አምባገነኖች ከትላንቱ ያለመማር አባዚያቸው የሚገርም ነው፤ያውም እኮ የሚጠቅማቸው ለራሳቸው ነበር። በተለይም የአፍሪካ አምባገነን ገዥዎች እትብታቸው በአንድ ምላጭ የተቆረጠ ይምስላል።
አንድነታችን ኣየፈረሰ፤ በጦርነት እየተለበለብንና በተመጽዋችነት በምንሰቃይባት በ’ኛዋ አገር፤ ገዥዋቻችን ከትንላቱ ለመማር ያለምፈልጋችን ግብዝነት የሚያውቁት እነሱ ብቻ ይመስሉኛል።
—– የትላንቱ እንቅፋት፣ ዛሬም ይመታናል
የትላንቱ እሽከላ፣ ዛሬም ይጠልፍናል
ላለመማር-መማር ፣ እኛ ተምረናል።——
የኦነጋዊ ብልጽግና ኃይል ከጡት አባቱ ከወያኔ እንኳን ለመመራ ፍቃደኛ አይደለም። በ’ርግጥ አሁንም መምበሩን ተፈናጠው የሚፈነጩብን ትላንት ወያኔ ጠፍጥፎ የሰራቸው ”እሰሩ ሲሏቸው- የሚደበድብ፤ ደብድቡ ሲሏቸው- የሚገሉ፤” በአጠቃላይ ”ሳይጠሯቸው አቤት!ሳይልኳቸው ወዴት፣!” ሲሉ የነበሩና፤ የህዝብን የስር -ነቀል ትግል ጠልፈው ”በተረኝነት” በህዝብና በአገር ላይ የሚፈነጩ የወያኔ ወራሾች ናቸው።
ለአገር አንድነትና ሰላም እንዲሁም ለቤተሰብ ሲባል ኃላፊነት የሚሰማው መንግሥት የፍርድ ወንጀሎኞችን እንኳን በይቀርታ ይፈታል። የኛዎቹ ተረኞች ግን መጀመሪያ ”ሳናጣራ አናስርም ” ብለው የሰበኩበት እንደበታቸው ሳይዘጋ፣ የካንጋሮ ፍርድ ቤት እንኳን ያልፈረደባቸውን የባልደራስ አመራራ አበላትን ፤ እስክንድር ነጋ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ አስቴር ስዩም እና አስካለ ደምሌ እስከዚች ሰዓት ድረስ ከአንድ ዓመት በላይ ያለፍርድ እስር ቤት ታጉረው ይሰቃያሉ። ከዚህ ላይ በጣም ”ቋቅ” የሚለው ነገር እነ እቶ እስክንድር በሽብርተኛነት መከሰሳቸው ነው። ተረኝነት፣ የወያኔ ግልባጭ።
አገራችን በውስጥም በውጭም እንደ ገና ዳቦ በምትነድበት በዚህ ሰዓት፤ የህሊና እስረኞቹ እነ አቶ እስክንድርን ይፈታሉ ብለን ስንጠብቅ፤ ይባስ ተብሎ ”ሃሳባችሁን ለምን በነጻነት ገለጻችሁ ” ተብልው፤ አቶ ታምራት ነገራ ፣ ወ/ት መዓዛ መሐመድና ሌሊችንም ጋዜጠኞች ወደ እስር ቤት ተወረወሩ።
‘’ሽግግር መንግስት መስርተናል!” ያሉ፤ በአራትና በስድስት ኪሎ ጎዳናዋች እየተጎማለሉና እየደነፋ፤ እነ አቶ እስከንደር ነጋንና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብታቸውን ገፎ ጋዜጠኞችን አስሮ ማሰቃየት ፤ የተረኞች ዓልማና ግብ ቢሆንም ህዝብ ግን ራሱን መጠየቅና ለማስፈታት መንቀሳቀስ አለበት። ፍትህ ከሌለ የአገር አንድነትም ሆነ ኢትዮጵያዊነት ሊጸና አይችልምና።
ፓለቲከኞች በፓለቲካ መለካከታቸው፣ ጋዜጦኞች በሚሰጡት ሃሳብ ላንስማማ እንችላለን፤ ግን ለተረኞቹ ማስገንዘብ የምንፈልገው ፍጹም መብታቸው መሆኑንና፤ ነገ – ከነገ ወዲያ ዋጋ ዋጋ እንደሚያስከፍላችሁ ልናሳስባችሁ እንወዳልን።
ህዝብንና አገርን በጦርነት አሮንቃ ውስጥ ከቶ፤ ሌላ ነገር እንዳይሰማ በማደናቆር ፣ በአስቸኳይ አዋጅ ስም እንደፈልግን ”ማሰርና መግደል” እንችላለን የሚለው መንገድ የትም አያደርስም። ህዝብ ከአገር እንድነትና ከኢትያጵያዊነት የሚበልጥ የለም ብሎ ስለታገሰ ፤ ትግሥቱን መፈታተን ለማንም አይበጅምና ፍትህን እንጠይቃለን።
መቸም እውነት እንነጋገር ከተባለ ፤ እቶ እስክንደር የታሰረበትን ምክንያት ከማናም የበለጠ በወያኔ ዘመን የትግል አጋሮቹ የነበራችሁ፤ ፎቶውን ጨረታ እያወጣችሁ የነገዳችሁ በውጭና በአገር ውስጥ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያንና በእስር ቤት አብራችሁ የተሰቃያችሁ ሁሉ ሃቁን ታውቃላችሁ ፤ ታዲያ በ’ሱ ጉዳይ ዝም ብትሉ ህሊናችሁና ታሪክ ዝም አይላችሁምና፣ አሁንም አልዘገያችሁም ፤ ለፍትህ ስትሉ ድምጻችሁን አሰሙ።
ጋዜጠኞች የሆናችሁ፤ የሞያ አጋሮቻችሁ እነ እቶ ታምራት ነገራ፣ እነ ወ/ት መዓዝ መሃመድን ሌሎቹን ጋዜጠኞች አሳስራችሁ ፤ ድምጻችሁን ማጥፋታችሁ፤ የሙያው ሥነ-መግባርም አይፈቅድላችሁም፤ ከታሪክና ከህሊና ተጠያቂነትም ነጻ አትሆኑምና ለትጮሁላቸው ይገባል።
ከዚህ ላይ እንደ ምሳሌ የህሊና እስረኞችን የባልደራስ አመራር አባላትንና የጋዜጠኞች ጉዳይ አነሳሁ እንጂ፤ ፍትህ ሙያ ወይም ጾታ ወይም ሃይምኖት የሌለው፤ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ መብት በመሆኑ ሁላችንም በአንድነት ለፍትህ መታገልና መጮህ እንዳለብን ማስገንዘብ እወዳለሁ።
እናም ……ፍትህ ለህሊና እስረኞች!!!!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኖራለች
——-//——ፊልጶስ
E-mail: [email protected]
ታህሳስ 2014