December 27, 2021
18 mins read

ትህነግ የለየለት ጭራቅ በመሆኑ ፣ ከእርሱ ጋር ለመደራደር አይቻለም – መኮንን ሻውል ወልደጊዮርጊስ

TLF 10ዛሬ ፣ በትግራይ ክልል በተግራይ ህዝብ ጉያ ውሥጥ የመሸገው ” የአሸባሪ ቡድን ” ፣ በዓለም ላይ በአሸባሪነት የተፈረጁ የሽብር ቡድኖችን በሙሉ የሚበልጥ ነው ። ሁሉም የዓለም አሸባሪ ቡድኖች በአንድ ላይ ተሰባስበው የሽብር ተግባር ቢፈፅሙ እንደ ትህነግ ወያኔ ፣ የለየላቸው ጭራቆች አይሆኑም ። የህወሓት / ወያኔንን ያህል በዓለም ላይ ጭራቅ ከቶም የለም ። ድሮ ልጅ ሆነንን በተረት ከተነገረን ሰው ከነነፍሱ ቀቅሎ ከሚበላ ጭራቅ የባሣ ሰው በላ ነው ። ያ ጭራቅ በተረት ይሄ በተግባር አንድ እና ያው ናቸው ። … የቢሊጮን ተረት አሥታውሥ ። እኔ ብልጮ ተበላልጬ የልጆን ሥጋ አበላኋት ልጬ ። ይልሃል ። በተረቱ መጨረሻ ። …

ወያኔ ” ቢሊጮ ” ከተባለ ፣ ጭራቅ የሚሥተካከል ” በላዔ ሰብ ” ነው ። የሰውነት ባህሪ ፈፅሞ የለውም ። ሲሰሙት ለጆሮ የሚቀፉ የጭካኔ ድርጊቶችን ያለአንዳች ፀፀት የሚፈፅም ህሊና ቢስ ነው ። በአገሬ ሰው ኃይማኖተኝነት የተነሳም ፣ ገና ያልተሰሙ አራዊት እንኳ ያለፈፀሙትን ድርጊት በአምሣየው ፣ በቢጤው እና በጓዱ ላይ ሣይቀር ሲፈፅም የኖረ ነው ። ትላንትም ፣ እኩይ እና በጭካኔ የተሞላ ድርጊቱን በቪዲዮ ቀድቶ በመያዝ ደጋግሞ በማየት ፣ ከጭራቅ ተመሳሥሎ የተገኘ ። በጭካኔ ድርጊት ብቻ ፣ እጅግ የሚረካ በሰው አምሳል የተፈጠረ ጭራቅ ነው ። ይኽ በቅዲስቲቱ አገር ለጉድ የተፈጠረ አንጎል አልባ ፍጡር ከጭራቅ ውጪ ከሰማይ በታች ሥም ልትሰጡት አትችሉም ። …

እርሱም እንደ ጭራቅ ተፈርቶ ፣ ሰው ሁሉ እየበረገገለት ከመቀሌ እየጋለበ ምንልክ ቤተመንግሥት ጭራቅነቱን በብርሃን እያሳየ መምጣቱን ያውቃል ።

የትግራይ ህዝብንም በጠመንጃ ና በሥለት በታጀበ ፣ ዘግናኝ የዕለት በዕለት ድርጊት ፣ እያሥፈራራ ለ47 ዓመት ምሽግና የጦርነት ማገዶ አድርጎታል ። ከመቼውም ጊዜ ይልቅ ደግሞ ዛሬና አሁን እየሸቀጠበት ነው ። ለወያኔ የትግራይ ህዝብ ቁሥ ነው ። መጠቀሚያ ነው ። ለጥቂት ጭራቆች ህይወት ሲል የወጣት ልጆቹን ገባሪ ነው ። በረሐቡና እርዛቱ የሚነገድበት ነው ። የጭራቆቹ( ልጆችማ በአውሮፓ ና አሜሪካ ይምነሸነሻሉ ። )

ዛሬ ና አሁን ፣ ጭራቁ ትህነግ ፣ ለጭካኔው በዓለም ላይ ተወዳዳሪ እንደሌለው ተመሥክሮለታል ። ከፈጠሩት አባቶቹም ምርቃት የተሰጠው መሆኑንን አትዘንጉ። ሕወሓት የአባቱ/ ትሕነግ /ወያኔ ቁርጥ የአባቱ ልጅ ነው ።

የጭራቁ ወያኔ አባት ማነው ካላችሁ ፣ የአሜሪካ መንግሥት ነው ።የአሜሪካ መንግሥትን ጨካኝነትን ደግሞ “ ከሄሮሾማና ከናጋሳኪ “ የአቶሚክ ቦንብ ፍጅት በቀላሉ ትረዳለህ ። ጉግል ጎልጉሎ ያሳይኻል ።

ይኽ ጭራቅ ቡድን ፣ ባለፉት ሥድሥት ወራት ፣ ከሰኔ አጋማሽ ፣ 2013 እሥከ ታህሣሥ 2014 ዓ/ም የመጀመርያ ሣምንት ድረሥ ወይም የኢትዮጵያ ጠ/ሚ በቢላዋ ቀልድ የለም በማለት ፣ በህዳር 13/ 2014 የኢትዮጵያን መከላከያ ሠራዊት በግንባር ተገኝተው ለመምራት እሥከዘመቱበት ጋዜ ድረሥ ፣ በአፋር ና በአማራ ክልል የጭካኔውን ጥግ ወይም ጭራቅነቱን ሞልቶ እሥከሚፈሥ ለዓለም አሳይቷል ።

ንብረት አውድሟል ። ዘርፏል ። ፋብሪካ ነቅሎ ወሥዷል ። በቁሣዊ ውድመት ና ዘረፋ ላይ ብቻ አላቆመም ። ይኽ የአሸባሪ ቁንጮ የሆነ ቡድን ፤ ይልቁንም በአማራ ና በትግራይ የሚኖሩ ሠላሚዊ ዜጎችን ሰብዓዊ መብት ጥሷል ። በየጎጇቸው በመግባት አካላዊ ሥቃይ ፈፅሟል ። ሴቶችን ደፍሯል ። አዛውንቶች ፣ መነኩሴዎች ሳይቀሩ ተደፍረዋል ። በታዛቸው ውሥጥ ፣ በጓዳቸው ና በመኝታ ቤታቸው ውሥጥ ያለአንዳች ሀፍረት ተጨማልቋል ። አብድ ፣ እብድ ተጫውቷል ። ለወሬ የሚቀፍ አያሌ አሥቀያሚ ተግባርም ፈፅሟል ።

ዛሬና አሁን ፣ በጀግናው መከላከያ እና በተባበሩት የየክልሎቹ ልዩ ኃይሎች ፣ በአማራ ፋኖ ፣ በአፋር ና በአማራ ህዝባዊ ጦር ተጠራርጎ ከአማራ ክልልና ከአፋር ክልል ወጥቷል ። መውጣቱ እርግጥ ቢሆንም መዘናጋት ፈፅሞ አያሥፈልግም ። የተጠና የተባለው እርምጃም ፣ ፋታ በማይሰጥ መልኩ ፣ ሊካሄድበትና ፈፅሞ መጥፋቱ እሥኪረጋገጥ ደረስ ፣ በልዩ ወታደራዊ ኃይል መቀጥቀጥ አለበት ። ችላ ከተባለ ፣ ወይም ፋታ ካገኘ ዳግም ያንሰራራ ና አገር ማድማቱን ይቀጥላል ። በዓለም አንድ ቁጥር አሸባሪ መሆኑንንም ያሥመሠክራል ።

ከአፋር ና ከአማራ ክልል ፣ በተባበረው የኢትዮጵያዊያን ክንድ ተቀጥቅጦ ሲወጣም ፣በጨካኝ ድርጊቱ ፤ በኃይማኖታዊ አክራሪነት ከታወቁ ፣ ከእነ ” አልቃይዳ ፤ አይስስ ፤ አልሻባባ ና ከቦኩ ሃራም ” የባሰ ቁጥር አንድ አሸባሪ እንደሆነ ፣ ተመሥክሮለት ነው ። ጨካኘ ፣ ግፈኛ ና ጭራቅ መሆኑ በተግባሩ ሺ ጊዜ ቢያረጋግጥም ፣ የአሜሪካ መንግሥት ፣ ይሄ አሸባሪ ፣ ጥቅም የሚያሥገኝለት መሆኑን በማመኑ የተነሳ ፣ የሰው ዘር ጠላት መሆኑንን በሥውር ሳተላይቱ በተጨባጭ እየተመለከተ እንኳ ጭራቅነቱን በመካድ ድጋፉን ለዚህ አረመኔ እሥከዛሬ እየሰጠ ነው ።

ዛሬ ና አሁን በአሜሪካ መንግሥትና በአንዳንድ የአውሮፖ አገር መንግሥታት በኩል ፣ በተባበሩት መንግሥታት አማካኝነት ፣ ይኽንን አሸባሪ ከሞት ወደህይወት ለማምጣት ፣ በየቀኑ ሤራ መጎንጎኑ የአደባባይ ምሥጢር ነው ። ይኽንን እውነት በቀላሉ የምንገነዘበው ባለፉት አሥራአንድ ወራቶች ብቻ በውሥጥ ጉዳያችን ለ15 ጊዜ የተባበሩት መንግሥታት ሥብሠባ መጠራቱ ነው ።ተመድ በኢትዮጵያ ጉዳይ ፣ በወር ውሥጥ ሁለቴ ሥብሠባ የተጠራበት ጊዜ አለ ። ለሶርያ ፣ ለየመን ፣ ለሊቢያ ሠላም ግን ተመድ ያዙኝ ፣ ልቀቁኝ በማለት በአሜሪካና በጥቅም ሸሪኮቻ አማካኝነት ሲፎክር አልታየም ።

በእኛ የውሥጥ ጉዳይ ግን ለ15 ጊዜ ጣልቃ ገብቷል ። አፍሪካውያን ያልደገፉት ፣ አንድ ሥብሰባ ፣ የፀጥታው ምክር ቤት ድምፅን በድምፅ የማይሽረው ጉባኤ ሢሰምርለት ፣ የተቀሩት 14 ስብሰባዎች በፀጥታው ምክር ቤት ፣ የድምፅ ጉልበት ወይም ውሳኔን የመሻር ኃይል ባላቸው ቻይና እና ሩሲያ ከሽፏል ። ሩሲያ ና ቻይና ሤራውን ባያከሽፉት ኗሮ ዛሬ የጦርነት አውድማ በሆነችው ኢትዮጵያ የኔቶ ና የአሜሪካ ዘራፊ ጦር ተሠማርቶ ፣ የኢትዮጵያን ወርቅ ፣ አልማዝ ኦፓል ፣ ዩራኒየም እና ሌሎች ውድ መአድናትን ከአገራችን እየዘረፈ ፣ወደ ሀገሩ ያግዝ እንደነበር አትጠራጠሩ ።

በነገራችን ላይ ፣ የአውሮፖም ሆነ የአሜሪካ መንግሥታት ሠልጥነውም እንኳን የሤጣን አሥተሣሠብ ሥላለቀቃቸው የኢትዮጵያን ህዝብ ሠላምና ብልፅግና ፈፅሞ አይሹም ። የሤጣን አእምሮ ባይኖራቸው ና ቅኖች ቢሆኑ ዓለም በሠላም እንድትኖር በማድረግ ፣ ድህነት የሌለበት ዓለምን ለመፍጠር ይችሉ ነበር ። …

አንዳንድ የአውሮፖ አገራት መንግሥታት ና አሜሪካ ፣ ለጥቅማቸው ሲሉ ህውሃትን ከመጀመሪያው ኮትኩተው ያሳደጉት በመሆናቸው ፣ አጥፊ ምግባሩ ባይደንቃቸውም ፣ ለብዙው ወጣት ግን ፣ የህወሃት ወይም የትህነግ ወይም የወያኔ እኩይነት ፣በቅርቡ ና ዛሬ የተከሰተ ይመሥለዋል ።

የህወሓት እኩይነት ወይም ጭራቅነት የተከሰተው ድሮ ነው ። የህወሓት ያለፈ ታሪኩን ለማወቅ ፣ የተለያዩ የታሪክ ሰነዶችን ” ከጎግል በማውረድ ” እንዲሁም ፣ በህወሓት ወያኔ ዙሪያ የተፃፉ መፅሐፍቶችን እና የመፅሔት ላይ መጣጥፎችን በማንበብ ኢትዮጵያን ለማፍረሥ በውጪ ጠላቶቻችን ድጋፍ የተፈጠረ መሆኑንን መገንዘብ ይቻላል ። ።( ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ ፣ በህቡ ፣ በከፍተኛ ደረጃ የግብፅ መንግሥትን ድጋፍ ያገኝ እንደነበር መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ይኽን ጉዳይ በሌላ ርዕሥ እመጣበታለሁ ። )

እነዚህን የቆዩ መረጃዎችን እና የዛሬን የህወሓትን እኩይነት ና ጭራቅነት በቅጡ በመረዳት ፣ ከዚህ የሰው ህሊና ከሌለው ጭራቅ ቡድን ጋር ፣ ፈፅሞ መደራደር እንደማይቻል መንግሥት በቀላሉ የተገነዘበ ይመሥለኛል ።

የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ ይኽ የገንጣይ ሥም ና የዘረኝነት አሥተሣሰቡ ያለው አሸባሪ ቡድን ፣ ከነጭራቅ መሪዎቹ መጥፋት ወይም መወገድ አለበት ብሎ የሚያምን ይመሥለኛል ።

አሸባሪ ድርጅት በመሆኑም ይኽንን ድርጅት በበላይነት የሚመሩት ዋና ፣ ዋና ቁልፍ ሰዎች እሥካልተወገዱ ጊዜ ድረሥ ፣የትህነግ የሽብር ድርጊቱ እንደማያባራ መታወቅ አለበት ። የአሸባሪው የህወሓት አመራሮች ፣ እነ ደብረ ፅዮን መወገድ አለባቸው ። የአሸባሪው ድርጅት የፕሮፖጋንዳ ማሽን ጌታቸው ረዳም ምላሡ መቆረጥ አለበት ።…ፈፅሞ መጥፋት አለባቸው ሥንልም በዋነኝነት ፣ ወያኔ ከ30ዓመት በፊት በአገሪቱ የተከለው ና መርዝ እያጠጣ ያበቀለው የዘር ፖለቲካ በራሱ ጭራቅ እንደሆነ በመገንዘብ ነው ። ደግሞም ፣ ይኼ ጭራቅ አሸባሪ ድርጅት ከምድረ ኢትዮጵያ እሥካልጠፋ ጋዜ ድረሥ ፣ ነገ ፣ ተነገወዲያ ፣ በእነ ኦነግ ሸኔ በኩል ፣ ሌላው ጁንታ መከሰቱ አይቀሬ እንደሆነ መንግሥት አሣምሮ ያውቀዋል ና የኦነግ ሸኔንንም ፋይል መዝጋት አለበት ። ከጭራቁም ወያኔ ጋር ፈፅሞ መደራደር የለበትም ።

ወዳጄ በደም ከተጨማለቀ ፣ ለሱሪውም ዚፕ ከሌለው … ዱሪዬ ጭራቅ ጋራ እንዴት ትደራደራለህ ? እንዴትሥ እጁ በሰው ደም ከተጨማለቀ ጭራቅ ጋሬ ትጨባበጣለህ ? ህሊና ላለው ሰው እጅግ ከባድ ነው ። በአውደ ግንባር ላይ ለአገራቸው ክብር ሲሉ ከተሰውት ጀግኖች ውጪ ፤ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ሲቪል ዜጎች በግፍ ተገድለው ሲያበቁ ፣ ለእነዚህ ህይወት መጥፋት ተጠያቂ የሆነው ለፍርድ ሳይቀርብሥ ከትግራይ ክልል ኗሪ ህዝብ ጋር ይቅር ተባብሎ እንዴት መኖር ይቻላል ?ከዚህ ጭራቅ ፣ አረመኔ ጋር ቁጭ ብሎ ለመነጋገር ማሰብ በራሱ ህሊናንን የሚያደማ እኮ ነው ። ሠርተው የሚኖሩ ፣ ወግ ያላቸውን ፣ ክብር ያላቸው ፣ ጨዋና ኃይማኖተኛ ፣በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን አሸባሪው ወያኔ ካፈናቀለ ና ተመፅዎች ካደረገ በኋላ ፣ እንዴት ነው ከሰው ፀር ከሆነ ቡድን ጋራ ለመደራደር አጀንዳ የምትይዘው ? ይኽ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው ።

የአገሬ መንግሥት መደራደር የሚችለው ጉያው የተሸጎጠውን ጭራቅ ለፍርድ ለሚያቀርብ አልያም በእነ ደብረፅዮን ላይ እርምጃ በመውሰድ ” ከወንድሜ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር በፍቅር እኖራለሁ ። ” ብሎ ከቆረጠ የህዝቡ ተወካይ ጋር ብቻ ነው ።ከዚህ ውጪ ሌላ የድርድር አማራጭ የለም ። የትግራይ ህዝብ ዛሬ የተሰጠው አማራጭ ይኽ ብቻ ነው ። እርሃቤ ፣ እርዛቴ ፣ ሥንዴ ለማኝነቴ ፤ ይብቃ ! ከተቀረው የአገሬ ዜጋ ጋር ተዋህጄ በፍቅር በመኖር ለመጫው ትውልድ ፣ ቂም አልባ አብሮነትን ልፍጠርለት ። ” ብሎ የሚያሥብ ከሆነ ፤ በዘረፉት ገንዘብ ተጠቅመው ፣ ሊደልሉት የሚፈልጉትን በመሣሪያ አጀብ ና በቅጥር ነፍሰ ገዳዮች ብዛት እያሥፈራሩት የሚኖሩትን ፣ እነዚህን ጭራቆች ለፍርድ ማቅረብ ብቸኛው አማራጭ ነው ። አልያም እነሱን አሥወግዶ ራሱን ነፃ በማውጣት ፣ በወንድሞቹና እህቶቹ ላይ ( በገዛ ፈቃዱም ይሁን ተገዶ ) የፈፀመውን የጭካኔ ተግባር አምኖ ፣ ፀፀቱን በይፋ በማመን ለይቅርታ ፣ ከልቡ ሲነሣ ነው ። የራሱን አሥተዳደር በራሱ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ለመምረጥም ሆነ በዜግነቱ ኮርቶ ፣ አንገቱን ቀና አድርጎ ለመራመድ የሚችለውም ትህትናን ወይም ዝቅ ማለትን በቅጡ ሲገነዘብ ብቻ ና ብቻ ነው ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

ከሃይለገብርኤል   አያሌው የኦቦ ሲራጅና የወይዘሮ ፉንታዬ ልጅ ጃዋር መሃመድ ትላንትን ዛሬንና ነጋችንን ሊያሳይ የሚችል መጽሃፍ አዘጋጅቶልናል:: በእውነቱ መጽሃፉ ሊነበብ በሚችል የሃሳብ ፍሰት ተቀንብቦ በአነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ጃዋርን እና የቄሮን ትውልድ በቅጡ ለመረዳት መጽሃፉ ማንበብ

የጃዋር የፖለቲካ ጅዋጅዌ! “ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ’’

Go toTop