ጥያቄ፡ የተጭበረበረው ምርጫ መጭበርበሩ ሙሉ በሙሉ ስለተረሳና ኦነጋውያን አዲሳባን ሙሉ በሙሉ ስለተቆጣጠሩ እስክንድር ነጋ ምንም አያመጣም ተብሎ ታሰበና ከእስር ተፈታ፡፡ ዐብይ አሕመድ ድምጹን አጥፍቶ አማራን እስኪያጠፋ ድረስ አፋቸውን ሳይከፍቱ በቅምጥል እየኖሩ ሊጠባበቁ የተስማሙት ጃዋር ሙሐመድና በቀለ ገርባ፣ ዐብይ አሕመድ አብዛኛውን አማራን የማዳከም ሥራውን አጠናቋል ተብሎ ታሰበና፣ መናኛው እገዳ ተነሳላቸው፡፡ በአማራ ሕዝብና በአማራ የጦር መኮንኖች ላይ የዘር ጭፍጨፋ የፈጸሙትና፣ የአማራ ሕዝብ በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት የተያዙት ቀንደኛ ወያኔወች ‹‹ምሕረት›› ተደረገላቸው፡፡ ለወያኔው ለዐባይ ወልዱ የተቸረው ምሕረት ለሱማሌው አብዲ ኤሌ ያልደረሰው ፀረ ኦነግ ስለሆነ ይሆን? መልሱን ላንባቢ ትቸ ወደዚህ ጦማር ርዕስ ልመለስ፡፡
———————–
ወያኔ ደብረብርሃን ገባሁ አልገባሁ እያለች በምታስፈራራበት ጊዜ ‹‹የዐብይ አሕመድ የድርድር ተውኔትና የደመቀ መኮንን ሚና›› በሚል ርዕስ በጦመርኩት ጦማር ላይ፣ ዐብይ አሕመድ በአማራ ሕዝብ ላይ የሚተውነውን ተውኔት በአራት ገቢሮች ከፍየ የሚከተለውን ጽፌ ነበር፡፡
ገቢር አንድ
በመጀመርያ ወያኔን መጣሁብሽ፣ ልመጣብሽ ነው እያለ በባዶ ዛቻ በማስፈራራት ውስጥ ለውስጥ ቆስቁሶ፣ በሰሜን እዝ የሚገኙትን የአማራ የጦር መኮንኖች እንድትጨፈጭፍ አነሳሳት፡፡ በዚህም የአማራ ሕዝብ አያሌ የጦር መሪወቹን እንዲያጣ አደረገ፡፡ ቀጠለና ደግሞ የአማራ ሕዝባዊ ሠራዊት በከፍተኛ መስዋእትነት ወያኔን ከሞት አፋፍ እስኪያደርሳት ድረስ አድፍጦ ከጠበቀ በኋላ፣ ሕግ በማስከበር ሰበብ በትግራይ ላይ ዘመቶ ትግራይን በሻሻ አደረጋት፡፡ ትግራይን በሻሻ ካደረገ በኋላ ደግሞ ትግራይ ላይ በሾማቸው ብልጽግናወች አማካኝነት ከወያኔ ጋር ውስጥ ለውስጥ እየተገናኘ፣ ወያኔ እስከ ደብረብርሃን ድረስ በመውረር የአማራን ክልል በሻሻ እንድታደርገው ተስማማ፡፡ በስምምነቱ መሠረት ደግሞ ቃሉን አክብሮ ወያኔ ደብረብርሃን ደጃፍ እስከምትደርስ ድረስ ማድረግ የሚችለውን እገዛ ሁሉ አደረገላት፡፡ የአማራ ክልልም እንደ ትግራይ ክልል በሻሻ ሆነ፡፡
ገቢር ሁለት
እባብ ለእባብ ይተያያል ካብ ለካብ እንዲሉ፣ አጭበርባሪው ዐብይ አሕመድ የወያኔን አጭበርባሪነት በደንብ ያውቃል፡፡ ስለዚህም፣ ዐብይ አሕመድን ያስጨነቀው አንድና አንድ ነገር ብቻ ነበር፡፡ እሱም እኔ ቃሌን አክብሬ ወያኔን ደብረብርሃን እንዳደረስኳት፣ እሷም ቃሏን አክብራ ደብረብርሃንን ከመዘበረች በኋላ እዛው ትቆማለች ወይስ ቃሏን በልታ ወደ ኦሮምያ ትገፋለች የሚለው ጭንቀቱ ነበር፡፡ ዐብይ አሕመድ ከወያኔ ጋር መደራደር የሚፈልገው ይህን ጭንቀቱን ለማስወገድ ሲል ብቻ ነው፡፡ በሌላ አባባል ዐብይ አሕመድ ድርድር ሲል፣ እንደራደር ማለቱ ሳይሆን አስቀድመን በሕቡዕ የተዋዋልነውን ውል ላለማፍረስ በዓለም ሕዝብ ፊት በይፋ ቃል እንግባ ማለቱ ነው፡፡ ወያኔና ኦነግ ሁለቱም ጀቦች ናቸው፣ ወያኔ የቀን ጅብ ኦነግ የጠራራ ጅብ፡፡ ሁለቱም ጅቦች በመሆናቸው ደግሞ ስለማይተማመኑ ጎን ለጎን እንጅ ፊትና ኋላ አይሄዱም፡፡
ገቢር ሦስት
ወያኔ ቃሏን ካከበረችና ከደብረብርሃን ካላለፈች በወረራ ያገኘችውን ሁሉ በስምምነት መልክ ሙሉ በሙሉ ሊያጸድቅላት ሙሉ በሙሉ ዝግጁ ነው፡፡ ቃሏን ካላከበረችና ወደ አዲስ አበባ እገፋለሁ ብላ አሻፈረኝ ካለች ግን፣ በተለያየ ሻጥር እጅ እግሩን አስሮ አላላውስ፣ አላንቀሳቅስ ያለውን የአማራን ሕዘባዊ ኃይል መጠነኛ ነጻነት ይሰጠውና ወያኔን ድባቅ እንዲመታት ያደርጋል፡፡
ገቢር ዐራት
እንዳያያዟ ከሆነ ወያኔ ያቀደችው ከዐብይ አሕመድ ጋር በሕቡዕ የተዋዋለችውን ውል በግላጭ አፍርሳ፣ ደብረብርሃንን መዝብራ አልፋ፣ አዲሳባ ገብታ ሁሉን በጇ በደጀዋ ማድረግ ነበር፡፡ ይህን አያያዟን በተክክል የተረዳው፣ ለስልጣኑ ሲል ማናቸውንም ነገር ለማድረግ ቅንጣት የማያመነታው ዐብይ አሕመድ ደግሞ፣ ከራሱ በላይ ለሚያፈቅረው ለስልጣኑ ሲል ከፍተኛ ሥጋት አደረበት፡፡ በዚህም ምክኒያት በአማራ ኃይሎች (በተለይም ደግሞ በፋኖ) ላይ የሚሻጥረውን ሻጥር በመጠኑም ቢሆን ጋብ ለማድረግ ሳይወድ በግድ ተገደደ፡፡
የአማራ ኃይሎች ሻጥር ካልተሻጠረባቸው ባጭር ጊዜ ውስጥ ወያኔን ገርፈው እንደሚያባረሯት በርግጠኝነት ስለሚያውቅ ደግሞ፣ በነሱ መስዋዕትነት የሚገኘውን ድል፣ በሱ አዝማችነት የተገኘ ድል ለማስመሰል እዘምታለሁ፣ ዘምቻለሁ በማለት በሰፊው እያስወራ ቱልቱላ ነፋ፡፡ የአማራ ኃይሎችም ወያኔን እየሸነቆጡ እስከ አለማጣ ድረስ ነዷት፡፡
ዐብይ አሕመድም በአማራ ኃይሎች ላይ የሚሻጥረውን ሻጥር ለጊዜው ጋብ በማድረግ ብቻ፣ ሁለት ታላላቅ ጥቅሞችን አገኘ፡፡ የመጀመርያው ጥቅም ስልጣኑን ልትመነጭቀው ዙርያውን አሰፍስፋ የነበረችው ወያኔ፣ በአማራ ኃይሎች ከፍተኛ መስዋእትነት ተጠራርጋ፣ ለስልጣኑ እስከማታሰጋበት ርቀት ድረስ እንድትርቅ መደረጓ ነው፡፡
ሁለተኛው ጥቅሙ ደግሞ በወጉ እንዳይታጠቁ የተሻጠረባቸው የአማራ ኃይሎች በለበንና በውጅግራ ያገኙትን አንጸባራቂ ድል ሰርቆ፣ በድሮን ያገኘው የራሱ ድል አስመስሎ አቅርቦ፣ ጀግና ለመባል የሞከረው ሙከራ በማይናቅ ደረጃ የተሳካለት መሆኑ ነው፡፡ በዚህ ረገድ ደግሞ ዐማራ መስለው ዐማራን ለማስበላት ቆርጠው የተነሱት፣ ዐማራ የለም የሚለው የአንዳርጋቸው ጽጌ ቅጥቅጦች የሆኑት፣ ድነታችንም ሞታችንም በዐብይ አሕመድና በዐብይ አሕመድ ብቻ ነው ያሉት፣ ኢሳቶችና ዜና ቲዮቦች የዋሉለትን ከፍተኛ ውለታ መቸም መርሳት የለበትም፡፡ ዐብይ አሕመድ ግን ያመኑትን ሁሉ በደንደሳቸው የሚጥል ሌንጮ ፈረስ መሆኑን በነ ዲባቶ ዐመባቸው መኮንን ላይ በግልጽ አስመስክሯል፡፡ ስለዚህም ጭራቸውን የሚቆሉለትን ያንዳርጋቸው ጽጌ ባልደረቦች ኦሮሞ ባለመሆናቸው ብቻ አላምጦ ሲጨርስ አንቅሮ እንደሚተፋቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡
ፋኖወች ወያኔን እየሳደዱ ወደ አላማጣ ሲቃረቡ፣ ዐብይ አሕመድ ደግሞ ወያኔ ከናካቴው ልትጠፋብኝ ነው የሚል ከፍተኛ ሥጋት አደረበት፡፡ በዚህም ምክኒያት ወያኔን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የማጥፋት ዘመቻው በትክክል ከመጀመሩ አስቀድሞ፣ ጦርነቱ ቁሟል የሚል መግለጫ ተሸቀዳድሞ አወጣ፡፡ ወያኔን ያጠፋብኛል ብሎ አለመጠን በሚፈራው በፋኖ ላይ ደግሞ መጠነ ሰፊ የስም ማጥፋት ዘመቻ ከፈተ፡፡
ገቢር አምስት
ይህ ገቢር ደግሞ ዐብይ አሕመድ ባሁኑ ወቅት እየተወነው ያለው ገቢር ነው፡፡ ወያኔ የአማራ ክልልን በሻሻ እያደረገች ደብረ ብርሃን በር ከደረሰች በኋላ የአማራ ሕዝብ በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ሳትወድ በግዷ ወደኋላ ተመልሳለች፡፡ ስለዚህም፣ በዐብይ አሕመድ እይታ መሠረት ወያኔ የአማራን ክልል ድምጥማጡን አጥፍታ ወደ ኋላ ለመመለስ የተዋዋለችውን ውል ተገዳም ቢሆን አክብራለች ማለት ነው፡፡ ስለዚህም እሱም በበኩሉ ውሉን በማክበር፣ በወረራ ያገኘችውን ሁሉ በሕግ ያጸድቅላታል፡፡
ውሉን ማክበሩን ደግሞ በአማራ ሐዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል የፈጸሙትን፣ የአማራ ሕዝብ በከፈለው ከፍተኛ መስዋዕትነት ተይዘው የነበሩትን፣ ትላልቆቹን የወያኔ ወንጀለኞች በመፍታት ጀምሮታል፡፡ የሚቀጥለው ርምጃው ደግሞ የይስሙላ ፓርላማውን በመጠቀም ራያን የኦሮም፣ ወልቃይትን ደግሞ የትግሬ በማድረግና የቀረውን የአማራን ክልል ለአስር በመበጣጠስ አማራን ቢችል ጨርሶ ማጥፋት ባይችል ደግሞ ምንም ተጽእኖ የሌለው ሕዳጣን ማድረግ ነው፡፡
ዐብይ አሕመድ የጭቆናን ምንነት በቅጡ ሊረዳ በማይችልበት ለጋ እድሜው “ያማራ ጨቋኞችን” ለመታገል ጫካ ገብቶ የወያኔን ጡት እየጠባ ባማራ ጥላቻ ተመርዞ፣ በወያኔ እኩይ ባሕርያት ተሰቅዞ ያደገ፣ አማራዊ ናት የሚላትን ጦቢያን አፈራርሶ በሷ መቃብር ላይ የኦሮሞ አጼጌ (Oromo empire) ለመመሥረት ቆርጦ የተነሳ ኦነጋዊ አውሬ ነው፡፡ ዐብይ አሕመድ ወያኔን የሚጠላት በስልጣኑ ስትመጣበትና ከመጣችበት እንጅ፣ በአማራ ጥላቻዋ ሲወዳት ዓይን የለውም፡፡ ስለዚህም የዐብይ አሕመድ እቅድ፣ ወያኔ የኦነግን የበላይነት ተቀብላ፣ በሱ (ማለትም በዐብይ አሕመድ) ሥር ሁና፣ ለስልጣኑ ሳታሰጋ፣ ከአማራ ጋር ተጠግታ አማራን ዘላለም እያስለቀሰች የምትኖር የአጋም እሾህ እንድትሆንለት እንጅ እንድትጠፋ አይደለም፡፡
ዐብይ አሕመድ የአማራ ሕዝብ መሪር ጠላቶች ከሆኑት ከወያኔና ከኦነግ ከሁለቱም የተቀዳ የሁለት ሰይጣን ነው፡፡ ይህ የሁለት ሰይጣን የጦቢያ መሪ እስከሆነ ድረስ ደግሞ፣ የኣማራ ሕዝብ መቸም ቢሆን ሰላም አያገኝም፣ እንደውም ከናካቴው ጨርሶ ሊጠፋ፣ ማለትም እንደ ሕዝብ ሕልውናውን ሊያጣ ይችላል፡፡ ስለዚህም፣ የአማራ ሕዝብ ለሕልውናው ሲል ማድረግ ያለበትን ሁሉ ባፋጣኝ ማድረግ አለበት፡፡ አልሞት ባይ ተጋዳይነት ደግሞ በምድር አስከብሮ በሰማይ የሚያስጸድቅ ቅዱስ ተግባር እንጅ፣ በምድርም አያስወነጅልም፣ በሰማይም አያስኮንንም፡፡
የጦቢያ ምሰሶ ያማራ ሕዝብ ሆይ
ኢትዮጵያን ለማፍረስ አንተን ጥሎ ግዳይ
ኦነግ አሉት ሸኔ፣ ወያኔ የትግራይ
በሕልውናህ ላይ ሲመጣብህ ስታይ፣
ሳትቀደም ቀድመህ ባገኘኸው ዲንጋይ
መምታትህን እንጅ ወሳኝ ብልቱ ላይ
ጭራሽ አያሳስብህ የመሞቱ ጉዳይ፡፡
በታችም በምድር በላይም በሰማይ
ወንጀለኛ አይደለም አልሞት ባይ ተጋዳይ፡፡
መስፍን አረጋ