ብአዴን ያሁኑን ስሙን ከመቀበሉ በፊት ሁሉ በህዝብ ያላሳለሰ ትግል እና የረጂም ጊዜ ተጋድሎ ከፊት ሲገፋ በብልጣብልጦች ወደ ኋላ መሰለፉ እና ሁሉን እናዳለየ ማለፉ ከአገር እና ህዝብ ይልቅ ለአዉራ ድርጂቶች(ፓርቲዎች ) ያለዉ ወገንተኝነት ዛሬ የሚጀምር አይደለም፡፡
በራሱ ጥላ ስር ከጥፋት የዳኑት ትናንሽ ዕንክርዳዶች ከስሩ እየበሉት አድርቀዉ ደረቅ የዋርካ ዛፍ ግንድ አድርገዉታል፡፡
ከምስረታ እስከ ኢህአዴግ የመገለባበጥ ጊዜ መጋቢት 2011 ዓ.ም. ድረስ የህዝብ መከራ እና ስቃይ ሞልቶ ሲተርፍ ት.ህ.ነ.ግ . ሲንሳፈፍ የህዝብ እና አገር ጉዳይ ችላ ብሎ ለህገ መንግስት( ህገ -ኢ.ሀ.ዴ.ግ) ይቅደም ማለት የ. ብ.አ.ዴ.ን. በክፉ ቀን ኋላ በሠላም ፊት አዉራሪ መሆንን የተቀበለዉ ዛሬ ሳይሆን 1981 ዓ.ም ጀምሮ ነበር ፤ ነዉ ፡፡
እናም የኢህዴን / ብአዴን ህገ መንግስት ( የኢህዴግ ጋሻ) እንጂ የህዝብ እና የአገር ( ህገ -ህዝብ/ አገር) እንዲጠብቅ አዉቆም ይሁን ሳያዉቅ ቃል የገባዉ ጥንት ነዉ እና ከኖረበት አምልኮ ለመዉጣት መዉቀስ ሳይሆን ማቀሰስ ሳይሻል አይቀርም ፤ ይህም ለንስኃ ሲዘጋጂ እና ከኢኃዴግ ክደማ ለመዉጣት ወደ ህዝባዊ እና ብሄራዊ ወገንተኝነት በይቅርታ እና በአወንታ ሲመለስ እና በዚህም ህዝብን ሲክስ ብቻ ነዉ ፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲ ንቅናቄ (ኢ.ህ.ዴ.ን) ከአስራ ዘጠኝ መቶ ስድሳ ዓ.ም. ከበቀሉት የኢትዮጵያ የጥፋት ኃይሎች እንደአሸን ሲዥጎደጎዱ የኢትዮጵያ ህዝቦች ፓርቲ(ኢ.ህ.ፓ) በወረቀት እና ከተማ ክተት የከተማ ጦርነት በህዝብ ላይ ሲከፍት ማጣፊያዉ ሲያጥረዉ ወደ ሰሜን ጎንደር እና ሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ጥግ እንዲይዝ ሆኗል፡፡
ስም በመለወጥ እና በመገለባበጥ የማይታማዉ የታች አምነዉ ኢህዴን የዛሬዉ ብአዴን ስም እና ቦታ ብቻ ሳይሆን ቦታ መልቀቅ እና መከተል እና መናጆ መሆን አመል የቆየ ነዉ ፡፡
በ1982 ዓ.ም. ት.ህ.ነ.ግ ከደደቢት ዋሻ እንዲወጣ እና በኢህዲን ጥሪ ኢ.ኃ.ዴ.ግ እንዲቆቋም ሆኖ ት.ህ.ነ.ግ ግንባር ኢ.ህ.ዴ.ን. ተከታይ በመሆን የኢትዮጵያዉያንን በተለይም የዓማራዉን የዓመታት መጋደል እና ድል ከዋሻ ተመርቶ ለመጣዉ ት.ህ.ነ.ግ አስረከበ ያኔ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ዓማራነት በሞት መቃብሩ ላይ የጥፋት እና ሞት ዕንክርዳድ ተዘርቷል፡፡
ከኢኃዴግ ምስረታ የአስራ ዘጠኝ መቶ ሠማንያ አንድ ዓ.ም. ዋዜማ ጀምሮ ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ማዕከላዊ መንግስት ለማብረክረክ የጥፋት ኃይሎች የዘመናት የጥላቻ እና የአቻ መሆን የበታችነት እና ምቀኝነት ምኞት ዕዉን መሆን ዋዜማ ላይ መሆናቸዉን አረጋግጠዋል፡፡
ለዚህም ብ.አ.ዴ.ን. ስሙን ከተግባሩ ሲያቀያይሩለት ሲሰድቡት ዝም፤ ሲረግሙት አሜን የሚል አስከሆነ የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት ሆነ የህዝቦችን ሉዓላዊ ክብር አሳልፎ ለመስጠት ከጠላት በላይ አገልጋይ መሆኑን ማረጋገጫ ሆኗል፡፡
ኢትዮጵያን እና ኢትዮጵያዊነት ጠረን እና ማንነት ያለባቸዉን ( ኢትዮጵያዊነት፣ ዓማራ ፣ የኃይማኖት ተቋማት….) ቅርስ እና ዉርስ ሁሉ ለመፋቅ የሚደረገዉን የወደፊት ኢትዮጵያን የማክሰም ትልም ለማሳካት ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በስሙ ከሚኖርበት የኢትዮጵያ ምድር እና ህዝብ (ዓማራ) ጀምሯል፡፡
ብ.አ.ዴ.ን. ራሱን እና ኅዝቡን ከካደ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ በሁሉም ግዛቶች በኢትዮጵያዊነት ላይ ለደረሱ የመከራ ገፈት ቀማሽ ኅዝብ የሆነዉን ኢትዮጵያዊ ሁሉ በተለይም ዓማራ ጠላት በማድረግ ት.ህ.ነ.ግ. በግብረ አበሮች ሲያሳድድ እና ሲያርድ በአንድም የአገሪቷ ክፍል ከሞት እና ከስደት ለመታደግ ማሰብ ቀርቶ መኖሩን ለድፍን ሠላሳ ዓመት ማወቁን ዛሬም እንደ በደነ ለመሆኑ ከሚታዩ ገሀድ ዕዉነታወች ማየት ይቻላል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝብ እጂ ዓመድ አፋሽነቱ ከጥንት ቢጀምርም የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝብ( ጎንደር፤ ወሎ እና ጎጃም) በተለይ ብ.አ.ዴ.ን.ን ቀርቶ ት.ህ.ነ.ግ.ን ከከተማ ወጥቶ ደደቢት እስኪደበቅ ከዚያም ከደደቢት አስከ ሚኒሊክ ቤተ መንግስት ያደረሰዉ ህዝብ በአገረስኩ እጀን ተነከስኩ ቢል አዲስ አይሆንም ፡፡ አስቀድሞም“ የመከራን ቀን ያወጣ መከራን ይመስላል ” የሚለዉን ትዉፊት አይሉት ትንቢት የሀበሻ ምርጥ ብሂል መዘንጋት አይቻልም፡፡
በ፴(ሠላሳ) ዓመት የአገር ምስቅልቀል እና የኢትዮጵያዉያን በሁሉም የአገሪቷ ክፍል መሳደድ፤መወገድ ፤መዋረድ ያልተሰማዉን ብ.አ.ዴ.ን. መኖሩን ወይም በድን መሆኑን መጠየቅ እንጂ በአገር እና በህዝብ ጉዳይ መዉቀስ ሠዉ የመሆን ድክመት ነዉ ፡፡
በአዴን ህዝብ እና አገር ቀርቶ በቅርቡ ያሉት እና የነበሩት የህዝብ ልጆች እነ ክቡር የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር የነበሩት ሙሉዓለም አበበ እና ዶ/ር አምባቸዉ መኮንን የመሳሰሉትን ሲያጣ ሞት አብሮት እናዳለ የማይረዳ ዛሬ በዚህ ደረስ ፤ አዚያ ድረስ ማለቱ ትርፉ ምን ሊሆን ነዉ ፡፡
የህዝብ ልጆች ለጊዜዉ የማይገለጡ ታሪክ እና ትዉልድ ወደ ፊት የሚዘክራቸዉ የህዝብ እና አገር ጉዳይ ዕንቅልፍ ነስቷቸዉ በተለይ የኢትዮጵያ አንድነት እና የህዝቦች የመከራ ዙር ሳይጨምር በእኝጭጩ እንዲቀጭ ዕምቢ ለአገሬ ፣ እምቢ ለክብሬ ያሉትን እነ ፕ/ር አስራት፣ አስማረ ዳኜ ፣ ሳሙዔል ዐወቀ…. የመሳሰሉት ምን አሉ የማይል አሁን ተነስቶ በዚህ ህዝብ ፣ በዚህ አገር ፤ በዚህ ድንበር…የምንለዉ ለማን ይሆን፡፡
በተለያዩ የአገሪቷ ግዛት አስተዳደሮች ከሚኖሩት ኢትዮጵያዉያን ጋር በተደረገ ዉይይት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በምትገኝ ከተማ መበት ፤ ደህንነት ….ያሉ ኢትዮጵያዉያን (1997 አስከ 2007 ዓ.ም) በሰዉ አገር መብት ምናምን የሚል ምላሽ የማዕከላዊ አባል ዕኮ የት.ህ.ነ.ግ ቁንጮ እና ዛሬም ድረስ በ.ብ.አ.ዴ.ን. ጥላ ስር አምባሳደር ሆኖ የሚገኝ ነዉ ፡፡
ብ.አ.ዴ.ን. ጥፋቱም ሆነ ክፋቱ የምጠብቀዉ እኔን እና ህገ መንግሰቱን( የህገ መንግስቱን ባለቤት ኢ.ኃ.ዴ.ግ.ን/( ህገ -ኢ.ኃ.ዴ.ግ) ነዉ ከዚያ ዉጭ አገር እና ህዝብ የሚል የህገ መንግስት ስምምነት ስለሌበት ብሎ ከጥዋት አስካሁን ለህዝብ አለመንገሩ ብቻ እና ብቻ ነዉ ፡፡
የአስራ ዘጠኝ መቶ ስዳሰ ስድስት “ጉልቻ ቢለወጥ ወጥ አያጣፍጥም ” የተባለዉን ብሂል “ፓርቲ ቢቀያየር / ምን ስያሜ ቢያምር ከመከተል በቀር አያድንም አገር ” ማለትን ምነዉ ረሳንዉ ፡፡
፡፡ ስሙልን ካልሆነ ማንም መዉቀስ የዋህነት ነዉ ፡፡
በሁሉ ድረሱልን ታሪክን አለማወቅ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ዕንክርዳድ መሆን ነዉ እና የሚበጀዉ ራስን ፣ ህዝብን እና አገርን ከመከራ ዉሽንፍር ለመታደግ ብቸኛዉ መንገድ በራስ መቆም ( መተባበር፣ መደራጀት እና ዘመኑ የሚጠይቀዉን ሁሉ መዋጀት ….) ነዉ ፡፡
ከዚህ ዉጭ በአሁኑ ሰዓት የትኛዉንም የፖለቲካ ድርጅት ኮሽ ባለ ቁጥር ድረሱልን ……ማን የደረሰዉን ይደርሳል፡፡ ድሮም ቢሆን ህዝብ እንጂ ድርጂት ለህዝብ እና አገር ደርሶ አያዉቅም፡፡ ካለ …….
ለግማሽ ምዕተ ዓመት በአራቱም ማዕዘን በሞት ጥላ ሆኖ ድረሱልን ማለት ፣
ሲጨልም አድፍጦ ቀን ሲወጣ እያየ ካለሁ ባይ አታላይ ከወዳጂ ጠላት ጥበቃ /መፍትሄ ከመሻት ፣
እየሞቱ መኖር ነፃነት ካሳጣ ተዋርዶ ከመኖር ከሚከፋዉ ሞት ፣
የሚበጂ መላ መንቃት ፤መደራጀት መቆም ነዉ ባንድነት ሠዉ በጠፋ ጊዜ ችግር በጠናበት ፡፡
ማላጂ
አንድነት ኃይል ነዉ