።

1957 የኢትዮጵያ የለውጥ ፈር ቀዳጅ ምሁራንን ያፈራው የቀ ኃ ሥ ዩኒቨርስቲ ተማሪወች እንኳን በቅጡ ወግ ባለው አንድ ወጥ ማሕበር ለማቋቋም ያልደረሱበት ግዜ መሆኑን በመረዳት የጎንደር የሁለተኛ ደረጃ እና የጤና ኮሌጅ ተማሪወች የንቃት ደረጃ ከፍተኝነትን የሚያሳይ ነበር። በመሆኑም ከላይ የተጠቀሱት ተማሪወች ወደ ዩኒቨርስቲ ሄደውም ሆነ በትውልድ አካባቢያቸው የተጫወቱት የለውጥ ሚና የሚደነቅ እንደነበር አቶ ታደለ ገዛኸኝ በቀጣይ ምእራፎች በበቂ አብራርተውታል። ለአንዳንድ አሁን ላይ ጥያቄ ለሚያቀርብ ልቦና ለአገራዊ ትግሉ ቀደምት የሆነው የጎንደር ጎጃም አካባቢ እያለ ያውም ለአንዳንድ የድርጅትን ስራ ለማካሄድ ከውጭ ግንኙነት ለመፍጠር የሚያስችል ጅኦግራፊ እያለው የትጥቅ ትግሉን አሲምባ ትግራይ መጀመሩ ለምን አስፈለገ? ተብሎ መጠየቁ በኋላ ድርጅቱን እስከማጥፋት የተሄደው የጠባብ ብሒርተኞች እና የተገንጣዮች በትርን ማምለጥም ሆነ የተከተለው የፖለቲካ ቀውስን ማስቀረት ይቻል ነበር በሚል የሚሞግቱ እንዳሉ እንደተጠበቀ ሁኖ አቶ ታደለ ይህን የታሪክ ድባብ በጥሩ ሾፌርነት ትውልድ እንዲማር በዚህ መጽሐፍ አሳይተዋል ባይ ነኝ።

በዚሁ ምእራፍ በኋላው ትግሉን እስከመጨረሻ የሞት በራፍ የተጓዙት እና ቃል ኪዳንን ያላፈረሱት ውብ ታጋዮች እንደነ ስጦታው ሁሴን እና ከበደ አይነት ታጋዮች የበቀሉበት መሆኑን በውብ ብእር አስቀምጠዋል። አቶ ታደለ እነዚህን ቀደምት የአካባቢው ተወላጅ ታጋዮችን የድርጅት ጥያቄ መልእክተኛ በመሆን ያደራጁ በመሆኑ እና ይህን ታሪካቸውንም በመልኩ ማስቀመጣቸው እጅግ የሚመሰገን ነው። በገጽ 89 እንደተቀመጠው የጎንደርን መዋቅር ማዋቀር እና የቀጠና ኮሚቴውን በመሰየም ወደ ጎንደር ተጉዘው መንግስቱ ቀፀላ፣ አክሎክ አስካል፣ ሰሎሞን ከበደ (ሽባባው በሚል ስም ወደባሕርዳር ተልኮ የዚያን አካባቢ መዋቅር እንዲያግዝ የሆነ እና ባሕርዳር የተሰዋ ብለዋል ታጋዮችን መልምለው የመጀመሪያውን ቀጠና ኮሚቴ ማዋቀራቸውን ይገልጻሉ። በሪሁን ዳኘ ወደ ደብረማርቆስ ሄዶ ያነን ከባቢ የቀጠና ኮሚቴ እንዲያጠናክር የተላከ እና በተግባር ላይ እያለ ስራውን ሰርቶ በዚያው መስዋ’እትነት የከፈለ ለነዚህ ሁሉ ታሪካቸው እና የትግል አስተዋጸኦ ከጸሐፊው ተግባራት ጋር የተቆራኘ መሆኑን ስናይ በእርግጥም በኋላ እንዲህ ተብየ ነበር የሚለው ግላዊ አስተሳሰብ ውጭ የሚያኮራ የትግል ታሪክ ይሰኛል ባይ ነው (ገምጋሚ)።

የጀመሩትን ስራ ዳር ለማድረስ የእድገት በሕብረት ምድባቸውን ወደ ጎጃም ጎንደር ለማዞር አዲስ አበባ በመመለስ ያሰቡትን አሟልተው ምድባቸው ባሕርዳር ጣቢያ ማድረጋቸው ቀደም ብሎ ተጀምሮ የነበረውን የማደራጀት የማሰባሰብ ስራ በእርግጥም ዳር ማድረስ የሚያስችል ዝግጅት ፈጽመዋል። ለዚህ ሁሉ የቀደምት ንቃተህሊና እንደነበራቸው የዚያ ትውልድ መሪወች ከግዜ ቀድመው መፈጠር እና እጅግ በትንሽ ስህተት እና የነዚያን ተርብ ታጋዮች ህልም ጠላት ተረባርቦ እንዴት እንዳደበዘዘው ይህን መጽሐፍ ያነበበ በግልጽ የሚረዳው ይሆናል።

ተጨማሪ ያንብቡ:  Bollywood charms Ethiopia

ገጽ 96 “ኮሎኔል አስናቀን ከሌላ ድርጅት ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ካወቅሁ በኋላ በድርጅት መልክ ያዝኳቸው።”

“ከዚያ የሚቀጥለው ኮሎኔል እምሩን መገናኘት ነው። የጎንደር ክፍለሐገር አስተዳዳሪ ሆኖ ተሹሞ መጥቷል። ከኮሎኔል አስናቀ ጋር የማይለያዩ ጓደኛሞች ናቸው። በ1956-57 በነበረው መፈንቅለመንግስት ተጠርጥረው (ንጉሠ ነገስቱን ለመገልበጥ ማለት ነው) ለአምስት አመታት አብረው ታስረዋል።”

ከአቶ ታደለ ትላልቅ የማደራጀት ሥራወች ውስጥ አንዱ እነዚህ በጎንደር ክፍለሐገር ስም የነበራቸው እና ጥንታዊውን የመሳፍንት እና ንጉሳዊ አገዛዝ በግልጽ ይቃወሙ የነበሩ ሁለት ሰወችን ወደኢሕአፓ ማስጠጋት ብሎም በድርጅት ከሌሎች አስተዋውቆ ለትግል ማሰለፍ ትልቅ ውጤት ነበር። ያ ብቻ አይደለም አቶ ታደለ በቀጣይ ከጓዶቻቸው ሁሉ ጋር በተዘዋዋሪም ቢሆን አሽሙር ውስጥ ያስገባቸው እነዚህን ሰወች የኢሕአፓ አባል ወዳጅ አድርጎ ሌላ ቀኝ ዘመም ድርጅት አዋቅሮ የዚያ መሪወች እንዲሆኑም ማስቻል ትልቅ አስተዋጽኦ ቢሆንም በተደራጀው ድርጅት ግን ሳይሰራበት ቀርቷል ወይንም የኢሕአፓን መሰረታዊ መርህወችን ወደመጻረር ሔዷል የሚያሰኝ ስራውች በመሰራታቸው በአንድ ወቅት ሀገር ወዳድ አልፎ ተርፎ በድርጅቱ ላይ የተነሳውን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ “የቢትወደድ አዳነ መኮነንን ሞት” ተከትሎ አንዱ አራጋቢ እንደነበር ገምጋሚው የሚያስታውሰው ጉዳይ ነበር። ከአያያዝ ይሁን የትላይ ስህተቱ እንደተጀመረ ይህ ገምጋሚ ባያውቅም በአርማጭሆ ይንቀሳቀሱ የነበሩ አንዳንድ የጎበዝ አለቆች ይህን የሀሰት ትርክት ተጠቅመው ጦርነት እስከማወጅ እና የታጋዮችን የአላግባብ መስዋ’እት መሆንን አድርሰው እንደነበር ይታወሳል። ሆኖም ሁለቱም ግለሰቦች የኢሕአፓ እስከ ህይወት ፍጻሜ ወዳጅም እንደነበሩ የኮሎኔል አስናቀ እንግዳ ከዘራቸውን ይዘው በ94 አመታቸው የቀድሞ የኢሕአፓ ጓዶችን መልሶ ማሰባሰብ በተጠራው የአትላንታ ጉባኤ ጭምር ድረስ መገኘት እና የኢሕአፓን አንጸባራቂ ተጋድሎ መስካሪ እንደነበሩ ነፍሳቸው በአጸደ ገነት ያኑርልን እና ይታወሳል። ይህ ስራ የአቶ ታደለ ገዣኸኝ አስተዋጸኦ መሆኑን እንድንገነዘብ በዚህ የግለ ታሪክ ድርሳንም ቀርቧል ውብ ዘገባ (ገምጋሚ)።

“ገጽ 100 የኢሕአሰ ጎንደር መግባት እና የበለሳው ቀውስ” ይላል ንዑስ እርእስ ነው።

ኢሕአሰ (የኢትዮጵያ ሕዝብ አብዮታዊ ሰራዊት) ጎንደር ከመግባቱ በፊት የጎንደር ቀጠና ኮሚቴ ጽናቶች እንደነበሩት እና ሁለት ቀበሌወችን ለሰራዊቱ መግባት የፖለቲካ ማህበራዊ ጉዳዮችን በመገምገም መርጦ ለበላይ አካል ማስተላለፉን ጸሐፊው ዘግበዋል። ያነንም ተከተሎ ጓድ እስክንድ ወደ ክፍለሀገሩ እንደተላከ እና ጠለምት እና መተማን አጥንቶ መመለሱን ያሳያል። ከአጭር ግዜ በኋላ ጠለምት መመረጡን እና በህቡ የሰራዊት አባላት መግባታቸውን ያትታል። በጸሀፊው አስተያየት ግን ሁኔታወችን በክፍለ ሐገሩ እዚህ እንዲደርሱ ያደረጉ ጓዶች ሳይሆኑ የበላይ አካል በኮሚቴ የተያዘ ውሳኔ ማድረጉ ተገቢ አይደለም ባይሉትም አጸጻፋቸው ገላጭ ነበር። ሆኖም ሰራዊቱን ለመረዳት እና ገና ያልጠና ጉልበቱን ለማጎልበት የቀጠናው የድርጅት ኮሚቴ ሰፊ ሚና መጫወቱን ያሳያሉ። ዋና ታሪካዊ ትምህርት ሰጭነቱ የበለሳው ኦፕሬሽን ሲጀመር አግባብ ያልነበረው የአመራር ብቃትም ታስቦ ያልታደለው ስለነበር ከፍተኛ መስዋእትነት ድርጅቱ መክፈሉን በተለይም የክፍለ ሐገሩ አስተዳዳሪ የቆሰሉ ጓዶችን ደም የተነከረ ኩሽክ በማየት ያሳዩትን ጸጸት ጨምረዋል። ይህ ለግንዛቤ እና አስተማሪነቱ ይጠቅማል ምናልባትም ዝግጅት ቢኖር እና ግልጽ የሆነ ቅንጅት ቢሰጠው አደጋው ባልተከሰተ ማለት ነው።

ገጽ 106 – የጎንደር ጎጃም በይነ ቀጠና (ኢንተርዞን)

በይነቀጠናው በሦሥት ቀጠና (ዞናል) ኮሚቴወች የተዋቀረ ነበር ይላል።

ጸሐፊው ግለታሪካቸውን ሲዘግቡ በብዙ የግል ማስታወሻወች መውሰዳቸውን ይጠቅሳሉ። በዚህ መጻሕፍ እና ውብ አቀራረብ ላይ ካየኋቸው ጉድለቶች እና እንደአንባቢ ማወቅ የፈለግኋቸው ቀናት እና ወራት ግን በብዙ ቁልፍ በሆኑ እርዕሶች ላይ አላገሁኋቸውም። የጎንደር ጎጃም በይነ ቀጠና (ኢንተር ዞን) ሲቋቋም ሦስት ቀጠናወችን ማቀፉን እና የመጀመሪያው የጎንደር ቀጠና መሆኑን ይጠቅሳሉ። በቀጣይ የተቋቋመው የባሕርዳር ቀጠና ሲሆን መጨረሻ የደብረማርቆስ ቀጠና መቋቋሙን ያሳያሉ ሆኖም መቸ? እነዚህ ቀጠናወች ተቋቋሙ የግዜ ሰሌዳ የለም። ለታሪክ ይህ አስቸጋሪ ይመስለኛል። ይህ ገምጋሚ በነዚህ ቀጠናወች ስር የታገለ እና ብዙ የተቀያየሩ የተጨመሩም እንደነበሩ ሁሉ ቀናትን እና ወራትን ባለማሳየቱ አፈ ታሪክ እንዲመስል አድርጎታል። በይነ ቀጠናው ለምሳሌ ጸሐፊው በ 1968 መጨረሻ ተቋቋመ የባህርዳርን እና የደብረማርቆስን ቀጠናወች ለማቋቋም እገዛ ሽባባው እና በሪሁን ዳኘው ባህርዳር እና ደብረማርቆስ ተልከው አጠናከሩ ይልና መቸ ሄዱ መቸ ሁለቱ ጓዶች እስር ገቡ መቸ ተሰው የሚለው የለም። የበይነ ቀጠናው አባላት ታደለ፣ አያ እጅጉ፣ ደማስ እና መንግስቱ የመጀመሪያ የበይነ ቀጠናው የኮሚቴ አባላት እንደብበሩ ያትታል። ሸዋ አረጋ የባህርዳር ቀጠና ከሌሎች ሁለት ጓዶች ጋር እንደነበረም ያሳያል። ሸዋ’አረጋ ሳሕለሚካኤል ይባላል የባህርዳር ሁለተኛ ደረጃ እርእሰ መምህር ሆኖ በመጋቢት 19 ቀን 1970 እራስ ማጋለጥ በሚባል የእስታዲዮም የደርግ ዘመቻ እራሱን ተራ አባል እንደነበር አጋልጦ በአሰሳ የተገኙ የኢሕአፓን ወረቀቶች በእስታዲዮሙ የማጋለጥ ስራ ሸዋ’አረጋ ወረቀቶችን አቃጣይ ሆኖ እንደዋለ ከጓዶች የተሰማ ታሪክም አለ (ገምጋሚ)።

ለማነኛውም ይህ የጎጃም ጎንደር በይነ ቀጠና (ኢንተር ዞን ኮሚቴ) ያቋቋሙት እና ለትግል ያበቁት አቶ ታደለ ታደለ ገዛኸኝ እንደጠቀሱት በይነ ቀጠናውንም ሆነ አራቱን ቀጠናወች በ1966 ከውጭ የገባው የዴሞ ግሩፕ ሰወች አሉኝ ቢልም ምንም አለመገኘቱን እና ኮሚቴወቹ በ እርሳቸው በነበሩበት የአብዮት ግሩም የተዋቀሩ መሆናቸውን በዚህ ገጽ ይገልጻሉ። ምን ያህል እውነት መሆኑን አስረጅ ግን ሌላ ሶርስ የለም።

“ገጽ 109 ከኢሕአፓ ማህከላዊ ኮሚቴ ጋር  እስከ 1969 አጋማሽ” በዚህ እርእስም “እስከ 69 አጋማሽ” ይላል አጋማሹ መች ይሆን?

ውህደቱ ይልና ጸሐፊው ድርድሩ እና ንግግሩ አልቆ በአብዮት በኩል ለአንዳንድ አካባቢወች እንዲዘገይ ተወስኖ ጸሐፊው የነበሯቸውን ግንኙነቶች አስታውቀው ወደጎንደር ሔደው ለመስራት ዝግጁነታቸውን መግለጻቸውን ያሳያሉ። እዚህም ላይ መች ነበር ይህ የሆነው የሚለው ቢጠቀስ ውብ እና ምሉእ ነበር ግን አልተጠቀሰም። በስራቸውም ይገናኙ የነበረው ከዶክተር ተስፋየ ደበሳይ እና አንድ ቀን ከሳሙኤል አለማየሁ ሌላ ቀን ከዮሴፍ አዳነ ተገናኘሁ ይላሉ። ዶክተር ተስፋዬ ወደሐረር እንዲሄዱ ምድባቸው በሙያተኝነት እዚያ እንደነበር ቢነገራቸውም የጀመርሁት እና ውጤት ሊኖረኝ የምችል ጎንደር ነው በማለት ያለ ተጨማሪ ጥያቄ እና ተጽእኖ ወደ ጎንደር ጎጃም በይነቀጠና አምርተው በቀጣይ የሰሩትን ስራ በዝርዝር አስፍረዋል።

በገጽ 111 እንደጠቀሱት ምንም እንኳን አብዮትን ወክለው ወደአመራር የገቡት ጌታቸው ማሩ ጋር እርሳቸው አንዱ ቢሆኑም፡ እንደሚታወቀው ጌታቸው ማሩን በረጅሙ የአብሮ ቆይታቸው ቢያውቁት እና የድርጅቱ ስራ አስፈጻሚ አንዱ ቢሆንም እንዲህ ይላሉ።

“ዞር ብዬ ወደ ኋላ ስመለከት ለመሐከላዊ ኮሚቴው እንሰጥ የነበረ አክብሮት እና እምነት ሰማይ የደረሰ ነበር”

ይህ ማለት የሚያሳልፈው ውሳኔም ትክክል እና ስህተት የለሽ ነው ለማለትም ይሆናል እና መጠየቅ አያስፈልግም ብለው ያስቡ እንደነበር ይገልጻሉ። ችግሩ ደግሞ አመራሩ የጋራ አመራር ባህል መያዝ ያስገደደው የብርሐነ መስቀልን የይገባኛል አስተሳሰብ እና ተክለሰውነትን ለማስወገድ ነበር። አቶ ታደለ በዚህ አጸጻፋቸው ከአንድ ሰው ተክለ ሰውነት የብዙሐኑን ማመናቸው ክፋት የለውም ግን እንደአንድ መሪ ደግሞ እራስ መተማመንን የሚያደበዝዝ አስተሳሰብ እንደሆነ እና ለብዙ ስህተቶች በተለይ በ አራተኛ ማኮ ስብሰባ ድርጅቱ እራሱን መውቀስ የቀደመ የ3 ኛው ፕሌንዬም ያመነባቸውን ልክ አልነበሩም ማለቱ ማኮ ትክክል እና መጠየቅ የማይችል የሚለው አስተሳሰብን ማደብዘዝ ብቻ ሳይሆን ጨርሶ እምነት እንዲሸረሸር እና ሁሉ በየ ፊናው ድርጅትን እየበተነ መጓዝን ያስከተለ አስተሳሰብ በእሳቸውም ውስጥ ማደጉን በዚህ አጣጣፋቸው ያሳዩናል።

የ ሀ እና ለ ጉዳይ ገጽ 123 የአቶ ታደለ የመጀመሪያ የማኮ ስብሰባ መሳተፍ ሲሆን ጉዳዩም በድርጅቱ የተነሳው ልዩነት ዋና ጉዳይ ነበር። ግዜው 1968 ዓም የመጨረሻ ወራት እንደመሆኑ በዚህ የግዜ ሰሌዳ ደግሞ ወታደራዊው መንግስት ያለምንም ተቀናቃኝ የማርሽ ወታደራዊ ጥሩንባውን እያሰማ የሚገድልበት እንጅ በተቃዋሚወች አንድም የተተኮሰ ጥይት ያልነበረበት ቢሆንም የኢሕአፓ አባላት መሪወች ጭምር ያለ እንበለ ፍርድ የታሰሩ እና የተረሸኑበት ሁኒታ ነበር። በዚያ የ1968 የክረምት ወራት ወታደራዊው መንግስት ፍጹም ሽብር ያካሂድበት የነበር ጊዜ ከመሆኑ አልፎ እንኳን ሲቪሊያን ይቅር እና የደርጉ አባል ሲሳይ ሐብቴ ጭምር የነጻው እርምጃ ሰላባ የሆነበት ሰአት ነው። የድርጅቱ አመራር የራስ መከላከል አስፈላጊነት ላይ ቢያምን እና የመከላከያ አሀዶች ቢያቋቁም የነጌታቸው ብርሐነመስቀል ማፈንገጥ ምን ባይ እንደነበር እስካሁን ለብዙወች የሚገባ አይመስለኝም። ደርግ ጋር እናብር ማለትም የትም የማያስኬድ ስንካላ የክህደት ጉዞ ካልሆነ በቀር አመት ባልሞ ግዜ ውስጥ ደርግን ደግፈው Critical Support ያሉት እና የአንድ ትውልድን ፍጅት እስትራቴጅ በቀይሽብር ለደርግ ያሰለጠኑትን ሳይቀር እነ ኃይሌ ፊዳ፣ ንግት አዳነ፣ አይነት ሰወችን መትሮ የበላ መንግስት መሆኑን አሳይቷል። የብዙሐኑ የኢሕአፓ አመራር አቋምም ልክ እንደነበር መስካሪው የደርግ ስራ እና ተባር ነበር። በ አንጃው የተበላውን ታጋይ ወጣት ሳይሆን ክህደት የፈጸሙትን ዛሬ ዛሬ ሊያወድሱ የሚነሱ ስናይ ግዜው የተገላቢጦሽ መሁኑን አንስተውም።

ለማነኛውም አቶ ታደለ በገጽ 125 በማኮ የቀረበበትን ጌታቸው ምላሽ ሲሰጥ የተናገረውን እና ሙሉ ፖሊት ቢሮው ያስተባበለውን ቃል “በከተማ ትጥቅ ትግል ፓርቲው ስልጣን ይይዛል ያለህ ማን ነው?” “ለመጀመሪያ ጊዜ ተስፋየ ደበሳይ ተናዶ ሲናገር አየሁ፤ ጌታቸው ደግሞ ብላችኋል ብሎ ግግም አለ” ይላሉ። ወረድ ብለው ሳሙኤል (በላይ) ስለዚህ ቀን ስብሰባ ጭልጋ እያለን አንስቶ ጌታቸውን ማነው ያለህ ሲሉት ታስታውሳለህ ወይ ብሎ ጠየቀኝ” ይላሉ። ነፍሳቸውን ከደጋጎች ጎን ያኑር የነዚያ ጓዶች እና አንዳቸውም ይህን ቃል አለ አሉ የሚለን ከምን እና እንዴት ተነስቶ መለዋወጣቸውን አቶ ታደለ ባለማብራራት የሚያልፉቸው ሁሉ ብዙ መብራራት ይፈልጋል። ጓድ በላይ ታስታውሳለህ አለ የሚለው ቃል ለማንም ግልጽ አይደለም። ምክንያቱም አንጀኝነትን እና ብተናን ተቃውመው ትግሉን ካስቀጠሉት ትቂት ጓዶች አንዱ ሳሙኤል ስለነበረ ነው። እናም በየትኛውም መስፈርት ጌታቸውን እንዲህ አሉት ሊል ፈለገ የሚለው አያኪኬድም።

ገጽ 130 – ስለ የከተማ እራስን ተከላካይ አሀዶች አስመልክቶ በአራተኛው ፕሌኒዬም ላይ የቀረበ ጥያቄ እና መልስን አቶ ክፍሉ ሁለት ቅጅወች መኖራቸውን ስለከተማው መከላከያ አሀዶች ተናገረ ይሉን እና “እኔም በላይም የቱን ነበር ያሳያችሁን” የሚሉ ጥያቄወች አቅርበን መልስ አላገኘንም ይላሉ።

በዚሁ ገጽ “በቀንደኛ ገዳይ አስገዳዮች ላይ እርምጃ የመውሰድ እረቂቅ ለማኮ በነሐሴው ስብሰባ ሲቀርብ ጌታቸው ወዲያው ተቃወመ” ይላሉ በዚያን ግዜ በነበረው የኢትዮጵያ ተጨባጭ ሁኔታ ያለፈ ሁሉ እንደሚያውቀው የመንግስቱ ኃይለማርያም እድሜ በየትኛውም መልክ ቢያጥር ኖሮ ሐገራችን አሁን ካለችበት አጣብቂኝ ውስጥ ባልገባች ብለን ከማለፍ ውጭ ሌላ ማለት አይቻልም። በዚያ ትውልድ ትግል ምርጥ አዋቂ ምሁራን እና ኋላቀር ህብረተሰባችንን በየትኛውም አይነት መስዋእትነት ለመለወጥ የተነሱ Best of the best minds ቀድሞ የታያቸው በእውነትም ትክክል ብበር። መንግስቱ ኃይለማርያም አንድ ትውልድን ብቻ ሳይሆን ሐገርንም ለፊጥኝ አስሮ ለጠላት አስረክቦ የፈረጠጠ ፋሽስት ነበር ያ ደግሞ በዚያች ነሐሴ 1968 የኢሕአፓ ማኮ ስብሰባ ለተሰብሳቢው ታይቶት ነበር። ብርቅየ መሪወች እንደጧፍ ነደው በሕዝባቸው ፊት ተሰው እንጅ በጭካኔ ሐገር ያፈራቻቸውን ከወታደራዊ መኮንኖች እስከ ብርቅ ድንቅ ምሁራን አስጨርሰው እንደመንጌ አልፈረጠጡም የተስፋየ የመጨረሻ ሰአት ውብ የትውልድ ምስክር ነው።

ገጽ 132 ስለነበረው ተጨባጭ ሁኔታ የፖሊት ቢሮው ያቀረበውን ሰነድ በተመክከተ አቶ ታደለ ገዛኸኝ ከ (ሀ) እስከ (ሐ) የተዘረዘሩ የሀገሪቱን ሁኔታወች ይጠቅሳሉ። አቶ ታደለ ሊያሳዩ የፈለጉት በ (ሐ) ረድፍ “በቂ ዝግጅት መደረግን እና ሕዝባዊ አመጽ መቀስቀስን” ሲሆን ፖሊት ቢሮው ይህ ካልተደረገ ፓርቲው እና ሕዝቡ ሊደርስበት የሚችለውን ከባድ ጉዳት አስገንዝቧል። በእውነቱ እነዚያ ድንቅ ታጋዮች መጭውን የቀይ ሽብር ያላዩትን መጥቀሳቸው እንደነበር ማንም ሊረዳ ይገባል። እንዳሉትም ሆነ መንግስቱ ኃይለማርያም የደም ጠርሙስ በአብዮት አደባባይ ከሰከሰ የኢትዮጵያ እናቶችም ማቅ ለበሱ አንድ ትውልድም እረገፈ። ጌታቸውም ሆነ ብርሐነ ትልቅ ስህተታቸው ያነን የብዙሐን ሐሳብ መጣስ እና ለደሙ ጎርፍ አጋዥ መሆናቸው ነበር።

ገጽ 136 “ያም ሆነ ይህ በአንጃ የተጠረጠሩት ጓዶች ሀ ም ሆነ ለ እንዲሁም በመጀመሪያው ወቅት በአዲስ አበባ ኢንተርዞን እና በወጣቶች ማህበር አካባቢ የነበሩት ጓዶች ትጥቅ ትግሉን አስመልክቶ ትክክል የሆነ የመስመር ጥያቄ አንስተዋል” ይላሉ ጸሐፊው።

ትንሽ ቆም ያልሁበት አስተያየት ግን ያልተጠበቀ አይደለም። አቶ ታደለ እድሉ ኖሯቸው የኢሕአፓ ማኮ ሆነው አገልግለዋል። ሀ ም ሆነ ለ ሀሳባቸውን ለመላ የማኮ አባላት ባቀረቡበት የነሐሴ 1968 ዓም ስብሰባም ተገኝተው አንድም ቃል ሳይሰጡ ወጥተዋል። እናም ያ የብዙሐኑ ሐሳብ ልክ እንዳልነበር የተከሰተላቸው መቸ ነበር? አሁን ከ 46 አመታት ሁኋላ? አብዛኛው በዚያች ጠባብ የውይይት ክፍል የነበሩት ጓዶች አፈር ሳይጨመርላቸው አልቃሽ እ ህ ህ ህ ብሎ እናት አባት አልቅሶ ሳይቀብራቸው በየጎዳናው ደማቸው የፈሰሰው እራሳቸውን በማይከላከሉበት። ሐሰት እውነት በማይሉበት በዚህ ሰአት ነው ውሳኔአቸው ስህተት ነበር ነው የሚሉን ማለት ነው? አጀእብ!! ለማነኛውም ያኔ ይህን ሀሳብ ቢያቀርቡ ሦስተኛ ቁጥር ወይንም እሳቸው የነበራቸው ሀሳብ አሳምኖ አራተኛም ወይንም የብዙሐን ሀሳብ ይኖር ነበር ግን ያኔ አላደረጉትም እንዴውም ከስብሰባው ወጥተው ለተስፋየ ደበሳይ ለምን አስቀድማችሁ አልነገራችሁኝም ብለው ወቀሱ እንጅ አንባቢ ሊያየው የሚገባ ትርክት ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ:  በምዕራብ ጎንደር ዞን የአማራና ቅማንት ወንድም ሕዝቦች መልካም ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል መከሩ

በቀጣዩ ገጽ 137 “ሀ እና ለ ሀሳባቸውን ለማሰማት መድረክ ሲጠይቁ በውስጥ መጽሔታችን ማውጣት ትችላላችሁ ሲባሉ ቀልድ ነበር” ይሉና አቶ ታደለ መልሰው ለራሳቸው መልስ ሲሰጡ “ቀልድ ነበር። በየትኛው መጽሔት ወጥቶ ስንቱን ሊያዳርስ? ያውም በዚያ ቀውጢ ግዜ ልዩነታቸውን የሚያሰሙበት መድረክ አልነበራቸውም።” ብለዋል በድጋሜ ለአንባቢ ግልጽ እንዲሆን ቀውጢው ግዜ ላይ ኢሕአፓ የእራስ መከላከያ አሀዶች አልመሰረተም ወይንም እየተከላከለም አልነበረም ግዜው ነሐሴ 1968 ነው። አቶ ታደለ እንዳሉት ሀ ም ሆነ ለ ግንባር እንፍጠር ያሉ እንዲህ መውጫ መግቢያ ካሳጣ ፋሽስት (ጨካኝ) መንግስት ጋር ነበር።

ገጽ 140 ላይ ከጎንደር ቀጠና ኮሚቴ ጋር በተወያዩበት ግዜ “አንዳንድ ጓዶች በከተማ ትጥቅ ትግል ስልጣን ይያዛል ይላሉ ብዬ ሳልነግራቸው አለቀረሁም” ይላሉ አቶ ታድለ።

ይህ የአንጃው ክስ እንጅ የኢሕአፓ ማኮም ሆነ ፖሊት ቢሮው አልወጣውም በዚህ ገምጋሚ አተያይ አቶ ታድለ ያራመዱት የአንጃውን አሉባልታ ነበር እናም ድርጅትም እንደጎዳ አይተናል በውስጡም አልፈንበታል ባጭሩ እንደአንድ የመጨረሻውን የማኮ ስብሰባ እንደተካፈለ የአመራር አባል ይህ የ ሀ እና ለ አሉባልታ ወጦ በአንድ መሪ የሚነገርም መሆን ለአባላት መነገር አልነበረበትም። ከላይ እንደተገለጸው በማኮ የመጨረሻ ስብሰባ ሀ እና ለ ፖሊት ቢሮውን በዚህ ጉዳይ አንስተው ቢከሱም ብዙሐን የማኮ አባላት አልተቀበሏቸውም ምክንያትም ነበራቸው። አሉ የተባሉት የፖሊት ቢሮ አባላት በተለይም ተናግሮ እና ኃይለቃል ወጦት አያውቅም ያሉት አቶ ታደለ ተስፋየ ደበሳይ በቁጣ ማን አለ ብሎ ሀ ን እናዳፋጠጠው በዚሁ መጽሐፍ ነግረውናል እናም ይህ አሉባልታን ነበር አቶ ታደለ ተናግሬው ይሁን አልተናገርሁት አላውቅም ብለው ያስቀመጡት።

ገጽ 163 “ትግራይ አሲምባ እንደተደረገው የእርምት እንቅስቃሴ ለተመሳሳይ እርምት እንቅስቃሴ ወደ በጌምድር ልዑክ እንዲላክ ተወሰነ። ለዚህ ተግባር የተላኩት ፀሎተ እና ገብሩ (ጋዙ) ነበሩ። እኔ ወደጎንደር ከልዑኩ ጋር እንድሄድ ያቀረብሁት ጥያቄ ውድቅ ሆነ። ዘሩ እና ፀሎተም አይሆንም አሉኝ” ይላሉ።

የኢሕአፓ ታጋዮች ሁሉም አቶ ታደለ እየላኩ እንዲያደራጁ ያደረጓቸው እንደነ ሽባባው አይነቶች ሄደው ሳይመለሱ የቀሩት ማለት ነው በፈለጉት ቦታ አልነበረም የታገሉት ተስፋየ ደበሳይ ሐረር አቶ ታደለን መመደባቸውን ሲነግራቸው አይ እኔ መሔድ የምፈልገው ወደ ጎንደር ነው ብለው እንደቀሩት ይህን ግዜ ግን የትም ሊታገሉ ይገባል በሚል ተከልክለው ይሆናል እንጅ ደግሞም ምርጫው የአታጋዩ ኃላፊነት ነው። በኢሕአፓ ባህልም ኮሚቴ ወይንም የበላይ አካል በሚመድበው ቦታ ያለ ጥያቄ ምድብን መቀበል እንጅ ይህ ይመቸኛል ያ አይመቸኝም ያለ ታጋይ አልነበረም። እንዴውም ተስፋየ ደበሳይ የደግነት ልኩ እንጅ ሐረር ሔደው ቢሆን ኖሮ ምናልባት የተሻለ ውጤት በጥሩ የማደራጀት ልምዳቸው ሊኖር ይችል ነበር።

ገጽ 167 የታዛቢ ኑሮ በሚለው ንኡስ አርስት ስር ጸሐፊው እንዲህ ይላሉ፦ “ፀሎተ ከአዲሳበባ ተጉዞ ጎንደር ሰራዊት ውስጥ እንደገባ ለኮሚሳሩ መሐሪ (ጌዲዮን) በከተማ በሚካሄደው ትግል በመተማመን በአጭር ጊዜ ውስጥ ሁሉ ነገር ሊያልቅ ይችላል ብሎ አጫውቶት እንደነበር ጌዴወን ጋር የሰሩ ጓዶች ይናገራሉ።”

ማነው ከጌዲዮን ጋር የሰራው ወይም የሰሩት? ስማቸው ተጠቅሷል?

አንድን የታሪክ ጸሐፊ ለጻፈው ጽሁፍ አመኔታ የሚሰጠው እከሌ እንዲህ ብሎ ነበር በሚል በሰሚ ሰሚ ታሪክን ማቅረብ አይደለም። ሲቻል በቀጥታ የእራስ ማስታወሻ ደፍተር አለበለዚያ አድራጊውን በቀጥታ ቃለመጠይቅ በማድረግ በቃለመጠይቁም የራስን ሐሳብ ሳይጨምሩ የሰውየውንም ሳይቀንሱ በማቅረብ ነው። ፀሎተ ዛሬ የለም ወይንም ጌዲዮንም ቃለምልልስ አልተደረገለትም ታዲያ እዴት አንባቢ ሊያምን ይችላል? በስነ ታሪክ አጻጻፍም አግባብ አይደለም። ይህን ነቅሸ ያወጣሁበት ምክንያት ሁሉንም የከተማ ትግል የተሳሳተ ወደሚያሰኝ ያዘነበለ አስተያየትም በመሆኑ ጭምር ሲሆን ደግሞም የከተማው ትጥቅ ትግል በጭፍን ስህተት ነበር ብለው የሚፈጸሙ ብዙ የድሮ የድርጅት አባላት ስለአሉም ነው። የዚያን ሰአት የሀገሪቱ ተጨባጭ ኒኔታ ያስገድድ የነበረው እራስን መከላከል የግድ ብበር።

በዚሁ በገጽ 167 “ኤሮግራም ከደብተራው ጠይቄ ደብዳቤ ለጎንደር ዞን ጽፌ የከተማውን ትግል አሁኑኑ አቁሙ አልሁ።” ይልሉ ጸሐፊው

ለምን የከተማው ትግል ይቆማል? ማንስ አለ እና እንዲህ አይነት ቀጭን ትእዛዝ ይተላለፋል ከአንድ ግለሰብ? ገና ታሪካቸው በቅጡ ያልተቀመጠ የአንድ ትውልድ ወጣት ታጋዮች ተሰልፈው ለመሪወቻቸው እምነት ጥለው ደማቸውን ያፈሰሱት እንዲህ በአንድ ግለሰብ ቅሬታ ትግል አቁሙ ትእዛዝም እንደሚተላለፍ አያውቁም ነበር። ደርግ በትግል እና በመስዋእትነት መውረድ ነበረበት ሀ እና ለ ወይንም ግራ እና ቀኝ በሚል የናቴ መቀነት አደናቀፈኝ አታጋዮች ምክንያት ሳይሆን ቀረ እና የደም ጎርፍ አዝንቦ እና ሐገርን ያለመሪ አስቀርቶ መጨረሻም ፈረጠጠ።

እንደሚመስለኝ የከተማው ትግል ይቁም ያለም ካለ ስህተት ነበር። የመከላከሉ ትጥቅ ትግል እንኳን ከአገሪቱ የያኔ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር ተመርምሮ መሆን ነበረበት እንጅ በጥቅልል እንደፎርሙላ ስህተት ነበር ማለት አግባብ አልነበረም አይደለም። ሻለቃ ገብረ ሕይወት እና ሻለቃ መላኩ ተፈራ እኮ የወገራን፣ የአርማጭሆን የወልቃይትን የጎንደር ዙሪያ አርሷደርን ሁሉ እየገደሉ የነበረበት ግዜ ነው። ታዲያ ያ በከተማው ትጥቅ ትግል መንሰኤ ነበር? የ ሀ እና ለ ጭፍን አቋም ትግሉ አያስፈልግም ድርድር እና ትብብር ከደርግ ጋር የሚለው ያኔም አሁንም ስህተት ነው/ነበር።

በግዜው አሲምባ የነበረው የኢሕአፓ አመራር በማንኛውም ግዜ ሊያጠፋኝ ይችላል የሚለው የአቶ ታደለ ጥርጣሬ ድንበር ዘልቆ እንዲህ አይነት አስተሳሰብም ውስጥ ገብቶ ነበር “ከህወሓት አመራር ውስጥ እራስ ወርቅን፣ ተወልደን እና ግደይ ዘራጺዮንን በቅርብ አውቃቸዋለሁ። የከፋ ነገር ቢመጣ የእነሱን እርዳታ መጠየቄ አይቀርም ብበር።”

የኢሕአፓ ሰራዊት በሦስተኛው ሪጅናል አርሚ ውስጥ የተፈጠረውም ይህ አይነት አስተሳሰብ ሳይሆን ይቀራል? የድርጅት መሰረታዊ ጠላት እና አጥፊውን አንድ የአመራር አባል እንዴት ሊተማመንበት ቻለ? በዚህ ገምጋሚ አተያይ የኢሕአፓን በማደግ ላይ የነበረ ሰራዊት ማፍረስ እድል የሰጠው ለገንጣይ እና አስገንጣይ ፀረ ኢትዮጵያ ጎራ ነበር እናም ዛሬ ላለንበት አስከፊ ሁኔታ ዳርጎናል። ከአስዲ እበባ በ ሀ እና ለ የጀመረ የ Anti-thesis ጸረ ድርጅት ስራ የተቋጨው ድርጅቱን ከድቶ በማስከዳት የተካሂደው ምናልባትም የጠላት ሰርጎገቦች ስራ ነበር።

ገጽ 172 የሳሙኤል አለማየሁ (በላይ) አሲምባ መምጣት (ነዑስ እርዕስ)

የሳሙኤል ከአዲስ አበባ መምጣት ትልቅ የሚያጓጓ ሁኔታ ፈጠረ ይል እና አንባቢ የሚያጓጓውን ሁኔታ ለማንበብ በብዙ በሚያጓጓ አረፍተነገር ይጀምራል። ወረድ ብልኮ ግን ስለክፍሉ ታደሰ ምሬት እና ተባባሪ ስለነበረው እና አስዲ አብባ ስለተሰዋው ጓድ ስም ጠቅሶ ጸሐፊው በተገኙበት ስብሰ እንደገምጋሚው ብዙ ሊብራራበት የሚገባ ስብሰባ ቢሆንም ዝርዝር ገለጻ የለውም። የጓዱ የሳሙኤል ወረቀት እና ሌላው በሰራዊቱ ውስጥ ስለተበተነውም የሚያትት የጸሐፊው አስተያየት እና ስለወረቀቶች ጠለቅ ያለ ታሪክ አልተጻፈበትም። ይህ ጉዳይ ሰፊ ልዩነትን ያስተናገደ ከመሆኑ ባሻገር “ዘሩ እና ፀሎእተ ተያይተው ፀእሎተ ሐላፊነት ወስዶ ግለሂስ አድርጎበታል” የሚለው አጸጻፍ የፀሎእተን ግለሒስ ከየት እና እንዴት ተመስርቶ ማድረጉንም ቢብራራ ወይንም ዘርዘር ተብሎ ቢጠቀስ ለመጭ የታሪክ ተመራማሪወች ይረዳል ለአንባቢ በተለይም የኢሕአፓን ገድል ለመማር የሚፈልጉ የአዲስ ትውልድ አባላት የተሻለ እውቀት በሁኒታው ላይ ይሰጥ ነበር ይላል (ገምጋሚው)። በአጭሩ በትግሉ መስዋዕትነት የከፈለውን ግርማቸውን ስም ጠቅሶ በአንድ ስንኝ ማለፍ የግርማቸው እና የክፍሉ የሚስጥር ስራ ምን ይሆን ብለን እንድናልፍ ከማድረጉ በቀር ዝርዝር የለውም ለማለት ነው።

ሌላው ዋና ጉዳይ በህይወት ከተረፉ በከተማ እና በሜዳ ከነበሩት የኢሕአፓ ማኮ በተለይም የነሐሴ 1968 መለስተኛ ስብሰባ እና ውሳኔወች የሚያውቁ ሰወች ቁጥር እጅግ ትቂቶች መሆናቸው ምስጋና ይግባው እና እስከአሁን ያነን ስብሰባ እና የልዩነቶችን አካሄድ የዘገቡት ከአቶ ታደለ ገዛኸኝ ሌላ አቶ ክፍሉ ብቻ መሆናቸው ይህን የታሪክ ገጠመኝ በብዙው ማወቅ የሚያስፈልግ ዋና ጉዳይ ስለሆነ ምናልባት አንድ እና ሁለት ሰወች ካሉ በተሻለ እንዲያቀርቡት ለማሳየትም ስለሚጠቅም ነው የዚህ ገምጋሚ ዋና ፍላጎት እና ትንሽም ቢሆን ለመገምገም የተነሳሳው።

ገጽ 179 የአሲምባው እርምት እንቅስቃሴ (አንጃ)

አሲምባ የነበረው የፓሪው ቋሚ አመራር አበላት በሰራዊቱ ውስጥ የአንጃው ተጽእኖ መኖሩን አምነው ወይንም ጠርጥረው ጉዳዩን በፖለቲካ እርማት ለመቋጨት የወሰኑትን የመጸሐፉ ደራሲ ይጠቅሳሉ። እናም እርምት እንቅስቃሴ ለማድረግ ጽሁፎችን አመራሩ አዘጋጅቶ ለአባላት አውርዷል ይህ ሁሉ ቀና መሆኑን በመገንዘብ ሆኖም የመጸሐፉ ደራሲ ዘርዘር በማድረግ የነበረውን የውጥረት ኒኔታ፤ በፓርቲው እና በሰራዊቱ በግራ ቀኝ ጠላት ያንዣበበውን አደጋ እንደዚህ ገምጋሚ አስተያየት በበቂ አልተብራራም ባይ ነው። አሁንም ይህን የታሪክ ገጠመኝ መጻፋቸው ክብር እና ሞገስ የሚገባቸው እኒህ ደራሲ (አቶ ታድለ) በውስጡ ያለፉ እንደመሆናቸው ይነን አሲምባ የነበረውን ሁኔታውን ከማንም በተሻለ የሚረዱ ስለነበር ቢብራራ መልካም ነበር። ሆኖም የእርምቱ እንቅስቃሴ በሴሚናር ተጀምሮ ያለቀው የተወሰኑ ጓዶችን ከሰራዊቱ አመራር መዝሙርን አይነቶችን መሳሪያ በማስወረድ ነበር ይላል። ያነን ሁኔታ እንዴት ተጀምሮ እንዴት እንዳለቀ ከሳቸው የተሻለ ሊያቀርብ የሚችል አልነበረም ሆኖም በዚህ ጽሁፍ ከሳሽ ተከሳሽ እና የክሱን እና የመከላከሉን ሂደት በደንብ አልታየም የሚል አስይያየት ጸሐፊው ያላቸው ይመስላል (ከገምጋሚ)። ያም ሆኖ ግን ሊመሰገን የሚገባ የታሪክ ማስታወሻ ነው ፣.

ገጽ 182 14-ህወሓት እና ኢሕአፓ

መልካም አድረገው አስቀምጠዋል እዚህም ላይ በመጠኑም ቢሆን በህወሓት የደረሱ የተገፉ ሀሳቦችን እና በኢሕአፓ አመራር ግጭቱን ለማስወገድ ትግሉን በትግራይ ሜዳ ለማስቀጠል የተሞከሩ ጥረቶች ነበሩ ጸሐፊው ትንሽም ቢሆን ለታሪክ አድርሰውልናል ቢቻል ግን የበለጠ ጥልቀት ባለው መልክ እንዲብራራ ያስፈልጋል። ምክንያቱ ግልጽ ነው። ህወሓት የኋላ ኋላ ከአለማቀፍ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር በማበር በጎንደር እና ጎጃም በተደረገ ጦርነት የኢሕአፓን አመራር እና ሰራዊት የበተነች ድርጅት ናት። ኢትዮጵያን በዘር ክልል ሸንሽና ገና ለመጭ ትውልድ የሚተርፍ ክፉ ጥላቻ ዘርታለች። አሁንም ያላለቀ ጦርነት ውስጥ አስገብታናለች። አበው “በእንቁላሌ በቀጣሽኝ” እንዳለው ልጅ ሁሉ ኢሕአፓ በአንጃ እና በውስጥ ችግር ባይወጠር የህወሓትን ተፈጥሮ ከጅምሩ ጠንቅቆ ቢረዳ ይህ ሁሉ ላይሆንም ይችል ነበር።

ጓድ-X፣ ገጽ 286

ፈረንጆች “Straight from the horse’s mouth” እንደሚሉት ማለት ነው አቶ ታደለ “ከአራተኛውም ፕሌንዬም በፊት ዘሩ ክህሽን ወይንም (ጓድ-X) ወደሜዳ መምጣት የማይችል መሆኑ ከታወቀ በኋላ ልዑክ ተላከ። የተላኩት ጓዶች ሳሙኤል፣ ታደለ ጋዙ እና ካሱ ከውጭ እንድናናግረው ካርቱም ሄድን ይሉ እና የነበረውን ልውውጥ በተለይም በሳሙኤል እና በ X መካከል በዚህ መጽሐፍ አስፍረዋል። ይህ ውብ የታሪክ ማስታወሻ ሁሉም ልብ ብሎ ሊያነበው የሚገባ በመሆኑ ጠቃሚ እና ዝርዝር ቀጥታ ከማስታወሻቸው አካፍለውናል። ጉዳዩ የከተማው የመከላከል ውሳኔን ማን ከመጠን ባለፈ ገፋው በሚለው ላይ ሲሆን X እራሱን እና ፖሊት ቢሮውን አምርሮ ተከላክሏል ሳሙኤል ገና አሲምባ ጀምሮ ሲገባ እና ከተማ ለቆ ለወራት ሲጓዝ ይህን ጉዳይ በጽኑ የገፋበት በመሆኑ ለአራተኛው ፕሌኔምም እንዲቀርብ ቁርጠኛ ውሳኔ ያሳደረ በኋላም የከተማው ዲፌንስ ያለቅጥ ተገፍቶ አስከተለ የተባለውን ጉዳት የፓርቲው ማኮ እርምት ወስዶ እራሱን ወቅሶበታል።

ገጽ 289 አራተኛው ፕሌንዬም ጥር – የካቲት 1971

የከተማውን ትጥቅ ትግል በፓርቲው ውስጥ መኮነን የተጀመረው በላይ አሲምባ ከመጣ በኋላ ነበር ይላሉ ይህ በእዚህ እንዳለ ደግሞ በዚሁ ገጽ የከተማውን ትጥቃዊ ዲፌንስ አስመልክቶ ወጣቱ እና ላባደሩ ግርማቸውን (ኮንነው) እንደነበር ይጠቅሳሉ። ይህ ክስ መቸ እና እነማን የሚለውን ግን አያሳይም ምክንያቱም በአስዲ አብባ ኢንተርዞን ውስጥ የነበሩት የኢንተርዞኑ መሪወች የአንጃው አካል ነበሩ እና በኋላ የደርጉን የቤት ከቤት አስሶ መግደል ተባባሪ እንደሆኑ የተነገረላቸው ሊሆኑ ስለሚችሉ በዚህ አባባል ግርማቸውንም ሆነ በላይን ወደአንድ ጠርዝ በማይከላከሉበት ሁኔታ ማስቀመጡ ተገቢ አቀራረብ አይደለም።

አቶ ታደለ ስለዚህ የጥር 1971 ዓም የኢሕአፓ መሐከላዊ ኮሚቴ ከቀዩ ሽብር የማለቂያ ወራት ላይ እራሱን እና አካሉ በነዚያ የደም ጎርፍ በፈሰሰባቸው አመታት የተሰሩትን ደግም ሆነ የተሰሳቱ ስራወችን የመረመረበት ስብሰባ ነው። ይህ ስብሰባ እራሱ ድርጅቱ በግራ በቀኝ እና በውስጥ የሰርጎገብ አንጃው ቅሬቶች የሚታመስበት ግዜ ላይ ሆኖ የመረመረው እና 90 ፐርሰንት የማኮ አባላቱ እና ከሁለት የፖሊት ቢሮ አባላት ሲተርፉ በቀር ሁሉም መሪወቹ በሚባል በከተማው የአስሦ ግደል የደርግ መኢሶን እና በኋላም ጠቋሚ እና መንገድ መሪ በሆኑ በውስጥ በተፈጠሩ አንጃው ያለቁበት ማግስት ያደረገው ግምገማ ሲሆን፡ አቶ ታደለ ከአቶ ክፍሉ ቀጥሎ የዚህን ታሪካዊ ስብሰባ አካሄድ ያስነበቡን በመሆኑ ከምስጋና ጋር በሁለተኛ ክፍል ገምጋሚው ይመለስበታል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Share