November 2, 2020
11 mins read

“ቢተዋ አማረበት…”በእርቅ ይልስ …

ዐቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወመንፈሳዊ

“አንበሳው ግሥላው ተሰፍቶ በልክ፣
ቢተዋ አማረበት አጤ ምኒልክ።”


ቢተዋ-የዕጅ ጌጥ(የአለቃ ታየ ቅኔ)ከአፄ ዮሐንስ ፬ኛ ጋር ሊያደርጉት የነበረውን ጦርነት በመተዋቸው ጥሩ ሆነ ለማለት ነው።

የኔው ቅኔ ደግሞ፦

ዶክተር ዐቢይ ልቡ በመላ ዘይዶ፤
በእርቅ ይልስ ይሆን ካለዚያም ተገዶ፡፡

መቼም የኢትዮጵያን ውስብስብ የግጭቶች ታሪክ ደጋግመን ብንመለከተው ሕዝቦቿ በአንድም በሌላ ሳያውቁት እየደጋገሙት ነው፤እንደ መዝሙረ ዳዊት፣ያንኑ፦በዚህ በዚያ፣በግራ በቀኝ፣ወደላይ ወደታች፣ጧት እና ማታ፣በፊት ልፊት በስተጀርባ፣በቅርብና በሩቅ፣እስኪመርና እስኪጣፍጥ፤ስንቱ ይነገራል ይህንኑ የአብሮነት ድግግሞሽ ሕይወት በዘመናት ውስጥ ደጋግመውታል።ብዙም ሩቅ ሳንሄድ በዳግማዊ ሚኒልክና በአፄ ዮሃንስ ሊደረግ ስለነበረው ጦርነት በዝርዝር ለማብራራት ሳይሆን፣ልበሰፊውና አንበሳው አጤ ምኒልክ ቁጡዉንና ግሥላውን አፄ ዮሐንስን እንዴት በትዕግስት ወደጦርነት ማገዶ እንዳይገቡ እንዳደረጓቸው ከታሪክ መዛግብት ላይ እናገኛለንና እንመርምር።
መቼም የኢትዮጵያ ታሪክ ሥጋዊና መንፈሳዊ በመሆኑ ተዝቆ አያልቅምና አፈታሪክ ሆኖ እንዳይቀር በወሬ መልክ ለማወቅ ከመፈለግ ተቆጥበን፣ ምክንያቱም የአገራቸው
የኢትዮጵያን ታሪክ ጠንቅቀው የማያውቁ ከሙሕራንም መካከል እንድሉ ትክክለኛ መረጃዎች ተመዝግበዋልና(ሆን ብለው፣ለጥቅም፣ለሥልጣን፣ለደሞዝ ወዘተ)ነገሮችን እያጣመሙ ይተረጉማሉና ራሳችን ከመፅሐፍቱ እንድናነብ እመክራለሁ፤እንደ አለቃ ታዬ።
ወደተነሳሁበት ወቅታዊ ርዕስ ስንመጣ፦በኢትዮጵያ ያለው የውስጥ የመሪዎችና የተመሪው ሕዝብ ውስጥ ያለውን ችግራችንን ለመቅረፍ ትልቁ አስፈላጊው የሰውነት ክፍላችን ከአንገታችን በላይ ያለው ሆኖ እናገኘዋለን፤አንገት በተገቢው መንገድ በተፈ
 ገው ፍጥነት፣ባሻው አቅጣጫ ያለምን እክል መዟዟር ከቻለ ጭንቅላት ፍፁም ችግር አይኖርበትም።ዳሩ ግን አንገት በሶስት ሰበቦች ከተዘናጋ ወዳልፈለገው ይጠመዘዛል፤አሊያም በሶስት ምክንያቶች ከተዟዟረ በፍጥነት ችግሩን በሚገባ እየፈታ ይገኛል፤ በዘመናችን የጠቅላይ ሚንስቴር ዐቢይ አህመድን ምንሊካዊ አንገት እንመልከት።
ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በሦስት ሰበቦች ያለመውደዱ፣እንደገናም በሦስት ምክንያቶች አለመፈቀሩ በግድ የአለቃ ታዬን ሕብር እንድናስታውስ ታሪክ በደም በተፃፈ የብዕር ልሳኑ እንድንመረምረው ይመክረናል።
***ሦስቱ ሰበቦች ዶ/ር ዐቢይ ፩ኛ/ብሔሬን አይወክልም፣፪ኛ/ለብሔሩ ነው የሚያደላው ፫ኛ/ጴንጤ ስለሆነ ኦርቶዶክስን አይፈልግም የሚሉት ናቸው፤እነዚህ በሙሉ ማብራሪያ ያስፈልጋቸዋል እና አንገቱ
ን   አዙሮ ማየት ለሚችል ሰበቦች እንጂ ምክንያት አለመሆናቸውን በቀላሉ ይገነዘባል፤እናም በእነዚህ ሰበቦች ዶክተር ዐቢይ አህመድን ለመቃወም መነሳት ተገቢ አይደለም።
***ሦስት የማይፈቀረብት ምክንያት ፩ኛ/የትግሬን እና የአማራን ሕዝብ ይጠላል ፪ኛ/የኦሮሞ ነኝ ይላል ዳሩ ግን ለታገልንበት ኦሮሞነተ ለኦሮሞውም ሆነ ለአማራው አያደርግም።፫ኛ/ሕዝብ የታገለው ለየብሔሩ ነፃነት እንጂ ለኢትዮጵያዊነት አይደለም፣ከሆነም ቅድሚያ ብሔራችንን ነው የሚሉት ናቸው።
^^^ እንግዲህ ሕሊና ያለው እና አንገቱን ማዞር የሚችል፤ማለትም የአገራችንን አካባቢ፣የኢትዮጵያን ተጨባጭ ሁኔታ በደምብ በመመልከት ለእነዚህ የኢትዮጵያ ችግሮቻችን መፍትሔ እንዲሰጠን በታሪክ አጋጣሚ በሕዝብ እሺታ በአገር ይሁንታ ጠ/ሚ ዶ/ር አቢይ አህመድ የዓለም ሕዝብ በቀጥታ እያየው መንበረ ሥልጣኑን አገሪቱን ሲዘርፏት፣ሲገድሉና ሲያጋድሏት ከነበሩት የገዢዎች ቡድን ፈለጉም አልፈለጉም ከመካከላቸው ብድግ ብሎ “አገር እንዲህ አይመራም ብሎ”በተለሳለሰ አመፅ ከጓዶቹ ጋር አብሮ ፈንቅሎ መውጣቱ እና እስከዛሬም ድረስ ኢትዮጵያን ተረክቦ እያስተዳደረን ይገኛል።ኦሮሞን አማራን ወይም ትግሬን አሊያም ቤንሻንጉልን እና ኮንሶን አሊያም”አገሪቷን”ብቻ ሳይሆን በዓለም ላይ ያሉትን ዜጎቿን በትክክለኛ አባባል”ኢትዮጵያን!!!”እየመራ ይገኛል።
^^^አንባቢዎቼ የሰው ልጅ ሕሊና ቢ
ረውም አንገቱን ከውስጥ አዙሮ ነገሮችን በፍጥነት ካላየ የማይታረም ጥፋት ይፈፅማል እናም እየሆነ ያለውም ይሄው ነው፤ምን ማድረግ ይጠበቅበናል?ፍረንጆቹ ወደተግባር የሚሉትን(አክሽን ፕላን)ፈተና ነው።
እንግዲህ ምን እናድርግ ስንል ከደረስንበት ጀምሮ እስከ ፍፃሜ ለዓላማችን የምናደርገውን ጉዞ 
ወሳኝ ነው፤አሊያም አስቀድሞ የተጀመረ በመሆኑ ማቀድ ነው።

መግቢያ ፩ኛ/ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያ ሕዝብ በነፃነቱ ትክክለኛ ምርጫ እንዲያካሂድ አድርጎ መሪውን መምረጥ ነው።
፪ኛ/ችግሮች በየፈርጃቸው ሲታዩ በመጀመሪያም የውስጥና የውጭ ወይም የባዕድ እና የኛው ዜጋ(ሥልጣን፣ለዘረፋ፣ለማጭበርበር…)
፫ኛ/ጎራ ተቃራኒ(ፀረ-ሕዝብ)፣ወገንተኛ(ቡድኖች) እና የሕዝብ(ያለውን ሕግ(ባያምኑበትም(አንገታቸው…) የሚከተሉ)ናቸው፤ስለዚህ ለያይቶ ማወቅ ይገባል።
፬ኛ/ያለን የጊዜ መ
ን ዓይነትና ብዛት በየተግባሩ ሊተነተኑ እና ከእነ-ሊገጥሙን ይችላሉ ጋር ተለይተው በሚመለከተው የሰው ኃይል ሊታወቅ ይገባል።
፭ኛ/የሚጠበቁ እና የማይጠበቁ ድንገተኛ ችግሮችና መፍትሄዎችን ሊያመጣ የሚችል ኃይል ማቋቋም ይገባል።
ያም ሆነ ይህ”ፈረስ ያደርሳል እንጂ ነውና…”የኳስ ሜዳውን ምስል አድርሼአለሁ የተጫዋቾቻችንንም ግብረ-ዝርዝር የዳኞቹንም አቀማመጥ ለማሳየት ሞክሬአለሁ ለብርቱካን ሚደቅሳ በዚያን የጨለማ ዓመታት በገጠምኩላት እሰናበታችኋለው።
Wee-Menfesawe
December 22, 2011 – 11:28 am
*********”ደሀ ተበድሎ ማሩኝ ይላል ቶሎ”********

ከአቢይ ኢትዮጵያዊ ሥጋዊ ወ-መንፈሳዊ


አቅሙንም አውቆ፣

ጊዜውን ደብቆ፤
ማሩኝ ይላል ቶሎ፤
ድሃ ተበድሎ ::
ገፍተውት በሁሉም፣
ይሙት ዛሬ ቢሉም፤
ቀምተውት ሀብቱን፣
ነፃነቱን መብቱን፤
ወንጀለኛ እያሉት፣
ለዛሬ እንዳይገሉት፤
አሁን አቅሙን አውቆ፣
ጊዜውን ደብቆ፤
ማሩኝ ይላል ቶሎ፤
ድሃ ተበድሎ ::
አዎን”ሁሉም ያልፋል፣
እስከሚያልፍ ያለፋል፤”
መባሉን ያወቁ፦
እንደእነ ብርቱካን ትዕግስት የታጠቁ፤
በልብ የሰበቁ፤
ወኔያቸው ያልሞተ፤
ከውስጥ የሸፈተ፤
ሕዝብ ሆኖ ይመጣል፣
ጥቁር ደም ያስምጣል።
እናም አቅሙን ያውቃል፤
ድሉን ይጠብቃል።
እስከዚያው ጊዜ ግን፤
የማይለቀው ሃቅን፤
ማሩኝ ይላል ቶሎ፤
ድሃ ተበድሎ ::

ለጀግና ብርቱካን ሚደቅሳ

መዝሙረ ዳዊት ፹፪፥፫ ለድሆችና ለድሀ አደጎች ፍረዱ፤ ለችግረኛውና ለምስኪኑ ጽድቅ አድርጉ፤
መጽሐፈ ምሳሌ ፳፰፥፫ ድሆችን የሚያስጨንቅ ምስኪን ሰው እህልን እንደሚያጠፋ እንደ ዶፍ ዝናብ ነው። 

Leave a Reply

Your email address will not be published.

Latest from Blog

ከነፃነት ዘገዬ የአራት ኪሎው ኦነግ ሸኔ ከቁጥር ጋር እንደተጣላ ዕድሜውን አገባደደ፡፡ ኦነግ/ኦህዲድ ዛሬም ሆነ ዱሮ፣ በቤተ መንግሥትም ይሁን በጫካ ቁጥር ላይ ያለው አቋም ምን ጊዜም ያስደንቀኛል፡፡ ደግሞም እየባሰባቸው እንጂ ሲቀንሱ አይታዩም፡፡ ጥቂት

80 ቢሊዮን ብር ስንት ብር ነው?

በላይነህ አባተ ([email protected]) መልአከ ብርሃን አድማሱ ጀምበሬ ምዕራባውያን የኢትዮጵያን ልጆች እያታለሉና እየደለሉ ከእምነታቸው ለመንጠቅ ሲቃጡ በ1951 ዓ ም ባሳተሙት ‘መድሎተ አሚን ወይም የሃማኖት ሚዛን ጥልቅ መጽሐፍ ሽፋን ላይ ሕዝብ ልቡናውን፣ ዓይኑን፣ ጀሮውንና

ሰው ሆይ!

“በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ።”  መዝሙረ ዳዊት 39:1 ወንድሙ መኰንን፣ ኢንግላንድ 15 January 2025 መግቢያ የአገር መሪ፣ በስሜታዊነት እንዳመጣለት አይዘረግፍም። እያንዳንዷ ንግግሩ እየተሰነጠቀች ትታይበታለች። ንግግሩ ቁጥብ መሆን

ከተዘራ ያልታረመ አንደበት የጠቅላይ ሚኒስትር አነጋጋሪ ንግግሮች

አስቻለው ፈጠነ የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃ ከዘመናዊ ተፅዕኖዎች ጋር በማዋሃድ ባሳየው ልዩ ችሎታ የተቸረው አርቲስት ነው ። ጥበባዊ ጥረቱ ብዙ ጊዜ የኢትዮጵያን ጥልቅ ባህላዊ ትሩፋት እና የሙዚቃ ልምምዶች በልዩ ሚዛን፣ ዜማ እና ዜማ

አሞራው ካሞራ | አስቻለው ፈጠነ

January 15, 2025
ፈራ ተባ እያልን እንጂ ስለፋኖ ትግልና አደረጃጀት ብዙ የሚባል ነገር አለ፡፡ እንዳጀማመሩ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ፋኖ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ከታወጀባቸው የመፈራረስና የዕልቂት ኦነግ-ኦህዲዊ ዐዋጅ ነጻ ባወጣቸው ነበር፡፡ ይሁንና በምናውቀውም በማናውቀውም በምንገምተውም

ይድረስ ለፋኖ አደረጃጀቶች በያሉበት – ነፃነት ዘገዬ

የአማራ ሕዝብ የኅልውና ትግል፦ ዘርፈ ብዙ የጥቃት ሰለባ የሆነ መንግሥት መር፣ ማንነት ተኮር እልቂት ለታዎጀበት ሕዝብ በጥብአትና በጀግንነት የሚከናወን የዘመናችን ሐቀኛ አብዮት ነው። አማራው በዋለበት እንዳያድር፣ ባደረበት እንዳይውል ተወልዶ ያደገበት ቀዬ ድረስ

ከአማራ ፋኖ አደረጃጀቶች የተሰጠ የጋራ መግለጫ!

January 14, 2025
ኤፍሬም ማዴቦ ([email protected]) ባለፉት ሁለት ወራት አገር ውስጥና በውጭ አገሮች ያሉትን የኢትዮጵያ ሚዲያዎች ካጨናነቁ ዜናዎች ውስጥ አንዱ ፓርላማው ይህንን ወይም ያንን የህግ ረቂቅ አጸደቀ የሚሉ ዜናዎች ናቸው። የኢትዮጵያ ፓርላማ ምንም ይሁን ምን

የኢትዮጵያ ፓርላማ ሲመረመር

 ፈቃዱ በቀለ(ዶ/ር)   ጥር 2፣ 2017(January 10, 2025) መግቢያ ባለፉት ሃምሳ ዓመታ በአገራችን ምድር ሲያወዛግበንና በብዙ መቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ህይወታቸውን እንዲያጡ የተደረገበት ዋናው ምክንያት በፖለቲካ ስም የተደረገው ትግል ነው። ይህ ብቻ

ፖለቲከኛ ማለት ምን ማለት ነው? ፖለቲከኛ ራሱን የቻለ ሙያ ነው ወይ? በምንስ ይገለጻል? ለአንድ ህብረተሰብ የሚሰጠው በተጨባጭ የሚታይና የሚመዘን ነገር አለ ወይ? ፖለቲካ ሲባልስ ምን ማለት ነው? አገርን መገንቢያ ወይስ ማፈራረሺያ መሳሪያ?

Go toTop