የአፋር ክልል ህዝብ በሀገሩ ላይ የመጣውን የጥፋት ቡድን አሳፍሮ በመመለስ በየቀኑ አኩሪ ገድል እየፈጸመ ነው

qwel

ሰመራ፤ ነሐሴ 7/2013(ኢዜአ) የአፋር ክልል ህዝብ በሀገሩ ሉአላዊነትና ክብር ላይ የመጣውን አሸባሪውን የጥፋት ቡድን ከፀጥታው ሃይል ጋር እጅና ጓንት በመሆን አሳፍሮ በመመለስ በየቀኑ አኩሪ ገድል እየፈጸሙ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ተናገሩ።
የኦሮሚያ ክልል በአፋር አካባቢ አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ወገኖች የምግብና መድሃኒት ድጋፍ ባደረገበት ወቅት ርዕሰ መስተዳደሩ እንዳሉት የትህነግ ርዝራዥ ቡድን የሁላችንም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ጠላት ነው።።
በዚህም ልክ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለልዩነት የጥፋት ቡድኑን ግብአተ-መሬት ለማፋጠን ገንቢ ሚና መጫወት ይጠበቅብናል ብለዋል።
እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአፋር ክልል ህዝብ በሀገሩ ሉአላዊነትና ክብር ላይ የመጣውን የጥፋት ቡድን አሳፍሮ ለመመለስ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር እጅና ጓንት በመሆን በየቀኑ አኩሪ ገድል እየፈጸመ ይገኛልም ነውያሉት።
በዚህም ከአሸባሪው ላይ ታንክን በጩቤ ከመማረክ ጀምሮ አርብቶ አደሮች በድንጋይና ዱሉ ዲሽቃና ክላሽ ጨምሮ ዘመናዊ የጦር መሳሪያዎችን በመቆጣጠር ህዝቡ አይበገሬነቱን በተግባር አሳይቷል።
የኦሮሚያ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አማካሪ አቶ ግርማ ወተሬ በበኩላቸው፤ “የሽብር ቡድኑ ከውጭ ጠላቶቻችን የጥፋት ተልዕኮ እየተቀበለ በማስፈጸም በሀገራችን ላይ አደጋ ደቅኖብናል” ብለዋል።
ኢዜአ
ተጨማሪ ያንብቡ:  ተ.መ.ድ. በወልድያ አማራን የጨፈጨፉት የትግራይ ወታደሮች መሆናቸውን አመነ

ሀሃሳብ እና አስተያትዎን ይስጡ

Your email address will not be published.