August 13, 2021
7 mins read

ያብይ አሕመድ ውሃ ቅዳ ውሃ መልስ – መስፍን አረጋ

abiy

  1. ወያኔ በሰሜን እዝ ላይ ለፈጸመው ጭፍጨፋ ዋናው ተጠያቂ ወያኔ ሳይሆን የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ የሆነው ዐብይ አሕመድ ነው፡፡  ተጠያቂ የሆነበት ምክኒያነት ደግሞ ወይም ከወያኔ ጋር በመመሳጠር ጭፍጨፋውን በማመቻቸቱ ወይም ደግሞ ግድግዳው ላይ የተጻፈውን ግልጽ ማስጠንቀቂያ አይቶ እንዳላየ በመሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለመውሰዱ ነው፡፡  ግራም ነፈሰ ቀኝ በሰሜን እዝ ላይ በተፈጸመው ጭፍጨፋ አማካኝነት፣ ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ወደ ኦነጋዊ ግቡ በሚያመራው ጎዳና ላይ አንድ ትልቅ ርምጃ ተራምዷል፡፡  እርምጃውም ኦነጋዊ እቅዱን ሊያኮላሹበት የሚችሉ የአማራ መኮንኖች በአማራነታቸው እየተለዩ በወያኔ መጨፍጨፋቸው ነው፡፡
  2. ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ በሕግ ማስከበር ሰበብ ጦርነት ከፍቶ መቀሌን ሲቆጣጠር፣ ወደ ኦነጋዊ ግቡ በሚያመራው ጎዳና ላይ ሦስት ትላልቅ ርምጃወችን ተራምዷል፡፡  የመጀመርያው ርምጃ፣ የወያኔ ኃይል ከሞላ ጎደል ሙሉ በሙሉ ባማራ ልዩ ኃይል ላይ እንዲያርፍ በማድረግ፣ ያማራ ልዩ ኃይል ከፍተኛ መስዋእትነት እንዲከፍል ማድረጉ ነው፡፡  ሁለተኛው ርምጃ አያሌ ያማራ አርሶ አደሮችን ፈንጅ ረጋጭ በማድረግ አሰጨፈጭፎ፣ የአማራን የወታደር ምልመላ ምንጭ በተወሰነ ደረጃ ማመንመኑ ነው፡፡  ሦስተኛው ርምጃ ደግሞ ኦነግ በወያኔ ላይ የበላይነት መቀዳጀቱንና ጊዜው የኦነግ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡ ነው፡፡
  3. ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ትግራይን ለስምንት ወራት በተቆጣጠረበት ጊዜ፣ ወደ ኦነጋዊ ግቡ በሚያመራው ጎዳና ላይ ሦስት ትላልቅ ርምጃወችን ተራምዷል፡፡  የመጀመርያው ርምጃ፣ ከነ አንቶኒ ብሊንከን ጋር በመመሳጠር ያማራ ልዩ ኃይል ያለ ኃጢያቱ በዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲከሰስ ማድረግ ነው፡፡  ሁለተኛው ርምጃ ትግሬወች አማራን እንደ መሪር ጠላት፣ ኦሮሞን እንደ ልብ ወዳጅ እንዲያዩ ያደረገው ጥረት በከፍተኛ ደረጃ መሳካቱ ነው፡፡  ሦስተኛው ርምጃ በጦርነቱ ክፉኛ የተዳከመው ወያኔ ባጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያንሰራራ ማስቻል ነው፣ የኦነጋውያን እቅድ ወያኔ የኦነግን የበላይነት አሚን ብሎ ተቀብሎ አማራን ሰቅዞ የሚይዝ ጎጠኛ ሎሌ እንዲሆን እንጅ እንዲጠፋ አይደለምና፡፡
  4. ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ በተኩስ ማቆም ሰበብ፣ ያማራን መሬት ለወያኔ ሲያስረክብ፣ ወደ ኦነጋዊ ግቡ በሚያመራው መንገድ ላይ ሁለት ትላልቅ ርምጃወችን ተራምዷል፡፡   የመጀመርያው ርምጃ ከጦርነቱ ቁስል ማገገም የጀመረውን የአማራን ሚሊሻና ልዩ ኃይል እያስከበበና እያስቆረጠ ማስጨፍጨፉ ነው፡፡  ሁለተኛው ርምጃ የደግሞ አማራን የትግሬን ቅራኔ የበለጠ ማክረሩ ነው፡፡
  5. ኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ ወያኔን እንደገና ሊወጋው የተነሳ የሚያስመስልበትን የቁጩ መግለጫ ያወጣው ግን በሚከተለው ምከኒያት ነው፡፡  በዐብይ አሕመድ አመቻችነት ወያኔ አማራን ሲወር፣ የአማራ ሕዝብ በዐብይ አሕመድ መንግስት ላይ የነበረውን ዕምነት አሽቀንጥሮ ጥሎ የራሱን እድል ራሱ ለመወሰን ሆ ብሎ ተነሳ፡፡  አማራ ባማራነቱ ሆ ብሎ ከተነሳ ደግሞ ለወያኔና ለኦነግ የሸዋ አማራ ብቻ እንደሚበቃቸው ዐብይ አሕመድ አሳምሮ ያውቃል፡፡  ስለዚህም ዐብይ አሕመድ ራሱ ያስታጠቀውን ወያኔን ትጥቅ ለማስፈታት መመሪያ ቢጤ ያስቀመጠው፣ እውነትም ትጥቅ ሊያስፈታው አስቦ ሳይሆን፣  ያማራ ሕዝብ በራሱ መተማመኑን ትቶ በፌደራል መንግስት ላይ በመተማመን እንዲዘናጋና ለዳግም ጭፍጨፋ እንዲመቻች ለማደረግ ብቻና ብቻ ነው፡፡
  6. ስለዚህም ሰፊው ያማራ ሕዝብ ሆይ፣ ወያኔና ኦነግ ጠባቸው የሰልጣን እንጅ አንተን በተመለከተ የልብ ወዳጅ መሆናቸውን አውቀህ፣ የኦነጋዊው የዐብይ አሕመድ ዲስኩር ብቸኛ ዓላማ አንተን ለማዘናጋት ብቻና ብቻ መሆኑን ተረድተህ፣ ሒሳብ ሊያወራረድብህ ያሰፈሰፈውን፣ በህልውናህ ላይ የመጣውን ወያኔን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ማጥፋት የምትችለውና ማጥፋት ያለብህ አንተና አንተ ብቻ መሆነህን ተገንዝበህ፣ አሁን በያዝከው ወያኔን በራስህ ዘዴ፣ በራስህ ልጆች፣ በተባበረ ክንድህ መደቆስህን አጠናክረህ ቀጥልበት፡፡
  7. አማራ ከኦነጋዊው ዐብይ አሕመድ አፍዘ አደንግዝ ከተላቀቀ፣ ወያኔና ኦነግ እዳቸው ገብስ ነው፡፡

 

መስፍን አረጋ
[email protected]

 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop