January 8, 2022
15 mins read

ለልብ ሰባሪው ሰበር (ከፈረሱ በፊት ለቀደመው ጋሪ)  የሚሰጡ ማብራሪያዎች ሁሉ የንፁሐንን እንባ አያብሱም። ሲና ዘ ሙሴ

Abiy Ahmed the killerሰበር ዜና ፤ እነ  ጃዋርን እና እነ ሥብሐትን ፣ በነሱ ክስ የተመዘገቡትን ሁሉ ከሞራል አንፃር ፈታናቸው ። ከሞራል አንፃር እነ ጃዋርን እነ ሥብሐትን ፈታናቸው ። ተባለ ። ለነጃዋር ፣ ለነሥብሐት ደጋፊዎች ይህ ታላቅ ድል ነው ። ሰበር ዜና ብቻ አይደለም ። ለብዙዎቹ ኢትዮጵያኖች   ይኽ ዜና ሰበር አይደለም ። ልብ ሰባሪ እንጂ !! ስብሐት ነጋ፣ ቅዱሳን ነጋ፣ ዓባይ ዘውዱ፣ አባዲ ዘሙ፣ ሙሉ ገ/እግዚአብሔር፣ ኪሮስ ሐጎስ፣ ጃዋር ሞሐመድና በእሱ ክስ መዝገብ ሥር ያሉት በሙሉ ከሞራል አንፃር ተፈተዋል ። ከወንጀል አንፃር ግን በአእምሯቸው እንደታሰሩ ናቸው ። ተገቢውን መማሪያ ቅጣት ሳያገኙ ከእሥር በመለቀቃቸው ዳግም ወንጀል ከመሥራት የሚያመነቱ አይመሥለኝም ።

ልብ በሉ እነኝህ አገርን የካዱ ፣ ወገን ከወገኑ ጋር ደም እንዲቃባ ያደረጉ ፣ በልዩ ልዩ ወንጀል የተጠረጠሩ ፣ ከዘር ማጥፋት ጥቃት እስከ ሀገርን ያራቆተ ዝርፊያ ውሥጥ ተሰማርተው ፣ ህዝብንም ለሌብነት ያሰማሩ ። ሰውን ከሰው በነገድ ፣ በዘውግ  ያገዳደሉ ። የዘውግ  ክፍፍልን በማጦዝ ፣ የጠቅላይ ሚኒሥቴርነትን ወንበር ለማግኘት የቋመጡ ። ግለሰቦች ፣ እንዴት ነው ከሞራል አንፃር የሚፈቱት ?? የተወነጀሉበት ወንጀል  ደግሞ በየትኛውም ሕግ ምሕረትም ሆነ ይቅርታ የሚያሰጥ አለመሆኑንም ልብ በሉ ። ታዲያ በምን ሂሳብ ነው ድንገት በሰበር ዜና ( የምንዱባኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ልብ በሚሰብር ዜና ) የሥንት ንፁሐን ደም በእጃቸው ያለ ወንጀለኞችን ያለ ቅጣት ከሞራል አንፃር ብቻ አይቶ ከእሥር መልቀቅ የተፈለገው ??

ይህ ድርጊት ሆድ ብቻ ላልሆነው ፣ በሥጋ ና በፍራንክ ለማንገዛ ፤ ሞት ሁሌም ከእኛ ጋራ እንደሚያዘግም ለምንረዳ ፣ ዛሬ እንደምንሞት ጠንቅቀን ለምናውቅ ፣ በሰውነት እንጂ በዘር ሰውን ለማናውቅ ( አማራ ፣ ኦሮሞ ፣ ትግሬ ፣ ሱማሌ ፣ አፋር ፣ ወዘተ። ነን ለማንል ። እኔ ሰው ነኝ ለምንል ።  ሰው ሁላ ወገናችን ለሆነ ። )  በእጅጉ ያሳዛነናል ።

በመላ ኢትዮጵያ በግፍ ለተጨፈጨፉት ፣ በአማረ ክልል ና በአፋር በጥይት ለተረሸኑት ንፁሐን ዜጎች ፤ በሳንጃ ለታረዱ የዋሆች  ፣ በየጎጆቸው  ለተቃጠሉ  ምንዱባን አማሮች  ፣ በባሎቻቸው  እና በልጆቻቸው ፊት  ለተደፈሩት ፤ በሻሸመኔ በየጎዳናው አሥከሬናቸው ለተጎተተ ፤ በሜንጫ ለተቆራረጡት  ፤ ወዘተ ። ማነው ከመንግሥት ውጪ ፍትህ የሚሰጣቸው ? ማንሥ ነው ነገ ገንዘብ ህሊናውን ያናወዘው ፣ በቢሊዮን ዶላሩ የአሜሪካንን መንግሥት ድጋፍ ማግኘት የሚችል ፣ ለሰው ፈፅሞ ርህራሄ የሌለው ፣ ሰብአዊነት ፈፅሞ የሌለው ፣ በዘረኝነትና ለጥቅም ሲል በነገድ ፖለቲካ ያበደ ፣ ክቡሩን ሰው ፣ አገር ሰላም ነው ብሎ በተቀመጠበት ቤቱ ቢያርድ ፣ ሺዎችን ጎዳና ለጎዳና እያሳደደ ቢጨፈጭፍ ፤ ካለእኔ ነገድ ውጪ ሌሎቻችሁ ቁንጫ ና በረሮዎች ናችሁ በማለት ዘውግ እየለየ ቢያጠፋ ማን ሊከለክለው ይችላል ።

በዚች አገር ከትላንት እሥከዛሬ ፍትህ መሣቂያ መሆኖ ይገርመኛል ። ደግሞም ያለ አንዳች ተጨባጭ ወንጀል ፣ በጅምላ የትግራይ ተወላጆችን ማሰሩ ለምን አሥፈለገ ? ዛሬ  እነ ሥብሐት  ” ይቅርታ ጠይቀው ” ተፈቱ ማለት ጌታቸውም  ሆነ ደብረፅዮን ነገ ይቅርታ ጠይቀው  ከሰሩት ወንጀል ነፃ እንደሚሆኑ  ማን ይጠራጠራል ? (…)

በዚች አገር በግብታዊነት የሚሰሩ ፤ ከፍትህ ጋር የሚጋጩ  ፤ አሠራሮች ከትላንት እሥከዛሬ እየተከናወኑ ነው ። አብይ መራሹ መንግሥት የትላንትናዎቹን  ህገ ወጥ ተግባራት ና “ ከመንግሥት በላይ መንግሥት “ የሆኑ ግለሰቦች ና “ በህቡ  የተደራጁ “ ኃይሎች ያሥከተሉትን ውድመት በጊዜ ብዛት የረሳው ይመሥለኛል ። ጠ/ሚሩን ጨምሮ የመንግሥት ባለሥልጣናት የህግ የበላይነትን ለማሥከበር የሚሂዱበትን ርቀት ደጋግመው ገልፀዋል ።  በኢትዮጵያም ድርድር እንደሌለ አሳውቀዋል ። እና ዛሬ ምን ተፈጥሮ ነው ፣ ከፈረሱ በፊት ጋሪው የቀደመው ?

እነዚህ ሰዎች እኮ የትግራይን ህዝብ ከአማራና ከአፋር  ጋር ደም ያቃቡ ናቸው ። ጃዋርም ቢሆን ሰው ማለት ኦሮሞ እንጂ ሌላው በረሮ ነው ባይ ነው ። እምነተ ቢስ ነው ። አንድ በሬ በእሥልምና እና በክርስትና ሥም አርዶ  ለፖለቲካ ፍጆታ ህዝብ  በግድ የሚያሥበላ ነው ። ይኽንን ሃቅ መራራ መሥክሯል ። አብይን ለመጣል ትንሽ ሲቀራቸው በፊኒሽንግ ችግር ምክንያት እንደተሸነፉ ። እነዚህ ሰዎች ከሥልጣን የዘለለ ህልም የሌላቸው ናቸው ።ጃዋር የሚኒልክ ሀውልት ይፍረስ ብሎ በአማራ ጠልነት ሁሌም እንደ አበደ ውሻ የሚንከወከወ ለምንድ ነው በታላቅ ሁከትና ብጥብጥ ወደሥልጣን በመምጣት ለአንድ ቀን ጠ/ሚ ሆኜ ኢትዮጵያን መርቼ ( ኢትዮጵያዊያንን ገዝቼ ልሙት  ። ) በማለት አይደለምን ? ጃዋር

ዛሬም ከአማራ ና ከኢትዮጵያ ጠልነቱ የተፈወሰ አይመሥለኝም ። በበኩሌ እንዲህ ዓይነት የወረደ ሂትለራዊ አቋም ያላቸው ነገም የዚች አገር አጥፊዎች መሆናቸውን አሳምሬ አውቃለሁ ። አጥፊነታቸውንም በተግባር በቅርቡ ያሳዩናል ብዬ እጠረጥራለሁ ። አብይ ዛሬ ሥለፈታቸው ነገ ለአብይ ያዝናሉ ብላችሁ አጠብቁ ። … አብይ  ታሪኩን በድንቅ ና በግሩም ታሪክ ጀምሮ በመጥፎ ታሪክ እንዲደመድመው የሚያደርጉት በግብፅ ዶላር የናጠጡት እነ ጃዋር  እንደሆኑ ካልተረዳ እንደ እርግብ የዋህ ፣ እንደ እባብ ብልህ ሁን የተባለውን ጥቅሥ ዘንግቷል ና ቆም ብሎ መፀሐፍን ይመረምር ዘንድ ትሁት ምክሬን እለግሰዋለሁ  ። ነገ ፣ ተነገ ወዲያ እውነቱ ይፋ ሥለሚወጣ የነገሬን እውነትነት ይገነዘባል  ። … ምንም ድመት ብትመነኩስ አመሏን ትረሳለች ብሎ  የሚያሥብም አይመሥለኝምና በወቅቱና በጊዜው እውነቱን ይረዳል ። ለሁሉም ጊዜ አለው። …     ።

ለማንኛውም አሁን “ አውጣን ! “ ብቻ ነው ፣ ለማለት የምንችለው ። በተለይም ለኢትዮጵያ አንድነት ፣ ክብር ፣ ታላቅነትና ህልውና ሥንጮኽ የነበርን እና ዛሬም “ ኡ!ኡ! ቤት ይፈርሳል ። ቤት ይቃጠላል ። ሰው ዕለት ፣ ዕለት እየደኸየ ፣ ዘራፊ እየበለፀገ ይሄዳል ። አሜሪካንን ያመነ ጉም የዘገነ አንድ ነው ። “ ሥንል የነበርነው ።

ከዚህ ልብ ሰባሪ ዜና በኋላ ፤ መጪው ዘመን ለእኔ ከጦርነቱ የባሰ ጨለማ በመሆኑ  “ አውጣን ። ኢዝጊኦ ! ፈጣሪያችን በታላቅ ምህረትህ ጎብኘን   ።  “ እላለሁ ።

እንኳን እኔ ፣ ሥለህግ በጥልቀት የማላውቀው  የፍትህን ቁልፍ የጨበጡ በየክልሉ ያሉ ሃቀኛ የፍትህ ሰዎች  በዚህ ድንገተኛ ድርጊት አውጣን ማለታቸው አይቀርም  ።  “ እንዴት እንዲህ ይደረጋል ?   እንዴት ? በምን ዓይነትስ ሞራላዊ ግዴታ ፣ ግዴታ ፣ መንግሥት የተሰሩትን ፈታ ። በምን ዓይነት ሞራላዊ ግዴታ ? ግልፅ አይደለም ። በእሥክንድር ጉዳይ ከሆነ አዎ ሞራላዊ ግዴታ እንደሆነ እናምናለን ። በነሥብሐት ና በጃዋር የወንጀል ድርጊት ጉዳይ ግን የአያሌ የንፁሐን ሰዎች ደም ይጮኻል ና  አፈታታቸው ሞራላዊ አይደለም ። ” በማለት ።

ይኽ ፀሐፊም በግል ማንንም አያውቅም ። ከማንም ጋር ቂምና ቁርሾ የለውም ። የማንም የፖለቲካ ድርጅት አባልም አይደለም ። ከእውነት ጋር ለመቆምና ለመሰዋት የተዘጋጀ ነው ።እናም ማንኛውም ሰው  ጠ/ሚሩን ጨምሮ  ከህግ በታች እንደሆነ ያምናል ። ማንም ሰው ወንጀል ከሰራ ፣ ድርጊቱ ከተረጋገጠ  በጥፋቱ ልክ   ዜጎች ይማሩበት ዘንድ ተገቢውን ቅጣት ባልዘገየ መልኩ መቀጣት አለበት ብሎ ያምናል ።

ለአገራዊ እርቅ እነ ሥብሐትን እና  ጃዋርን መፍታቱ  አሥፈላጊ ነው ከተባለም ፣ በቀጥታ በደሉ የደረሰበት የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በዛሬው ተጨባጭ ሁኔታ ፣ የአማራና የአፋር ክልል መወያየት ነበረበት ። ሰው እኮነው የሞተው ። ያውም ለመስማት በሚከብድ አገዳደል ።ግፉ የተፈፀመባቸው ክልሎቹ  በምክር ቤቶቻቸው ፤ ህዝብንም ባሳተፈ ደረጃ አሥቀድሞ በመወያየት ከእሥር መፈታታቸውን መደገፍ ወይም መቃወም  ወይም የተለየ አሥተያየት ሊሰጡ ይገባቸው ነበር  ። ከሞራል አንፃር የሻሸመኔው ፣ የዴራው ፣ የቡራዩው ፣ የአዳማው ፣ የአዲስ አበባው ፣ የአጋርፋው ፣ የጉራ ፈርዳው ፣ ወዘተ ። ግፍ ፣ ተነሥቶ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑት ቤተሰቦች ለውይይት መጋበዝ ነበረባቸው ። ይኽ ባልቀደመበት ፣ በተዋከበ መልኩ በሐገር ክህደት ና በአሸባሪነት የተወነጀሉ ሰዎችን በይቅርታ መፍታት ፣ ያውም ወደፊት ለሚካሄድ የእርቀ ሠላም ወይይት ብሎ ከፈረሱ በፊት ጋሪውን ማሥቀደም ነው ። ከሞራል አኳያ  ተገቢ ና ትክክል የሚሆነው ከውይይቱ በኋላ ቢሆን በተሻለ ነበር   ። መንግሥት በግዴለሽነት ና በሞራለ ቢስነት ” ለኢትዮጵያውያን ሞት ብርቃቸው  አይደለም ።” እንደሚሉት እንደነ አሜሪካ የሚያላግጥ የመንግሥት ባለሥልጣናትም ያለ አይመሥለኝም ።  የአንድ ንፁህ ሰው ደም በከንቱ መፍሰስ ህሊና ያለውን ሰው ሁላ ፣ ያገበግበዋል ።  ብዬ አምናለሁ ። እናም ከፈረሱ በፊት ሥለቀደመው ጋሪ ሁኔታ  እንዴት አይነት አሳማኝ ማብራርያ መንግሥት እንደሚሰጠን ከቶም አላውቅም ።  ደግሞም የእልፍ ንፁሐን የሰቆቃ  እንባ ሳይታበሥ  ፤ ደመ ቀዝቃዛ ጨካኞችን መፍታት ፍትሐዊ አይሆንም  ።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop