አዲሱ ትውልድ አምቆ የያዘውን አልበገር ባይነት ወቅትን ጠብቆ ተነሳ !!! ኢትዮጵያን አዳነ እውነትም አኩሪ ተግባር ፈፀመ የማንነታችን ተምሳሌት በዚህ ዘመን የተገኙ ከቀድሞዎቹ ጀግኞች ተርታ አሰለፈው እምቢ እነኔቴን አሳልፊ አልሰጥህም የሚለው ማንነት ለመስዋት የቀረበ ለኢትዮጵያ ፍቅር መገለጫ አደረገው። የተከፈተውን አገር የማፍረስ ሴራ አክሽፈው በቆራጥ አመራር በፍራት ተውጥረን በነበርንበት ከመጨረሻው ሰአት የተጀመረ መስዋትነት ነበር ። ሁሉ የአምላካችን ፍቃድ ሆነና አገር እንደ አገር ልትቀጥል አንድ ምዕራፍ አለፈን። ወራሪው ህውአትም በቆፈራቸው ምሽጎች ተቀብረው ታሪክ ሆነ ቀረ። ዛሪ ላይ ሆነን የትናንቱን እረስተን ነገን እንናፍቃለን የትግራይም ምድር ከደም መፋሰስ ይዳን ብለን ይበቃል የጥቂት ግለሰቦች ትምክህተኛ አስተሳሰብ የፈጠረው ስህተት አገራችን ብዙ እንድትደማ መላውን መፍጠር በእኛው በአገሪው ህዝቦች ይመከር እላለሁ። የሴቶች፣ የህፃናት እና የኑፁሃን ደም በከንቱ ፈሷል፤ የአገሪቷ ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎድቷል።
የተሸነፈ ወይም የአሸነፈ ብሄር የለም የጥቄቶች አስተሳሰብ ነው የተገራው አገር እንደአገር እንድትቀጥል የተከናወነ የአንድነት ምላሽ ነው ብዬ አምናለሁ። ሁሉ በሰላም አልቋል የማለት ሃሳቦች ላይ ያተኮርኩ መሰልኩ አይደለም! የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ ይገባኛል፣ የተረታውም አካል የሞኝ በትሩን ማንሳቱ ባይቀርም እኔ ከሞት ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያይቱ የትግራይ ህዝብ መስዋት ባይሆን ይመረጣል። ሌላው ግን ምዕራባውያኑ ያስቀመጡት የመጨረሻ ሙከራ እንዳለ መታወቅ እንዳለበት ይሰማኛል።
በሰሜኑ፣በምስራቅ አፋር እና የሰሜን ምዕራብ የቤሻንጉልን አካባቤዎች ላይ የነበረው የዘር እና የሃይማኖት ማጥፋት የምዕራባውያኑ ሴራ ነበር ብለን በቀደሙ የነፃው አስተያየት ሃሳቦችን አስቀመጫለሁ። የቀጣይ የምዕራብያኑ ስውር ቀጣይ መሰሪነት በደቡብ፣ በምዕራብ እና በቀሩት የምስራቅ አገራችን አካባቢዎች ስራዎቻቸውን እንዴት ይጀመራል ብሎ ማሰብ ይበጃልና ትንሽ የራሴን አስተሳሰቦች ልንገራችሁ።
ለሃሳቤ መነሻ የሆኑኝ ሁለት መሰረታዊ እና ታሪካዊ አስተሳሰቦችን ለማንሳት ፈለኩ።
የኦሮሞ ህዝቦች በአገር ጉዳይ እና በአገር ፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ልዩነቶች በተለይ እራሳቸውን የኦነግ እና ኦፒድዮዎቹ ውስጥ በመወገን በህዝባችው ላይ የፈፀሙአቸው ጥፋቶች ቂም በቀል እና አለመተማመን ይዘው መገኘት አንደኛው ሲሆን። በሁለተኝነት ደግሞ ኬንያውያን በኢትዮጵያ ላይ ያላቸው የቀደሙ አስተሳሰቦች እና ጥቅም ፈላጊውን በዋንኛነት የምመለከተው ይሆናል
ኬንያውያን በእንግሊዞቹ በቀኝ አገዛዝ ስር መሆናቸው ታሳቢ በማድረግ ጎረቤት ከሆነቻት ታላቅ እህት አገራችን ኢትዮጵያ ጋር ተቀራርባ በልማት የተሰለፈችባቸው ጊዜያትን ለመማግኘት ብቸገርም ከትናንሽ የቦርደግ ግጭቶች ውጭ በግልፅ የለየለት ጦርነት አውጃብን አታውቅም። መረሳት የሌለበት ግን የእንግሊዞቹ አስተሳሰብ በኬንያውኑ ውስጥ ሰርፆ መግባቱ መረሳት የለበትም። ግልፅ ባልሆኑ ሁኔታዎች ኬንያን ከተወዳጁት አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳይኖረን ስታደርግ ቆይታለች። አፍሪካውያን ወንድሞቻችን ምክንያት የሚያደርጉት የመግባብያው ቋንቋ እንደሆነ ያነሳሉ በአብዛኞቹ የኪሱዋልኛ ተናጋሪ መሆናቸው ከኬኛን ጋር የበለጠ እንዳጣመረቸው እና በምስራቅ አፍሪካው ውስጥም በኢኮኖሚም የተሻሉ መሆናቸው ይነግሩናል። የሚያሳዝነው ግን በኢትዮጵያ ኬንያ ድንበር የሚኖሩት የአገራችን ህዝቦች የኪሱዋልኛ አለመናገራቸው ተዘግቶ የቆየ የህዝብ ትስስር እንደነበር ያሳያል። ከአገራችን ድንበር ወደ ኬንያም የሚደረገው ከ 400 ኪሎ ሜትር በላይ የሚሸፍነው በአግባባቡ ያልተሰራ የጥርጌያ መንገድ ታስበው የተረሱና ለኢትዮጵያዎቹ ቦረናዎች በቦርደር ኑዋሪዎች እና ብሎም የመሃል አገሩም ህዝብ የተመቻቸ ግንኑኝነት እንዳይኖራቸው ታስቦበት የተከናወኑ ናቸው። የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫው ዋናው አማራጭ የጭነት ስራዎችን የሚያከናውኑት ከአገራችን የቁም ከብቶችን በኮንትሮባንድ የሚጭኑት ዋንያዎቹ ናቸው። ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የሚገባው የተለያዩ የሰብል ምረቶችን ጨምሮ የኮንትሮባንድ ቡና ኬንያን በአለም ገበያ ውስጥ ምርጥ የቡና አቅራቢ ባለቤት እንድትሆን አድርጓታል። ከምስራቅ አፍሪካ አገራት የተሻለ ሆኖ መገኘታቸው ቢገልፁትም መፎካከርያ በማድረግ ባይጠቀሙበት በወደድኩ ነበር። የደበቁትን ማንነታችንን ከሌላው የአፍሪካ ወንድሞቻችን ለመነጠል ተጠቅመውበታል ፤ ወዳጅ ለሚለው ቃል ምትክ ቢፈለግለት ማንነታቸውን እንዲያውቁ ይረዳ ነበር እላለሁ። የኬንያውን ባለስልጣናት ተወዳዳሪ የሌለው እራስ ወዳድነታቸው ከጉበኝነት አልፎ ለግል ተጠቃሚነት ባለተራ የሚያስቀምጣቸው ያህል የሚሰማቸው ናቸው። በቅርቡ ጊዜያት እየተሰዋለ ያለው ኬንያን በምዕራቡ እይታ ውስጥ ማስገባት ባለስልጣናቷ ለሞቆጣጠር እንደሚያመች ሁኔታዎችን ይፈጥራል። የራሳቸውን ድርሻ ማስቀደማቸው አገሪ በሚለው አስተሳሰብ ውስጥ ጥያቄ ይኖረዋል። ይህም አስተሳሰብ አገራችንን ኢትዮጵያን አሳልፈው ለምዕራባውያኑ አይሰጡም አያስብልምና ደጋግሞ መመርመር ይኖርበታል።
በቀድመት ተሞክሮዎች መራባውያኑም በተለያየ ሁኔታዎች ኬንያዎቹን ያውቋቸዋል፤ ቦታ ሰጥተው በአለም አቀፍ መድረኮች የተዩበት አጋጣሚዎች እምብዛም ሲሆኑ፣ አሁን ከአሜሪካኖቹ ጋር ያለው ቅርርቦሽ የደበቁት ሚስጥር እንዳለ ያሳያል።
ለኬንያው ቱሪዝም እድገት አስተዋፅኦ ያደረገው ደርግ ስልጣን ሲይዝ በሰው ሰራሽ መንገድ ተነድተው ወደ ኬንያ የገቡት የዱር እንስሳቶቻችን የክፉ ቀን ወዳጅነታቸው መገለጫዎቻቸው ባይዘነጋ እወዳለሁ። ያንንም ተከትሎ በሰው ሰራች መንገድ የተገነባው ገደል እና የታጠረው አካባቤ የአገሪ ህዝቦችን ለግጭት እና የባለቤትነት ጥያቄ ሲዳርግ በአገራችን መሪት ላይ ተንጣሎ የነበረው የቱርካና ሐይቅ በከፍተኛ ደረጃ እንዲቀንስ ሆኗል። በአሁኑ ውቅትም በኬንያኖቹ በኩል የተፈጥሮ ሃብት ባለመብትነት ማንሳቱ አጋጣሚዎችን በመጠቀም የበላይ ሆኖ የመቆጣጠር ስውር አካሄድ ይኖረዋል በሚደረገው የድርድር ስራዎች የምዕራብያኑን ቀልብ መያዙ አይቀርምና በአካባቤው ላይ ለሚወሰዱ ስራዎችን ነቅቶ መጠበቁ ተገቢ ይሆናል።
ለቱርካና ሐይቅ ዋናው ገባሪ የሆነው ከኢትዮጵያ የሚፈሰው የኦሞ ወንዝ ሲሆን በአካባቤው ለሚኖሩት የአገሪ አርብቶ አደር የመኖር ዋስትና ነው። ከኢትዮጵያ ክልል ውስጥ በሰፊው የሚገኘው ረግራጋማው እና የግጦሽ መሪት በኬንያም ውስጥ ለሚገኘው የቱርካና ሃይቅ የውሃ ሃብት መሰረት ነው። ለአለፉት አመታት ኬንያንስ ወደአገራችን ዘልቀው በመግባት የሚያነሷቸው ችግሮች አካባቢውን በባለቤትነት ለመያዝ ካላቸው ፍላጎት የተነሳ እንደነበር የምናስታውስ ነው።ኢትዮጵያ ያለችበትን የውስጥ ችግር የተረዱት ኬንያውያን ጥቅማቸው በማስቀደም ከምዕራባውያኑ እድል መፈለጋቸው አይቀሪ ነው። ተግባራዊ ለማድረግ የመዕራባውያኑን ጣልቃ ገብነት መሰረት እያደረገ መጥተዋል። በድርድር መፍታትንም ትኩረት በመስጠት የሚጋብዙንም አጭበርብሮ ውሳኔ እንዲያገኙ የማድረግ መከራዎችን ማስተዋል ይጠበቅብናል።
ሌላው አሳሳቢው ጉዳይ ከኬንያ ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ስለሚችለው በምዕራባውያን የሚረዳው ጦር ይኖር ይሆን ብሎ መገመትን ታሳቢ ማድረግ ነው። ለአለፉት እረጅም አመታት በኬንያ ውስጥ በስደት የሚሰቃዩት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በኬንያ ውስጥ ትጥቅ ታጠቀው በመርሳቤት እና በአካባቤው የሚገኙ የቦረና እና የኦሮሞ ህብቦችን የሚመለከት ይሆናል።
ከኦነግ ተገንጥሎ የወጣውና ከሱማልያ አልሻባብ ጋር የሚሰራው አንዱ ሲሆን ቀደም ባሉት አመታት ከ 2003 እስከ 2010 እንደ ኤ.አ ከአቃይዳ እርዳታ ተደርጎለት ከኬንያ የወጣው በአብዛኛው በአሁኑ ወቅት መሰረቱን በካናዳ፣ በአሜሪካ ውስጥ ያደረገው የኦሮሞው (የኢትዮጵያ ተቃዋሚ) ቡድን አባላትን ይመለከታል።
የዚህ ቡድን መሰረታዊ ሃሳብ መነሻው የኦሮሞን ህዝብ (ሙስሊም) ጥቅም ለማስጠበቅ ሲሆን አሁን በአለው የመንግስት መዋቅር የመካተት እድል ካገኘው ኦፒዲዮ ጋር የሚያቃርናቸው መሰረታዊ ልዩነቶች ቢኖሩም ይብልጥ ስልጣን ለመያዝ በነበረው ሂደት ውስጥ በዶክተር አብይ መበለጡን የተረዳ የአገር ውስጥም ተሳታፈዎች ያሉት ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በወያኔ ዘመን ባለማወቅም ይሁን አውቀው በፈፀሙት ክፍተኛ የሆነ የዘር ማጥፋት የግል ጥቅማቸውን በማስቀደም በአደርባይነት ወንድም ወንድሙን፣ አባቱን ልጁን እናቶች በግፍ የተጨፈጨፉበት፤ በአስከፊ ሁኔታ የተፈፀመ ወንጀል ለቂም በቀል የዳረጋቸው ሁኔታ መኖሩ ነው።
ቀድሞ የነበራቸው የሃሳብ ልዩነቶች እርስ በርስ ያደረጉት አሰቃቂ ወንጆሎች እና የተገኙት የጅምላ አስከሪኖች። እንዲሁም ከአስከፊው እስርቤቶች ያመለጡት ባለእድለኞች ጊዜን የሚጠብቅ የቂም በቀሉ መኖሩን የሚያሳዩ እውነታዎችን መደበቅ ሞኝነትን ያመጣልና በሰፊው ሊሰራበት ይገባል።
የባሌዎችን ከዶዶላ እስከ ጊኒር ያለው የሰላማዊ ህዝቦች ፍራቻ እና ውጥረት መፍትሔ ከሚፈልጉ ዋንናዎቹ ናቸው። በሐረሮችም በኩል ያለው ውጥረት በአገር መከላከያው ብርታት ችግሮች ጉልተው ባይወጡም የአርሲ ፣የባሌ አካባቤዎች ጋር ያመሳስላቸዋል። ቀድመው የደረሱት በደሎች ታምቀው መያዟቸው እና የማንነት ጥያቄዎች በተገቢው ሁኔታ በውይይቶች መፈታት ያስፈልጋቸዋል። የአልቃይዳው በአለም አቀፍ የሚያደርገው እንቅስቃሴው ትንሽ አረፍ ማለቱ ለአገራችንን ከፈጣሪዋ የተላከ ጠባቂ መኖሩን ሲያሳየን ። የፈሰሰው የንፁሃን ደም ምክንያት አድርገው ተሸናፊነት የማይዋጥላቸው ምዕራባውያኑ የሚበቀሉን በደም እንዳይሆን የአልቃይዳውን ጠላታቸው አስነስተው ስውር ስራቸውን እንዳይጀምሩብን ክትትል መድረግ ይፍልጋል ።
የተነሳሁበት ሃሳብ ማጠቃለያ የማደርገው በኬንያ ሞያሌ ቦረና ፣ በሱማልያ ጎዴ እና የሐረርጌው መዳረሻዎች ከባሌው ጌነር እስከ ዶዶላ ውስጥ ያለው ሁኔታን ትኩረት እንዲሰጠው ሲሆን ምዕራብያውያኑም የሁለተኛ ምዕራፍ ስራዎችን መስራት የመጀመራቸውን ምልክቶች እንዳሉ ማስተዋል ተገቢ ነው።
በመጨረሻም አስደሳች ሁኔታዎችንም ለመግለፅ በቅርቡ ለቡዙ ዘመናት በኬንያ በተለየዩ የስደተኞች ካምፕ በተለይ በካኩማው ከ30 አመት በላይ በስደተኝነት የነበሩትን ወንድሞቻችንን በኬንያ ውስጥ ተንቀሳቅሰው መስራት እንዲችሉ የተደረገው ሁኔታ፣ በኬንያን መንግስት ላይ ጫናውን ለፈጠረው አካል ሳላወድስ አላልፍም። ህዝቦቻችን በጉልበታቸው ሰርተን የመኖር መብት ተጠበቆላቸው፣ በሰውነት የአለም አንድ አካል መሆናቸው ታሳቢ መደረጉ ሊያኮራ ይገባል።
አገራችንን ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ይጠብቅልን!
በቀለ